Eco-Terk Main Channel
50 subscribers
13 photos
1 video
1 file
17 links
ኢኮ-ተረክ፦ የዕለት ተዕለት ውሳኔዎቻችን እና ምርጫዎቻችን ሳይንሳዊ ትርጉም በሚያስደንቅ መልኩ ያገኙበታል ።
​ዓለማችን ዜጎቿን የምታይበት ማጣኔ ሐብታዊ እንድምታ እንዲሁም እርሶ በዚህ ውስጥ ያሎውትን ሚና በምክንያታዊነት ለመረዳት ና በገንዘብ ነክ ጉዳዮች ላይ ግንዛቤዎን ለማሳደግ 'Subscribe' በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ
Making economics simple and practical for everyone
Download Telegram
በአሁኑ ሰዓት በዓለማችን ላይ ያለው እጅግ የከፋው ድህነት "የገንዘብ ማጣት" ሳይሆን "የሥነ-ምግባር መውደቅ" ነው። በየዓመቱ በአፍሪካ ብቻ በሙስና ምክንያት የሚጠፋው ገንዘብ፣ አህጉሪቱን ለአሥር ጊዜ ሊገነባ የሚችል ነው።
In the long run, almost everything becomes endogenous. This is the central insight of Growth Theory. The most important question in economics

"Why do some countries grow rich while others stay poor?"

is fundamentally about making the "exogenous" variables of one model the "endogenous" outcomes of a deeper, more powerful model. https://t.me/ECOTEREK
በኢኮኖሚክስ ውስጥ ትልቁ እውነት "የሰው ፍላጎት ወሰን የለውም፣ ግብዓቶች ግን ውስን ናቸው" የሚለው ነው። ጊዜ፣ ገንዘብ እና ተፈጥሯዊ ሀብቶች ውስን በመሆናቸው ሁልጊዜ ምርጫ ማድረግ ግድ ይለናል።
​ የዕድል ዋጋ (Opportunity Cost)
​አንድን ምርጫ ስንመርጥ የምናጣው ሌላኛው አማራጭ "የዕድል ዋጋ" ይባላል። ለምሳሌ፦
​ዛሬ ማታ ለትምህርት ካነበብክ፣ ያጣኸው የእንቅልፍ ወይም የፊልም ማየት ጊዜ የጥናቱ 'Opportunity Cost' ነው።
​ቁምነገሩ፦ ማንኛውም ነገር ዋጋ አለው፤ ዋጋውም የገንዘብ ብቻ ሳይሆን የምናጣው አማራጭ ጭምር ነው።
❤1
የብር ዋጋ መሬት ሲያርፍ ሸማቹ ምን ማድረግ አለበት? 📉

የምንዛሬ ተመን ማሻሻያው የውጭ ገቢ እቃዎችን ዋጋ እንደሚያሰቅለው ይታወቃል። 💸 ነገር ግን የዋጋ ግሽበቱ በኪሳችን ላይ የሚያሳድረውን ምት በስልታዊ ውሳኔ መቋቋም እንችላለን።

📌 3 ወሳኝ የሸማች ህጎች፡

1️⃣ በስሜት አትግዛ (Avoid Panic Buying) 🛑: "ነገ ይወደዳል" በሚል ስጋት አላስፈላጊ ሸቀጦችን ማከማቸት የሰው ሰራሽ እጥረት አካል ያደርግሃል።

2️⃣ ሀገር በቀል አማራጮችን ፈልግ 🇪🇹: ለውጭ ምርቶች ተመሳሳይ አገር በቀል አማራጮችን በመጠቀም ገበያውን ማረጋጋት ይቻላል።

3️⃣ የመግዛት አቅምህን ከፋፍል 💰: ቅድሚያ የሚሰጣቸውን መሰረታዊ ፍላጎቶች ብቻ በመለየት የወጪ በጀትህን አስተካክል።

💡 ብልህ ሸማች በዋጋ ንረት አያማርርም፤ አሰራሩን ተረድቶ ውሳኔውን ያስተካክላል! 🧠
🆒1
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ወንዙን ስጠጣ

ምንጩን አስብ
በስኳር፣ ዘይትና ስንዴ ላይ የታየው ከፍተኛ ጭማሪ የሐምሌን የዋጋ ግሽበት ወደ 15.3% ከፍ አደረገው 📈

የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት እንዳስታወቀው ፤ የዋጋ ግሽበቱ በሐምሌ ወር 15.3 በመቶ ሆኖ ተመዝግቧል ይህም በሰኔ ወር 2018 ዓ.ም. ከነበረው 13.9 በመቶ ጋር ሲነጻጸር የ1.4 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል።

የአገልግሎቱ መረጃ እንደሚያሳየው ፣ በሐምሌ ወር 2018 ዓ.ም. የተመዘገበው አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት መጠን ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ከነበረው 13.7 በመቶ ጋር ሲወዳደርም ጭማሪ አሳይቷል።

በወሩ ውስጥ የታየው ይህ አጠቃላይ የዋጋ ንረት ግፊት በዋናነት በምግብ እና ምግብ ነክ ባልሆኑ ሸቀጦች ላይ በተመዘገበው ጭማሪ የተከሰተ መሆኑ ተመላክቷል።

ለሐምሌ ወር አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት መጨመር ከፍተኛውን ድርሻ የያዘው የምግብ እና አልኮል ያልሆኑ መጠጦች ዋጋ ግሽበት ሲሆን፣ በወሩ 15.7 በመቶ ደርሷል።

በዚህ የምግብ ምድብ ውስጥ እህል (13.6 በመቶ)፣ ስንዴ (21.6 በመቶ)፣ የወተት ተዋጽኦዎችና እንቁላል (18.9 በመቶ)፣ ፍራፍሬ (19.2 በመቶ)፣ ዘይት (20.34 በመቶ) እና ስኳር (39.4 በመቶ) በመቶኛ ከፍተኛ ጭማሪ አሳይተዋል።


በሌላ በኩል ደግሞ ምግብ ነክ ያልሆኑ ሸቀጦች የዋጋ ግሽበት በሐምሌ ወር 14.8 በመቶ ሆኖ ተመዝግቧል። በዚህ ዘርፍ ትራንስፖርት 15.6 በመቶ፣ አልኮል መጠጦችና ትምባሆ 16.0 በመቶ፣ ምግብ ቤቶችና ሆቴሎች 15.6 በመቶ እንዲሁም ሌሎች እቃዎችና አገልግሎቶች 19.3 በመቶ ድርሻ እንዳላቸው ሪፖርቱ አክሎ ገልጿል።
👏2❤1
Channel name was changed to «Eco-Terk Main Channel»
Channel photo updated
Channel photo updated
ሒሳብ ሳይከፍሉ
ሀሳብ አይጀምሩ
እንኳን ለዘመነ ሉቃስ አዲስ ዓመት ባሕረ ሐሳብና ምዑዝ መንፈስ በሰላም አደረሳችሁ! 🌍✨
ዘመን ሲለወጥ በታሪክ መዝገብ ላይ አዲስ ገጽ ይከፈታል፤ ተስፋ ደግሞ በልቦናችን ውስጥ እደ-ጥበቡን ይዘረጋል🌱። ያለፈው ዓመት የደከምንበት፣ የታገልንበትና ብዙ ልምድ የሰነቅንበት የዕውቀትና የጥንካሬ መሠረት ሆኖ ሲሸኝ፤ አዲሱ ዓመት ደግሞ ያልተነቡ ዕድሎችንና አዳዲስ የስኬት አድማሶችን ይዞልን ብቅ ብሏል 📈።


በዚህ በበጋው መባቻ፣ የብርሃንና የዕድገት ምዕራፍ በሆነው አዲስ ዘመን፡

🏆 ስኬትና ጥበብ  በጥረታችሁ ሁሉ ጥልቅ አስተዋይነትና የተዋጣለት ስኬት ይንገሥ፤ የዘራችሁት የመልካምነትና የዕውቀት ዘር ፍሬ አፍርቶ ለታላቅ ፍሬ ያብቃችሁ።
💪 ጽናትና በረከት  የሚያጋጥሙ ተደራራቢ እንቅፋቶችን በጽናትና በጥበብ የመሻገር፣ ህልሞቻችሁን ወደ ተጨባጭ እውነታ የመለወጥ ሚስጥርና ኃይል ከእናንተ ጋር ይሁን።
🕊️ ሰላምና አንድነት በቤታችሁ አፈረ-በረከት፣ በልባችሁ ደግሞ የማይናወጥ የውስጥ ሰላም፣ ፍቅርና የስምምነት መንፈስ ይንገሥ።

አዲሱ ዘመን የነጠረ አስተሰብ፣ የላቀ የዕድገት እርምጃና ድል የተጎናጸፉበት የተባረከ ዘመን ይሁንላችሁ! 🌟
መልካም አዲስ ዓመት! 🎉
🔥1
Channel photo updated
The Pursuit of Happyness 🎬
ላይ ብዙ የምወደው ትዕይንቶች ቢኖሩም አባት እና ልጅ በመንገድ እየሄዱ ህፃን ክርስቶፈር ጋርድነር ለአባቱ ክሪስ ጋርድነር አንድ ታሪክ የነገረበት ፓርት እንዴት እንደምወደው🥰። ብቻ ህፃኑ ለአባቱ እንዲህ ይለዋል፦

አንድ ቀን የሆነ ሰውዬ ውሃ ውስጥ ሰምጦ ነበር🪱። ታድያ ሰውዬውን ሰምጦ የተመለከተ አንድ ትልቅ ታንኳም መጣና እንዲህ አለው፦«እርዳታ ትፈልጋለህ?» 🛳

ሰውዬውም፦«አይ አመሰግናለሁ እግዚአብሔር ያድነኛል» ብሎ መለሰት🙏።

ትንሽ ቆይቶም ሌላ ታንኳም መጣ እንዲህ አለው፦«ወንድም እርዳታ ትፈልጋለህ?» ⛴

ሰውዬውም በድጋሚ፦«አይ አመሰግናለሁ እግዝአብሔር ያድነኛል» ብሎ መለሰ🙏።

ከዛ ይህ ሰውዬ ሰምጦ ወደ ገነት ሄደ🌳። ሲድርስም በታላቅ ቁጣ እንዲህ አለ፦ «እግዚአብሔር ሆይ ለምን አላደንከኝም?»😡

እግዚአብሔርም፦«ሁለት ትላልቅ ታንኳዎች ላኩልህ እኮ አንተ ግብዝ ሰነፍ!»☹
          @thoughts_painting
🥰1