EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
127K subscribers
16.5K photos
129 videos
79 files
9.98K links
Ethiopian Broadcasting Corporation (EBC)
Download Telegram
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ስትራይድ ኢትዮጵያ ኤክስፖን ጎበኙ
*****************

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ እና ሚኒስትሮች ስትራይድ ኢትዮጵያ ኤክስፖን መጎብኘታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ስትራይድ ኢትዮጵያ 2024 ኤክስፖ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ግንቦት 10 ቀን 2016 ዓ.ም በይፋ መከፈቱ ይታወቃል።

ዓመታዊው ኤክስፖ "ሳይንስ በር ይከፍታል፤ ቴክኖሎጂ ያስተሳስራል፤ ፈጠራ ወደ ፊት ያራምዳል" በሚል መሪ ሀሳብ በሳይንስ ሙዚየም እስከ ግንቦት 18 ቀን 2016 ዓ.ም ለሕዝብ ዕይታ ክፍት ሆኖ ይቆያል።

ትኩረቱን ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ፈጠራና ዲጂታላይዜሽን ላይ ያደረገው ስትራይድ ኢትዮጵያ ኤክስፖ በርካታ የቴክኖሎጂና የፈጠራ ተቋማትን በማሳተፍ ላይ ይገኛል።

በኤክስፖው ላይ የመንግሥትና የግል ተቋማት እንዲሁም ስታርት አፖች የቴክኖሎጂ ፈጠራ ሥራዎችን ለዕይታ አቅርበዋል።https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid024mftynvRRd4Mjn2SqrC9jEohuxaPFLoguaxAHxpnpatNtCkYpErJJyHkys23SwFjl
ፓስፖርት በሀገር ውስጥ እንዲታተም የሚያስችል ሥራ እየተከናወነ ነው - የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት
**********************

በተያዘው ዓመት ፓስፖርት ጠይቀው ይጠባበቁ ከነበሩ ዜጎች መካከል ከ600 ሺህ በላይ ለሚሆኑት መስጠት መቻሉን የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ገልጿል።

የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ከሚሰጣቸው አገልግሎቶች መካከል የፓስፖርት አገልግሎት አንዱ እና ዋንኛው ነው። ይሁን እንጂ የፓስፖርት አሰጣጥን በተመለከተ የሚነሱ ቅሬታዎችን በተደጋጋሚ ይስተዋላል።
ኢቢሲም ይህን ጉዳይ በተመለከተ ተደጋጋሚ ዜናዎች መስራቱ ይታወሳል።

በኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ከሚነሱ ቅሬታዎች አንዱ መጉላላት ነው የሚለው የአዲስ አበባ ነዋሪው አቶ ያሬድ መንግሥቱ፤ እርሱ ራሱም ላላገኘው አገልግሎት ሁለት ቀን በሰልፍ መጉላላቱን ለኢቢሲ ሳይበር ተናግሯል።
https://www.ebc.et/newsdetails.aspx?newsid=6743
ከችግሮች ነፃ የሆነች ኢትዮጵያን እውን ሆና ለማየት ምክክሩ ሊያመልጠን አይገባም ፡-አቶ እውነቱ አለነ
****************

ከችግሮች ነፃ የሆነች ኢትዮጵያን እውን ሆና ለማየት ምክክሩ ሊያመልጠን አይገባም ሲሉ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰላምና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ እውነቱ አለነ ገለጹ።

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን "የኢትዮጵያ ሚዲያ ለኢትዮጵያውያን ውጤታማ ሀገራዊ ምክክር" በሚል መሪ ሃሳብ ከፌዴራል፣ ከክልል፣ ከግል የሚዲያ አመራሮችና ከፍተኛ ባለሙያዎች ጋር እየመከረ ነው።

አቶ እውነቱ፤ የምክክር ኮሚሽኑን በተመለከተ ከገለልተኝነት ጋር ተያይዞ የሚቀርብበት ወቀሳ በሕግ የተፈታ ነው ሲሉም ተናግረዋል።

ኮሚሽኑ ተጠሪነቱ ለምክር ቤቱ ቢሆንም፤ ምክር ቤቱ ስራውን ከማገዝ ያለፈ ጣልቃ አይገባበትም ነው ያሉት።

መገናኛ ብዙኀንም የተሳካ ምክክር እንዲደረግና ልዩነቶች በሰለጠነ መንገድ እንዲፈቱ አቅም ሊሆኑ እንደሚገባም ገልጸዋል።https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid04hxbS8AFHy8nHr5gMtGK3NaiJXkXZP9yDSbacoPfHRbmRgWx22GSabBmg5kkJduRl
በክልሎች እና በከተማ አስተዳደሮች በሚከናወን አጀንዳዎችን የማሰባሰብ ሂደት ተሳታፊ እንዲሆኑ የተለዩ ባለድርሻ አካላት
***********

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በክልሎች እና በከተማ አስተዳደሮች ለሚያከናውነው አጀንዳዎችን የማሰባሰብ ስራ የተለያዩ ባለድርሻ አካላትን ለይቷል፡፡

በኮሚሽኑ የተዘረዘሩት ባለድርሻ አካላት በሚቀርብላቸው ይፋዊ ጥሪ መሰረት በክልሎች እና በከተማ አስተዳደሮች በሚከናወነው አጀንዳዎችን የማሰባሰብ ስራ ተሳታፊ በመሆን፤ በሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ላይ እንዲንፀባረቅላቸው የሚፈልጓቸውን አጀንዳዎች እንደሚያቀርቡ ይጠበቃል ሲል ኮሚሽኑ በማሕበራዊ ትስስር ገፁ ባወጣው መረጃ ገልጿል፡፡
የኢትዮጵያን የዲጂታል ሽግግር ለማሳካት የግሉ ዘርፍ የመሪነት ሚና መወጣት እንዳለበት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ተናገሩ
*****************

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ሚኒስትሮች እና የቴክኖሎጂ ዘርፍ ባለድርሻዎች በተገኙበት የኢትዮጵያ ዲጂታል ኢኮኖሚ ላይ ያተኮረ የፓናል ውይይት በሳይንስ ሙዚየም ተካሂዷል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፤ ዲጂታላይዜሽን አይቀሬ በመሆኑ፣ ኢትዮጵያ ወሳኝ ኢኒሼቲቮችን ቀርፃ መተግበር ጀምራለች ብለዋል።

ለኢትዮጵያ ዲጂታላይዜሽንን ማፋጠን የግድ የሆነባቸው ምክንያቶች አሉ ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ አንደኛው፥ ዲጂታላይዜሽን ዕድገትን የሚያፋጥን በመሆኑ ነው ብለዋል።

ሁለተኛው፥ መንግሥታዊ አገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻልና መልካም አስተዳደርን ለማስፈን እንደሚያግዝ ታምኖ መሆኑን ገልፀዋል።https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid02BJCBnEqHA4JPZAvatSgtSuYM5Lpd1dSefoDZufYqZr2B2wP4MP5zr3EtQsaW6fYwl
ኤፍ ኤም አዲስ 97.1ን በቴሌግራም ቻናላችን የቀጥታ ስርጭት ይከታተሉ
https://t.me/FMADDIS
www.ebc.et
**********
በእጅዎ ባለ ስልክ፣ቢያሻዎ በኮምፒውተርዎ መከታተል እንዲችሉ ዘምኖ እና ምቹ ሆኖ ቀርቦልዎታል፡፡
ከዘመኑ ሚዲያ ተቀዳሚ አማራጭ እየሆነ የመጣው የድረ ገፅ አካል የሆነው www.ebc.et በአዳዲስ ገጽታዎች እና አቀራረብ ወደ እናንተ መድረሱን ይቀጥላል፡፡
"በአየር መንገዱ ላይ የተከሰተ የእሳት አደጋ የለም፤ አካባቢው ላይ ተከስቶ የነበረው አደጋ ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር ውሏል”፦ የአዲስ አበባ ከተማ እሳት እና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን
********************

በአዲስ አበባ ቦሌ ኤርፖርት አካባቢ ዛሬ ከቀኑ 9፡41 ላይ ተከስቶ የነበረው የእሳት አደጋ ሙሉ ለሙሉ በቁጥጥር ስር መዋሉን እና አደጋው ከአየር መንገዱ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት እንደሌለው የአዲስ አበባ እሳት እና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።
አደጋው ከአየር መንገድ ግቢውም ሆነ ከተርሚናሉ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት የለውም ያሉት አቶ ንጋቱ በተለያዩ ማህበራዊ ትስስር ገፆች እና ሚዲያዎች የእሳት አደጋው በአየር መንገዱ ውስጥ እንደተከሰተ አድርገው የሚያሰራጩት ዘገባ ፍፁም ከእውነት የራቀ መሆኑን አረጋግጠዋል።
አደጋው በአንድ የድንገተኛ እሳት አደጋ ባለሞያ ላይ ቀላል ጉዳት ማድረሱንም አቶ ንጋቱ ጠቁመዋል።
የእሳት አደጋው በኮሚሽኑ ባለሞያዎች፣ በአየር መንገዱ የእሳት አደጋ ሰራተኞች እና ሌሎች የፀጥታ ኃይሎች ባደረጉት ርብርብ ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር መዋሉን የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሞያ አቶ ንጋቱ ማሞ በተለይ ለኢቢሲ ሳይበር ገልፀዋል።
የእሳት አደጋው መነሻ ምክንያት እና ያስከተለው የጉዳት መጠን የማጣራት ስራው ሲጠናቀቅ ለህብረተሰቡ ይፋ እንደሚደረግም ባለሞያው ገልፀዋል።
በሜሮን ንብረት
https://www.facebook.com/permalink.php?story_fbid=pfbid0wN9WyTuiJwEaetkr5Cc9AtSJkvk5rYRnBNKXcLWVxSRmiGBGk7GCWjhrun3xjgZ4l&id=61550945701729