EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
136K subscribers
20.5K photos
170 videos
79 files
10.6K links
Ethiopian Broadcasting Corporation (EBC)
Download Telegram
16ኛው የጋራ ሚኒስትሮች ኮሚሽን የግማሽ ዓመት አፈጻጸም መድረክ የንግድ ግንኙነት ድህረ- ውይይት እየተካሄደ ነው
****************

በቅርቡ በጅቡቲ በተካሄደው 16ኛው የጋራ ሚኒስትሮች ኮሚሽን የግማሽ ዓመት አፈጻጸም ላይ የሁለቱ ሀገራት የንግድ ግንኙነት አስመልክቶ በተነሱ ነጥቦች ላይ ለመወያየት ያለመ መድረክ ዛሬ ተጀምሯል።

በውይይቱ ላይ ለመሳተፍ በንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ካሳሁን ጎፌ የተመራ ልዑክ ጅቡቲ የተገኘ ሲሆን፤ የጂቡቲ የንግድ እና ቱሪዝም ሴክሬተሪ ጄኔራል አሊ ዳውድ፣ የጂቡቲ ንግድ ሚኒስቴር የሥራ ኃላፊዎች፣ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የሚሲዮን መሪ አምባሳደር ብርሀኑ ፀጋዬ እና ዲፕሎማቶች ተሳትፈዋል።https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid0kohKuCSJVhuuYfp3D34VY84ZRK6uargQs2ZBpQSr3rfdTi9gtD5NJuJtisYUndt4l
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተለያዩ ሹመቶችን ሰጡ
***************

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዛሬው ዕለት የተለያዩ ሹመቶችን ሰጥተዋል።

በዚህም መሰረት፡-

1. ኢንጂነር አይሻ መሀመድ የመከላከያ ሚኒስቴር ሚኒስትር፣

2. አብረሃም በላይ (ዶ/ር) የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ሚኒስትር፣ እና

3. መሀመድ እንድሪስ (ዶ/ር) በሚኒስትር ዴኤታ ማዕረግ በዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ከግንቦት 13 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ መሾማቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አስታውቋል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የ1ሺህ 445ኛውን የሐጅ ጉዞ በስኬት ለማካሄድ የሚያስችለውን ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታወቀ
**************

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የ1ሺህ 445ኛውን የሐጅ ጉዞ በስኬት ለማካሄድ የሚያስችለውን ልዩ ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታውቋል።

ይህ ልዩ ዝግጅት ለተከታታይ ዓመታት የተደረገ መሆኑን ነው አየር መንገዱ በማኅበራዊ ትስስር ገፁ ባወጣው መረጃ ያመላከተው።

አየር መንገዱ ወደ ሳዑዲ ዓረቢያ ማለትም ጂዳ፣ መዲና፣ ሪያድ እና ደማም ከተሞች በሳምንት 35 የመንገደኛ በረራ እያደረገ እንደሚገኝም ጠቁሟል።

ከዚህ በተጨማሪም ሥድስት የጭነት በረራ እንያደረገ መሆኑንም ነው የገለጸው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ያደረጓቸው ንግግሮች እና ያስተላለፏቸው መልዕክቶችን የያዘው 'ከመስከረም እስከ መስከረም' መጽሕፍ ዛሬ ይፋ ይሆናል
*****************

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከመስከረም 24 ቀን 2015 ዓ.ም እስከ መስከረም 24 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ ያደረጓቸው ንግግሮች እና ያስተላለፏቸው መልዕክቶችን የያዘው 'ከመስከረም እስከ መስከረም' መጽሕፍ ዛሬ ይፋ እንደሚሆን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አስታውቋል።
የሼካ ፋጢማ ቢንት ሙባረክ የዐይነ ስውራን አዳሪ ትምህርት ቤት
ኢትዮጵያና ሞሮኮ ትብብራቸውን ለማጠናከር ተስማሙ
*******************

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ በሞሮኮ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሁለትዮሽ ጉዳዮች ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ፉዓድ ያዙሁር የተመራ የልዑካን ቡድን ተቀብለው አነጋግረዋል።

ሁለቱ ወገኖች ኢትዮጵያና ሞሮኮ ያላቸውን የሁለትዮሽ ግንኙነት አጠናክሮ ማስቀጠል በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ምክክር አድርገዋል።

በተለይም ሁለቱ አገራት ቀደም ሲል አብረው ለመስራት ስምምነት የደረሱባቸውን የንግድ፣ የኢንቬስትመንት፣ የፋይናንስ፣ የአየር አገልግሎት እና የትምህርት ዘርፍ የትብብር ስምምነቶች መልሶ በመቃኘት ለማጠናከር ተስማምተዋል።

አገራቱ ከሁለትዮሽ ግንኙነት ባለፈ በአህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮችም በትብብር መስራት በሚችሉባቸው መስኮች ላይ መክረዋል።

ውይይቱን ተከትሎም በሞሮኮ እና በኢትዮጵያ መካከል የጋራ የሚኒስትሮች ኮሚሽን ስብሰባ በቅርቡ ለማካሄድ ከስምምነት መደረሱን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
በሕግ እና በሕግ የበላይነት መከበር የሚያምን ትውልድ ሊኖረን ይገባል - የአማራ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ
***************

የአማራ ክልል ከነበረው የፀጥታ ችግር በመሻሻል አንፃራዊ ሰላም ላይ እንደሚገኝ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የአማራ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ ደሳለኝ ጣሰው ገለጹ።

ክልሉ በቀደሙት ጊዜያት ባልተጠበቀ ያለመረጋጋት ውስጥ ማለፉን አስታውሰው፤ ይህን ለመቅረፍ መንግሥታዊ ተልዕኮውን የሚወጣ አደረጃጀት የማዋቀር ስራ እየተሰራ እንደሚገኝም ነው የተናገሩት።

ለተገኘው ሰላም የመከላከያ ሠራዊት ሚና ላቅ ያለ ነው ብለዋል ኃላፊው።

የአመለካከት እና የአስተሳሰብ አንድነት በመፍጠር የተገኘውን ሰላም ለማስቀጠል የክልሉ የፀጥታ መዋቅር የአቅም ግንባታ ስልጠና እየሰጠ መሆኑን ገልጸዋል።
https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid02Hy1oNPBhvRbPtoj9oSJqzKQDUux3rDEhzp4wXgX3Ft7fHowSRKNREHuJG5QdC1wul
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. መንግሥት ለኢራን ሪፐብሊክ መንግሥትና ህዝብ የኀዘን መልዕክት አስተላለፈ
**********

የኢራን ፕሬዚዳንት ኢብራሂም ራኢሲ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሁሴን አሚር አብዱላሂያንን ጨምሮ የሀገሪቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት በሄሊኮፕተር አደጋ ሕይወታቸው ማለፉን ተከትሎ፣ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. መንግሥት ለኢራን ሪፐብሊክ መንግሥትና ህዝብ የኀዘን መልዕክት አስተላልፏል።

ከፍተኛ ባለስልጣናቱን ያሳፈረች ሄሊኮፕተር ላይ ትናንት አመሻሹን አደጋ መድረሱ ይታወቃል።

አደጋውን ተከትሎም የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ የኀዘን መግለጫቸውን ለኢራን ሪፐብሊክ መንግሥትና ህዝብ አስተላልፈዋል።

በኀዘን በመግለጫው ሕይወታቸው ላለፈው ባለሥልጣናት ቤተሰቦችና ወዳጆች መፅናናትን መመኘታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።
ጣሊያን ከኢትዮጵያ ጋር በተለያዩ ወታደራዊ ጉዳዮች ያላትን ትብብር ማጠናከር እንደምትፈልግ ገለጸች
***********************

በጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የተመራው የኢትዮጵያ መከላከያ የልዑካን ቡድን በጣሊያን ወገን በተደረገለት ግብዣ መሠረት ይፋዊ የስራ ጉብኝት በማድረግ ላይ ይገኛል።

የልዑካን ቡድኑ ጣሊያን ሲገባ በሀገሪቱ ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም አድሚራል ጁሴፔ ካቮ ድራጎን እና በሌሎች ከፍተኛ ወታደራዊ ባለስልጣናት ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል።

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በዛሬው ዕለት ከጣሊያኑ አቻቸው አድሚራል ጁሴፔ ካቮ ድራጎን ጋር በወታደራዊ ትብብሮች ዙሪያ ውጤታማ ውይይት አድርገዋል።

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በውይይቱ ወቅት በሁለቱ ሀገራት መካከል እያደገ የመጣውን ግንኙነት አውስተው፣ ለዚህም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በጣሊያን ያደረጉት ይፋዊ የስራ ጉብኝት እና ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ በኢትዮጵያ ያደረጉት ጉብኝት የሀገራቱን ግንኙነት መጠናከር አመላካች መሆኑን አንስተዋል።

አክለውም፥ አድሚራል ጁሴፔ ካቮ ድራጎን በቅርቡ በኢትዮጵያ ያደረጉት ጉብኝት በዘርፉ ያለውን ትብብር ለማጠናከር ጉልህ አስተዋጽኦ እንዳበረከተም ገልጸዋል።

አድሚራል ጁሴፔ ካቮ ድራጎን በበኩላቸው በሁለቱ ሀገራት መካከል በተለያዩ ወታደራዊ ጉዳዮች ያለውን ትብብር ይበልጥ ለማጠናከር ጣሊያን ያላትን ፍላጎት ገልጸዋል።

አያይዘውም፥ በዘርፉ በተለያዩ ደረጃዎች ያለውን ግንኙነት ማስቀጠል እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተው መናገራቸውን በሮም የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመለክታል።