#Education
In Amhara Regional State, insecurity across the Gojjam, Gondar and Wollo zones has left an estimated 4.1 million to 4.4 million children out of school, according to regional officials and United Nations monitors. In Tigray Regional State, between 1.2 million and 1.4 million remain outside active classrooms. More than 85pc of school buildings were damaged, looted or destroyed during the civil war.
@Addis Fortune

❤4🤮1
የኖቤል ሽልማት በምጣኔ ሀብት ዘርፍ
በይፋ የስዊደን ሪልስ ባንክ የኢኮኖሚክስ ሳይንስ ሽልማት የአልፍሬድ ኖቤል መታሰቢያ በመባል የሚታወቀው ይህ ሽልማት፣ በ1895 በአልፍሬድ ኖቤል የመጀመሪያ ኑዛዜ የተመሰረተ ሳይሆን በ1968 እ.ኤ.አ. በስዊደን ማዕከላዊ ባንክ አዘጋጅነት የተቋቋመና ለመጀመሪያ ጊዜ በ1969 እ.ኤ.አ. የተሰጠ ነው። በሮያል የስዊደን ሳይንስ አካዳሚ የሚመራው ይህ ሽልማት እንደ ማክሮ ኢኮኖሚክስ፣ የስራ ገበያ ጥናቶች፣ እና የባህሪ ኢኮኖሚክስ ባሉ ዘርፎች የጎላ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ተመራማሪዎች የሚሰጥ ሲሆን አሸናፊዎቹም የወርቅ ሜዳሊያ፣ የምስክር ወረቀት እና የገንዘብ ሽልማት ይረከባሉ።
ባለፉት 6 አመታት ደግሞ በኢኮኖሚክስ ዘርፍ የኖቤል ሽልማት (The Sveriges Riksbank Prize in Economic Sciences in Memory of Alfred Nobel) ያሸነፉ ተመራማሪዎች ቅደም ተከተል እና ያበረከቱት አስተዋጽኦ የሚከተሉት ናቸው።
2025፦ ጆኤል ሞኪር፣ ፊሊፕ አጊዮን እና ፒተር ሃዊት
ቀጣይነት ያለው የኢኖቬሽን (የፈጠራ) ኢኮኖሚ እድገት እና ለፈጠራዊ ውድመት (creative destruction) ታሪካዊና መዋቅራዊ ቅድመ-ሁኔታዎችን በመለየታቸው የተሸለሙ ናቸው።
2024፦ ዳሮን አሴሞግሉ፣ ሲሞን ጆንሰን እና ጄምስ ኤ. ሮቢንሰን
ማህበራዊ ተቋማት እንዴት እንደሚመሰረቱ እና በረጅም ጊዜ ሀገራዊ የኢኮኖሚ ብልጽግና እና የሀብት ልዩነት ላይ የሚያሳድሩትን ተፅዕኖ ባደረጉት ምርምር የተሸለሙ ናቸው።
2023፦ ክላውዲያ ጎልዲን
በስራ ገበያ ውስጥ የሴቶችን ተሳትፎ፣ የደመወዝ ልዩነትን እና ታሪካዊ የስራ ሃይል እንቅስቃሴዎችን ግንዛቤ በማሳደጋቸው የተሸለሙ ናቸው።
2022፦ ቤን ኤስ. በርናንኬ፣ ዳግላስ ደብሊው. ዳይመንድ እና ፊሊፕ ኤች. ዲብቪግ
የንግድ ባንኮች በኢኮኖሚ ውስጥ ስላላቸው ሚና እና የፋይናንስ ቀውስን ስለመቆጣጠር ባደረጉት መሰረታዊ ምርምር የተሸለሙ ናቸው።
2021: ዴቪድ ካርድ፣ ጆሹዋ ዲ. አንግሪስት እና ጊዶ ደብሊው. ኢምቤንስ
በሌበር ኢኮኖሚክስ (labor economics) ላይ ላበረከቱት ተግባራዊ አስተዋጾ እና በተፈጥሯዊ ሙከራዎች (natural experiments) የምክንያትና ውጤት ግንኙነቶችን ለማወቅ አዳዲስ ዘዴዎችን በመቀየሳቸው የተሸለሙ ናቸው።
2020፦ ፖል አር. ሚልግሮም እና ሮበርት ቢ. ዊልሰን
የጨረታ ቲዎሪን (auction theory) በማሻሻላቸው እና ውስብስብ ለሆኑ ዕቃዎችና አገልግሎቶች አዳዲስ የጨረታ ቅርጾቶችን በመፍጠራቸው የተሸለሙ ናቸው።
ከነዚህ ውስጥ ማንበብ የምትፈልጉትን ምርምር ጻፉልኝ፥እልክላችኋለሁ።

🥰2👏1
ዋና ዋና ዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ መረጃዎች
1. የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ (Oil Prices Surge)
በዩናይትድ ስቴትስ እና በኢራን መካከል ባለው አለመግባባት ምክንያት የብሬንት ነዳጅ ዋጋ በበርሜል ከ95–96 ዶላር ደርሷል። ይህም በአቅርቦት እጥረት (Supply Shock) ምክንያት የሚከሰት የዋጋ ንረትን (Cost-Push Inflation) እና የዓለም አቀፍ ምርት ማስተላለፊያ መስመሮች (Supply Chains) መታጎልን ያሳያል።
2. የዓለም አቀፍ የምግብ ዋጋ ጭማሪ (Global Food Prices)
የተባበሩት መንግሥታት የዕርሻና የምግብ ድርጅት (FAO) የምግብ ዋጋ አመልካች በኦገስት ወር 133.3 ደርሷል፤ ይህ አሀዝ ከ2022 ወዲህ ከፍተኛው ነው። ይህም በከባድ አየር ንብረት እና በጂኦፖለቲካዊ ግጭቶች ምክንያት የሚከሰት የምግብ ዋጋ ንረትን (Food Inflation) እና የምግብ ዋስትና (Food Security) ስጋትን ያመላክታል።
3. የህንድ ሩፒ መጠናከር (Indian Rupee Performance)
የህንድ ሩፒ ከውጭ ሀገር በሚገቡ የገንዘብ ፍሰቶች እና በህንድ ማዕከላዊ ባንክ ጣልቃ ገብነት ምክንያት በሳምንቱ የ0.9% እድገት አሳይቷል። ይህም በማዕከላዊ ባንክ የምንዛሬ ተመን ጣልቃ-ገብነት (Exchange-Rate Intervention) በውጭ ምንዛሬ ክምችት (Forex Reserves) እና የገቢ ምርቶች ዋጋ ንረት መካከል ያለውን ቁርኝት ያሳያል።
4. የባይትዳንስ (ByteDance) የብድር ስምምነት
የቲክቶክ እና የባይትዳንስ ኩባንያ ለሁለገብ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) ማስፋፊያ የሚሆን የ29.6 ቢሊዮን ዶላር ብድር አግንተዋል። ይህም በትላልቅ የቴክኖሎጂ ኢንቨስትመንቶች ውስጥ የካፒታል ወጪ (Capital Expenditure) እና የድርጅቶች ብድር (Corporate Borrowing) የሚጫወቱትን ሚና ያሳያል።
5. የአሜሪካ የሥራ ዕድል ፈጠራ (U.S. Job Growth)
በኦገስት ወር 245,000 አዳዲስ የሥራ ዕድሎች የተፈጠሩ ሲሆን፣ የሥራ አጥነት ምጣኔው በ4.1% ጸንቶ ቀጥሏል። ይህም የማክሮ ኢኮኖሚውን የሥራ ገበያ ጥንካሬ፣ የሥራ አጥነት ምጣኔን (Unemployment Rate) እና የማዕከላዊ ባንክ የገንዘብ ፖሊሲ (Monetary Policy) ውሳኔዎችን ለመረዳት ይጠቅማል።

❤2🥰1
#ድህነት
እንደ አለም ባንክ እና ተመድ የቅርብ ጊዜ መረጃዎች በአሁኑ ወቅት በመላው አለማችን ከ680 እስከ 700 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች (የአለማችንን ህዝብ 8.5% ያህል) በቀን ከ 2.15 ዶላር በታች በሚያገኙበት የከፋ ድህነት ውስጥ ይኖራሉ።
በከፋ ድህነት ከሚኖሩት አጠቃላይ የአለም ህዝቦች መካከል ከሁለት ሶስተኛ በላይ የሚሆኑት (ከ67% በላይ) የሚኖሩት ደግሞ በአፍሪካ (በተለይም ከሰሃራ በታች ባሉ ሀገራት) ውስጥ ነው። ይህም ማለት ቁጥሩን በትክክል ስናስበው ከአለም አቀፉ 680 ሚሊዮን ውስጥ በግምት ከ460 ሚሊዮን በላይ የሚሆነው ህዝብ የሚገኘው እዚሁ አህጉራችን አፍሪካ ውስጥ ነው።
የገቢ ድህነት መስመሩን ከፍ አድርገን በቀን ከ3.65 እና ከ6.85 ዶላር በታች የሚኖሩትን ብንቆጥር ደግሞ የአለም ቁጥር ወደ 1.8 ቢሊዮን እና 3.5 ቢሊዮን ከፍ ይላል። ከእነዚህም ውስጥ በርካታ አፍሪካውያን የዚሁ ከባድ ፈተና አካል ናቸው።
ይህ የሆነው ደግሞ በሙስናና መልካም አስተዳደር ችግሮች እንድሁም በእርስ በርስ ጦርነቶች ምክኒያት ነው።
#Economics #Poverty #Africa #DevelopmentEconomics

❤2🥰1😢1
ኢትዮጵያ በ100 ቢሊዮን ብር ካፒታል የመጀመሪያውን የቤት ብድር መልሶ ፈንድ ሰጪ ኩባንያ ልታቋቁም ነው ተብሏል።
ሀገሪቱ የመጀመሪያውን የቤት ብድር መልሶ ፈንድ ሰጪ ኩባንያ ለማቋቋም በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እና በዓለም አቀፍ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን (IFC) መካከል የትብብር ስምምነት ተፈራርማለች።
ተቋሙ በ100 ቢሊዮን ብር ካፒታል የሚቋቋም ሲሆን IFC ቢያንስ 200 ሚሊዮን ዶላር ያመጣሉ ተብሎ ይጠበቃል። ተቋሙ ባንኮች የረጅም ጊዜ የቤት ብድር እንዳይሰጡ አግዶ የነበረውን የገንዘብ እጥረትና የጊዜ አለመጣጣም ችግር ይፈታልም ተብሏል።
ኩባንያው ከተለመዱት አበዳሪ ባንኮች በተለየ መልኩ ባንኮች ቀደም ብለው የሰጧቸውን የቤት ብድሮች በመግዛት ለንግድ ባንኮች የረጅም ጊዜ ገንዘብ ያቀርባል። ይህም የቤት ብድር ተደራሽነትን የሚያሰፋ ሲሆን፣ 1.5 ሚሊዮን አነስተኛ ዋጋ ያላቸው ቤቶችን ለመገንባት የተያዘውን የመንግሥት ዕቅድ እንደሚያግዝም ተገልጿል።
@EBR

👍1🥰1
📢 ኢትዮ ቴሌኮም ለአዲስ ባለአክሲዮኖቹ የትርፍ ክፍፍል (dividend) ሊከፍል ነው!
ከሁለት ዓመት በፊት የኢትዮ ቴሌኮምን አክሲዮን የገዙ 47,377 ባለአክሲዮኖች ለመጀመሪያ ጊዜ የትርፍ ክፍፍል (ዲቪደንድ) ሊያገኙ መሆኑ ተሰምቷል።
መንግስታዊው የቴሌኮም ተቋም አዲሶቹን ባለአክሲዮኖቹን ባለፈው የበጀት ዓመት ለተገኘው ትርፍ ተጋሪ እንደሚያደርጋቸው አስታውቋል። ክፍፍሉ በጥሬ ገንዘብ ይሁን ወይም ተጨማሪ አክሲዮን በመስጠት የሚለው ደግሞ የሚወሰነው በኩባንያው ጠቅላላ ጉባኤ ይሆናል ተብሏል።
ኢትዮ ቴሌኮም ባለፈው የበጀት ዓመት የ33.2 በመቶ እድገት በማሳየት 215.82 ቢሊዮን ብር ገቢ ያገኘ ሲሆን፣ 92.9 ቢሊዮን ብር ያህል ደግሞ ጠቅላላ ትርፍ ማስመዝገቡ ይታወቃል። የሶስት ዓመት ዕቅዱ ደግሞ በጠቅላላው 111.3 ቢሊዮን ብር የትርፍ ክፍፍል ለማከናወን ያለመ ነውም ተብሏል።
@Addis Fortune
#Ethiotelecom #Dividend #Ethiopia #businessnews

Freakonomics - በSteven D. Levitt እና Stephen J. Dubner የተጻፈ የኢኮኖሚክስ መጽሃፍ!
መጽሃፉ ስለምን ያወራል?
ተራ የሚመስሉ ጉዳዮችን ከኢኮኖሚክስ እና ከData አንፃር የሚመረምር ሲሆን ዋናው ሀሳቡ ደግሞ ከነገሮች ጀርባ ያለው እውነተኛ incentive ምንድነው? የሚለውን መጠየቅ ነው።
ለምሳሌ፦
👉 ሰዎች ለምን ማጭበርበር ይፈጽማሉ?
👉 መምህራን እና የSumo ተወዳዳሪዎች ምን ያመሳስላቸዋል?
👉 የልጆች ስም በሕይወታቸው ላይ ተፅዕኖ ያሳድራል?
👉 የሰዎች ውሳኔ ከmoney, incentives and information ጋር እንዴት ይገናኛል? የሚሉትን መጥቀስ ይቻላል።
የመጽሐፉ ትልቁ ትምህርት የኢኮኖሚክስ አስተሳሰብ ማለት ገንዘብን ብቻ ማጥናት አይደለም፤ ሰዎች ለምን እንደሚወስኑ መረዳት ጭምር እንጅ የሚል ነው።
ከFreakonomics ልንጠቀምባቸው የሚችሉ 10 አስደናቂ ሀሳቦች
1️⃣ Incentives ሰዎችን ይመራሉ። ሰዎች ውሳኔ ሲወስኑ የሚያገኙት ጥቅም ወይም የሚያጡት ነገር በጣም ትልቅ ሚና አለው።
2️⃣ የተሳሳተ Incentive የተሳሳተ ውጤት ሊያመጣ ይችላል። ሰዎችን ለመልካም ውጤት ለማበረታታት የተዘጋጀ ሽልማት እንኳን በስርዓት ካልተነደፈ ተቃራኒ ውጤት ሊያመጣ ይችላል።
3️⃣ Information ኃይል ነው።
የበለጠ መረጃ ያለው ብዙ ጊዜ የተሻለ ውሳኔ መወሰን ይችላል።
4️⃣ ቁጥሮች ከንድፈ ሃሳብ የበለጠ ሊናገሩ ይችላሉ። አንድ ነገር “እንዲህ ነው” ከማለት ይልቅ dataን መመልከት ከጀርባው ያለውን እውነታ ሊያሳይ ይችላል።
5️⃣ Correlation ≠ Causation
ሁለት ነገሮች አብረው ቢከሰቱ አንዱ ሌላውን አስከትሏል ማለት አይደለም።
6️⃣ ሰዎች ሁልጊዜ Rational አይደሉም።
ይህም ማለት ውሳኔዎቻቸውን በገንዘብ ብቻ ሳይሆን በልማድ፣ በስሜት እና በማህበራዊ ጫናም ይመሰርታሉ።
7️⃣ የተለመደው ምክንያት ሁልጊዜ ትክክለኛው ምክንያት አይደለም።
Economics አንድን ጉዳይ በ“common sense” ብቻ ሳይሆን በevidence እንድንመረምር ያስተምራል።
8️⃣ የሰዎች ባህሪ በIncentives ሊቀየር ይችላል።
ትንሽ የሽልማት ወይም የቅጣት ለውጥ እንኳን የሰዎችን behavior ሊቀይር ይችላል።
9️⃣ “Why?” ብሎ መጠየቅ የEconomist አስተሳሰብ ነው።
ከላይ የሚታየውን ውጤት ብቻ ሳይሆን፣ ከጀርባው ያለው ምክንያት ምንድነው? ብሎ መጠየቅ ዋናው ነገር ነው።
🔟 Economics በዕለት ተዕለት ሕይወት ውስጥ አለ።
የምንገዛው ነገር፣ የምንሠራው ሥራ፣ የምንወስነው ውሳኔ—ሁሉም ከscarcity, incentives, opportunity cost እና choice ጋር ይያያዛል።
💭 Freakonomics የሚያስተምረው ትልቁ ነገር ከተለመደው መልስ በፊት የተደበቀውን ምክንያት ፈልግ የሚለውን ነው።
#EconZone #EconomicsBeyondtheClassroom
#financialitracy #bookreview #besteconomicsbooks
መጽሀፉን የምትፈልጉ 👇👇👇

❤3
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መደበኛ የዉጪ ምንዛሬ ጨረታ በነገዉ ዕለት ያካሄዳል።
ባንኩ 28ተኛ ዙር የዉጪ ምንዛሬ ጨረታዉን ነገ ረቡዕ ሊያደረግ መሆኑን አስታውቋል። በዕለቱ ለሚደረገው መደበኛ ጨረታም 125 ሚሊዮን ዶላር ማቅረቡን ገልጿል።
#NBE #FXauction

❤3👍1
ኢንቨስትመንትት_ማበረታቻን_ለማስፈጸም_የወጣ_መመሪያ_3.pdf
546.3 KB
የኢንቨስትመንት ማበረታቻን ለማስፈጸም የወጣውን መመሪያ ቁጥር 1064/2017 ማንበብ ለምትፈልጉ!
📘 ሜታ ኢኮኖሚክስ (Metaeconomics)
የኢኮኖሚክስ ንድፈ ሐሳቦች፣ ግምቶች፣ ዘዴዎችና ገደቦች ላይ የሚያተኩር የኢኮኖሚክስ የጥናት ዘርፍ ነው።
ይህም ዘርፍ፦
👉 የኢኮኖሚክስ ግምቶችን ይመረምራል።
👉 ኢኮኖሚስቶች ንድፈ ሐሳብና ሞዴሎችን እንዴት እንደሚገነቡ ይመለከታል።
👉 የኢኮኖሚክስ ሞዴሎችን ጥንካሬና ገደብ ይመረምራል።
👉 እንደ ምክንያታዊ ባህሪ (Rationality)፣ እርካታ (Utility) እና የኢኮኖሚ ደህንነት (Welfare) ያሉ መሠረታዊ ጽንሰ-ሐሳቦችን ይመረምራል።
👉 Metaeconomics = ስለ ኢኮኖሚክስ እውቀትና አሰራር የሚያጠና ኢኮኖሚክስ ነው።
በተጨማሪም ሜታ ኢኮኖሚክስ እንደ ሌሎች የፍልስፍናና የሳይንስ ዘርፎች (ለአብነት ያህል Meta-physics ወይም Meta-philosophy እንደሚባሉት) ከኢኮኖሚክስ በስተጀርባ ያለውን ዕውቀትና የጥናት መንገድ (Economics of Economics) መርምሮ የሚያጠና ዘርፍ ነው።

ካፒታሊዝም እና ነፃነት (Capitalism and Freedom)
በሚልተን ፍሪድማን (Milton Friedman) በ1962 የተጻፈና ስለኢኮኖሚ፣ ፖለቲካል ኢኮኖሚክስ እና ነፃ ገበያ የሚያወራ መጽሀፍ ነው።
1. የመጽሐፉ ዋና ሐሳብ
ካፒታሊዝም እና ነፃነት የተሰኘው ይህ መጽሐፍ የኢኮኖሚ ነፃነት ለፖለቲካዊ ነፃነት መሠረት እንደሆነ ያብራራል። የመጽሐፉ ደራሲ ሚልተን ፍሪድማን ነፃ ገበያ እና የግል ኢኮኖሚያዊ ውሳኔዎች የግለሰቦችን ነፃነት ለመጠበቅ ወሳኝ ሚና እንዳላቸው ይከራከራል።
2. ዋና ዋና የመጽሐፉ ሐሳቦች
👉 የኢኮኖሚ ነፃነት፦ ግለሰቦች በራሳቸው ፍላጎት መሠረት የኢኮኖሚ ውሳኔዎችን የማድረግ መብት ሊኖራቸው ይገባል።
👉 ነፃ ገበያ፦ የገበያ ውድድር የኢኮኖሚ ቅልጥፍናን፣ ፈጠራን እና የሸማቾችን ምርጫ ሊያበረታታ ይችላል።
👉 የመንግሥት ሚና፦ መንግሥት በኢኮኖሚ ውስጥ የሚኖረው ተሳትፎ ውስን መሆን እንዳለበት ይሞግታል።
👉 የግል ምርጫ፦ ሰዎች በትምህርት፣ በሥራ እና በንግድ ዘርፎች የራሳቸውን ምርጫ የማድረግ ነፃነት ሊኖራቸው ይገባል።
3. በመጽሐፉ የተነሱ የፖሊሲ ሐሳቦች
ፍሪድማን በመጽሐፉ ውስጥ የገንዘብ ፖሊሲ፣ የትምህርት ሥርዓት፣ የሙያ ፈቃድ አሰጣጥ፣ የውጭ ንግድ ገደቦች እና የማኅበራዊ ድጋፍ ፕሮግራሞችን ይዳስሳል። በተለይም በትምህርት ዘርፍ የቫውቸር ሥርዓትን (School Vouchers) እና በገበያ ውድድር ላይ የተመሠረቱ መፍትሔዎችን ይደግፋል።
4. የመጽሐፉ ታሪካዊ አስተዋጽኦ
መጽሐፉ በ1962 በቀዝቃዛው ጦርነት ዘመን የታተመ በመሆኑ በዘመናዊ ኢኮኖሚክስ እና በነፃ ገበያ አስተሳሰብ ላይ ትልቅ ተጽዕኖ አሳድሯል። መጽሐፉ በመንግሥት ቁጥጥር እና በነፃ ገበያ መካከል ባለው የኢኮኖሚ ፖሊሲ ክርክር ውስጥ አሁንም ዋና ማጣቀሻ ሆኖ ቀጥሏል።
5. መጽሃፉ ላይ የሚነሱ ትችቶችና ክርክሮች
የመጽሐፉ ደጋፊዎች የግለሰብ ነፃነትን፣ የገበያ ውድድርን እና የግል ምርጫን ማበረታታቱን ያወድሳሉ። ተቺዎች ደግሞ በበኩላቸው መጽሐፉ የገበያ ውድቀትን፣ የሀብት አለመመጣጠንን እና የመንግሥት ደንቦችና ማኅበራዊ ድጋፎች ያላቸውን ጠቀሜታ በቂ ትኩረት እንዳልሰጠ ይከራከራሉ።
በአጠቃላይ ይህ መጽሐፍ በኢኮኖሚ ነፃነት፣ በነፃ ገበያ እና በመንግሥት የኢኮኖሚ ተሳትፎ ላይ ያሉ የተለያዩ አስተሳሰቦችን ለመረዳት የሚረዳ ተጽዕኖ ፈጣሪ የኢኮኖሚክስ መጽሐፍ ነው።
መጸሃፉን ማንበብ የምትፈልጉ👇👇👇

የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም (UNDP) ከኦክስፎርድ የድህነትና የሰው ሀብት ልማት ተቋም (OPHI) ጋር በመተባበር ያወጣውን የ2026 የዓለም አቀፍ ሁሉን አቀፍ የድህነት መለኪያ (Global MPI) ሪፖርት በዋና ዋና ነጥቦቹ ከፋፍለን ስናየው የሚከተለውን ይመስላል።
1. ዋና ዋና ቁጥሮችና እውነታዎች
በድህነት ውስጥ የሚገኘው ሕዝብ ብዛት፦ በ108 በማደግ ላይ ባሉ ሀገራት ውስጥ ከሚኖረው 6.3 ቢሊዮን ሕዝብ መካከል 1.2 ቢሊዮን ያህሉ (18.9%) በከባድ ሁሉን አቀፍ ድህነት ውስጥ ይኖራሉ።
ያልተጠበቀው ጭማሪ፦ ከ2010 ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ በድህነት ውስጥ የሚገኘው ሕዝብ ቁጥር በ51.5 ሚሊዮን ጨምሯል። ይህም ከዚህ ቀደም የነበረውን የመቀነስ አዝማሚያ ወደኋላ የመለሰ አሳሳቢ ክስተት ነው።
2. ክፍፍሉ በጂኦግራፊና በገቢ ደረጃ
ከሰሃራ በታች ያለችው አፍሪካ፦
የዓለም አቀፉን የድህነት ጫና በዋናነት የሚሸከመው ይሄው ቀጠና ነው። 616 ሚሊዮን ድሆች በዚህ ክልል ውስጥ ይኖራሉ፤ ይህም በዓለም ላይ ካለው አጠቃላይ ድሃ ሕዝብ ከግማሽ በላይ (ከ50% በላይ) ማለት ነው።
በቀጠናው ያለው የድህነት ምጣኔ 51.4% ይደርሳል።
ከፍተኛ የድህነት ስርጭት ካለባቸው የዓለም አምስት ደሃ ሀገራት መካከል ቻድ፣ የመካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ፣ ኒጀር፣ ቡሩንዲ እና ኢትዮጵያ ይገኙበታል።
ደቡብ እስያ፦ በ393 ሚሊዮን ድሆች ሁለተኛውን ደረጃ ትይዛለች።
መካከለኛ ገቢ ያላቸው ሀገራት፦ የሚገርመው አብዛኞቹ ድሆች (65.1% ወይም 779 ሚሊዮን) የሚኖሩት ደሃ በሚባሉ ሀገራት ሳይሆን በመካከለኛ ገቢ ደረጃ ላይ ባሉ ሀገራት ውስጥ ነው።
3. ድህነቱ በምን በምን ይገለጻል?
የMPI መለኪያ ድህነትን በገቢ ብቻ ሳይሆን በጤና፣ በትምህርት እና በኑሮ ደረጃዎች እጥረት ይለካል።
የማብሰያ ኃይል (Cooking Fuel)፦ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከ1 ቢሊዮን በላይ ድሆች ንጹህ የማብሰያ ኤሌክትሪክ/ጋዝ አያገኙም። ከእነዚህ ውስጥ 600 ሚሊዮኑ የሚኖሩት ከሰሃራ በታች ባለው አፍሪካ ነው።
ኤሌክትሪክና ንጹህ ውሃ፦ በዓለም ደረጃ ኤሌክትሪክ ከማያገኙት ድሆች መካከል 81.2% እና ንጹህ የመጠጥ ውሃ ከማያገኙት 70.7% የሚኖሩት ከሰሃራ በታች ባለው አፍሪካ ውስጥ ነው።
የሕፃናት ሞት፦ ከሕፃናት ሞት ጋር የተያያዘ ድህነት ከገጠማቸው ሰዎች መካከል 56.1% የሚገኙት በተመሳሳይ ከሰሃራ በታች ባለው አፍሪካ ነው።
4. ተስፋ ሰጪ ጎኖች
አጠቃላይ የዓለም ድሆች ቁጥር ቢጨምርም ባለፉት 15 ዓመታት ውስጥ 33 ሀገራት የድህነት መጠናቸውን በግማሽ (50%) መቀነስ ችለዋል።
ይህም የሚያሳየው ትክክለኛና ዘላቂ የፖሊሲ እርምጃ ከተወሰደ ድህነትን መቀነስ ፈጽሞ የማይቻል ነገር አለመሆኑን ነው።

❤1
በኪስ ያለ 100 ብር ወይስ በባንክ አካውንት ያለ 100 ብር? የትኛው ይበልጣል?
በአንድ ቀላል ጥያቄ እንጀምር።
በኪስህ 100 ብር አለህ፤ በባንክ አካውንትህም 100 ብር አለህ። ከሁለቱ የትኛው ይበልጣል?
በመጀመሪያ ስናየው ሁለቱም 100 ብር ስለሆኑ እኩል ናቸው ብለን እንመልሳለን። ነገር ግን ጥያቄውን ከኢኮኖሚክስ አንጻር ስንመለከተው የገንዘብን መጠን ብቻ ሳይሆን የሚያስገኘውን ጥቅም፣ የመጠቀም ችሎታ፣ የግብይት ወጪና የወለድ ገቢ ጭምር ማየት አለብን።
1. የግብይት ወጪ (Transaction Cost)
Transaction Cost ማለት አንድን ግብይት ለመፈጸም ከሚከፈለው ዋጋ በተጨማሪ የሚወጣ ወጪ ወይም የሚባክን ጊዜና ጥረት ነው።
ለምሳሌ በመንገድ ላይ ስትሄድ ውሃ ለመግዛት ፈለግህ እንበል። ውሃው 100 ብር ቢሆን፣ በኪስህ ያለውን 100 ብር አውጥተህ መክፈል ትችላለህ። ነገር ግን ገንዘቡ ባንክ አካውንትህ ውስጥ ብቻ ካለ፣ ክፍያውን ለመፈጸም ኤቲኤም መፈለግ፣ ወደ ባንክ መሄድ ወይም ሌላ የክፍያ ዘዴ መጠቀም ሊያስፈልግህ ይችላል።
እነዚህ ተጨማሪ ጊዜና ጥረቶች የግብይት ወጪዎች ናቸው። ወደ ኤቲኤም ለመሄድ የትራንስፖርት ወጪ ካወጣህም ይህ የግብይት ወጪህን ይጨምራል። በድጅታል መንገዶች የሚደረግ የገንዘብ ዝውውርም የራሱ የሆነ ወጭ ይኖረዋል። ለምሳሌ ባንክ አካውንትህ ላይ ያለውን 100 ብር ለማስተላለፍ 2 ብር ብትከፍል በተዘዋዋሪ ያለህ ገንዘብ 98 ብር ነው ማለት ነው።
ስለዚህ ገንዘቡ በኪስህ ሲኖር አንዳንድ ግብይቶችን በቀላሉ ትፈጽማለህ። ይህም የግብይት ወጪህን ሊቀንስ ይችላል።
2. የፈሳሽነት ጥቅም (Liquidity)
ፈሳሽነት ማለት ገንዘብን ወዲያውኑ ለክፍያ የመጠቀም ችሎታ ነው።
በኪስህ ያለው 100 ብር በቀጥታ ለክፍያ ሊውል ይችላል። በባንክ አካውንትህ ያለውም 100 ብር በካርድ፣ በሞባይል ባንኪንግ ወይም በሌሎች የክፍያ ዘዴዎች ሊውል ይችላል።
ሆኖም የክፍያ መሠረተ ልማቱ በሌለበት ቦታ በኪስ ያለው ገንዘብ የበለጠ ጠቀሜታ ይኖረዋል።
3. የጊዜ ዋጋ (Time Value of Money)
የጊዜ ዋጋ መርህ የዛሬ ገንዘብ ከወደፊት የሚገኝ ተመሳሳይ መጠን ካለው ገንዘብ የበለጠ ዋጋ ሊኖረው እንደሚችል ያብራራል።
ለምሳሌ ዛሬ 100 ብር ቢኖርህና ነገ 100 ብር እንደምታገኝ ቃል ቢገባልህ፣ ዛሬ ያለውን ገንዘብ ወዲያውኑ መጠቀም ወይም በሚያስገኝልህ መንገድ ማዋል ትችላለህ።
ነገር ግን በጥያቄያችን ውስጥ ሁለቱም 100 ብሮች በአሁኑ ጊዜ ካሉ የጊዜ ዋጋ መርህ ብቻውን አንዱን ከሌላው አያስበልጥም።
4. የኦፖርቹኒቲ ኮስት (Opportunity Cost)
የምርጫ ዋጋ(opportunity cost) ማለት አንድን ምርጫ ስንወስድ በመተው የምናጣው የቀጣዩ ምርጥ አማራጭ ጥቅም ነው።
በኪስህ 100 ብር ስታስቀምጥ ገንዘቡን በቀጥታ ለመጠቀም ትችላለህ፤ ነገር ግን ወለድ አታገኝበትም። ገንዘቡን ወለድ በሚከፍል የባንክ አካውንት ውስጥ ካስቀመጥክ ደግሞ ተጨማሪ ገቢ ልታገኝበት ትችላለህ።
ስለዚህ የባንክ አካውንቱ ወለድ የሚከፍል ከሆነ፣ የምታገኘው ወለድ በኪስህ በማስቀመጥ የምታጣው ጥቅም ነው።
5. የኬይንስ የፈሳሽነት ምርጫ ቲዎሪ (Keynes's Liquidity Preference Theory)
በታዋቂው ኢኮኖሚስት ጆን ሜይናርድ ኬይንስ የተብራራው የፈሳሽነት ምርጫ ቲዎሪ፣ ሰዎች ገንዘባቸውን በፈሳሽ መልኩ ለመያዝ የሚፈልጉበትን ምክንያት ያብራራል።
ሰዎች ገንዘብን በዋናነት ለሦስት ምክንያቶች ይይዛሉ።
የግብይት ዓላማ (Transaction Motive)፦ ለዕለታዊ ግዢዎችና ክፍያዎች።
የጥንቃቄ ዓላማ (Precautionary Motive)፦ ላልታሰቡ ወጪዎችና አደጋዎች።
የግምት ዓላማ (Speculative Motive)፦ በወለድ ምጣኔና በሌሎች የፋይናንስ ሀብቶች ዋጋ ላይ በሚጠበቁ ለውጦች ምክንያት ገንዘብን በፈሳሽ መልኩ ለመያዝ።
ለምሳሌ ሰው በኪሱ ገንዘብ የሚይዘው ለቀኑ ወጪዎች ወዲያውኑ ለመጠቀም ሲሆን፣ በባንክ ያለውን ቁጠባ ደግሞ ለወደፊት አጠቃቀም ሊያስቀምጥ ይችላል።
6. ታዲያ የትኛው ይበልጣል?
ወደ መነሻ ጥያቄያችን እንመለስ።
በኪስህ ያለው 100 ብርና በባንክ አካውንትህ ያለው 100 ብር በቁጥር እኩል ናቸው። ሆኖም በኪስህ ያለው ገንዘብ ለአንዳንድ ግብይቶች የበለጠ ምቹ ሊሆን ይችላል፤ በባንክ ያለው ደግሞ ወለድ ሊያስገኝና በተሻለ ደህንነት ሊቀመጥ ይችላል።
ስለዚህ ከኢኮኖሚክስ አንጻር የትኛው ይበልጣል የሚለው በገንዘቡ መጠን ብቻ ሳይሆን በሚሰጠው ጥቅም፣ በግብይት ወጪ፣ በወለድ ገቢና በተጠቃሚው ፍላጎት ላይ ይወሰናል።
በኢኮኖሚክስ የገንዘብ ዋጋ ማለት በላዩ የተጻፈው ቁጥር ብቻ ሳይሆን በምን መንገድና በምን ወጪ ለፍላጎታችን ማዋል እንደምንችል ጭምር ነው።

❤7
በክሪፕቶ ኤክስቼንጅ ታሪክ ትልቁ የሳይበር ጥቃት - የባይናንስ (Binance) የ$6.3 ቢሊዮን ዶላር ዝርፊያ!
የክሪፕቶፕረንሲው ዓለም ባለፉት ጥቂት ቀናት ውስጥ አድስ አስደንጋጭ ክስተት አስተናግዷል። የዓለማችን ትልቁ የክሪፕቶ ኤክስቼንጅ የሆነው ባይናንስ በታሪኩ ገጥሞት የማያውቅ ከፍተኛ የሳይበር ጥቃት እንደተፈጸመበት ይፋ አድርጓል። በጥቃቱም እስከ 6.3 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት የዲጂታል ሀብት በሃከሮች እጅ ሊወድቅ ችሏል።
የብሎክቼይን ደህንነት ተመራማሪዎች እንደሚሉት ከሆነ ይህንን ጥቃት በስተጀርባ ሆነው የመሩት በሰሜን ኮሪያ መንግሥት የሚደገፉትና “TraderTraitor” በመባል የሚታወቁት የላቁ የሳይበር ሃከሮች ናቸው። ቡድኑ የባይናንስ የገንዘብ ማስተላለፊያ ሥርዓት (Hot Wallet) እና የሶፍትዌር ክፍተቶችን በመጠቀም በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ ከተለያዩ የብሎክቼይን ኔትወርኮች ላይ ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ ጠራርጎ መውሰድ ችሏል።
ሆኖም ጥቃቱ ከተፈጸመ በኋላ በኢንዱስትሪው ውስጥ ያሉ ዋና ዋና ተቋማት ፈጣንና የተቀናጀ ምላሽ ሰጥተዋል። በየኔትወርኮቻቸው ላይ የተደረጉ የገንዘብ እንቅስቃሴዎችን በመከታተል ከተዘረፈው ሀብት ውስጥ ወደ 3 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋውን ወዲያውኑ እንዳይንቀሳቀስ ማገድ ችለዋል።
የባይናንስ አመራሮች የደንበኞቻቸው ገንዘብ ሙሉ በሙሉ ደህንነቱ የተጠበቀ መሆኑን እና የደረሰውን ኪሳራ ኩባንያው “SAFU” ከተሰኘው የራሱ የአደጋ ጊዜ መጠባበቂያ ፈንድ ሙሉ በሙሉ እንደሚሸፍነው አረጋግጠዋል።
ከሁለት አመት በፊት ደግሞ ባይቢት የተሰኘው የክሪፕቶ መገበያያ "ላዛሪየስ" በተባሉ የሰሜን ኮሪያ ሀከሮች ጥቃት ደርሶበት እንደነበር ይታወሳል።