Ethiopian Electric Utility
26.8K subscribers
4.6K photos
29 videos
54 files
1.57K links
EEU Official Telegram Channel
Web: www.eeu.gov.et
Download Telegram
በጋምቤላ ክልል የቅድመ መከላከል ስራ ለማከናወን ሲባል በዕቅድ የኤሌክትሪክ ኃይል የሚቋረጥባቸውን አካባቢዎች ለማየት ድረ-ገፃችንን ይጎብኙ:-http://www.eeu.gov.et/power-interruption?lang=am
የሃይል ብክነትን እንዴት መከላከል እንችላለን?

ኤሌክትሪክ ለአንድ ሃገር ሁለንተናዊ የልማት እንቅስቃሴ ሚናው የጎላ ቢሆንም ቴክኒካል እና ቴክኒካል ባልሆኑ ምክንያቶች ሲባክን ይስተዋላል፡፡

በሃይል አጠቃቀም ችግርና ምክንያት ሊከሰት የሚችለውን የሃይል ብክነት ለመቀነስ ኃይል ቆጣቢ የሆኑ የኤሌክትሪክ መገልገያ ዕቃዎችን መጠቀምና የኤሌክትሪክ መጠቀሚያ ዕቃዎችን ኃይል ቆጣቢ መሆናቸውን ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ለረዥም ጊዜ ያገለገሉ የኤሌክትሪክ ምጣድ፣ ምድጃ፣ ማሽን እና ሌሎች የኤሌክትሪክ መገልገያ ዕቃዎችን በአዳዲስ መቀየር እና የኃይል ጭነት በማይበዛበት ጊዜ ማለትም ከምሽቱ 4፡00 ሰዓት እስከ ንጋቱ 11፡00 መጠቀም የሃይል ብክነትን በከፍተኛ ሁኔታ ይቀንሳል፡፡

እርስዎ ከላይ የተጠቀሱትን ዘዴዎች በስራ ላይ ሲያውሉ የሃይል መቆራረጡን ለመቀነስ በሚደረገው ጥረት የበኩልዎን አስተዋፆ ከማበርከት በተጨማሪ የፍጆታ ወጪ ይቀንሳሉ፡፡

የኤሌክትሪክ ኃይልን መቆጠብ መልካም ዕሴታችን እናድርገው!

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት
በኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ላይ ባጋጠመ ብልሽት ምክንያት የኃይል አቅርቦት ተቋርጧል

በጎንደር ቁጥር 1 ልደታ ኃይል ማከፋፈያ ፓወር ትራንስፎርመር ላይ ባጋጠመ ብልሽት ምክንያት ዛሬ ከጠዋቱ 1 ሰዓት ጀምሮ ለፋሲል፣ለአራዳና ለትክል ድንጋይ ኃይል የሚያቀርበው መስመር እንዲቋረጥ ተደርጓል፡፡

በዚህም ምክንያት በጎንደር ከተማ ፒያሳ፣አውቶፓርኮ እና ዩሐንስ ቀበሌ 10 የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተቋርጧል፡፡

ስለሆነም በአካባቢው የምትገኙ ክቡራን ደንበኞቻችን ጥገናው ተጠናቆ አገልግሎቱ እስኪመለስ ድረስ በትዕግስት እንድትጠብቁን እንጠይቃለን፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት
በሐረሪ ሪጅን ጥቅምት 23 ቀን 2017 ዓ.ም የመልሶ ግንባታና አቅም ማሳደግ ስራ ለማከናወን ሲባል በዕቅድ የኤሌክትሪክ ኃይል የሚቋረጥባቸውን ቦታዎች ለማወቅ ድረ-ገፃችንን ይጎብኙ፡፡
http://www.eeu.gov.et/power-interruption?lang=am
#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት
ለጥገና ሥራ ሲባል የሚቋረጥ የኃይል አቅርቦት

ዛሬ ጥቅምት 23 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 1፡00 እስከ ቀኑ 8፡00 ድረስ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በአዲስ ሴንተር ኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ላይ የጥገና ሥራ ስለሚከናወን በአዲስ አበባ ሜክሲኮ ደብረወርቅ ህንጻ፣ ኤግዚቢሽን ማዕከል፣ ኦሎምፒያ፣ ገነት ሆቴል፣ አይናለም ቨዜ ሕንፃ፣ ልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት፣ኢቢሲ፣ ሂልተን ሆቴል፣ መቻሬ፣ ልደታ ፀበል፣ መብራት ኃይል ክበብ ጀርባ፣ አፍሪካ ህብረት እና በአካባቢያቸው፤

በተመሳሳይ ጥቅምት 24 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 1፡00 እስከ ቀኑ 9፡00 ድረስ በመካኒሳ ኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ላይ የጥገና ሥራ ስለሚከናዎን በጀሞና አካባቢው፣ በአርሴማ እና አካባቢው፣ በጀረመን አደባባይ እና አካባቢው፣ በካፒታል ሲሚንቶ፣በመስታውት ፋብሪካ ፣ በላፍቶና አካባቢው የኃይል አቅርቦት ተቋርጦ ይቆያል፡፡

ስለሆነም ክቡራን ደንበኞቻችን የጥገና ስራው ተጠናቆ ወደ አገልግሎት እስኪመለስ ድረስ በትግዕስት እንድትጠብቁ በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት
ከ3 ሚሊየን በላይ ቆጣሪዎች ወቅታዊ መረጃ ተሰበሰበ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከ3 ነጥብ 2 ሚለየን በላይ ቆጣሪዎች ወቅታዊ መረጃ መሰብሰብ ችሏል፡፡

የቆጣሪ መረጃ መሰብሰብ ከተጀመረበት 2014 ዓ.ም እስከ 2017 በጀት ዓመት መስከረም ወር መጨረሻ ድረስ የ3 ሚለየን 211 ሺህ 782 ቆጣሪዎች መረጃ ተሰብስቧል፡፡

በኦሮሚያ ከ1 ሚሊየን በላይ ቆጣሪ መረጃ፣ በአማራ ከ7 መቶ ሺህ በላይ፣ በአዲስ አበባ ከ6መቶ ሺህ በላይ እንዲሁም በደቡብ ከ400 ሺህ በላይ ቆጣሪ መረጃ ተሰብስቧል፡፡

የቆጣሪ መረጃ መሰብሰቡ ደንበኞች በተበላሸ ቆጣሪ ምክንያት ላልተገባ ወጪ እንዳይዳረጉ፣ አገልግሎቱም ትክክለኛ የፍጆታ ሂሳብ እንዲሰበስብ የሚያግዝ ይሆናል፡፡

ወቅታዊ የቆጣሪ መረጃ ለማሰባሰብ 74.7 ሚሊየን ብር በጀት የተመደበ ሲሆን አፈፃፀሙም 78 በመቶ ደርሷል፡፡


#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት
የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ላይ ባጋጠመ ብልሽት ምክንያት የኃይል አቅርቦት ተቋርጧል
**
በጎንድር 01 ቁጥር ኃይል ማከፋፊያ ጣቢያ ላይ ባጋጠመ ብልሽት ምክንያት ፋሲል፣ አራዳ፣ ትክል ድንጋይ እና አካባቢዎቻቸው የኃይል አቅርቦት ተቋርጧል፡፡

በተመሳሳይ በድሬ ዳዋ ኃይል ማከፋፊያ ጣቢያ ላይ ባጋጠመ ብልሽት ምክንያት በድሬ ዳዋ ከተማ በከፊል የኃይል አቅርቦት ተቋርጧል፡፡

በመሆኑም ክቡራን ደንበኞቻችን በሁለቱ ኃይል ማከፋፊያ ጣቢያ ላይ የተፈጠረውን ችግሩን ለመፍታት ርብርብ እየተደረገ ስለሆነ በትግዕስት እንድትጠብቁን በአክብሮት እናሳውቃለን፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት
በአድዋ፣ በድሬዳዋ እና በጎንደር ከተሞች ከጥቅምት 23 ጀምሮ 2017 ዓ.ም ለመልሶ ግንባታ፣ ለአዲስ ኃይል ማገናኘት እና ለቅድመ-ጥገና ሥራ በዕቅድ የኤሌክትሪክ ኃይል የሚቋረጥባቸውን ቦታዎች ለማወቅ ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ
http://www.eeu.gov.et/power-interruption/detail/999?lang=am

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት
የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ላይ ባጋጠመ ብልሽት ምክንያት የኃይል አቅርቦት ተቋርጧል

በሁርሶ ኃይል ማከፋፊያ ጣቢያ ላይ ባጋጠመ ብልሽት ምክንያት በምስራቁ የሃገራችን ክፍል በሚገኙ የድሬ ዳዋ፣ የሀረረ ፣ የጅግጅጋ ከተሞች እና አካባቢያቸው የኃይል አቅርቦት ተቋርጧል።

በመሆኑም ክቡራን ደንበኞቻችን በኃይል ማከፋፊያ ጣቢያው ላይ የተፈጠረው ችግር በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በኩል ተጠግኖ አገልግሎቱ እስኪመለስ ድረስ በትግዕስት እንድትጠብቁን በአክብሮት እናሳውቃለን፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት
ተቋርጦ የነበረው የኃይል አቅርቦት ወደ አገልግሎቱ ተመልሷል

በሁርሶ ኃይል ማከፋፊያ ጣቢያ ላይ ባጋጠመ የቴክኒክ ብልሽት ምክንያት በምስራቁ የሃገራችን ክፍል በሚገኙ የድሬ ዳዋ፣ የሀረረ፣ የጅግጅጋ ከተሞች እና አካባቢያቸው ተቋርጦ የነበረው የኃይል አቅርቦት ወደ አገልግሎቱ ተመልሷል፡፡

የጥገና ስራው ተጠናቆ አገልግሎቱ እስኪመለስ ድረስ በትዕግስት ለጠበቃችሁ ደንበኞቻችን ከልብ እናመሰግናለን፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት
ወርሃዊ የኤሌክትሪክ ፍጆታ ክፍያን በቀላሉ፣ የትም ሳይሄዱ ባሉበት ሆነው ከዚህ በፊት በሚከፍሉበት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ካሻዎ በቴሌ ብር፣ በሲቢኢ ብር፣ በሞባይል ባንኪንግ፣ በአዋሽ ብር ፕሮ ወይም በኤም ፔሳ በኩል ይፈፅሙ፡፡

ፍጆታዎ በስልክዎ!
ዘመናዊ የክፍያ አማራጭ በመምረጥ ኑሮዎን ያቅሉ!

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት
የጋዜጣዊ መግለጫ ጥሪ (ለሁሉም መገናኛ ብዙሃን)

ተቋማችን በ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት አፈፃፀም ላይ ነገ ማክሰኞ ጥቅምት 26 ቀን 2017 ዓ.ም ጠዋት 3፡30 ለሁሉም መገናኛ ብዙሃን ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣል፡፡

ጋዜጣዊ መግለጫው ሜክሲኮ አዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ ንግድ ሥራ ት/ቤት ፊት ለፊት በሚገኘው ንብ ባንክ ዋና መስሪያ ቤት ህንፃ 17ኛ ፎቅ ላይ ስለሚሰጥ፤ ሁሉም መገናኛ ብዙሃን በቦታው ተገኝታችሁ እንድትሳተፉና መረጃውንም ተደራሽ እንድታደርጉልን በአክብሮት እንጋብዛለን፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት
ሁለተኛው ምዕራፍ የሬዲዮ ኮሙኒኬሽን ተግባራዊ ተደረገ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ሁለተኛ ምዕራፍ የሬዲዮ ኮሙኒኬሽን በአዲስ አበባ እና በክልል ከተሞች ተግባራዊ ተደርጓል።

የፕሮጀክቱ ሁለተኛ ምዕራፍ ትግበራ በአዲስ አበባ እና በክልል ከተሞች ስር በሚገኙ 13 ሳይቶች ሲሆን አቃቂ ቃሊቲ፣ አለምገና፣ አዳማ፣ ሃዋሳ፣ ድሬደዋ፣ ጅማ፣ ባህርዳር፣ ሐረር፣ መቀሌ፣ ወላይታ ሶዶ፣ አርባ ምንጭ እና ጅግጅጋ ከተሞች ይገኙበታል፡፡

ተቋሙ ተግባራዊ ያደረገው የሬዲዮ ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ በየደረጃው በሚገኙ የሥራ ኃላፊዎችና ሰራተኞች መካከል ፈጣን የመረጃ ልውውጥ እንዲኖር በማድረግ ቀልጣፋና ጥራት ያለው የአስቸኳይ ጥገና አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል ነው፡፡

በሁለተኛው ምዕራፍ የሬዲዮ ኮሙኒኬሽን ማስፋፊያ ሥራ 160 የእጅ፣ 64 የጠረጴዛ /ቤዝ ፣ 74 እና 64 የመኪና በአጠቃይ 298 ሬድዮዎች ተሰራጭተዋል።

የመጀመሪያው ምእራፍ የሬዲዮ ኮሙኒኬሽን በአዲስ አበባ በሁለት ሪፒተር ሳይቶች ተግባራዊ መደረጉ የሚታወስ ነው።

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት
በአዲስአበባ ከተማና በሐረሪ ሪጅን የመልሶ ግንባታና አቅም ማሳደግ ስራ ለማከናወን ሲባል በዕቅድ የኤሌክትሪክ ኃይል የሚቋረጥባቸውን ቦታዎች ለማወቅ ድረ-ገፃችንን ይጎብኙ፡፡
http://www.eeu.gov.et/power-interruption/detail/1000?lang=am
#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት
በቤት ውስጥ የሚኖረን የኤሌክትሪክ አጠቃቀም እና ልናደርጋቸው የሚገቡ ቅድመ ጥንቃቄዎች 👇

👉የኤሌክትሪክ አገልግሎት ለአንድ ሃገር ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት የሚያበረክተው አስተዋጾ እጅግ ከፍተኛ ቢሆንም በአጠቃቀምና ጥንቃቄ ጉድለት ምክንያት በአካል እና በንብረት ላይ ጉዳት ብሎም ሞት ሲያስከትል ይስተዋላል፡፡

👉ተቋሙ አዲስ ደንበኞቹን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ለማድረግ የመስመር ዝርጋታ የሚያከናውነው እስከ ቆጣሪ ድረስ ያለውን በመሆኑ ከቆጣሪ በኋላ በቤት ውስጥ የሚከናወኑ የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታዎች በቂ ልምድ ባለው ባለሞያና ደረጃቸውን በጠበቁ የኤሌክትሪክ ቁሳቁሶች መሆን ይኖርበታል፡፡

👉ደንበኞች በቤት ውስጥ ሆነ ከቤት ውጪ የሚጠቀሙባቸው ማንኛውም የኤሌክትሪክ ቁሳቁሶች ከህፃናት ዕይታ ማራቅ እንደሚያስፈልግና ለጊዜው የማይጠቀሙባቸውን የኤሌክትሪክ መገልገያ ቁሳቁሶችን ከሶኬት ላይ ነቅሎ ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል ፡፡

👉ከዚህ በተጨማሪም ለኤሌክትሪክ አደጋ ስጋት የሚሆኑ ቁሳቁሶችን ማስወገድ፤ እርጥበት እና እርጥበት አዘል ሁኔታዎችን ከኤሌክትሪክ አካባቢ ማስወገድ፣ ትክክለኛ እና ደረጃቸውን የጠበቁ የኤሌክትሪክ ቁሳቁሶችን መጠቀም አስፈላጊ ነው፡፡

👉የቤት ውስጥ የመስመር ዝርጋታ የሚያከናውን አካል ቅድሚያ ከቆጣሪ ኤሌክትሪክ በማቋረጥ ሁሌም በጥንቃቄ እና ሀሳቡን ሰብስቦ ስራውን በትኩረት ሊያከናውን ይገባል፡፡
ከ90 ሺህ በላይ አዳዲስ ደንበኞች የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ሆኑ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት 90 ሺህ 573 አዳዲስ ደንበኞን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ በማድረግ የዕቅዱን 75 በመቶ ማሳካት ችሏል፡፡

ይህ አፈጻጸም ከባለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር 28 ነጥብ 2 በመቶ ጭማሪ አለው፡፡

የአዲስ ደንበኞች ዕድገት ከባለፉት ዓመታት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር ከ2015 በ 46 ሺህ 713 ደንበኞች ወይም 54.5 በመቶ እና ከ2016 በ15 ሺህ 63 ደንበኞች ወይም 17.6 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል፡፡

በተጨማሪም በሩብ ዓመቱ 30 የገጠር ቀበሌዎችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ለማድረግ ታቅዶ 26 የሚሆኑ የገጠር ቀበሌዎች ተጠቃሚ በማድረግ የእቅዱ 83.9 በመቶ ተሳክቷል።

የኃይል መቆራረጥ ድግግሞሽን ለማሳጠር በተሠራው ሥራ በሩብ ዓመቱ መሻሻል ማሳየቱ ተመላክቷል፡፡

አገልግሎቱ በሩብ ዓመቱ ባከናወናቸው አንኳር ተግባራት ዙሪያ በዛሬው እለት ለጋዜጠኞች ማብራሪያ ሰጥቷል፡፡

የመግለጫውን ሙሉ ይዘት ለማንበብ ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ:-
http://www.eeu.gov.et/news/detail/1002?lang=am

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት