"7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ለኢትዮጵያ የሀገረ መንግሥት ግንባታ ትልቅ ስኬት ነው" ኢንጂነር አሸብር ባልቻ
…..///….
7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ለኢትዮጵያ የሀገረ መንግሥት ግንባታና ለቀጣይ መዋቅራዊ ሥራዎች ስኬት ትልቅ መነሳሳትን የፈጠረ ታሪካዊ ምዕራፍ መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኢንጂነር አሸብር ባልቻ አስታወቁ፡፡
የተቋሙ የሥራ መሪዎችና ሠራተኞች "ከምርጫ ድል ማግስት፤ ጠንካራ መንግሥት" በሚል መሪ ቃል በወቅታዊና ተቋማዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት አካሂደዋል፡፡
በመድረኩ ላይ የመወያያ ሰነድ ያቀረቡት በተቋሙ የኮርፖሬት ፋይናንስና ሀብት አስተዳደር ዘርፍ ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ደመረ አሰፋ እንደገለፁት 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ሰላማዊ፣ ፍትሃዊ፣ ነፃና ዲሞክራሲያዊ እንዲሁም የኢትዮጵያ አሸናፊነት የተረጋገጠበት ሆኖ ተጠናቋል፡፡
የምርጫው ስኬት የተገኘው ጊዜ ተወስዶ በተከናወኑ የቅድመ ምርጫ ሥራዎችና በማህበረሰቡ ፅናት መሆኑን ገልፀው በቅድመ ምርጫው ወቅት የታየው ፅናትና ከፍተኛ ርብርብ በድህረ ምርጫ ተግባራት ላይም ሊደገም እንደሚገባ አስረድተዋል።
ጠንካራ ሀገረ መንግስት ለመገንባት ሠራተኛው የህዝብን ፍላጎት የሚያሳካ እና ሀገራዊ ትልሞችን አውቆ የሚተገብር መሆን እንዳለበትም ጠቅሰዋል።
በድህረ-ምርጫ ወቅት የተቋማት ዝግጁነት፣ የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራትና የመንግሥት ሠራተኛው የሥራ ዲስፕሊን ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች መሆናቸውንም ነው አቶ ደመረ ያነሱት፡፡
የሀገሪቱን ሁለንተናዊ ዕድገት ለማፋጠን በኃይል ልማት ዘርፉ ላይ ያሉትን ሥራዎች በከፍተኛ ቁርጠኝነትና በትጋት ማከናወን እንደሚገባና ለዚህም ሠራተኛው የተሰጠውን ኃላፊነት በአግባቡ በማከናወን ለሀገረ መንግሥት ግንባታ የበኩልን ድርሻ እንዲወጣ አሳስበዋል፡፡
በተቋሙ የኢንጂነሪንግና ኮንስትራክሽን ቢዝነስ ዘርፍ ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኢንጂነር ውድነህ የማነ በበኩላቸው በኢትዮጵያ ለሚስተዋሉ መሠረታዊ ችግሮች ዋናው መንስኤ የሀገረ መንግሥት ግንባታ ሂደቱ ዘላቂና ተቋማዊ አሠራርን ተከትሎ አለመከናወኑ መሆኑን ገልፀዋል።
ይህንን ክፍተት በዘላቂነት ለመቅረፍም ገለልተኛና ጠንካራ ተቋማትን መገንባት እንደሚያስፈልግም ነው ያብራሩት፡፡
በአሁኑ ጊዜ በተለያዩ የአፍሪካና የዓለም ሀገራት ከምርጫ ጋር ተያይዞ ከባድ አለመረጋጋትና ውጥረት የሚስተዋል ቢሆንም በኢትዮጵያ ግን ሂደቱ ሰላማዊ በሆነ መንገድ መጠናቀቁ ለቀጣይ መዋቅራዊ ሥራዎች ስኬት ትልቅ መነሳሳት መፍጠሩን አብራርተዋል።
በውይይቱ ላይ የማጠቃለያ ሃሳብ የሰጡት የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኢንጂነር አሸብር ባልቻ እንደተናገሩት 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ሕዝቡ ለሀገረ መንግሥት ግንባታ ያለውን ፅኑ የሆነ አቋም ያሳየበት ነው፡፡
በምርጫው ወቅት ከፍተኛ የተለያዩ ጫናዎች የነበሩ ቢሆንም መራጩ ህዝብ ጫናዎቹን ተቋቁሞ ሂደቱን በከፍተኛ ዲሲፕሊን እና ቁርጠኝነት ማካሄዱን ተናግረዋል።
ምርጫ በሰላማዊ መንገድ መጠናቀቁ ለኢትዮጵያ ተቋማዊ የሀገረ መንግስት ግንባታና ለቀጣይ መዋቅራዊ ስራዎች ስኬት ትልቅ መነሳሳትን የፈጠረ ታሪካዊ ምዕራፍ መሆኑንም አመላክተዋል፡፡
ይህም ሀገሪቱ በቀጣይ መዋቅራዊ ሥራዎች ላይ በሰላም ለመወያየት እንድትችል ትልቅ ማሳያ መሆኑን ጠቅመዋል፡፡
ለዲጂታላይዜሽን ሥራዎች የተሰጠው ትኩረት ውጤት እያመጣ መሆኑን የገለፁት ኢንጂነር አሸብር ሀገራዊ ምርጫው ላይ የተጀመረው የዲጂታላይዜሽን የአሰራር ሥርዓት የዜጎችን እንግልት ለመቀነስ አስተዋፅኦ ማድረጉን አንስተዋል፡፡
የምንመኛትን ሀገር ለቀጣዩ ትውልድ ለማስተላለፍ በሚደረገው ጉዞ ውስጥ የኢነርጂ ዘርፉ የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ መሆኑን ጠቅሰው አዲስ መንግሥት በይፋ እስከሚመሰረት ድረስ ሁሉም ሠራተኛ የተጣለበትን ሀገራዊ አደራ በመገንዘብ ኃላፊነቱን በአግባቡ መወጣት እንዳለበትም አሳስበዋል።
የውይይቱ ተሳታፊዎችም በመድረኩ ላይ የተለያዩ አስተያየቶችና ጥያቄዎችን አቅርበው በሥራ ኃላፊዎቹ ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል።
"ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”
ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric
ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication
ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia
ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power
ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia
ቲክቶክ↠https://tiktok.com/@ethio_power
ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et
ሰኔ 15 ቀን 2018 ዓ.ም

Facebook
Log in or sign up to view
See posts, photos and more on Facebook.
❤15👍4👎4
አረንጓዴ የፋይናንስ ምንጭ (Green Financing)
......///.....
ከአገር ውስጥና ከውጭ የገንዘብ ምንጮች ጋር የምናደርጋቸው የብድር ውይይቶችና ድርድሮች በሙሉ አረንጓዴ ኢንቨስትመንትን ማዕከል ያደረጉ ናቸው። በኮፕ 32 (COP 32) የአየር ንብረት ጉባኤ ላይ በምናደርገው ንቁ ተሳትፎም ለታዳሽ ኃይል ግንባታ የሚውሉ ዓለም አቀፍ አረንጓዴ የፋይናንስ አጋርነቶችን (Green Financing) ይበልጥ ለማጠናከር እንሠራለን። 💳🌐
#COP32 #GreenFinance #ClimateAction #RenewableEnergy #EEP
"ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”
ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric
ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication
ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia
ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power
ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia
ቲክቶክ↠https://tiktok.com/@ethio_power
ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et
ሰኔ 16 ቀን 2018 ዓ.ም

❤5
ተቋሙ የሠራተኛውን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየሰራ ነው
…///…
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሠራተኛውን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ገለፁ፡፡
ዋና ሥራ አስፈፃሚው ኢንጂነር አሸብር ባልቻ እንደተናገሩት የተቋሙ የሥራ መሪዎችና ሠራተኞች በተለያዩ ጊዜያት የጥቅማጥቅም ጥያቄዎችን ሲያቀርቡ የቆዩ ቢሆንም ከተቋሙ የፋይናንስ ቁመና ጋር ተያይዞ በወቅቱ ምላሽ ሳይሰጥ ቆይቷል፡፡
ይሁን እንጂ በተያዘው በጀት ዓመት የተቋሙ የፋይናንስ አቅም እያደገ በመምጣቱና ወደ ትርፋማነት በመሸጋገሩ ምክንያት ሲነሱ ለነበሩ የተለያዩ የጥቅማጥቅም ጥያቄዎች ምላሽ መስጠት መቻሉን ገልፀዋል፡፡
ይህም የሠራተኛውን የኑሮ ሁኔታ ከመደገፍ ባለፈ የተቋሙን ምርታማነትና የፕሮጀክቶችን አፈፃፀም ለማሳደግ ከፍተኛ እገዛ እንደሚያደርግ ጠቅሰዋል፡፡
መንግሥት ለተቋሙ መለወጥና መጠናከር ከፍተኛ ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ያብራሩት ኢንጂነር አሸብር ተቋሙ የነበረበትን ከፍተኛ ዕዳ ወደ ካፒታል እንዲቀየርለት ማድረጉን አስታውሰዋል፡፡
የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት መጠናቀቅ፣ የነባር የኃይል ማመንጫዎች አፈፃፀም መሻሻል እና በሀገር ውስጥ ለሚገኙ የዳታ ማይኒንግ ኩባንያዎች በዶላር የኤሌክትሪክ ኃይል መሸጥ መጀመሩ የተቋሙን የውጭ ምንዛሬ ገቢ በከፍተኛ ሁኔታ እንዳሳደገው አብራርተዋል፡፡
ይህ የገቢ ዕድገት ተቋሙ ለጀመራቸው አዳዲስና ነባር ፕሮጀክቶች የሚያስፈልጉ ግብዓቶችን በራስ አቅም ለመሸፈን ዕድል መፍጠሩንም ተናግረዋል፡፡
የተቋሙ ዕድገትና የሠራተኛው ጥቅም በቀጥታ የተሳሰሩ መሆናቸውን የጠቀሱት ዋና ሥራ አስፈፃሚው እያንዳንዱ የሰው ኃይል በቁርጠኝነት ከሠራ ተቋሙን ይበልጥ ትርፋማ ማድረግ እንደሚችል አስገንዝበዋል፡፡
በመሆኑም እያንዳንዱ ሠራተኛ ጥቅምን ብቻ ከመጠበቅ ይልቅ ለተቋሙ ዕድገትና ውጤታማነት ማበርከት የሚጠበቅበትን ድርሻ በተግባር ማሳየት እንዳለበት አሳስበዋል፡፡
ተቋሙን በዘላቂነት ለማሳደግ በፕሮጀክቶች አፈፃፀም ላይ የሚታዩ መዘግየቶችን ማስወገድ፣ በሥራ አፈፃፀምና በኦፕሬሽን ላይ የሚባክኑ ሀብቶችን መቀነስ እንዲሁም ጠንካራ ስትራቴጂ በመንደፍ በቀጣይ በራስ ገቢ ሌሎች ትልልቅ የኃይል ማመንጫዎችን መገንባት እንደሚገባ አመላክተዋል፡፡
እንደ ኢንጂነር አሸብር ገለፃ የሠራተኞችን ጥቅማጥቅም ማረጋገጥ በሥራ ገበታቸው ላይ ተረጋግተው እንዲሠሩ ስለሚያስችል ለተቋማት ውጤታማነት ያለው ሚና የጎላ ነው፡፡
በአሁኑ ወቅት ተቋሙ የሀገሪቱን የኤሌክትሪክ ተደራሽነት ለማሳደግ ሰፊ የኢንቨስትመንት ሥራዎችን በማከናወን ላይ እንደሚገኝ ገልፀው ሠራተኛውና አመራሩ ይህንን ትልቅ ሀገራዊ ግብ ለማሳካት በቁርጠኝነትና በቅንጅት መሥራት እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡
💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”
📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric
📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication
📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia
📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power
📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia
📌ቲክቶክ↠https://tiktok.com/@ethio_power
📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et

❤20👍3⚡2
ተቋሙ በራስ አቅም የሚያከናውናቸውን የፕሮጀክት ግንባታዎች አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገለፀ
…///…
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በራስ አቅም የሚያከናውናቸውን የኃይል ማከፋፈያና ማስተላለፊያ መስመር ግንባታዎች አጠናክሮ እንደሚቀጥል በተቋሙ የኢንጅነሪንግና ኮንስትራክሽን ቢዝነስ ዘርፍ አስታወቀ፡፡
የዘርፉ ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኢንጂነር ውድነህ የማነ እንደተናገሩት ፕሮጀክቶችን ከዲዛይን እስከ ግንባታ ያለውን ሙሉ ሂደት በራስ አቅም በማከናወን ረገድ እየተመዘገበ ያለው ውጤት አበረታች ነው፡፡
ተቋሙ ወደፊት በራስ አቅም የሚከናወኑ ሥራዎችን ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግ የውስጥ አሰራርን ከማሻሻልና የውጭ ተፅዕኖዎችን ከመቆጣጠር አንፃር የተለያዩ የሪፎርም አቅጣጫዎችን ለይቶ እየሰራ እንደሚገኝም አስረድተዋል።
የውስጥ አሰራርን ለማሻሻል በግንባታ እና በድጋፍ ሰጪ የሥራ ክፍሎች መካከል ያለውን ቅንጅት፣ ቅልጥፍና እና የጋራ ግንዛቤ በማሳደግ የሚስተዋሉ ተግዳሮቶችን በዘላቂነት መፍታት እንደሚገባ ኢንጂነር ውድነህ አብራርተዋል፡፡
ተጨማሪ ለማንበብ…
https://www.eep.com.et/?amh-news=ተቋሙ-በራስ-አቅም-የሚያከነውናቸውን-የፕ&lang=am
💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”
📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric
📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication
📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power
📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia
📌ቲክቶክ↠https://tiktok.com/@ethio_power
📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et
ሰኔ 17 ቀን 2018 ዓ.ም

❤4👏1