ᏃᗩᏦᏆᖇ’Official Channel”
4.75K subscribers
55 photos
25 videos
2 files
20 links
ትክክለኛውን የኢስላም እምነት (አቂዳ) እና የነብዩን ﷺ ሱና በሰለፎች (ቀደምት ደጋግ አባቶች) ግንዛቤ የምናሰራጭበት ቻናል ነው።
Download Telegram
መመሳሰል!!

⎬يَٰٓأُخْتَ هَٰرُونَ مَا كَانَ أَبُوكِ ٱمْرَأَ سَوْءٍۢ وَمَا كَانَتْ أُمُّكِ بَغِيًّۭا⎨
«የሃሩን እኅት ሆይ! አባትሽ መጥፎ ሰው አልነበረም፡፡ እናትሽም አመንዝራ አልነበረችም» አሏት፡፡

የሃሩን እኅት የተባለችው መርየም عليها السلام  ስትሆን አባታቸው ዒምራን ይባላል። መርየም ቢንት ዒምራን እና ሃሩን ብን ዒምራን ወንድምና እህት ናቸው። ሙሳ عليه السلام ወንድሙ ሃሩን ሲሆን አባታቸው ዒምራን ይባላል። ሙሳ ብን ዒምራን እና ሃሩን ብን ዒምራን ወንድማማቾች ናቸው።

◈ የሙሳና ሃሩን አባት የመርየምና ሃሩን አባት አይደለም። ምክንያቱም በሙሳና መርየም መሀከል ብዙ ክፍለ ዘመን ስለነበር እና ቁርአን ላይ አንድም አንቀፅ የነብዩሏሂ ሙሳ እህት መርየም ናት የሚል የለም።
   ─┅──═••••✦✿✦••••═──┅─
🥰33👍25❤4🤔3
“ልብህ ሲጨነቅ ወደ አላህ ተመለስ፤ በሱጁድህ ውስጥ አልቅስ፣ ዱዓ አድርግ፣ በትዕግስትም ጠብቅ። ሰዎች የማያውቁትን
የልብህን ስብራት አላህ ያውቃልና።

﴿أَلَا بِذِكْرِ اللَّهِ تَطْمَئِنُّ الْقُلُوبُ﴾

«ንቁ! ልቦች በአላህ ማውሳት ይረጋጋሉ።» (ሱረቱ አር-ረዕድ፡ 28)
👍68🥰19❤5👏1
አላቹ?
👍73❤3
እሺ፣ እንዴት ናቹ? ሕይወት እንዴት እየሄደች ነው? ቤተሰብ ሁሉ ሰላም? እናንተ ሰላም ናችሁ? 😊
👍85🥰26👏3
ያ ረብ! ሕይወቷን በመልካም ሥራና በበረከት አስውብልን። የመልካም ሥራ መዓዛ ከእርሷ አይለይ፤ በምትነካውም ሁሉ ሰናይ ዜናን፣ ደስታንና በረከትን ሙላላት። አሚን!
❤64👍23🥰6
قال رسول الله صلى الله عليه وسلم:
«وَمَن صَنَعَ إِلَيْكُم مَعروفاً فَكافِئوهُ، فَإِن لَم تجِدوا ما تُكافِئونَهُ فادعوا لَهُ حتّى ترَوا أَنَّكُم قَد كافَأتُموهُ»

“ማንም ሰው መልካም ነገር (ውለታ) ቢያደርግላችሁ፣ ውለታውን መልሱለት። የምትመልሱለት ወይም የምትክሱበት ነገር ካላገኛችሁ ግን ውለታውን እንደመለሳችሁ እስኪሰማችሁ ድረስ ለእርሱ (ዱዓ) አድርጉለት።
🥰47👍26❤2
ሲጀመር ቡናና ሽቶ ታናሽና ታላቅ ናቸው፤ አንዱ ለልብ ደስታ፣ ሌላው ለአፍንጫ ደስታን ይሰጣሉ! 😁☕️
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
😁115👍18
“በህይወት ጉዞችን ላይ የስኬታችን መገንቢያ መሠረት፣ የለውጣችንም መጀመሪያ «መወሰን» መቻል ነው ብየ አስባለሁ። ብዙዎቻችን የትኛው መንገድ እንደሚበጀን፣ የትኛው ስራ እንደሚያተርፈንና የትኛው ግንኙነት ለህይወታችን እንደሚበጀን ጠንቅቀን እናውቃለን። ይሁንና እውቀቱ እያለን፣ ጥበቡ ሞልቶን ሳለ ግን አንዲት እርምጃ ወደፊት ለመራመድ እንቸገራለን። ለምን?የመወሰን ድፍረት ስለሚያጥረን!

«ቢያከስረኝስ? ባይሳካልኝስ? ሰዎች ምን ይሉኝ ይሆን?» የሚሉ የፍርሃት ሰንሰለቶች እግራችንን አስረው ከቆምንበት ንቅንቅ እንዳንል ያደርጉናል። አንዳንዴ ካለመወሰን የተነሳ የምናጣው ዕድል፣ ወስነን ከሚደርስብን ኪሳራ በላይ እጅግ የከፋ ነው። ጊዜው ካለፈ በኋላ «ምነው በወሰንኩ ኖሮ» የሚል የቁጭት እንባ ከማፍሰስ በላይ ምን የሚያም ነገር አለ? ውሳኔ በመዘግየቱ ብቻ ስንት ታላላቅ ህልሞች ሳይቀበሩ ሞተዋል?
✍️منقول
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍66🥰3
እኔ ምለው፣ ሰዎች አንድ ሀሳብ መጥቶልኝ ነበር። 🤔
👍32🤔17
ᏃᗩᏦᏆᖇ’Official Channel”
እኔ ምለው፣ ሰዎች አንድ ሀሳብ መጥቶልኝ ነበር። 🤔
ቡና ሲፈላ ለምንድነው ስኳሩ ከመጀመሪያው አብሮ የማይጨመረው፣ አብሮ እንዲፈላ? አሁን እኮ ትዝ ብሎኝ ነው!😁🫢
😁70🤔5
እሺ፣ ጀበና ለምንድነው ጥቁር የሆነው? ቀይ ቢሆንስ? አሁን ይሄም ሀሳብ መጥቶልኛል እኮ ነው!😁🤔
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
😁63❤1🤩1
ሌላም አንድ ሀሳብ እኮ መጥቶልኛል! 😁
😁52❤2
ᏃᗩᏦᏆᖇ’Official Channel”
ሌላም አንድ ሀሳብ እኮ መጥቶልኛል! 😁
ዝናብ ሲዘንብ ለምንድነው የምንሮጠው?🤔
😁85❤2
~አንዳንዴ…አሞራ በዓሳ ፍቅር ሲነደፍ ታያለህ።ግና እስቲ የትና እንዴት ይኑሩ።
ዉሃ ዉስጥ ወይስ ሰማይ ላይ?

ምን ለማለት መሰላችሁ…እንዲሁ እየታወቀ፣ እሷም እንደማታገኘው፤ እሱም እንደማያገኛት እያወቀ ያፈቅራል።ይህ የብዙ ወንዶችና ሴቶች የፍቅር ታሪክ ነው።

በመጨረሻም ከዕለታት አንድ ቀን  ....
በዉሃ ዳር ሲሽከረከር የነበረው አሞራ ነገሩ እንደማይሆን ሲያውቅ ተስፋ ቆርጦ ይበራል።ቢሆንም ግን ፍቅሩ ከዉስጡ አይጠፋም። በበረረበት ዓሳዉን ይዞ ይበራል።

ዓሳዉም ወደ ዋናው ይመለሳል።
ግና በሙሉ ልብ አይዋኝም።የተወጋ ልቡን ይዞ እያቃሰተ በሀሳብ ዉሃዉን ይሰነጥቃል። •አንዳንዴ…🥲
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👌64👍15😁8❤1🥰1
አንዳንዴ… ጨረቃን የሚያፈቅር ኮከብ ታያለህ። ሌሊቱን ሙሉ በአጠገቧ ይበራል ግን ፈጽሞ ሊነካት አይችልም። ጨረቃም የእሱን ፍቅር ሳታውቅ ትበራለች።

አንዳንድ ፍቅሮች ለመገናኘት ሳይሆን፣ ከሩቅ ሆነው ለመኖር የተፈጠሩ ይመስላሉ። 🥲
💔43👍18🥰5❤‍🔥2
እኔ እኮ አሁንም አንድ ሀሳብ መጥቶልኝ ነበር።🤔
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
😁63🤔12🙊1
• ምን ያመጣል? ምን ታመጣለች?ብላችሁ…የትከሻዋን መሳሳት፣ ሁነኛ ዘመድ እንደሌለው አስልታችሁ በግፍና በጭካኔ የሰበራችሁት ልብ ከአላህ ጋር ያለው ትስስር ጠንካራ ቢሆንስ ምን ሊውጣችሁ? በጥሩ ሁኔታ መለያየትም እኮ አንድ ጥሩነት ነው።
فإمساك بمعروف أو تسريح بإحسان
እንዲል ቁርአኑ…በደልን ተጠንቀቁ!
🥰48👍21💯6❤1💔1🍓1
~በቃ ምንም ብታፈቅሪው ምንም ያክል ብታምኚው..…ሰው ነው ብለሽ አስቢ… እንዳሰብሽው ባይሆን እና ስህተት ቢሰራ ህመምሽን ምትቋቋሚበት ትንሽ ጥንካሬ ለራስሽ አስቀምጪ። ለሱ ካለሽ ፍቅር እና እምነት ትንሽ ለራስሽም አስቀሪ።ሰው ነው ብለሽ አስቢ.... በፍቅርሽ እና በእምነትሽ ልክ ፍፁም አታድርጊው ጥንካሬ እንዲሆንሽ ለራስሽም የመፅናኛ ቃል አስቀምጪ ሰው ነው ብለሽ አስቢ .....

«ሰው ነው»
✍️منقول
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍63👏8👌5😁3❤‍🔥2🥰1💯1
እኔ ምለው ስታገቡም፣ ስትወልዱም፣ ስታተርፉም፣ ስትከስሩም ሮጣችሁ ላይቭ የምትገቡት እኛ ምስክር እንድንሆንላችሁ ነው? ቆይ ምን አድርጉ ነው የምትሉን?🤔
😁98👍7💯2👀2🤔1