EECMY Youth Ministry
1.74K subscribers
3.34K photos
8 videos
263 links
Fellowship - Discipleship - Evangelism

1Thimothy 4:12

This is the official telegram channel of EECMY Head Office - Youth Ministry
Download Telegram
Forwarded from EECMY Children Ministry: MY Sunday School (Wondmagegn Udessa)
*ልዩ ድጋፍ የሚሹ ልጆችን መደገፍ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ውይይት ተካሄደ*

መቀመጫውን በአሜሪካን ሀገር ካደረገው የበጎ አድራጎት ተቋም ጋራ  ልዩ ድጋፍ የሚሹ ልጆችን መደገፍ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ውይይት ተደርጓል:: በውይይቱም ልዩ ድጋፍ የሚሹ ልጆችን በመቀበል እና በመደገፍ ዙርያ የቤተክርስቲያን ድርሻ ከፍተኛ በመሆኑ በወላጆች ላይ: በልጆች መምህራን እና በቤተክርስቲያን መሪዎች ላይ መስራት አስፈላጊ መሆኑ ተነስቶ: አብሮ መስራት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ የድርጅቶቹ ዓለምዓቀፍ ግንኙነት አስተባባሪዎች ፓስተር ትራሲይ ግ.: ፓ/ር ማቲው ግ. እና የኢ/ወ/ቤ/ክ/መካነ ኢየሱስ የልጆች እና ወጣቶች አገልግሎት መምሪያ ዳይሬክተር ወንድማገኝ ኡዴሣ ውይይት አድርገዋል::

****
Daa'imman Deeggarsa Addaa Barbaadan Deeggaruun Akkaataa Danda'amu Irratti Mariin Gaggeeffameera***


Continue reading...
👇👇👇

@MYSundaySchool
*የድንበር ዘለል አገልግሎት ሚስዮናዊ ምደባና የሽኝት መርሃግብር ተካሄደ *

የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ በውጪና በአገር ውስጥ የምስራቹን ይዘው የሚሄዱ ጥሪ ያላቸውን አገልጋዮችን በመመልመል፣ በማሰልጠን እያሰማራች ትገኛለች፡፡
በማዕከላዊ ደቡብ ኢትዮጵያ ሲኖዶስ ስር የምትገኘው የሐዋሳ ቤቴል ማኅበረ ምዕመናንም የድንበር ዘለል አገልግሎት ሚስዮናዊ ደበላ ቦቴን ከነቤተሰቡ ወደ ምስራቅ አፍሪካ ለመላክ የምደባና ሽኝት መርኃግብር አድርጋለች፡፡
በዕለቱም: ከቤተክርስቲያኒቱ ዋና ጽ/ቤት: ከዓለም አቀፍ ሚስዮን ማኅበር ቦርድ: የተለያዩ አብያተ ክርስቲያናት ተወካዮች እና መሪዎች እንዲሁም የሲኖዶስ መሪዎች እና የሐዋሳ ከተማ ማኅበረ ምእመናናት መሪዎች ተገኝተዋል:: በዕለቱም የቤተክርስቲያኒቱ ተባባሪ ጠቅላይ ፀሐፊና የዓለም አቀፍ ሚስዮን ማኅበር ቦርድ ሰብሳቢ ቄስ ፈቃዱ ቤኛ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን የምደባና የሽኝት ሥነ ሥርዓቱ በሚስዮን ማኅበሩ ዳይሬክተር ቄስ ጥላዬ ከበደ መሪነት ተከናውኗል፡፡
በቀጣይም ይህን ታላቁን የወንጌል ተልዕኮ ከግብ ለማድረስ በፀሎት፣በገንዘብ በተለያዩ መንገዶች ድጋፍ እንዲደረግ ጥሪ ቀርቧል::
(Source: EECMY- International Mission Society)
***
''በወንጌልም ማኅበረተኛ እሆን ዘንድ ስለ ወንጌል ሁሉን አደርጋለሁ።'' 1ቆሮንቶስ 9:23

ስለ ሁሉ እግዚአብሔርን እያመሰገናችሁ
በጸሎት፣ በምክር ፣ በድጋፍ ከአለምአቀፍ የሚስዮን ማህበር አገልግሎት ጎን እንድትቆሙ በጌታ ፍቅር ጥሪ እናቀርባለን።

EECMY-IMS

1000008166432 CBE/ EECMY-IMS
2600280004746 BIRHAN BANK /EECMY-IMS
01320008596702AWASH/ EECMY-IMS

@eecmyyouthministry
*የደም ልገሳ መርሃግብር ተካሄደ*

በኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ ኢየሱስ የመካኒሳ ማህበረ ምዕመናን የወጣቶች አገልግሎት አስተባባሪነት ከደም ባንክ ጋር በመተባበር የደም ልገሳ መርሃግብር ተካሂዷል:: የደም ልገሳው ባለፉት 2 ዓመታት ውስጥ ለ 3ኛ ጊዜ የተደረገ ሲሆን: በዚህኛው ዙር በድምሩ 56 ሰዎች ደም ለግስዋል። በደም ልገሳ መረሃግብሩ ላይ የቤተክርስቲያኒቱ የልጆች እና ወጣቶች አገልግሎት መምርያ ዳይሬክተር ወንድማገኝ ኡዴሳ ደም ተገኝተው ደም ከለግሱ በኋላ: የመካኒሳ ማ/ም ወጣት መሪዎችንም ስለ መልካም ስራቸው አበረታተው: ሌሎች ወጣቶችም ከዚህ ልምድ በመውሰድ በየአካባቢያቸው ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር የደም ልገሳ እና መሰል የበጎ ፈቃድ ተግባራት ላይ በምሳሌነት እንዲሳተፉ መልዕክት አስተላልፈዋል::
===


Source: EECMY Mekanissa Congregation

#EECMY #YouthMinistry #BloodDonation