የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል ECGBC
9.68K subscribers
9.62K photos
134 videos
1 file
1.55K links
ይህ የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል የቴሌግራም ቻናል ነው።

"ወንድሞች በህብረት ቢቀመጡ፤ እነሆ፤ መልካም ነው፤ እነሆም፤ ያማረ ነው።
Download Telegram
በኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን የደቡብ ምስራቅ አዲስ አበባ እና አካባቢው ክልል የወንጌል መስካሪዎች የአንድነት ፕሮግራም ተካሄደ።

ነሐሴ 6/2017 ዓ.ም በሴሚሲ ሙሉ ወንጌል አጥቢያ በተካሄደው የወንጌላውያን እና የወንጌል መስካሪ አገልጋዮች የአንድነት ፕሮግራም ላይ 118 አገልጋዮች ተገኝተዋል። በዘማሪ አላምረው ኢያሱ ዝማሬ ቀርቦ ጉባኤው እግዚአብሔርን አምልኳል።

በመቀጠል በክልሉ የወጣቶች ቤተሰብ አገልግሎት ፣ የወንጌል ስርጭት አገልግሎት ሃላፊ በሆኑት በመጋቢ ኤልያስ አየለ "መቼ እንደ ሐዋርያቶችሁ" በሚል ርዕስ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት አቅርበዋል።

የፕሮግራሙ አላማ አመቱን ሙሉ ወንጌልን ሲሰብኩ የቆዩትን አገልጋዮች ጌታ ስለረዳቸው ለማመስገን እና ለማበረታታት መሆኑን ታውቋል።

መረጃው የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን ነው።

ለኢቫንጀሊካል ቲቪ ፡ ቤተልሔም ደረጄ
የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ የልጆች እና ወጣቶች አገልግሎት መምሪያ ለሲኖዶሶች የመንፈሳዊ መጽሐፍት ድጋፍ ተደረገ።


የኢ/ወ/ቤ/መ/ኢ የልጆች እና ወጣቶች አገልግሎት መምሪያ ለመማር ማስተማር ሂደት እና ለአገልጋዮች የሚረዱ የተለያዩ መንፈሳዊ መጽሐፍትን ለቤጊ ግዳሚ ሲኖዶስ (ቤጊ): ለቦረናና አካባቢው ሲኖዶስ (ያቤሎ): ለአዶላ ገናሌ ሲኖዶስ (አዶላ ወዩ) በድጋፍ መልክ አበርክቷል። መጽሐፍቶቹም በየሲኖዶሶቹ ለሚገኙ የትምህርት ተቋማት እና ምዕመናን አገልግሎት የሚውሉ መሆኑ ተገልጿል።

የመምሪያው ዳይሬክተር ወንድማገኝ ኡዴሳ የተለያዩ መንፈሳዊ መጽሐፍትን ለቤተክርስቲያኒቱ ድጋፍ ያደረጉትን ተቋማትን ማለትም ራፊኪ ፋውንዴሽን (Rafiki Foundation) ፣ ሉተራን ሄሪቴጅ(Lutheran Heritage Foundation) እና ሌሎችንም በማመስገን ፣ መጽሐፍቶቹን ለቤተክርስቲያኒቱ ሴሚናሪዎች ፣ መጽሐፍ ቅዱስ ኮሌጆች እና ት/ቤቶች ፣ እና ማ/ምዕመናን ጥቅም እንደሚውል እና ከተባባሪ ድርጅቶች ጋር በመሆን ድጋፍ የማድረጉ ስራ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።

መረጃውን ከኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ አገኘነው።

ለኢቫንጀሊካል ቲቪ ፡ ቤተልሔም ደረጄ
በማህበራዊ ሚድያዎች እየተሰራጨ የሚገኘውን የስም ማጥፋት ዘመቻ አስመልክቶ ከመሠረተ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን የተሰጠ የአቋም መግለጫ
የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተ ክርስቲያን ሀገርዓቀፍ ጾም እና ጸሎትን አወጀች።

የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተ ክርስቲያን ከጳጉሜ 1 -3 ድረስ በሁሉም የቤተ ክርስቲያኒቷ ክልሎች ፣ አጥቢያዎች እና አዳጊ ቤተ ክርስቲያናት ህብረት ጾም እና ጸሎት አውጃለች።

ጾም እና ጸሎት እንዲደረግባቸው የታሰቡት ርዕሶችም በመላው አገራችን በሁሉም ቦታ ሰላም እና ፍቅር እንዲሰፍን ፣ በሕዝቦች መካከል መፈቃቀርና መግባባት እንዲኖር ፣ በቀጣይ ዓመት ወንጌል ለምድራችን በመንፈስ ቅዱስ ሀይልና ጉልበት እንዲዳረስ ፣ በቤተ እምነት ደረጃ ተዘጋጅቶ ለሁሉም የቤተ ክርስቲያኒቱ መዋቅሮች የተላለፈው የ5 ዓመት ስልታዊ እቅድ ጌታ መከናወንን እንዲሰጥ ፣ በቀጣይ ዓመት በቤተ እምነት ደረጃ ስላለው የመሪዎች ምርጫ በተመለከተ ጸሎት እንዲደረግ እንዲሁም በ2018 ዓ.ም የሚደረገው የመንግስት ምርጫ በሰላም እንዲጠናቀቅና ሰላማዊ እንዲሆን ጸሎት እንዲደረግ የሚሉት ናቸው።

ቤተ ክርስቲያኒቱ ባወጣችው በዚህ አዋጅ መሰረት የቤተ ክርስቲያኒቱ አባላት እና መላው የወንጌል አማኙ ማህበረሰብ በእነዚህ ቀናት በተሰጡት ርዕሶች ላይ በጾም እና በጸሎት በእግዚአብሔር ፊት እንደሚቀርብ ይጠበቃል።

መረጃውን ከቤተ ክርስቲያኒቱ የፌስቡክ ገጽ ላይ አገኘነው።

ለኢቫንጀሊካል ቲቪ ፡ አማኑኤል ዴቢሶ