EECMY Youth Ministry
2.07K subscribers
4.11K photos
8 videos
280 links
Fellowship - Discipleship - Evangelism

1Thimothy 4:12

This is the official telegram channel of EECMY Head Office - Youth Ministry
Download Telegram
'ONE BODY, ONE SPIRIT, ONE HOPE'
The 13th LWF General Assembly, Krakow, Poland 🇵🇱
===
The Thirteenth The Lutheran World Federation  Assembly took place in Poland. Its theme was One Body, One Spirit, One Hope.

In a fragmented world, we are called to unity in the one body of Christ.  The Assembly theme is drawn from Ephesians 4:4, “There is one body, one Spirit, just as you were called to one hope when you were called”.
The venue of the LWF Thirteenth Assembly was in the historic Polish city of Kraków,  In total, some 355 official delegates attended it. Also representatives of associate members, ecumenical guests, official presenters, advisors, ex officio participants, volunteers and staff presented.

The 13th #LWFAssembly in Krakow, our #OneBodyOneSpiritOneHope is renewed by our gathering together and will continue across 150 member churches in the days, months, and years to come.

📷 LWF Media Communication

#LWFAssembly #LWF #Krakow #Poland
#OneBodyOneSpiritOneHope
EECMY Youth Ministry
Photo
በአይሁዶች ላይ የተፈጸመ አሰቃቂ የጅምላ ግድያ
==(ከትናንት ታሪካዊ ስህተቶች እንማር)
ይህ ቦታ 'Auschwitz Birkenau' ይባላል። በፖላንድ ሀገር ውስጥ ይገኛል:: በ20 ኛው ክፍለ ዘመን በናዚ ጀርመን በአይሁዶች ላይ የተፈጸመውን ግፍ የሚያሳይ የመታሰብያ ስፍራ እና ሙዝዬም ነው::
በመጀመርያ ይህ የማጎሪያ ካምፕ የፖላንድ ፖለቲከኞችን እና የሶቪየት ሩሲያን የጦር እስረኞች ለማሰር በናዚዎች የተገነባ ነበር። በኋላ ግን በ1942-1945 ዓ.ም ከመላው አውሮፓ የመጡ አይሁዶች የሚሰቃዩበት እና በአሰቃቂ ሁኔታ የተገደሉበት የሞት ፋብሪካ ሆነ። ናዚዎች በወቅቱ በተቆጣጠሩባቸው የተለያዩ የአውሮፓ አገሮች የተለያዩ የማጎሪያ ካምፖችን ገንብተው ነበር። ይህ ግን ከማጎሪያ ካምፖች ሁሉ ትልቁ ነበር።

በዚያን ጊዜ ብዙ አይሁዶች በፖላንድ ይኖሩ ስለነበር እና ፖላንድ የምትገኘው በመካከለኛው አውሮፓ ውስጥ ስለነበረ በእነዚህ የፖላንድ ማጎሪያ ካምፖች ውስጥ አይሁዶችን ከተለያየ የአውሮፓ ሀገራት በጅምላ ሊገድሏቸው ሰብሰቧቸው:: በማጎሪያ ካምፖች ከተገደሉት 1.3-1.5 ሚሊዮን ሰዎች ውስጥ ከ90% በላይ የሚሆኑት አይሁዶች ሲሆኑ የፖላንድ የፖለቲካ እስረኞች እና ሌሎችም ተገድለዋል ። ከ1942 ዓ.ም ጀምሮ ግን ቦታው አይሁዶች በጅምላ የሚታሰሩበትና የሚገደሉበት ቦታ ሆነ። በፎቶዎቹ ላይ እንደምትመለከቱት ከተለያዩ የአውሮፓ ሀገራት አይሁዶችን ለስራ እንፈልጋችኃለን ብለው ወደዚህ ቦታ አስመጧቸው። አይሁዶች እውነት መስሏቸው ንብረታቸውን ጠቅልለው ወደ ፖላንድ ሄዱ።

ወደ ካምፑ ሲደርሱም በሁለት ጎራ እንዲሰለፉ ተደረጉ፡ አንደኛው መስመር ስራ ለመስራት አቅም ያላቸው ወንዶች ሲሆኑ ሁለተኛው መስመር ደግሞ ሴቶች፣ ህጻናት፣ አዛውንቶች፣ ታማሚወች እና አካል ጉዳተኞች ነበሩ። ከዚያም ያልጠበቁት አስፈሪ ነገር አጋጠማቸው፡ በመጀመሪያ ይዘውት የመጡት ንብረቶቻቸው ሁሉ ጫማና ልብሶቻቸውን እና የቤት ንብረቶቻቸውን ጨምሮ የያዙትን ሁሉ ተቀሙ። ናዚዎች ከዘረፉት ንብረቶች ውድ ዕቃዎችን ሰብስበው ወደ ጀርመን ይልኩ ነበር። ንብረቱ ከተወረሰ በኋላ የሴቶቹ ፀጉር ተቆርጦ/ተላጭቶ ወደ ፋብሪካዎች ይላክ ነበረ።

ከዚያም የግዳጅ ሥራ የሚሠሩትን ብርቱ ወንዶችን ብቻ ለይተው ወደ ማጎርያው ካምፕ ያስገቡአቸውና ከዚያም ወደ ተለያዩ የግዳጅ ሥራዎች ያሰማሯቸው ነበር። ለግዳጅ ሥራ የማይታዘዝ፣ ለማምለጥ የሞከረ እና ለማመፅ የሚሞክር፣ ከብዙ ሰዎች ጋር በጨለማ ጠባብ ክፍል ውስጥ ይታሰር ነበረ። ሌሎች ይሰቀላሉ፣ሌሎች በጠመንጃ ይገደላሉ... ሥራ ሲደክሙ የዋሉት ሲገቡ በቂ ምግብ አይሰጣቸውም፣ንፁህ የመጠጥ ውሃ ማግኘት አይቻልም፣ንጽህናቸውን ለመጠበቅ በቂ ውሃ የለም፣መጸዳጃ ቤት በቀን ሁለት ጊዜ ብቻ ይፈቀዳል።

ሰዎች በክፍት መጸዳጃ አብረው በጋራ ይጠቀማሉ፣ የሚኖሩበት ቤት እጅግ በጣም ቀዝቃዛ ቤት ነው፣ ሌላኛው ቤት ደግሞ ለፈረስ የተሰራ ቤት ነው።

በጣም በሚቀዘቅዝበት ጊዜ አብዛኛው ሰው በቦታው በቅዝቃዛው ምክንያት ይሞታል: ምክንያቱም በበረዶው ወቅት በቂ ልብስ እና ሙቀት ማግኘት አይቻልም:: እነዚህ ለጉልበት ስራ የተመረጡ ሰዎች እስኪሞቱ ድረስ ይሠራሉ: ከዚያም በመከራ ሞት ይሞታሉ::
ናዚዎች የጉልበት ሥራ መሥራት የማይችሉትን አረጋውያንን፣ ሕጻናትንና ሴቶችን፣ ሕሙማንን፣ አካል ጉዳተኞችን እንደደረሱ በአሰቃቂ ሁኔታ ይገድሏቸው ነበር። በሥዕሉ ላይ እንደሚታየው ከ 70 በመቶ በላይ የሚሆኑት ወዲያውኑ ወደ ሞት ፋብሪካ ይወሰዳሉ ይገደላሉ:: እንዴት እንደተገደሉ ለመናገር በጣም ከባድ እና ዘግናኝ ነው ... ልብሳቸውን አውልቀው በጠባብ እና በታጠረ ክፍል ውስጥ ብዙ ሰዎችን ሰብስበው ገዳይ የኬሚካል ጋዝ ይለቁባቸውና አሰቃይተው ይገሏቸዋል ... ከገደሏቸው በኋላ ሬሳቸውን ሰብስበው ያቃጥሉና አመዱን እንደ ማዳበሪያ ይጠቀሙ ነበር። እነዚህ ሁሉ ግድያዎች የተፈፀሙባቸው ያለ ምንም ምክንያት ወይም ጥፋት አይሁዳዊ በመሆናቸው ብቻ ነበር። የእነዚህ ግድያዎች ምንጭ ጥላቻ፣ በጥላቻ ላይ የተመሰረተ የፖለቲካ ፕሮፓጋንዳ፣ ‘ዘረኝነት’፣ ሽብርተኝነት እና የመሳሰሉት ናቸው። ለምሳሌ ያህል፣ በጊዜው (1944) ናዚዎችን በመወከል የፖላንድ ገዥ የሆነው ሃንስ ፍራንክ ‘የአይሁድ ዘር ከዓለም ሙሉ በሙሉ መጥፋት ያለበት ዘር ነው’ በማለት ይፎክር ነበረ።

በአጠቃላይ 6 ሚሊዮን የሚሆኑ አይሁዶች የፖላንድ ጨምሮ በተለያዬ ማጎሪያ ካምፖች በናዚዎች በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለዋል። ይህ በ20ኛው ክፍለ ዘመን በናዚዎች የተፈፀመው እጅግ አረመኔያዊ እና አሰቃቂ ድርጊት ነው።

መላውን የ 'Auschwitz Birkenau' የማጎርያ ካምፕ ስንዞር ስሜታችንን መግታት አልቻልንም፣ እንባችንንም መግታት አልቻልንም፣... ከአይሁድ ሴቶች የተቆረጠው ፀጉራቸው ፣ ጫማና ልብሳቸው፣ የቤት ዕቃቸው... በሙዝዬሙ ውስጥ ተቀማጧል።
መጀመሪያ ወደ ውስጥ ስንገባ መግቢያው ላይ የተሰቀለው ጽሁፍ እንዲህ የሚል ነው: ‘Those who do not remember the past are condemned to repeat it’ (George Santayana),፣ ትርጉም “የትናንቱን ስህተት የማያስታውስ ሰው እነዚያን ስህተቶች እንዲደግም ተፈርዶበታል” ይላል።

በየቀኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የኦሽዊትዝ ቢርኬናዉ ማጎሪያ ጣቢያን ይጎበኛሉ: ከዚህ ክፉ ክስተት እንድማሩ በተለያዩ ቋንቋዎች በባለሙያዎች ዝርዝር ማብራሪያ ይሰጣቸዋል። እኛም ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ ጎበኝተን በመጨረሻም እግዚአብሔር ምህረቱን እንዲያበዛልን እና ማስተዋልን እንዲጨምርልን: የዛሬዋ አለም ከትናንት ስህተቶች እንድትማር እና ስህተቶቹን እንዳትደግም ጸልይን ጉብኝታችንን አጠናቀቅን።

ከትናንት የታሪክ ስህተት እንድንማር: ዕድል አግኝቼ የጎበኘሁትን እናንተም እንድትማሩበት ይህን ታሪክ አጠናቅሬ አጠር አድርጌ ጻፍኩላችሁ። የእግዚአብሔር ቃል ማስተዋል የሌለው ሕዝብ ይጠፋል: ይወድቃል: ይገለበጣል (ሆሴዕ 4፡14) ስለሚል: ካለማስተዋል እንዳንጠፋ እግዚአብሔር ይርዳን : ማስተዋልንም ያብዛልን! ተባረኩ!

Via @wondmagegnudessa
@eecmyyouthministry
#LWFAssembly #Poland #AuschwitzBirkenau #Holocaustmemorial #HolocaustHistory
EECMY Youth Ministry
Photo
Ajjeechaan kun hundumtuu sababaa fi balleessaa tokko malee Yihuudota ta’uusaanii qofaaf irratti raawwatame. Maddi ajjeechaa kanaas jibba, olola siyaasaa jibbarraa madde, ‘Racism’, shororkeessummaa fi kkfdha. Fakkeenyaaf Naazii bakka bu’ee yeroo sana Poolaand bulchaa kan ture Haans Firaank namni jedhamu (1944), ‘Sanyiin Yihuudotaa sanyii addunyaa kanarraa guutummaatti baduu qabuudha’ jedhee dhaadachaa ture. Walumaagalatti, kaampii hidhaa fi ajjeechaa jumlaa ‘Auschwitz Birkenau’ biyya Poolaandiitti raawwatame dabalatee kaampiilee hidhaa fi ajjeechaa jumlaa adda addaatti Yihuudota naannoo miiliyoona 6tu Naaziidhaan haala sukkaanneessaa ta’een ajjeefaman. Kun gocha gara jabeenyaa, gocha sukkanneessaa, gocha fokkisaa fi dukkanaa dhala namaatiin jaarraa 20ffaa keessatti warra Naajiitiin gaggeeffameedha. Yeroo kaampii hidhaa fi ajjeechaa jumlaa ‘Auschwitz Birkenau’ kana keessa deddeemnee guutummaasaa ilaallu miira keenya towachuun nutta ulfaate, imimmaan keenya qabachuu dadhabne,… rifeensi dubartoota Yihuudotaarraa kukkutamee achitti hafe, kophee fi uffatnisaanii, meeshaaleen mana keessaa isaanii… ammayyuu seenaadhaaf achi keessa jira.
Yerooma jalqaba gara keessaa seennu barreeffama akkas jedhutu jira, ‘Those who do not remember the past are condemned to repeat it’ (George Santayana), Hiika: ‘Namni dogongora kaleessa hin yaadanne dogongora sana irra deebi’ee akka dogoggoruuf itti faradameera’ jedha. Bakka kaampii hidhaa fi ajjeechaa jumlaa ‘Auschwitz Birkenau’ kana kumaatamaan namootni daaw’achaa oolu, akka irraa baratanuuf immoo ibsi bal’aan ogeessotaan afaan garagaraatiin nikennamaaf. Nuutis jalqabaa hamma dhumaatti daaw’annee, dhumarrattis Waaqayyo araara Isaa akka nuuf baay’isuuf Waaqa kadhannee, addunyaan har’aas dogongora kaleessaarra akka barattuuf, dogoggora sana akka irra hin deebineef, Waaqayyo hubannaa akka nuuf baay’isuuf Waaqa kadhannee daawwannaa keenya xumurre.
Dogongora seenaa kaleessaarraa akka barannuuf jedhee, waan ani carraa argadhee daawwadhe isinis daawwadhaa, irraas baradhaa jedhee seenaa kana qindeessee gabaabsee isiniif barreesse. Sabni hubannaa hin qabne niballeeffama, nigaragala waan jedhuuf Sagaleen Waaqayyoo (R. Hose’aa 4:14), hubannaa dhabnee akka hin badne Waaqayyo nuhaagargaaruu, hubannaas nuuf haa baay’isuu! Horaa Bulaa!

Via @wondmagegnudessa
@eecmyyouthministry
#LWFAssembly #Poland #AuschwitzBirkenau #Holocaustmemorial #HolocaustHistory