EBS-አዲስ ነገር
214 subscribers
189 photos
2 videos
1 file
350 links
ቻናላችን በየቀኑ አዳዲስ እና ተአማኒነት ያላቸውን መረጃዎች በቅንነት እናደርሳለን
Download Telegram
ምንም ዓይነት ድርድር አይኖረም- የፌደራል መንግሥት
****
ህወሃት ከአማራና ከአፋር ክልል ሙሉ ለሙሉ ካልወጣና እያካሄደ ያለውን ሁከት እና ጥቃት ሙሉ ለሙሉ ካላቆመ ከፌደራል መንግሥቱ ጋር ምንም ዓይነት ድርድር ሊካሄድ እንደማይችል ሁለት ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት ወቅታዊ ጉዳዮች በማስመልከት ዛሬ ለአሜሪካ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትርና ለውጭ መገናኛ ብዙኃን ባለሞያዎች በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።

የኢትዮጵያ ፍትህ ሚኒስቴር ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቲዮስና የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት ቃል አቀባይ ቢልለኔ ስዩም ወቅታዊ ጉዳዮች በማስመልከት ዛሬ ለአሜሪካ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትርና ለዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙኃን ባለሞያዎች በኢንተርኔት ላይ በተደረገ ውይይት በሰጡት መግለጫ፤ ህወሃት በአዲስ አበባና በሌሎች ከተሞች ጥቃት ለማድረስ እያሴረ መሆኑ ተጨባጭ የደህንነት መረጃ እንደደረሳቸው ገልፀዋል።
@ebs1News @ebs1News
‘ሲኤንኤን’ ኢትዮጵያን በተመለከተ ሃሰተኛ መረጃ ማውጣቱን እንደቀጠለ ነው
*****************************

‘ሲኤንኤን’ የተባለው የቴሌቪዥን ጣቢያ ኢትዮጵያን በተመለከተ ሃሰተኛ መረጃ እያወጣ እንደሆነ ተጋለጠ።

ጣቢያው ኢትዮጵያን በተመለከተ ተከታታይ ዘገባዎችን እየሰራ ቢገኝም፤ የሚሰራቸው ዘገባዎች በትክክለኛ መረጃ ላይ ያልተመሰረቱ፣ ሐሰተኛ፣ የተዛቡና ሚዛናዊነት የጎደላቸው እንደሆኑ ተጠቁሟል።

ሲኤንኤን በኢትዮጵያ ስላለው ግጭት በሰራው አንድ ዘገባ ላይ ሀሰተኛ ምስል መጠቀሙን የቴክኖሎጂ አማካሪና ስትራተጂስት የሆነው የቴክቶክ ዋና አዘጋጅ ሰሎሞን ካሳ በማህበራዊ ትስስር ገጹ አጋልጧል።

‘ምንም ነገር ተሸሽጎ ለዘላለም አይቆይም’ በሚለው መርሁ የሚታወቀው ኡጋንዳዊው የምርመራ ጋዜጠኛው ዳኒኤል ሉታያ በበኩሉ ወደ ኢትዮጵያ ከማቅናቱ በፊት የሲኤንኤን ዘገባዎችን ተመልክቶ እንደነበር ገልጾ፤ በዚህም ወደለየለት የጦር ቀጣና እየገባ እንደሆነ ተሰምቶት እንደነበር በትዊተር ገጹ አስነብቧል።

ነገር ግን ኢትዮጵያ ሲደርስ ያጋጠመው የሲኤንኤን ዘገባ ከፈጠረበት ተቃራኒ እንደሆነ ገልጿል። @ebs1News @ebs1News
" ፊታቸውን ካዞሩብን ወዳጆች እጥፍ የቁርጥ ቀን ወዳጆች አግኝተናል " - ዶ/ር ዐቢይ አህመድ
**********************
ዛሬ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው መልዕክ ያስተላለፉት የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ፥ " የመጨረሻው ከባዱ ምጥ ልጁ የሚወለድበት ነው። ይህ ፈታኝ ጊዜም ጀግኖች የሚወለዱበት ነው " ብለዋል።

"የኢትዮጵያ ልጆች ከጫፍ እስከጫፍ ተነሥተዋል" ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ "ፈተናዎቹ አጠንክረውናል። ፈታኞቻችን ሌሎች መንገዶችን አሳይተውናል " ሲሉ ገልፀዋል።

" ፊታቸውን ካዞሩብን ወዳጆች እጥፍ የቁርጥ ቀን ወዳጆች አግኝተናል " ያሉት ዶ/ር ዐቢይ " የቅጠሎች መሰብሰብ ዋርካ አያደርጋቸውም። የዋርካዎች መሰብሰብ ግን ደኑን የማይደፈር እያደረገው ነው። የሚከፈል መሥዋዕትነት አለ። ያ መሥዋዕትነት ግን ኢትዮጵያን ዋጅቶ በዐለት ላይ ይተክላታል " ብለዋል።@ebs1News @ebs1News
የመንግሥት ሹሙ በዋሺንግተን ጥምረት የፈጠረውን የፖለቲካ ቡድን ይህ ነው የሚባል የፖለቲካ መሠረት የሌለው ደካማ ስብስብ ነው ሲሉ አጣጣሉት
************************** ዘጠኝ የፖለቲካ ቡድኖች ‹የኢትዮጵያ ፌደራሊስት እና ኮንፌደራሊስት ኃይሎች ጥምረት› በሚል በሥልጣን ላይ ያለውን የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መንግሥት እንተካለን በሚል በአሜሪካ ዋሺንግተን ጥምረት መመስረታቸውን ትላንት ምሽት አስታውቀዋል።

ጥምረቱን አስመልክቶ ለቢቢሲ ኒውስ አወር የተናገሩት የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዲኤታ አቶ ከበደ ዴሲሳ፣ ጥምረቱ ይህ ነው የሚባል የፖለቲካ መሰረት የሌለው ደካማ ስብስብ ነው ሲል አጣጥለውታል።

በጥምረቱ ውስጥ ትብብር ለመፈጠር ከፈረሙት መካከል ሕወሓት፣ የኦሮሞ ነጻነት ጦር፣ የሲዳማ ብሔራዊ ነጻነት ግንባር፣ የአገው ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ይገኙበታል።

ይህ ጥምረት በኢትዮጵያ የሽግግር መንግሥት የመመሥረት ዓላማ እንዳለው የኦሮሞ ነጻነት ጦር የተባለው ቡድን ቃል አቀባይ ኦዳ ታርቢ እንደነገረው ቢቢሲ ዘግቧል፡፡ ነገር ግን በዚህ ጥምረት መመስረት አለመደነቃቸውን ያመለከቱት የመንግስት ሹሙ፣ ስብስቡን ‹‹ደካማ የፖለቲካ ኃይል ነው›› በማለት ገልጸውታል።

በሥነ ሥርዐቱ ላይ የጥምረቱን አላማ በተመለከተ የተናገሩት የሕወሓት ኃይሎችን በመወከል የተገኙት አምባሳደር ብርሃነ ገብረክርስቶስ፣ አላማቸው የኢትዮጵያ መንግሥትን በኃይል አልያም በድርድር በማስወገድ የሽግግር መንግሥት ለመመስረት እቅድ እንዳላቸው አስታውቀዋል።

ሚኒስትር ዲኤታው ግን ‹‹እነዚህ አማጺያን ቡድኖች መሠረት የላቸውም። ምንም አይነት ማኅበራዊ መሠረት የላቸውም፤ ምንም ለውጥ ሳያመጡ ላለፉት 40 ዓመታት እዚያው የቆዩ ናቸው›› ብለዋቸዋል፡፡ አቶ ከበደ ዴሲሳ ጨምረውም ‹‹በአገሪቱ ውስጥ የፖለቲካ መረጋጋት በሚያስፈልግበት ጊዜ የኢትዮጵያ ዳያስፖራዎች መንግሥት ተዳክሟል፣ ሥልጣን ላይ መቆየት አይችልም ብለው ሲያስቡ ተሰባስበው ትብብር ይፈጥራሉ›› በማለት ሁኔታው የተለመደ መሆኑንም ተናግረዋል።

ዘጠኝ የፖለቲካ ቡድኖች ‹የኢትዮጵያ ፌደራሊስት እና ኮንፌደራሊስት ኃይሎች› በሚል በአሜሪካ ዋሺንግተን የፈጠሩትን ጥምረት ሬውተርስን ጨምሮ ሌሎችም ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን የቀጥታ ሥርጭት ሽፋን ሰጥተውታል፡፡

አንድ ዓመት የዘለቀው በፌዴራል መንግስት እና በሕወሓት ኃይሎች መካከል የሚካሄደው ጦርነት በቅርብ ቀናት የሕወሓት ኃይሎች የደሴ እና ኮምቦልቻ ከተሞችን አልፈናል ማለታቸውን ተከትሎ ተባብሶ መቀጠሉን የሚወጡ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡@ebs1News @ebs1News
ትዊተር በኢትዮጵያ በዘመቻ መልክ መነጋገሪያ አጀንዳ የሚፈጥርበትን አገልግሎት አቆመ
**********
ከዓለማችን ግዙፍ የማኅበራዊ ትስስር መድረኮች አንዱ የሆነው ትዊተር በኢትዮጵያ በዘመቻ መልክ መነጋገሪያ አጀንዳ የሚፈጥርበትን አገልግሎት ማቆሙን አስታውቋል፡፡

በኢትዮጵያ ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ እየተከታተለ መሆኑን ያመለከተው ኩባንያው፣ በማኅበራዊ መድረኩ የሚካሄዱ የመልእክት ልውውጦች ላይ አተኩሮ እየሠራ ስለመሆኑም ነው የገለጸው፡፡

ትዊተር ሁከትን ማበረታታት እና ሰዎችን ማዋረድ ከኩባንያው ህግ ውጪ መሆኑን አመልክቷል፡፡
በርከት ያሉ ዘመቻዎ የሚስተናገዱበት ትዊተር ኩባንያ፣ ከሰሞኑ ከኢትዮጵያ ጋር የተገናኙ አካውንቶችን አግዷል በሚል ቅሬታ ሲቀርብበት ነበር፡፡

በሌላ በኩል ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ ከሰሞኑ አቅም ያላቸው ዜጎች ሁሉ ማንኛውንም መሳሪያ ይዘው የሕወሃትን ጥቃት ለመቀልበስ እንዲዘምቱ በግል ትዊተር ገጻቸው ጥሪ ያቀረቡበት መልዕክት የሥነ ምግባር ፖሊሲውን እንደጣሰ አስታውቋል። ኩባንያው የጠቅላይ ሚኒስትሩን መልዕክት ከማጥፋት ይልቅ፣ መልዕክቱ የኩባንያውን የስነ ምግባር ፖሊሲ የጣሰ መሆኑን የሚገልጥ መግለጫ ከመልዕክቱ ጋር ማያያዝ እንደመረጠ ገልጧል።

ሌላኛው የማህበራዊ ትስስር መድረክ አቅራቢ ሜታ ኩባንያም የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ተመሳሳይ መልእክት ‹‹ሁከትን ያበረታታል›› በማለት ከፌስቡክ ማኅበራዊ ትስስር ዘዴ ማጥፋቱ ይታወሳል፡፡
@ebs1News @ebs1News
የጸጥታ ችግር ባለባቸው አካባቢዎች የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና በሁለተኛ ዙር ይሰጣል
*************************

የጸጥታ ችግር ባለባቸው አካባቢዎች የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና በሁለተኛ ዙር እንደሚሰጥ የአገር አቀፍ የፈተናዎች ኤጀንሲ አስታወቀ።

የኤጀንሲው ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ተፈራ ፈይሳ እንዳሉት፤ በ2013 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ከ600 ሺህ በላይ ተማሪዎች ከ2 ሺህ በላይ በሆኑ የፈተና ጣቢያዎች ለመፈተን ተመዝግበዋል።

በሁለት ዙር ፈተናው እንደሚሰጥ የተናገሩት ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ፤ ከ90 በመቶ በላይ ተፈታኞች በመጀመሪያው ዙር ፈተናቸውን እንደሚወሥዱ ገልጸዋል።

የጸጥታ ችግር ባለባቸው ቦታዎች ፈተናው በሁለተኛ ዙር እንደሚሰጥ ጠቁመዋል።

ፈተናው በሁለተኛ ዙር ከሚሰጥባቸው ቦታዎች መካከል በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ፣ ሠሜን ወሎ እና ዋግኽምራ ዞኖች እንደሚገኙበት ተናግረዋል።

“በሁለተኛው ዙር ፈተና የሚወሥዱ ተማሪዎች የሥነልቦና ግንባታና ክለሣ ተደርጎ ፈተና ይወሥዳሉ” ብለዋል።

በአማራ ክልል ከተለዩ ቦታዎች ውጪ በሌሎች አካባቢዎችም የሚለዩ ቦታዎች ካሉ ፈተናውን በሁለተኛው ዙር እንደሚወስዱ ገልጸዋል።
@ebs1News @ebs1News
ዋግ ኽምራ ዞን ሰዎች በረሃብ እየሞቱ መሆኑን ነዋሪዎችና ኃላፊዎች ገለፁ
********************** በአማራ ክልል በሚገኘው የዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር በርካታ ሰዎች በረሃብ ምክንያት እየሞቱ መሆኑን ከአካባቢው ወደ ባሕር ዳር እና እብናት የመጡ ነዋሪዎች እንዲሁም የአካባቢው ኃላፊዎች ለቢቢሲ ተናገሩ።
የዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ተስፋዬ ገብሬ የአካባቢው ማኅበረሰብ ላለፉት አራት ወራት ምንም ዓይነት እርዳታ አግኝቶ እንደማያውቅ ለቢቢሲ አረጋግጠዋል።
የብሔረሰብ አስተዳደሩ ዋና ከተማ ሰቆጣን ጨምሮ ሌሎች የዞኑ ከተሞች በህወሓት አማፂያን ቁጥጥር ሥር በመሆናቸው በብዛት ኑሮውን በእርዳታ የሚደጎመው የአካባቢው ማኅበረሰብ ካለፈው ዓመት ሐምሌ መጀመሪያ አንስቶ ምንም ዓይነት እርዳታ እንዳላገኘ ጨምረው ተናግረዋል።
የዛሬ ዓመት በትግራይ የተቀሰቀሰው ጦርነት ወደ አማራ ክልል ዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ከተስፋፋ ጀምሮ አብዛኞቹ ወረዳዎች ለሰብዓዊ እርዳታ ዝግ ሆነው መቆየታቸውን ምክትል አስተዳዳሪው ለቢቢሲ ገልፀዋል።
ቢቢሲ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች አካባቢውን ከላሊበላም ሆነ ከሰቆጣ የሚያገናኘው መንገድ ከሐምሌ 09/2013 ዓ.ም ጀምሮ በመዘጋቱ ሰብዓዊ እርዳታም ሆነ የመድኃኒት አገልግሎት ሙሉ በሙሉ በመቋረጡ ችግሩን አባብሶታል ይላሉ።
በዚህም ምክንያት በርካታ የአካባቢው ሕዝብ ለከፋ ችግር መዳረጉን፣ ብዙ ሰዎችም በረሃብ እየሞቱ መሆናቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች እና ኃላፊዎች ይናገራሉ።@ebs1News @ebs1News
በአዲስ አበባ መከላከያን የሚደግፍ እና ህወሓትና ሸኔን የሚቃወም ሰልፍ እየተካሄደ ነው

ህወሃት እና ሸኔን የሚያወግዝ እና የሀገር መከላከያ ሠራዊትን የሚደግፍ ሰላማዊ ሰልፍ በአዲስ አበባ ከተማ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

ዛሬ ከማለዳ ጀምሮ እየተካሄደ ባለው ሰልፍ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤን ጨምሮ በርካታ የከተማዋ ነዋሪዎች ታድመዋል።

በሰልፉ ላይ የታደሙ ነዋሪዎችም የተለያዩ መፈክሮችን ይዘው የወጡ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ፤ “የድላችን ሚስጥር ፍትህ ፣ሀቅና እውነት ናቸው፤ ለውጭ ጫና የሚበረከክ ማንንት የለንም፤ የአብሮነት ጉዟችን በሽብርተኞች አይደናቀፍም፤ በመራር ትግል ጣፋጭ ድልን እንቀዳጃለን” የሚሉ ተጠቃሽ ናቸው።

በተጨማሪም አንዳንድ ዓለም አቀፍ መጋናኛ ብዙሃን እና የምዕራቡ ዓለም ሀገራት በኢትዮጵያ ላይ የሚያደርጉትን ጫና እንዲያቆሙ የሚጠይቁ
@ebs1News @ebs1News
🚨 የዓለም ክብረወሰን 🚨

🇪🇹 በሊል ፈረንሳይ በተካሄደው በሴቶች 5ኪ.ሜ (mixed race) ውድድሩ ዳዊት ስዩም 14:41 በመግባት የዓለምን ክብረወሰን የግሏ አድርጋለች 👏

@ebs1News @ebs1News
አሜሪካንን ጨምሮ 16 የዓለማችን ሀገራት በኢትዮጵያ የተካሄደውን ጥምር ምርመራ ሪፖርት እንደሚቀበሉት ተናገሩ

ሀገራቱ ኢሰመኮ እና የተመድ የተመድ የሰብዓዊ መብት ቢሮ የምርመራ ሪፖርት ግኝቶች እንዲተገበሩ ግፊት እንደሚያደርጉም ገልጸዋል። የኢትዮጵያ መንግስት የግጭቱ ሰለባዎችን ለመርዳት እያደረገ ላለው ጥረት እውቅና እንደሚሰጡም ሀገራቱ አስታውቀዋል።
@ebs1News
አሜሪካን ጨምሮ 16 የዓለማችን ሀገራት በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል የተካሄደውን ጥምር ምርመራ ሪፖርት እንደሚቀበሉት በጋራ ባወጡት መግለጫ ገልጸዋል።

የጣምራ ሪፖርቱን እንደሚቀበሉ ያሳወቁት፦
• አሜሪካ
• አውስትራሊያ
• ቤልጂየም
• ካናዳ
• ዴንማርክ
• ፊንላንድ
• ፈረንሳይ
• ጀርመን
• አይስላንድ
• አየርላንድ
• ሉግዘንበርግ
• ኔዘርላንድ
• ኒውዝላንድ
• ኖርዌይ
• ስዊድን እና እንግሊዝ ናቸው።

ሀገራቱ በመግለጫቸው ሁለቱ የሰብአዊ መብት ጥበቃ ተቋማት በትግራይ ክልል ባለው ጦርነት ዙሪያ የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ዙሪያ ያወጡት ሪፖርት ገለልተኛ እና ተጠያቂነትን ሊያሰፍን የሚችል መሆኑን አስታውቀዋል።

በሪፖርቱ መሰረት በሰብዓዊ መብት ጥሰት ሁሉም አካላት መሳተፋቸው በመረጋገጡ ሁሉም ተሳታፊዎች ተጠያቂ እንዲሆኑ ሀገራቱ አሳስበዋል።

በተጨማሪ በሰብዓዊ መብት ጥሰቶቹ ላይ የተሳተፉ ሁሉም አካላት በሪፖርቱ ግኝቶች መሰረት ወደ መፍትሄ እንዲመጡም ጠይቀዋል።

በሌላ በኩል 16ቱ አገራት የኢትዮጵያ መንግስት በጦርነቱ ለተጎዱ አካላት እያደረገ ያለው ድጋፍ፣ ወንጀል ፈፅመዋል በሚል በተጠረጠሩ አካላት ላይ ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ ምርመራ መጀመሩ ና እያደረጋቸው ላለው ሌሎች ጥረቶች እውቅና እንሰጣለን ብለዋል።

መንግስት የጀመረውን ጥረት እንዲቀጥልበት የጠየቁ ሲሆን በተለይ ለተጎጂዎች ተጨማሪ የሰብዓዊ መብት ድጋፎች እንዲደርሱ፣ በወንጀል ፈጻሚዎች ላይ ተጨማሪ ምርመራዎች እንዲካሄዱና ጦርነቱን በዘላቂነት ለማስቆም ብሄራዊ ውይይት እንዲያካሂድ ጠይቀዋል።

ሀገራቱ ኢትዮጵያ ወደ ቀድሞ ሰላሟና መረጋጋቷ እንድትመለስ ድጋፍ እንደሚያደርጉና የግዛት አንድነቷን እንደሚያከብሩም አሳውቀዋል።
@ebs1News @ebs1News
ኢሰመኮ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ‹‹ማንነትን መሠረት ባደረገ በሚመስል ሁኔታ›› እስር መከናወኑ አሳስቦኛል አለ
********************* የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በመላው ኢትዮጵያ ከታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጋር በተያያዘ ‹‹ማንነትን መሰረት ባደረገ መልኩ በሚመስል ሁኔታ›› ሰዎች እያታሰሩ መሆኑን ገልጧል፡፡

ኮሚሽኑ ባወጣው መግለጫ አስቸኳይ ጊዜ ከታወጀበት ጥቅምት 23፣ 2014 ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ ሰዎች ከስራ ቦታቸው፣ ከመኖሪያ ቤታቸው እና ከመንገድ ላይ ጭምር ተይዘው በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ማረጋገጡን አስታውቋል።

በተጨማሪም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ለሕግ አስከባሪዎች ‹‹ከሽብር ቡድኖች ጋር ይተባበራሉ ተብለው ምክንያታዊ በሆነ መልኩ የተጠረጠሩ ሰዎችን›› መያዝን ቢፈቀድም፤ እስሩ ‹‹ማንነትን/ብሔርን መሰረት ያደረገ በሚመስል መልኩ መከናወኑ፣ በአንዳንድ ፖሊስ ጣቢያዎች የቤተሰብ ጥየቃ፣ ልብስና ስንቅ ማቀበል መከልከሉ እንዲሁም እስሩ ሕጻናት ልጆች ያሏቸው እናቶች አረጋዊያንን ጭምር ያካተተ መሆኑ›› አሳስቦኛል ብሏል።
ኢሰመኮ የህግ አስከባሪ አካላት ‹‹የህጋዊነት፣ የጥብቅ አስፈላጊነትና ተመጣጣኝነት እንዲሁም ከመድልዎ ነጻ መሆን›› የሚሉ መርሆዎችን ሊያከብሩ ይገባል ያለ ሲሆን፣ ከዚህ በተጨማሪም የህግ አስከባሪ አካላት ‹‹በማንኛውም ሁኔታ ሊገደቡ የማይችሉ ሰብዓዊ መብቶችን የማክበር እና የማስከበር ተግባራቶቻቸውንም በከፍተኛ የሙያ ስነምግባር በመመራት የማከናወን ኃላፊነት አለባቸው›› ሲል አሳስቧል።
ባለፈው ሳምንት ጥቅምት 23፣ 2013 የታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለስድስት ወራት የሚቆይ ስለመሆኑ መነገሩ አይዘነጋም፡፡@ebs1News @ebs1News
ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል፣ ከአፍሪካ ህብረት ልዩ መልእክተኛ ኦሊሴንጎ ኦባሳንጆ እና የኦቻ ሃላፊ ማርቲን ግሪፍትስ ጋር በመቐለ ከተማ መወያየታቸው ተሰምቷል!

የትግራይ ክልል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ደብረፅዩን ገ/ሚካኤል ከቀድሞው የናይጀሪያ ፕሬዝዳንት እና የአፍሪካ ህብረት ልዩ መልእክተኛ ኦሊሴንጎ ኦባሳንጆ ጋር በፅህፈትቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል ሲል የትግራይ መንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ በፌስቡክ ገፁ አሳውቋል።

በተመሳሳይ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ እርዳታ አስተባባሪ ኦቻ ሃላፊ ማርቲን ግሪፍትስ ተገናኝተው መወያየታቸው ተገልጿል።

በመቐለ በተካሄደው በዚህ ውይይት በኢትዮጵያ ያለውን የፖለቲካ ቀውስ እና በሰብአዊ እርዳታ እንቅስቃሴ እንዲሁም በቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል። ሁለቱም እንግዶች ትናንት ማምሻውን ከመቐለ ወደ አዲስ አበባ ተመልሰዋል ተብሏል።
@ebs1News @ebs1News
በሰሜን ኢትዮጵያ ያለው ግጭት እንዲቆም እና ሰላም እንዲወርድ መፍትሄ እያፈላለጉ ያሉት ኦሊሴንጉን ኦባሳንጆ ዛሬ ወደ አማራ ክልል አፋር ክልል ይጓዛሉ።

ኦባሳንጆ ከቀናት በፊት ወደ ትግራይ ክልል መቐለ ተጉዘው እንደነበር አይዘነጋም።

ዛሬ ወደ ባህር ዳር እና ሰመራ በማቅናት ከክልሎቹ ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር እያደረጉት ስላለው የሰላም ጥረት ይወያያሉ ተብሏል፤ እስካሁን ስለጉዟቸው ዝርዝር ነገር የለም።

በሌላ በኩል ኦባሳንጆ በሰሜን ኢትዮጵያ ያለውን ግጭት ለመፍታት በሚያደርጉት ጥረት ተልዕኳቸውን አልቀበልም ያለ አካል እንደሌለ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

የፌዴራል መንግስት ይሁን በትግራይ ክልል ያሉ አካላት እሳቸውን አልቀበልም ያለ እንደሌለ አሳውቀዋል።

ኦባሳንጆ ፥ "የአፍሪካ ሕብረት ሰላም ለማምጣት፣ ንግግርን ለማስጀመር እና ደኅንነትን ለማስጠበቅ ልዩ መልዕክተኛ መሰየሙን ሁሉም ወገን በበጎ ነው የተቀበሉት" ብለዋል።

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ፥ "የጠየቅኩትን ትኩረት ሰጥተውኛል። በሚገባው ልክ አስተናግደውኛል" ሲሉ ስለተደረገላቸው መልካም አቀባበል ገልጸዋል።

ትግራይ ክልል ሲሄዱም ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ኤርፖርት ድረስ ሄደው እንደተቀበሏቸው ገልፀዋል።

ሁለቱም ወገኖች የአፍሪካ ሕብረት ልዩ መልዕክተኛ ኦባሳንጆን "አልተቀበሉንም የሚለው ሐሳብ ፍጹም ስህተት ነው" መሆኑን አሳውቀዋል።

አሁን ላይ የድርድሩ ሂደት ምን ላይ እንዳለና በቀጣይ የሚፈጠረውን ጉዳይ በተመለከተ ኦባሳንጆ ፤ "አሁን ገና የመጀመሪያው ምዕራፍ ላይ ነኝ። ድርድሩ ወዴት እንደሚሄድ የምናገርበት ጊዜ አይደለም" ብለዋል።

አሁን ያሉበት ደረጃ በተደራዳሪ ወገኖች ዘንድ ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ ምን እንደሆነ የመለየት እንደሆነም ለቢቢሲ ፎከስ ኦን አፍሪካ አስረድተዋል። @ebs1News @ebs1News
ግጭት ካለባቸዉ አካባቢዎች የመጡ 144 የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች በአዲስ አበባ ፈተናዉን እየወሰዱ ይገኛል ተባለ!!
@ebs1News @ebs1News
ጥቅምት 29 ቀን 2014 ዓ.ም በተጀመረው እና በነገዉ እለት በሚጠናቀቀው የ2103 የ12ኛ ክፍል የመልቀቂያ ፈተና ግጭት ካለባቸው የአማራ ክልል የመጡ 144 ተማሪዎች በአዲስ አበባ ፈተናውን እየወሰዱ መሆኑን የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ አስታውቃል፡፡

የትምህርት ቢሮ የፈተና ዝግጅት እና አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር አቶ ዲናኦል ጫላ ከብስራት ሬድዮ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደተናገሩት ፈተናው ለመፈተን በስነልቦናም ሆነ በአቅም ዝግጁ ነን ያሉ በግጭት ምክንያት ፈተናው ከማይሰጥባቸው የአማራ ክልል የመጡ የመጡ ተማሪዎች በአዲስ አበባ ፈተናውም እየወሰዱ ይገኛል ብለዋል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ እነዚህ ተማሪዎች ለማስፈተን አንድ ጣቢያ በመክፈት እነዲሁም ተማሪዎች ያሉበት ቦታ የተበታተነ በመሆኑ ፈተናው ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ የምግብ አቅርቦት እንዲያገኙ ማመቻቸቱን አስታውቃል፡፡

ፈተናዉ በነገው እለት ሲጠናቀቅ የአዲስ አበባ ተፈታኝ ተማሪዎች ለተፈናቀሉ ወገኖች እና ለመከላከያ ሰራዊት የሚሆን ድጋፍ ለማድረግ በየግላቸው ከሁለት ፓስታ ጀምሮ አልባሳትን እና ሌሎች ቁሳቁሶችን ይዘው እንዲመጡም አቶ ዲናኦል ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የ2013 ዓመት የ12ኛ ክፍል የመልቀቂያ ፈተና መሰጠት ከጀመረበት ቀን አንስቶ ሂደቱ ላይ መስተጓጎል የሚያስከትል ችግር አለመፈጠሩን በመግለስ ጥቂት ተማሪዎች ስልክ ይዘው ወደ መፈተኛ ክፍል ለመግበት ሲሞክሩ እና ይዘው ከገቡ በኃላ የተያዙ እንዳሉ አቶ ዲናኦል ጫላ ጨምረዉ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል፡፡
የመንግሥታቱ ድርጅት የከባድ መኪኖች አሸከርካሪዎች የሆኑ ከ70 በላይ ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተዘገበ
********************* የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት 72 የዓለም ምግብ ፕሮግራም የከባድ መኪና አሸከርካሪዎች አፋር ክልል ሰመራ ውስጥ በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ሬውተርስ እና እና አዣንስ ፍራንስ ፕረስ ዘግበዋል፡፡

ሬውተርስ የድርጅቱ ቃል አቀባይ በዓለም ምግብ ድርጅት ተቀጥረው ይሰሩ የነበሩ 72 አሸከርካሪዎች ሰመራ ከተማ ላይ መታሰራቸውን አረጋግጠውልኛል ያለ ሲሆን፣ ‹‹ሠራተኞቹ ለምን እንደታሰሩ ለማረጋገጥ ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር እየተነጋገርን ነው›› እንዳሉት አስነብቧል፡፡

በተመሳሳይ በትላንትናው እለት ኢትዮጵያውያን የሆኑ ቢያንስ 16 የመንግሥታቱ ድርጅት ሠራተኞች እና ቤተሰቦቻቸው አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ በቁጥጥር ሥር መዋላቸው መነገሩ አይዘነጋም፡፡

በትላናትናው እለት አመሻሹ ላይ የወጣውን ይህን ዜና ተከትሎ የአሜሪካ መንግሥት ተፈጸመ የተባለው የዓለም አቀፍ ድርጅቱ ሠራተኞች እስር አሳስቦኛል ብሏል፡፡ መንግስት ሠራተኞቹ ለምን እንደታሰሩ ያለው ነገር ባይኖርም፣ አዣንስ ፍራንስ ፕረስ ዘግየት ብሎ ባወጣው ዘገባ ስድስቱ መለቀቃቸውን አስነብቧል፡፡

የመንግሥታቱ ድርጅት ታሰሩብኝ ስላላቸው ሠራተኞቹ ጉዳዩ የኢትዮጵያ መንግሥት እስካሁን የሰጠው ማብራሪያ የለም።
ቀደም ብለው ከወጡ ሕጎች እና መመሪዎች ውጭ ሲሠሩ በሚገኙ ባንኮች ላይ ጥብቅ ርምጃ እንዲወሰድ ትእዛዝ ተላለፈ


አምባ ዲጂታል፣ ሐሙስ ኅዳር 2፣ 2014 ― በአገሪቱ ቀደም ብለው ከወጡ ሕጎች እና መመሪዎች ውጭ ሲሠሩ በሚገኙ ባንኮች ላይ ጥብቅ ርምጃ እንዲወስድ ለብሔራዊ ባንክ ትእዛዝ ያስተላለፈው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዕዝ ነው፡፡


ይህንኑ ትላንት ምሽት ባወጣው መግለጫ ያስታወቀው እዙ፣ ትእዛዙን ለማስተላለፍ መነሻ የሆነው ‹‹ሕገ ወጥ›› ያላቸው ግለሰቦች ‹‹ብሔራዊ ባንክ ካወጣቸው ደንቦችና የአፈጻጸም መመሪያዎች እንዲሁም ከባንኮች ሕጋዊ አሠራር ውጭ፣ በተጭበረበረ መንገድ የገንዘብ ዝውውር እያካሄዱ መሆኑ›› ስለተደረሰበት እንደሆነ አስታውቋል፡፡


በመሆኑም ቀደም ብለው ከወጡ ሕጎች እና መመሪዎች ውጭ ሲሠሩ በሚገኙት ባንኮች ላይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን መሠረት በማድረግ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከሕግ አስፈጻሚ አካላት ጋር በመቀናጀት ጥብቅ ርምጃ እንዲወስድ ትእዛዝ ከማስተላለፉ በተጨማሪ፣ ከዚሁ ጋር በተያያዘ ማንኛውም የተጭበረበረ የገንዘብ ማዘዋወሪያ ሰነድ ይዘው በተገኙ ላይ ከወትሮው በተለየ ጥብቅ ርምጃ እንዲወሰድ ብሏል፡፡


በሌላ በኩል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዕዝ በዚሁ መግለጫው የጸጥታ ኃይሎች የተቀናጀ እንቅስቃሴ፣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ድንጋጌዎችን በማስፈጸም ባለፉት ቀናት ‹‹አኩሪ ውጤቶችን›› ማስመዝገቡን ያመለከተ ሲሆን፣ የጸጥታ ኃይሎች ለሕዝቡ ደኅንነት ሥጋት የሚሆኑትን ለመመንጠር ለሚያደርጉት እንቅስቃሴ እንዲያግዛቸው ማንኛውም ቤት አከራይ የተከራይን ማንነት የሚገልጽ ሙሉ መረጃ ከትላንት ኅዳር 1፣ 2014 ጀምሮ በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ፣ በአቅራቢያው በሚገኝ የፖሊስ ጣቢያ እንዲያስመዘገብ አዟል፡፡


አያይዞም የጸጥታ ኃይሎች የተቀናጀ እንቅስቃሴ በማድረግ ሕገ ወጦችን በቁጥጥር ሥር ማዋላቸውን፣ በርካታ ሕገ ወጥ የጦር መሣሪያዎችም እንደተያዙ ገልጧል፡፡ ነገር ግን ‹‹ይህ ያስደነገጠው›› ጠላት ያለው አካል፣ ‹‹የጸጥታ አካላትን መልካም ስም ለማጥፋት፣ ለማሸማቀቅና ሥራቸውን በሙሉ አቅም እንዳይሠሩ ለማድረግ እየተንቀሳቀሰ›› እንደሚገኝ አሳውቋል፡፡ በሌላ በኩል በዚህ አጋጣሚ ለመጠቀም የሚፈልጉ ጥቂት የጸጥታ አካላት መኖራቸውን አረጋግጫለሁ ያለው እዙ፣ በእነዚህ አካላት ላይ በጠራ መረጃ ላይ በመመሥረት የማያዳግም ርምጃ እንዲወሰድ ትእዛዝ መሰጠቱንም አክሏል፡፡@ebs1News @ebs1News
ትላንት የተሰጡት የታሪክ ፣ ኬሚስትሪ እና ባዮሎጂ ፈተናዎች ከፈተናው በፊት ቀድሞ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ መሰራጨቱን ከበቂ ማስረጃ ጋር ማረጋገጣችን ይታወሳል።

ዛሬ የተሰጠውም የስነ-ዜጋ እና ስነ-ምግባር (ሲቪክ) ትምህርት ከትላንት ምሽት ጀምሮ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ሲሰራጭ እንደነበርና ዛሬ የተሰጠው የፈተና ወረቀትም ትላንት ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ከተሰራጨው ጋር ተመሳሳይ መሆኑን በበቂ ማስረጃ አረጋግጠናል።

ኢትዮጵያ ውስጥ የማህበራዊ ሚዲያዎች ቢዘጉም የተለያዩ መንገዶችን በመጠቀም አገልግሎቶቹ ቀጥለዋል።

ይህ ትውልድና እና ኢትዮጵያን የመግደል ተግባር በማን እና እንዴት እንደተፈፀመ ግልፅ ማብራሪያ የሚፈልግ ሲሆን በዚህ ሂደት ውስጥ ተጠያቂው አካል መታወቅ ይኖርበታል።

ለዓመታት የለፉ ተማሪዎችን ድካም በሚያደናቅፍ ተግባር ላይ የተሳተፉ፣ ሲተባበሩ የነበሩ፣ ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ሲያጋሩ የነበሩ ሁሉ ሌላው ቢቀር ከሞራል ተጠያቂነት አይተርፉም።

በውጭ ያሉ የማህበረሰብ አንቂ ነን የሚሉ አካላትም ሆነ የፖለቲካ ሰዎች ከምንም ጋር ግንኙነት የሌላቸው ተማሪዎችን የግል የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት ብቻ ሲሉ ኢ-ስነምግባራዊ በሆነ ትውልድን የመጉዳት ተግባር ላይ መሳተፋቸው እጅጉን የሚያሳዝን ነው። @ebs1News @ebs1News

የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ዛሬ ተጠናቋል።
ቡርሃን ራሳቸውን የሱዳን ጊዜያዊ መሪ አድርገው ሾሙ

የሱዳን መፈንቅለ መንግስት መሪ  አብዱልፈታህ አል ቡርሃን በወታደራዊ ሀይል ስልጣን ከተረከቡ በኃላ አዲሱ የገዢ ምክር ቤት መሪ አድርገው ራሳቸውን ሾመዋል።በትላንትናው እለት ቃለ መኃላ ፈፅመዋል።

የጄኔራል ቡርሃን ምክትል መሀመድ ሃምዳን ዳጋሎ ወይም ሄሜቲ በመባል የሚታወቁት ሲሆን ከፍተኛ ወታደራዊ መሪዎች ከመፈንቅለ መንግስቱ በፊት በያዙት ቦታ እንዲቆዩ አድርገዋል።

14 አባላት ያሉት የሽግግር ምክር ቤት ውስጥ የሲቪል አመራሮች ቢካተቱም ከመፈንቅለ መንግስቱ በፊት በስልጣን ላይ ከነበረው የፖለቲላ ጥምረት አንድም ሰው አልተካተተም።ከስልጣን የተወገዱት የሱዳን የማስታወቂያ ሚኒስትር ሃምዛ ባሎል እርምጃው የመፈንቅለ መንግስቱን እድሜ ለማራዘም የተደረገ ሴራ ብለውታል።

መፈንቅለ መንግስቱን ለመቀልበስ የሀገር ውስጥ እና አለም አቀፍ ግፊት እየጨመረ ቢመጣም አዲሱ ምክር ቤት ግን እውን ሆኗል።በሱዳን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ተወካፕ ቮልከር ፔርቴስ የጦሩ ዋና አዛዥ የአንድ ወገን ሹመት ወደ ህገ መንግስታዊ ለመመለስ አስቸጋሪ ያደርገዋል ብለዋል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት መልዕክተኛ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ እንቅስቃሴን ወደ መደበኛ ሁኔታ ለመመለስ አስቸኳይ በመሆኑ ድርድር እንዲደረግ ጥሪ አቅርበዋል።ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክ ሙሉ ነፃነት እንዲሰጣቸው መልዕክተኛው ጠይቀዋል።
@ebs1News @ebs1News
ህወሓት በአማራ ክልል በወረራቸው አካባቢዎች ከ279 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በላይ የሃብት ውድመት አድርሷል **************************** የአማራ ክልል ፕላንና ልማት ቢሮ ህውሃት በወረራ ይዞ በኃይል እንዲለቅ በተደረገባቸው ቦታዎች አደረኩት ያለውን የዳሰሳ ጥናት ይፋ አድርጓል። መረጃዎቹ በጣም አስደንጋጭ ናቸው። የዳሰሳ ጥናቱ አሁን በህውሃት ተወረው የተያዙትን ቦታዎች እንደማያጠቃልል መገለጹ ደግሞ መጻኢው ግዜ ይበልጥ እንደሚያስፈራ አመላካች ነው።
እነ ዓብይ አህመድ "መለማመጃ፣ ማሟሻ" በማለት ደረጃ ባወጡለት ወቅት ላይ የደረሰውን ውድመትና ዘረፋ ከክልሉ ፕላን ቢሮ እንስማ። አሁንም ልብ ሊባል የሚገባው ውድመቱ አሁን ህውሃት በወረራ የያዘውን ቦታዎች አያጠቃልልም።
እነሆ፣
#1ኛ፡- ህወሓት በአማራ ክልል ወረራ በፈፀመባቸው የተለያዩ አካባቢዎች ከ279 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር የሚበልጥ የሀብት ውድመት አድርሷል።
(እንግዲህ ይሄ ማለት የአማራ ክልል የ5 አመት አማካይ በጀት ወድሟል)
#2ኛ፡- ጥናቱ በተካሄደባቸው 45 ወረዳዎች ከ6 ሚሊዮን በላይ ህዝብ ለችግር ተጋልጧል።
#3ኛ፡- ጥናቱ በተካሄደባቸው 45 ወረዳዎች 1 ሚሊዮን የሚጠጋ ህዝብን ከመኖሪያ ቀዬው ተፈናቅሏል።
#4ኛ፡- በጤናው ዘርፍ 1ሺህ 466 ሆስፒታሎች፣ ጤና ጣቢያዎችና ጤና ኬላዎች ላይ በተፈጸመ ጥቃት ከ2 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር በላይ ውድመት ደርሷል።
#5ኛ፡- በ6 ፖሊ-ቴክኒክ ኮሌጆች እንዲሁም በ17 የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ላይ በደረሰው ጉዳትም 2 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር የሚጠጋ ሃብት ውድመት ደርሷል።
#6ኛ፡- በመንገድ መሰረተ ልማትና በድልድዮች ላይ በደረሰው ጉዳት ከ2 ቢሊዮን ብር በላይ ውድመት አስከትሏል።
#7ኛ፡- በመስኖ ተቋምት ከ1 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር በላይ ሃብት ሙሉ በመሉ ከጥቅም ውጭ ሆኗል። @ebs1News @ebs1News
የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ሶማሊያ ጉዳይ ለመምከር በመጪው ሰኞ ወደ ኬንያ ያቀናሉ
************************ የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶን ብሊንክን በኢትዮጵያ እና ጎረቤቶቿ ሱዳን እንዲሁም ሶማሊያ ጉዳይ ለመምከር በመጪው ሰኞ ወደ ኬንያ እንደሚያቀኑ ጽሕፈት ቤታቸው አስታውቋል፡፡

አንቶንዮ ብሊንክን በኬንያ በሚያደርጉት ቆይታ ከአገሪቱ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ጋር እንደሚነጋገሩ ተገልጧል፡፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት አባል የሆነችው ኡሁሩ ኬንያታ የሚመሯት ኬንያ፣ ባለፉት ቀናት የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልእክተኛው ጄፍሪ ፌልትማንን ማስተናገዷ ይታወቃል፡፡

ባለፈው ሳምንት መጨረሻ በተመሳሳይ ኢትዮጵያ የተገኙት ፌልትማን፣ ኬንያ የተመለሱት አዲስ አበባ ደርሰው እንደነበር ተነግሯል፡፡

አሁን አንቶንዮ ብሊንክንን የሚቀበሉት የኬንያው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ፣ ከጥቂት ሳምንታት በፊት በአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ግብዣ ዋይት ሐውስ ተገኝተው ነበር፡፡
ኡሁሩ ከቀናት በፊት በጽሕፈት ቤታቸው በኩል በኢትዮጵያ ጦርነት ተፋላሚ አካላት መካከል በአስቸኳይ የተኩስ አቁም እንዲደረግም ጠይቀዋል፡፡

የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶን ብሊንክን ሰኞ በሚጀምሩት ጉዞ ከኬንያ በተጨማሪ፣ ናይጄሪያ እና ሴኔጋልን ይጎበኛሉ ተብሏል፡፡

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ብሊንክን በአገራቱ በኢትዮጵያ እና ሱዳን ጉዳይ ከመምከራቸው ሌላ ሽብርተኝነትን ለመመከት የሚደረጉ ትብብሮችን የማደስ አላማ እንዳላቸው አሳውቋል፡፡ @ebs1News @ebs1News