Ethiopian Educational Channel
6.9K subscribers
1.38K photos
34 videos
1.66K files
487 links
እንኳን ደና መጣችሁ
በዚህ ቻናል ላይ የሚያገኙት
1. ትምህርታዊ መረጃ መስጠት
2.የሳይኮሎጂ አስተማሪ ምክሮችንና አነቃቂ ንግግሮች
3.መፃህፍቶች በpdf እና የእንግሊዝኛ ትምህርት ይለቀቃሉ!
በዚህ ቻናል ሀይማኖታዊ እና ፓለቲካ ነክ አይለቀቅበትም !
የቴሌግራሙ ቻናል ሊንክ:👉https://t.me/EEC1227
Channel created by @BA1227
Download Telegram
Grade 6, 8 and 12
Model Exam Schedule

By: AACAEB
@eec1227
የሎተሪ ሿሿ!

ዛሬ ረፋድ ሜክሲኮ ጋ የታሸገ ፖስታ በእጇ የያዘችና ግራ የተጋባች ልጅ ገጠመችኝ። "እስቲ ስልክ ደውልልኝ" አለች በመደናገጥ ስሜት። እየተርበተበተች ቁጥሩን ነገረችኝ። ሞከርኩት "ስልኩ ዝግ ነው ይላል።
ሌላም ተለዋጭ ቁጥር ሰጠችኝ። እሱም ዝግ ነው።
" ኧረ ወይኔ ጉዴ . . . እስኪ ደግመህ ሞክርልኝ ጋሽዬ" አለች። ሞከርኩት። ለውጥ የለም። ላረጋጋጋት እየሞከርኩ የሆነችውን ጠየኳት።

"ሎተሪ ደርሶናል። ግን መታወቂያ የለንም" ያሉ የገጠር ልብስ የለበሱ፣ በገጠር ዘዬ የሚናገሩ 2 ልጆች "የሎተሪ ብር ተቀበይልን አሉኝ። ታሽጎ በቼክ ተሰጥቶን ነው። እኛ ማውጣት ስለማንችል አንቺ አውጪልን" ሲሉ ለመኑኝ።

"እሺ ከቻልኩ ምን ገዶኝ!" አልኳቸው። የሎተሪው ብር በቼክ ተጽፎ እዚህ ፖስታ ውስጥ ነው ያለው። ባንኩ ብቻ ነው መክፈት የሚችለው" ብለው ፈራ ተባ እያሉ የታሸገ ፖስታውን ሰጡኝ።

አንደኛው ግን "የኔ እህት ይቅርታ የምታወጪው ብር ብዙ ነው ከ250 ሺህ በላይ ነው በዚያው እብስ ብትይስ እንዴት እንመንሽ?" አለኝ።

"ችግር የለውም . . . ሀሳብ ከገባህ ስልኬን ያዙ" ስል አንዱ እሺ ብሎ ስልኬን ተቀበለ። ሌላኛው ግን "አይሆንም ያንሳል። ያን ሁሉ ብር እንዴት እንዲሁ በብላሽ . . . " ብሎ ተከራከረ።

ብሩን ካወጣሁላቸው 50 ሺህ ብር እንደሚሰጡኝ ቃል ገቡልኝ። ወደ ባንክ ልገባ ስል አንዱ "አይ አይሆንም . . . ብር ካላት ትስጠን" አለ።

"በእጄ ጥሬ ብር የለም" ስላቸው . . . በቃ በስልክሽ ትራንስፈር አድርጊልን" አሉኝ። ይሉኝታ እየያዘኝ እንዲያምኑኝ ስል በአካውንቴ ያለውን 17 ሺህ ብር በሙሉ በአካውንታቸው አስገባሁ።

እነሱ ውጪ እየጠበቁኝ። እኔ ወደ ባንክ ገባሁ። ከሁለት ሶስት ሰው ወረፋ በኋላ የሰጡኝን ሎተሪ እና የታሸገውን ፖስታ ለባንከሯ እየሰጠሁ የሎተሪ ብር እንድትሰጠኝ ስጠይቃት። "የኔ እህት እንዲህ ዓይነት አሰራር የለንም። ሎተሪውን ለብሔራዊ ሎተሪ ትሰጫለሽ። እነሱ ብሩን በአካውንትሽ ያስገባሉ" አለችኝ።

እንዳልተሳካ ልነግራቸው ስወጣ ልጆቹ በስፍራው የሉም። ይኸው ፖስታና ሎተሪ ወረቀት ይዤ ቀረሁ ብላ ፖስታውን ስንከፍተው ባዶ ምንም ያልተጻፈበት ነጭ ወረቀት ብቻ ነው ያለው።

ክው. . . ድርቅ. . . ብትልም የስልክ ቁጥሮችን ለማስታልወስ አልተቸገረችም። የሷ ስልክ ወዲያው ተዘግቷል። ሲደወል ዝግ ነው ይላል። ሌላ ቦታ ደውላ የሆነችውን በኔ ስልክ አስረዳች።

እኔም ተረጋጊ አንዴ ተበልተሻል። ወደ ቤትሽ ሂጂ ብዬ የትራንስፖርት ሰጥቼ ተሰናበትኳት።
ይሄ የሎተሪ ሿሿ በፊትም የነበረ ቢሆንም አሁን መልኩንና አይነቱን እየቀየረ መጥቷልና ሁላችንም እንጠንቀቅ!
Teddy Kassa
source:hageratube
1🤯1
ለጠቅላላ እውቀት👇👇👇
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫን ለመታዘብ ካመለከቱት የሀገር ውስጥ ታዛቢዎች ውስጥ በሕጉ ላይ የተቀመጠውን መሥፈርት ላሟሉ 55 ድርጅቶች ዕውቅና የሰጠ መሆኑ ይታወቃል። ድርጅቶቹም በተለያዩ አካባቢዎች ላይ የሚያሠማሯቸው 60,277 ወኪሎች (ቁጥራቸው ሊጨምር የሚችል) አስመዝግበዋል። የመታዘብ ዕውቅና ያገኙ ድርጅቶችን ዝርዝር ከታች ያገኛሉ።
-----------------------------------------------------------

1. ሆሊስቲክ ዴቭሎፕሜንት ኢንሼቲቭ አሶሴሽን
2. መሸሩመ ኢንተግረትድ ደቨሎፕመንት ኦርጋናይዘሽን
3. ምስራቃዊ ዕድገት ፋና
4. ሲራድ የምርምር እና የልማት ተቋም
5. ሳውዝ ዌስት በጎ አድራጎት ድርጅት
6. ሴንተር ፎር ኢምፓወርመንት ኢትዮጵያ ማህበር (ሲኢኢ)
7. ስቲም ፕላስ የማህበረሰብ ልማት ድርጅት
8. ስታንድ ፎር ኢንተግሬትድ ዴቨሎፕመንት ኢትዮጵያ
9. ቃል የተቀናጀ የማህበረስብ ልማት ድርጅት
10. ቦሮ ሺናሻ ልማት ማህበር
11. ተስፋብርሃን ትግራይ በጎ ኣድራጎት ማህበር
12. ትምራን
13. አክሽን ፎር ሬዚሊያንስ
14. አፍርካ ሥራ ፈጠራና ዘላቂ ልማት የበጎ አድራጎት ድርጅት
15. አዲስ አበባ ሴቶች ፌደረሽን
16. የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ድርጅቶች ህብረት(ኢሰመድህ)
17. የኢትዮጵያ ሴቶች ልማት ድርጅት
18. የኢትዮጵያ ሸማቾች መብት ተቆርቋሪ ድርጅት
19. ኦሮሚያ ሴቶች ማህበር
20. የመብቶቸ እና ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕክል
21. ኮሚዩኒቲ ሳስቴይነብል ዴቬሎፕሜንት ኤይድ(ኮስቲዳ)
22. የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ ሴቶች ማኅበር
23. የአማራ ክልል ወጣቶች ማህበራት ፌዴሬሽን
24. የአማራ ወጣቶች ማህበር
25. የአዲስ አበባ ከተማ ሴቶች ማህበር
26. የኢትዩጰያ ወጣቶች ምክር ቤት
27. የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር ማዕክላዊ ኢትዮጵያ ክልል ቅርንጫፍ
28. የኢትዮጵያ ሰላም ፣ ልማት እና ብልፅግና ድርጅት
29. የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ
30. የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ፎረም
31. የኢትዮጵያ ሴቶች ፌደሬሽን
32. የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ማህበራት ፌደሬሽን
33. የኢትዮጵያ ወጣቶች ፌዴሬሽን
34. የኢትዮጵያ የሲቪል ማህበራት ድርጅቶች ኅብረት ለምርጫ(ኅብረት ለምርጫ)
35. ነርቸር ኢጁኬሽን ኤንድ ዴቭሎፕመንት
36. የኢትዮጽያ ሴት አካል ጉዳተኞች ብሄራዊ ማህበር
37. የኦሮሚያ ወጣቶች ማህበር
38. የኦሮሚያ ወጣቶች ፌዴሬሽን
39. የጎንደር ልማትና ሰላም ማኅበር ወይም ጎልሰማ
40. ደቡብ ምክክርና ልማት ፎረም
41. ድሬ የተቀናጀ የማህበረሰብ ልማት ድርጅት
42. ጥላሁነን የበጎ አድራጎት ማህበር
43. ፊውቸር ጀነሬሸን ሆፕ ፎር ቨልነረብል ችልድሬን ኦርጋናይዘሽን
44. ፕሮጃይኒስት
45. ኦሮሚያ ሴቶች ፌዴሬሽን
46. መስጠት በጎ አድራጎት ድርጅ
47. ራምኖን ኢትዮጵያ የዕውቀት ፓርክ ማህበር
48. ሰኔ አስራ ስድስት የሰላምና የለዎጥ ተምሳሌት የበጎ አድራጎት ማህበር
49. ሶሻል አሊያንስ ቻሪቲ አሶስዬሽን
50. የኢትዮጵያ የህግ ባለሙያዎች ማህበር
51. ነፃ ትውልድ ሲቪክ ማህበር
52. አዎንታዊ ሰላም ለኢትዮጵያ
53. የተጋሩ የሰላምና ተሃድሶ ንቅናቄ ለኢትዮጵያ ማህበረ
54. የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማሕበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሠማኮ)
55. የአዲስ አበባ ወጣቶች ማህበር
1
የምርጫ ቅስቀሳ የተከለከለባቸው ቦታዎች የትኞቹ እንደሆኑ ያውቃሉ?
****

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባወጣው የምርጫ ቅስቀሳ ሥነ ምግባር መመሪያ ቁጥር 33/2018 አንቀጽ 11 መሰረት የምርጫ ቅስቀሳ የተከለከለባቸው ቦታዎች እና ሁኔታዎች የሚከተሉት ናቸው፦

1) በሚከተሉት ቦታዎች የምርጫ ቅስቀሳ ማድረግም ሆነ የምርጫ ቅስቀሳ ጥሪ ማድረጊያ ቁሳቁሶችን መለጠፍ፣ ማስቀመጥ ወይም በማንኛውም መንገድ ማስራጨት የተከለከለ ነው።

ሀ) ቤተ ክርስትያኖች፤

ለ) መስጊዶች፣

ሐ) ወታደራዊ ካምፖች እና ፖሊስ ጣቢያዎች፤

መ) በመንግስት መስሪያ ቤቶች እና ፅ/ቤቶች አካባቢ

ሠ) የመማር ማስተማር ሂደት ተግባር እየተከናወነ በሚገኝበት ወቅት በትምህርት ቤቶች እና በትምህርት ቤቶች አካባቢ በ200 መቶ ሜትር ርቀት ዙሪያ፤

ረ) ህዝብ የዕለት ተእለት ግብይት በሚፈዕምባቸው እና በተወሰኑ ቀናት በገጠርም ሆነ በከተማ በይፋ ገበያ እየተካሄደ በሚገኝባቸው ቦታዎች በ200 መቶ ሜትር ዙሪያ ክልል፤

ሰ) በቦርዱ ጽ/ቤት፣ በምርጫ ጣቢያ ጽ/ቤት፣ በምርጫ ከልል ጽ/ቤት እና የክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በ200 መቶ ሜትር ዙሪያ ክልል፤

ሸ) ሌላ ቀድሞ የተጀመረ ህዝባዊ ስብሰባ ወይም የምረጡኝ ቅስቀሳ እየተካሄደ ባለበት ቦታ።

2) በዚህ አንቀጽ በንኡስ አንቀጽ (1) ላይ የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ ከተከለከሉ ቦታዎች ውጪ በሆነ ቦታ የሚደረግ የምርጫ ቅስቀሳ የተከለከሉ ቦታዎች ላይ የሚደረገውን እንቅስቃሴ የማያደናቅፍ መሆን አለበት።
ይህ ሰነድ የሲቪል ሰርቪስ ሰራተኞች ቬርፊኬሽን (ማረጋገጫ) ስራ ከተቋማት የሚጠበቁ ተግባራትን የሚያሳይ ነው። በዋናነት ሶስት ክፍሎች አሉት፦

👉💥💥💥. የግድ መሟላት ያለባቸው ሰነዶች (11 ዓይነቶች)💥💥💥👈👈

· 👉ብሄራዊ መታወቂያ (ከተሰጠበት ስልክ ቁጥር ጋር)
· 👉የቢሮ መታወቅያ
· 👉የቅጥር ሰነድ/ደብዳቤ
· 👉የዝዉዉር ሰነድ
· 👉የደረጃ እድገት ሰነድ
· 👉ጡረታ የወጣ ሰራተኛ የአገልግሎት ማራዘሚያ ሰነድ
· 👉የትምህርት ማስረጃዎች
· 👉የጡረታ ፎርም
· 👉የስራ ልምድ ማስረጃ
· 👉ተሻሚ ከሆነ ደብዳቤ
· 👉ድልድል/ምደባ ደብዳቤ

👉ሌሎች ሰነዶች (ማሟላት ያለባቸው)
· የጋብቻ ሰርተፍኬት
· የልጆች የልደት ሰርተፍኬት (ልጆች ካሉ)
👉 የአሰራር ቅደም ተከተል
1. ሰነዶቻቸውን ያሟሉ ሰራተኞችን በቀን ለአንድ መረጃ ሰብሳቢ ቢያንስ 7 እንዲሆኑ በማዘጋጀት ቀኑን አስቀድሞ ማሳወቅ
2. በስራ፣ በወለድ፣ በዓመት እረፍት ምክንያት የሌሉ ሰራተኞች በአካል ቀርበው እንዲመዘገቡ ማድረግ
3. ጥንቃቄ ያለው፣ የIT ችሎታ ያለው ኃላፊ መመደብ
4. ስራቸውን በአግባቡ የማይሰሩ ከሆነ ለአሰአይታ ስታቲስቲክስ ቅ/ጽ/ቤት ማሳወቅ ወይም የወረዳው የሲቪል ሰርቪስ ሀላፊ ማሰወቅ ምክንያቱም ሰራው የሚከታተለው የሲቪል ሰርቪስ ሀላፊው ሰለሆነ ነው
3
ለተማሪዎች ውጤታማ የአጠናን ዘዴዎች!
#የጊዜ አያያዝ እና እቅድ ማውጣት
1. የጊዜ ሰሌዳ መዘርጋት - ለእያንዳንዱ ትምህርት ዓይነት የተወሰነ የጥናት ጊዜ መመደብ
2. ቅድሚያ የሚሰጣቸውን የትምህርት አይነቶችን መለየት
3. እቅድ ማውጣት - መነበብ ያለባቸውን ትምህርቶች በመለየት ዕቅድ ማውጣት
#የጥናት አካባቢ
1. ምቹ የጥናት ቦታ መለየት
2. ንጹህ አየር ያለበት ቦታ መምረጥ
3. ጸጥታ የሰፈነበት ቦታ - ከረብሻ ነፃ የሆነ ቦታ መምረጥ
4· ከስልክ እና ሌሎች ትኩረት ከሚሰርቁ ነገሮች መራቅ
#የማስታወስ ዘዴዎች
1. ቅድመ-ንባብ - አንድን ምዕራፍ ከማጥናቱ በፊት ጠቃሚ ይዘቶችን መለየት
2. መደጋገም - የተማርነውንና ያጠናነውን ወሳኝ ይዘት እንዳይረሳ በተደጋጋሚ መከለስ
3. ጎላ አድርጎ ማጉላት - ዋና ዋና ነጥቦችን በቀለም ማጉላት
4. የጎን ማስታወሻዎች - በደብተር ዳር አጫጭር ማስታወሻዎችን መጻፍ
5. ማጠቃለያ - ካነበብክ በኋላ በራስህ ሀሳብ በአእምሮ ማጠቃለል
6. ቁልፍ ቃላትን መለየት - አስፈላጊ ቃላትን እና ሀረጎችን መጠቀም
7. ቃላት አሳጥሮ መጠቀም - ለማስታወስ አጫጭር ስሞችን መጠቀም
8. ማስተማር - ከሌሎች ጋር መማማር ትምህርቱን ለማጠናከር ይረዳል
9. የማስታወሻ ቦታ ዘዴ - ነገሮችን በቀላሉ ለመያዝ ከቦታዎች ጋር ማዛመድ
10. ተረት መፍጠር - በቀላሉ ለማስታወስ መረጃዎችን በተረት መልክ መያዝ
#ንባብ እና ጽሑፍ
1. ቅድመ-ንባብ - አንድን ምዕራፍ ከማጥናቱ በፊት ወሳኙን ይዘት መለየት
2. ያለፉ ፈተናዎችን መለማመድ - የቀድሞ ፈተናዎችን በመስራት ልምምድ ማድረግ
3. ጎላ አድርጎ መፃፍ - ዋና ዋና ነጥቦችን በቀለም በጉልህ መፃፍ
4. ማጠቃለያ መጻፍ - ካነበብክ በኋላ በራስህ ሀሳብና ቃል ማጠቃለል
#የቡድን ጥናት
1. የጥናት ቡድን መመስረት - ከሌሎች ተማሪዎች ጋር በመሆን መወያየትና መጠያየቅ
2. የጥያቄ እና መልስ ክፍለ ጊዜ - እርስ በርስ መጠያየቅ
3. የቡድን አብሮ መስራት - አብሮ በመስራት መማማር
4. መምህራንን መጠየቅ - ያልተረዳህን ነገር መጠየቅ
5. የፈተና መረጃዎችን መለዋወጥ - ከሌሎች ተማሪዎች ጋር መረጃ መለዋወጥ
#ፈተና ለመፈተን ዝግጅት
1. አስቀድሞ መጀመር - በፈተና ቀን ቅድመ ዝግጅት ማድረግ
2. ዘና ማለት - በፈተና ወቅት መረጋጋት እና ጥያቄዎችን በጥንቃቄ ማንበብ
3. ጭንቀትን ማስወገድና ዘና ማለት
#ጤና እና ደህንነት
1. በቂ እንቅልፍ መተኛት
3. የአካል እንቅስቃሴ - በየቀኑ ትንሽ የአካል እንቅስቃሴ ማድረግ
4. ውሃ መጠጣት - በቂ ውሃ መጠጣት ለአዕምሮ ትኩረት ይረዳል
5. አጭር ዕረፍት - በማጥናት መካከል አጭር ዕረፍት ማድረግ
3
ለተሻለ የመማር ማስተማር ሂደት 30 ምርጥ ስነ-ዘዴዎች
ይህ ሰነድ መምህራን በክፍል ውስጥ ሊጠቀሙባቸው የሚገቡ ዘመናዊና ውጤታማ የማስተማሪያ ዘዴዎችን ዝርዝር መግለጫና አተገባበር ይዟል።
1. ገላጭ የማስተማር ዘዴ (Lecture Method)
ትርጉም: መምህሩ መረጃን ለተማሪዎች በንግግር መልክ የሚያቀርብበት ዘዴ ነው።
አተገባበር: አዳዲስ ርዕሶችን ለማስተዋወቅ ይጠቅማል። ረጅም ከመሆን ይልቅ አጫጭርና ግልጽ በሆኑ ነጥቦች መቅረብ አለበት።
2. የውይይት ዘዴ (Discussion Method)
ትርጉም: ተማሪዎች በአንድ ርዕስ ላይ ሀሳባቸውን የሚለዋወጡበት ነው።
አተገባበር: መምህሩ መሪ ጥያቄዎችን ያቀርባል፤ ተማሪዎች በቡድን ወይም በጋራ ይወያያሉ።
3. ተግባራዊ ማሳያ ዘዴ (Demonstration Method)
ትርጉም: መምህሩ አንድን ነገር እንዴት እንደሚሰራ በተግባር የሚያሳይበት ነው።
አተገባበር: በሳይንስ ሙከራዎች ወይም በቴክኒክ ትምህርቶች ላይ "በማየት መማርን" ያጎለብታል።
4. በችግር አፈታት ላይ የተመሰረተ ትምህርት (Problem-Based Learning - PBL)
ትርጉም: ተማሪዎች እውነተኛ ችግሮችን በመፍታት ሂደት ውስጥ እንዲማሩ ማድረግ ነው።
አተገባበር: ተማሪዎች አንድን ችግር ተቀብለው መፍትሄ ለመፈለግ ምርምር ያደርጋሉ።
5. የቡድን ስራ (Group Work/Collaborative Learning)
ትርጉም: ተማሪዎች በትንንሽ ቡድኖች ተከፋፍለው በጋራ የሚሰሩበት ነው።
አተገባበር: ማህበራዊ ግንኙነትንና የቡድን መንፈስን ያዳብራል።
6. የተገላቢጦሽ ክፍል (Flipped Classroom)
ትርጉም: ተማሪዎች ትምህርቱን በቤታቸው (በቪዲዮ ወይም በንባብ) አይተው ይመጣሉ፤ በክፍል ውስጥ መልመጃ ብቻ ይሰራሉ።
አተገባበር: የክፍል ጊዜን ለጥልቅ ውይይትና ለተግባር ስራ ይቆጥባል።
7. የጥያቄና መልስ ዘዴ (Socratic Method)
ትርጉም: መምህሩ መልሱን ከመናገር ይልቅ ተከታታይ ጥያቄዎችን በመጠየቅ ተማሪው ራሱ መልሱ ላይ እንዲደርስ ማድረግ ነው።
አተገባበር: ሂሳዊ አስተሳሰብን (Critical Thinking) ለማሳደግ ይረዳል።
8. በጨዋታ የታገዘ ትምህርት (Gamification)
ትርጉም: የጨዋታ ህጎችንና ውድድሮችን በትምህርት ውስጥ ማካተት ነው።
አተገባበር: የተማሪዎችን ተነሳሽነት ለመጨመር "ኩዊዝ" ወይም "ውድድሮችን" ማዘጋጀት።
9. የጉብኝት ዘዴ (Field Trip)
ትርጉም: ተማሪዎችን ከክፍል ውጭ ወደ ተቋማት ወይም ተፈጥሯዊ ቦታዎች በመውሰድ ማስተማር።
አተገባበር: ትምህርቱን ከእውነተኛው ዓለም ጋር ያገናኛል።
10. የግለሰብ ጥናት (Independent Study)
ትርጉም: ተማሪው በራሱ ፍጥነትና ምርጫ በአንድ ርዕስ ላይ ጥናት እንዲያደርግ መፍቀድ።
አተገባበር: ራስን በራስ የማስተማር ብቃትን ያሳድጋል።
11. አእምሮን ማንቃት (Brainstorming)
ትርጉም: በአንድ ርዕስ ላይ ተማሪዎች ያሰቡትን ማንኛውንም ሀሳብ ያለ ገደብ እንዲናገሩ ማድረግ።
አተገባበር: አዳዲስ ሀሳቦችን ለማመንጨትና ፈጠራን ለማበረታታት ይጠቅማል።
12. ሚና መጫወት (Role Playing)
ትርጉም: ተማሪዎች የታሪክ ወይም የማህበራዊ ገጸ-ባህሪያትን ወክለው እንዲተውኑ ማድረግ።
አተገባበር: ስሜትን የመረዳት (Empathy) እና የንግግር ችሎታን ያሳድጋል።
13. ንጽጽራዊ ትምህርት (Inquiry-Based Learning)
ትርጉም: ተማሪዎች ጥያቄዎችን በማንሳት ምርመራ የሚያካሂዱበት ዘዴ።
አተገባበር: መምህሩ መመሪያ ይሰጣል፤ ተማሪዎች መረጃ ፈልገው ድምዳሜ ላይ ይደርሳሉ።
14. ማይክሮ-ማስተማር (Micro-teaching)
ትርጉም: አጫጭር ትምህርቶችን ለጥቂት ተማሪዎች በመስጠት ግብረ-መልስ ማግኘት።
አተገባበር: በዋናነት ለመምህራን ስልጠናና ለተማሪዎች አቀራረብ ልምምድ ይጠቅማል።
15. የኬዝ ጥናት (Case Study)
ትርጉም: የተከሰቱ እውነተኛ ታሪኮችን ወይም ሁኔታዎችን መተንተን።
አተገባበር: ውሳኔ የመስጠት ብቃትን ለማዳበር ይረዳል።
16. ምስላዊ ትምህርት (Visual Learning)
ትርጉም: ስዕሎችን፣ ቪዲዮዎችንና ግራፎችን መጠቀም።
አተገባበር: መረጃን በምስል ለሚረዱ ተማሪዎች እጅግ አስፈላጊ ነው።
17. ተረት የመናገር ዘዴ (Storytelling)
ትርጉም: ትምህርቱን በተረት ወይም በአጓጊ ታሪክ መልክ ማቅረብ።
አተገባበር: ተማሪዎች ትምህርቱን እንዳይረሱት ያደርጋል።
18. የእርስ በእርስ ትምህርት (Peer Teaching)
ትርጉም: ተማሪዎች እርስ በእርሳቸው እንዲማማሩ ማድረግ።
አተገባበር: የሚያስተምረው ተማሪ ትምህርቱን በደንብ እንዲረዳው፣ የሚማረውም በቀላሉ እንዲገባው ያደርጋል።
19. በፕሮጀክት ላይ የተመሰረተ ትምህርት (Project-Based Learning)
ትርጉም: ለረጅም ጊዜ የሚቆይና ውጤት (Product) ያለው ስራ መስጠት።
አተገባበር: ለምሳሌ ሞዴል መስራት ወይም የጥናት ጽሁፍ ማዘጋጀት።
20. የሃሳብ ካርታ (Mind Mapping)
ትርጉም: መረጃዎችን በቅርንጫፍ መልክ በስዕል ማስቀመጥ።
አተገባበር: ውስብስብ ትምህርቶችን በቀላሉ ለማጠቃለል ይረዳል።
21. ተለዋዋጭ የማስተማር ዘዴ (Differentiated Instruction)
ትርጉም: እንደ ተማሪው ፍላጎትና ብቃት የማስተማር ስልቱን መቀየር።
አተገባበር: ለተለያዩ ተማሪዎች የተለያዩ ተግባራትን መስጠት።
22. የማስታወሻ አያያዝ ዘዴ (Note-taking Method)
ትርጉም: ተማሪዎች ዋና ዋና ነጥቦችን እንዲመዘግቡ ማስተማር።
አተገባበር: ለፈተና ዝግጅትና ለትኩረት ይረዳል።
23. ሙከራ (Experimentation)
ትርጉም: በቤተ-ሙከራ ውስጥ በተግባር ማረጋገጥ።
አተገባበር: ለተፈጥሮ ሳይንስ ትምህርቶች ወሳኝ ነው።
24. ዲጂታል ትምህርት (E-learning/Blended Learning)
ትርጉም: የኮምፒውተርና የኢንተርኔት ቴክኖሎጂን መጠቀም።
አተገባበር: ኦንላይን ግብአቶችንና ሶፍትዌሮችን መጠቀም።
25. ራስን መገምገም (Self-Assessment)
ትርጉም: ተማሪዎች የራሳቸውን ስራ እንዲገመግሙ ማድረግ።
አተገባበር: የኃላፊነት ስሜትን ይፈጥራል።
26. የተግባቦት ዘዴ (Communicative Language Teaching)
ትርጉም: ቋንቋን ለመግባቢያነት ብቻ ትኩረት ሰጥቶ ማስተማር።
አተገባበር: ተማሪዎች በቋንቋው እንዲናገሩ ማበረታታት።
27. ሞዴሊንግ (Modeling)
ትርጉም: መምህሩ ትክክለኛውን አሰራር ቀድሞ ሰርቶ ያሳያል።
አተገባበር: ተማሪዎች መምህሩን በማየት አርአያ ያደርጋሉ።
28. የክርክር ዘዴ (Debate)
ትርጉም: ተማሪዎች በሁለት ተቃራኒ ሀሳቦች ላይ ተከራክረው እንዲያሸንፉ ማድረግ።
አተገባበር: የማሳመንና የማመራመር ችሎታን ይገነባል።
29. የጥንድ ውይይት (Think-Pair-Share
ትርጉም: ተማሪው መጀመሪያ ለብቻው ያስባል፣ ከዚያ ከጓደኛው ጋር ይወያያል፣ በመጨረሻ ለክፍሉ ያጋራል።
አተገባበር: ዓይን አፋር ተማሪዎች እንዲሳተፉ ይረዳል።
30. የተቀናጀ ትምህርት (Integrated Teaching)
ትርጉም: የተለያዩ የትምህርት አይነቶችን አቀላቅሎ ማስተማር።
አተገባበር: ለምሳሌ ሂሳብን ከታሪክ ጋር አያይዞ ማቅረብ።
ወቅታዊ እና ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን #Join በማድረግ በቀላሉ ይከታተሉ።
tiktok.com/@eec1227
4
መልካም የእናቶች ቀን!!

እውነተኛ ወዳጅ የህይወት መንገድ መሪ
ናትና ደግ አዛኝ ልጆቿን አፍቃሪ
ትኑር ለዘለአለም ያቆያት ፈጣሪ።

✍️ዘሪሁን ከ አሰላ
ግንቦት 2/2018
8
ገንዘብ የመቆጠቢያ መንገዶች.....
ገንዘብን ለመቆጠብ እና የፋይናንስ ደህንነትን ለማረጋገጥ የሚረዱ ውጤታማ ስልቶች እንደሚከተለው ቀርበዋል፦

​1. በጀት ማውጣት (Budgeting)

​የገቢ እና ወጪ መመዝገቢያ፡ በየወሩ የሚገባዎትን ገቢ እና የሚወጣውን ወጪ በዝርዝር ይያዙ። ይህ ወዴት እንደሚሄድ ያላሰቡት ገንዘብ እንዳለ ለመለየት ይረዳል።

​የ50/30/20 ህግ፡ ገቢዎን ለሶስት ይከፍሉት።

​50%፡ ለቤት ኪራይ፣ ለምግብ፣ ለትራንስፖርት እና ለፍጆታ (ለአስፈላጊ ነገሮች)።

​30%፡ ለፈለጉት መዝናኛ ወይም የግል ፍላጎት።

​20%፡ ለመቆጠብ ወይም እዳ ለመክፈል ብቻ።

​2. ወጪን የመቀነስ ስልቶች

​የምግብ ዝግጅት፡ ውጭ ከመመገብ ይልቅ በቤት ውስጥ ማዘጋጀት ከፍተኛ ወጪን ይቆጥባል።

​ቅድሚያ የሚሰጡ ግዢዎች፡ አንድን ነገር ከመግዛትዎ በፊት "አሁን በጣም ያስፈልገኛል ወይስ ስሜታዊ ግዢ ነው?" ብለው ራስዎን ይጠይቁ።

​የቅናሽ ጊዜዎችን መጠበቅ፡ አስፈላጊ የሆኑ ቁሳቁሶችን በሚፈልጉበት ጊዜ ሳይሆን፣ ቅናሽ በሚደረግበት ወቅት መግዛት ተገቢ ነው።

​3. የቁጠባ ባህል ማዳበር

​ቅድሚያ መቆጠብ (Pay Yourself First)፡ ደመወዝ ወይም ገቢ እንደገባዎት ወዲያውኑ የተወሰነውን ክፍል ለቁጠባ ይለዩ። ቀሪውን ደግሞ ለወጪ ይጠቀሙ።

​የቁጠባ ግብ መኖር፡ ለምን እንደሚቆጥቡ ግልጽ ግብ ይኑርዎት (ለምሳሌ፡ ለድንገተኛ አደጋ፣ ለቤት ግንባታ ወይም ለትምህርት)። ግብ ሲኖር ቁጠባው ትርጉም ይኖረዋል።

​የድንገተኛ አደጋ ፈንድ (Emergency Fund)፡ ቢያንስ ከ3 እስከ 6 ወር የሚሸፍን የኑሮ ወጪ ማጠራቀም፣ በድንገተኛ ህመም ወይም በስራ ለውጥ ወቅት የሚፈጠረውን የገንዘብ ጫና ይቀንሳል።

​4. የፋይናንስ አስተዳደር ምክሮች

​እዳን በቅድሚያ መክፈል፡ ከፍተኛ ወለድ ያላቸውን እዳዎች (የብድር ካርዶች ወይም የግል ብድሮች) በተቻለ ፍጥነት መጨረስ ወለድን በመቆጠብ ገንዘብዎን በሌላ ስራ ላይ እንዲያውሉት ያደርጋል።

​ትንሽ ነገር ትልቅ ለውጥ፡ በየቀኑ በትንሽ በትንሹ የሚረግፈውን ገንዘብ ለምሳሌ የቡና ወይም የጫት ወጪን በመቀነስ በወር ውስጥ ምን ያህል እንደሚሰበሰብ ያሰሉ።

​5. የገቢ ምንጭን መጨመር

​ገንዘብ መቆጠብ ብቻ ሳይሆን ገቢን የመጨመር መንገዶችን መፈለግ ለምሳሌ ተጨማሪ የትርፍ ሰዓት ስራ ወይም ክህሎትን ተጠቅሞ ተጨማሪ ገቢ መፍጠር የረጅም ጊዜ የፋይናንስ ነፃነትን ያመጣል
4
#በወርቅ ሳጥን ላይ የተቀመጠው ለማኝ!

ሳታውቀው በወርቅ ሳጥን ላይ ተቀምጠህ ለሰዎች እጅህን እየዘረጋህ ይሆን? አሁን ራስህን መፈተሽ ያለብህ ጊዜ ነው!"
አንድ ለማኝ ከሰላሳ ዓመታት በላይ በአንድ አሮጌ ሳጥን ላይ ቁጭ ብሎ በመንገድ ዳር ይለምን ነበር። አንድ ቀን አንድ መንገደኛ በዚያ በኩል ሲያልፍ ለማኙ እንደለመደው እጁን ዘርግቶ "ስለ ፈጣሪ አንድ ሳንቲም ለግሰኝ?" ሲል ለመነው።
መንገደኛውም ቆም አለና እንዲህ ሲል ጠየቀው፦ "ለመሆኑ ይህ ለሰላሳ ዓመታት የተቀመጥክበት አሮጌ ሳጥን ውስጥ ምን አለ?"
ለማኙም ትከሻውን እየሰበቀ "እኔንጃ! አሮጌ ሳጥን እኮ ነው፤ በውስጡ ምንም የለም። ከፍቼውም አላውቅም" ሲል መለሰ። መንገደኛው ግን አልረካም፤ "እስቲ አንድ ጊዜ እንኳ ለመክፈት ሞክር?" አለው።
ለማኙ በግዴለሽነትና ተስፋ በመቁረጥ ሳጥኑን ከፈተው። በድንገት ግን ዓይኖቹ ፈጠጡ! ለሰላሳ ዓመታት ደሃ ሆኖ ሲለምንበት የነበረው ያ አሮጌ ሳጥን በወርቅ የተሞላ ነበር! ሰውየው ለዘመናት በሀብት ላይ ቁጭ ብሎ ሌሎችን ይለምን ነበር።
💡 ከዚህ ታሪክ የምናገኘው 3 ታላላቅ የሕይወት ትምህርቶች፦

💎 እውነተኛው ሀብት በውስጥህ ነው!

ልክ እንደ ለማኙ፣ ብዙዎቻችን ደስታን፣ ፍቅርንና ስኬትን ከውጭ እንፈልጋለን። ነገር ግን ፈጣሪ እያንዳንዳችንን ስንፈጠር በውስጣችን ትልቅ "የወርቅ ሳጥን" (ተሰጥኦ፣ ጥንካሬና አቅም) አኑሮልናል። ስኬት የሚጀምረው ወደ ውጭ እጅን በመዘርጋት ሳይሆን፣ ወደ ውስጥ በመመልከትና ያለህን አቅም በማወቅ ነው።

🚪 "ሳጥኑን" ለመክፈት ድፍረት ይኑርህ!

ለማኙ ለሰላሳ ዓመታት ሳጥኑን ያልከፈተው "ምንም የለውም" ብሎ ስላሰበ ነው። እኛም ብዙ ጊዜ "አልችልም፣ አቅም የለኝም፣ ዕድለኛ አይደለሁም" በሚሉ አሮጌ አስተሳሰቦች ተሸፍነን በውስጣችን ያለውን ድንቅ ማንነት ሳይከፈት እናስቀረዋለን። ዛሬ ራስህን የመመርመርና አቅምህን የመክፈት ድፍረት ይኑርህ።

🛑 ከልመና አስተሳሰብ ውጣ!

ልመና ማለት የግድ ገንዘብ መጠየቅ ብቻ አይደለም። ከሰዎች ማረጋገጫን መጠበቅ፣ በሌሎች ውሳኔ ላይ መደገፍና ለውድቀታችን ሌላውን መውቀስም ልመና ነው። አንተ "የወርቅ ሳጥን" ባለቤት መሆንህን ስታውቅ፣ ከሰዎች እጅ መጠበቅን ትተህ ለዓለም የምታበረክት ትልቅ ሰው ትሆናለህ።
🔥 የዛሬው መልእክት፦
አንተ ዛሬ የተቀመጥክበት "አሮጌ ሳጥን" (አስተሳሰብህ) ውስጥ ምን አለ? ሳጥኑን ሳትከፍተውና በውስጡ ያለውን ወርቅ ሳታውቅ ዕድሜህን በከንቱ አትጨርሰው። አሁኑኑ ወደ ውስጥህ ተመልከት!
1