EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
127K subscribers
16.5K photos
129 videos
79 files
9.98K links
Ethiopian Broadcasting Corporation (EBC)
Download Telegram
ጣሊያን ከኢትዮጵያ ጋር በተለያዩ ወታደራዊ ጉዳዮች ያላትን ትብብር ማጠናከር እንደምትፈልግ ገለጸች
***********************

በጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የተመራው የኢትዮጵያ መከላከያ የልዑካን ቡድን በጣሊያን ወገን በተደረገለት ግብዣ መሠረት ይፋዊ የስራ ጉብኝት በማድረግ ላይ ይገኛል።

የልዑካን ቡድኑ ጣሊያን ሲገባ በሀገሪቱ ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም አድሚራል ጁሴፔ ካቮ ድራጎን እና በሌሎች ከፍተኛ ወታደራዊ ባለስልጣናት ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል።

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በዛሬው ዕለት ከጣሊያኑ አቻቸው አድሚራል ጁሴፔ ካቮ ድራጎን ጋር በወታደራዊ ትብብሮች ዙሪያ ውጤታማ ውይይት አድርገዋል።

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በውይይቱ ወቅት በሁለቱ ሀገራት መካከል እያደገ የመጣውን ግንኙነት አውስተው፣ ለዚህም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በጣሊያን ያደረጉት ይፋዊ የስራ ጉብኝት እና ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ በኢትዮጵያ ያደረጉት ጉብኝት የሀገራቱን ግንኙነት መጠናከር አመላካች መሆኑን አንስተዋል።

አክለውም፥ አድሚራል ጁሴፔ ካቮ ድራጎን በቅርቡ በኢትዮጵያ ያደረጉት ጉብኝት በዘርፉ ያለውን ትብብር ለማጠናከር ጉልህ አስተዋጽኦ እንዳበረከተም ገልጸዋል።

አድሚራል ጁሴፔ ካቮ ድራጎን በበኩላቸው በሁለቱ ሀገራት መካከል በተለያዩ ወታደራዊ ጉዳዮች ያለውን ትብብር ይበልጥ ለማጠናከር ጣሊያን ያላትን ፍላጎት ገልጸዋል።

አያይዘውም፥ በዘርፉ በተለያዩ ደረጃዎች ያለውን ግንኙነት ማስቀጠል እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተው መናገራቸውን በሮም የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመለክታል።
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ንግግሮችና መልዕክቶችን የያዘ መጽሐፍ ለንባብ በቃ
***********************

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ንግግሮችና መልዕክቶችን የያዘና "ከመስከረም እስከ መስከረም" የተሰኘ መጽሐፍ ለንባብ በቃ።

በመጽሐፉ ላይ የዳሰሳ ውይይት በወዳጅነት ፓርክ ተካሂዷል።

በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ፕሬስ ሴክሪታሪያት የተዘጋጀው ይህ መጽሐፍ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከመስከረም 24 ቀን 2015 ዓ.ም እስከ መስከረም 24 ቀን 2016 ዓ.ም በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎችና ዓለም አቀፍ ጉባኤዎች ላይ ያደረጓቸው 91 ንግግሮችና መልዕክቶችን ያያዘ ነው።

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ፕሬስ ሴክሪታሪያት ኃላፊ ቢልለኔ ስዩም በውይይት መድረኩ ላይ ባደረጉት ንግግር፥ መጽሐፉ የጠቅላይ ሚኒስትሩን ንግግሮችና መልዕክቶች የያዘ 6ኛው መድብል መሆኑን ገልጸዋል።

የመሪ ታሪክ የሀገር ታሪክ አካል መሆኑን ጠቅሰው፤ ከዚህ አኳያ መጽሐፉ ለታሪክ አጥኚዎች፣ ለፖሊሲ አውጭዎችና ለፖለቲካ ተመራማሪዎች ግብዓት እንደሚሆን ተናግረዋል።

በመድረኩ ተማሪዎች ከመጽሐፉ የተመረጡ ገጾችን እንደ ውይይት መነሻ ሃሳብ በንባብ አቅርበዋል።

"ከመስከረም እስከ መስከረም" መጽሐፍ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአማርኛ፣ በአፋን ኦሮሞ በእንግሊዝኛ እና በአረቢኛ ቋንቋዎች ያስተላላፏቸውን ንግግሮችና መልዕክቶች ይዟል።

በሮዛ መኮንን
1 ሺህ 175 ኢትዮጵያውያን ከሳውዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ
****************

በዛሬው ዕለት በ3 ዙር በረራ በተከናወነ በሳውዲ አረቢያ በችግር ውስጥ የነበሩ ዜጎችን የመመለስ ስራ፣ 1 ሺህ 175 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገራቸው መመለስ ተችሏል።

ወደ ሀገር የተመለሱት 1 ሺህ 175 ዜጎች ሁሉም ወንዶች ሲሆኑ፤ ከተመላሾች መካከል 18 ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊ ህጻናት ይገኙበታል።

ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ከቤተሰብ ጋር የመቀላቀል ስራ እየተሰራ መሆኑን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

ከሚያዚያ 04 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እየተከናወነ በሚገኘው ዜጎችን ወደ ሀገር የመመለስ ስራ፣ እስካሁን ከ27 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያንን መመለስ መቻሉ ተገልጿል።
ሽንታችን ስለጤናችን ምን ይነግረናል?
*************

ሽንት በምንመገበው ምግብ፣ በምንወሰደው መድኃኒት እንዲሁም በምንጠጣው የውኃ መጠን ምክንያት ቀለሙ፣ ጠረኑ እንዲሁም ዓይነቱ ይቀያየራል።

ሽንት ሰውነታችን በፈሳሽ መልክ ቆሻሻን የሚያስወግድበት አንዱ መንገድ ሲሆን በዋናነት ውኃ፣ ጨው፣ ኤሌክትሮላይቶች እንደ ፖታሺየም እና ፎስፈረስ፣ ዩሪያ እና ዩሪክ አሲድ የሚባሉ ኬሚካሎች በውስጡ ይዞ ይገኛል።

እነዚህም ኩላሊት መርዛማ ንጥረ ነገሮችን እና ሌሎች መጥፎ ነገሮችን ከደም ውስጥ ሲያጣራ የሚከሰቱ ሲሆኑ፤ መድኃኒት፣ የተለያዩ ዓይነት ምግቦች እና ሕመሞች የሚወገደው የሽንት ዓይነት ላይ ለውጥ እንዲኖረው ያደርጋሉ።

ጤናችን ያለበትን ሁኔታ የሚነግሩን የቀለም ዓይነቶች እንዳሉ ስንቶቻችን እናውቃለን?

ጤናማ የሽንት ቀለም ምን ዓይነት ነው?

ሽንት ፈዛዛ ቢጫ ወይንም ወርቃማ ቀለም ሲኖረው ሰውነት በቂ ውኃ አግኝቷል፤ ጤናማ ነው እንላለን።

ሽንት ምንም ዓይነት ቀለም ከሌለው (ውኃ ቀለም) ከሆነ ደግሞ ሰውነታችን በብዛት ውኃ እንዳገኘ እና እንዳበዛን ያመላክታል።

ከልክ በላይ ውኃ ማብዛት በሰውነታችን ወስጥ የኤሌክትሮላይት መዛባት ያስከትላል፤ በመሆኑም የምንወስደውን የውኃ መጠን በመቀነስ በቀን ውስጥ ከ6 እስከ 8 ብርጭቆ ውኃ እንድንጠጣ ይመከራል።

ቀላ ያለ ሮዝ ቀለም ለኩላሊት እና ለተለያዩ በሽታዎች መጋለጥን ሊያመላክት ይችላል።https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid02u2BPuvN94L3mR5QgzsH2onD5wwzJvsGMEBQbxBHJMgw26QLHHPo6JRJvhqJuZrfsl
የግንቦት 13 ቀን 2016 የውጭ ምንዛሬ ዋጋ
ለመጀመሪያው ዙር የሐጅ ተጓዦች በቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሽኝት ተደረገ
***************

ለዘንድሮው ለ1 ሺህ 445ኛው የሐጅ ሥነ-ሥርዓት የመጀመሪያ ዙር ተጓዦች በቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሽኝት ተደረገ።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እንዲሁም የኢትዮጵያ አየር መንገድ አመራርና ሰራተኞች በተገኙበት ሽኝቱ መደረጉ ታውቋል።

የጠቅላይ ምክር ቤቱ ዋና ጸሃፊ ሸኽ ሃሚድ ሙሳ፤ በሂደቱ የምዝገባ፣ የቪዛ፣ የምክርና ተያያዥ አገልግሎቶች በተቀላጠፈ መልኩ መሰጠታቸውን ገልጸዋል።

ለሐጅ ሥነ-ሥርዓቱ ከጉዞ እስከ መመለሻ ድረስ በቴክኖሎጂ የተደገፈ አገልግሎት እየተሰጠ መሆኑንም ጠቅሰዋል።

በባለፈው ዓመት 11 ሺህ ሑጃጆች መጓዛቸውን አስታውሰው ዘንድሮ ደግሞ ከ12 ሺህ በላይ ተጓዦች ወደ ስፍራው የሚያቀኑ መሆኑን ገልጸዋል።

በዚህም መሰረት በዛሬው እለት የመጀመሪያው ዙር የሑጃጆች የሽኝት ሥነ-ሥርዓት መደረጉን ተናግረዋል።https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid0SoktYNCqtamPpThxFMcJ7TsJKct81qZNPfCzy9qPigBBU8Srns1qxUNMvhZWsVzdl
ባለፉት ጥቂት አመታት ዋናውን የዝናብ ወቅት ምርት ሳናስተጓጉል የበጋ ስንዴ ልማት ጥረታችንን ለማስፋፋት ችለናል። የዛሬው ምልከታ የስራዎችን ቀጣይነት የተመለከትንበት ነበር። ግብርና ጠንካራ ኢንቨስትመንት ይፈልጋል። በሰብል የምንሸፍነው የመሬታችን ይዞታም ቀስ በቀስ በመጨመር ላይ ይገኛል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid02waGXZW9S5uzfBsB9bVnZ2jmf2YfHTCnKRLki48aCCzmxDiKuHP1rP4vJdcYW11isl
የኢቢሲን አዳዲስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን በዋትስአፕ አማራጭ
Follow EBC on our new WhatsApp channel
https://whatsapp.com/channel/0029VaVefI79xVJoMGtunX2T
Live stream finished (2 days)
የዕለቱ የውጭ ምንዛሬ ዋጋ
Live stream finished (16 hours)
የሰላም ሚኒስቴር በሰሜን አሜሪካ ከሚገኘው የስተርሊንግ ፋውንዴሽን አመራሮች ጋር በሰላም ግንባታ ጉዳዮች ላይ ውይይት አካሄደ
************************

የሰላም ሚኒስቴር የስራ ኃላፊዎች ቡድን በሰሜን አሜሪካ ዩታሀ ግዛት ከሚገኘው የስተርሊንግ ፋውንዴሽን መሪዎች ጋር በሰላም ግንባታ ዙሪያ በትብብር መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገዋል።

በኢትዮጵያ በተለያዩ የሰላም ግንባታ ተግባራት ድጋፍ እያደረገ ከሚገኘው ስተርሊንግ ፋውንዴሽን አመራሮች ጋር ድጋፉ ተጠናክሮ በሚቀጥልበት መንገዶች ዙሪያ ለመወያየት በሰላም ሚኒስትሩ አቶ ብናልፍ አንዷለም የሚመራው ቡድን በግዛቷ መዲና ሳልት ሌክ ከተማ ጉብኝት በማካሄድ ላይ ይገኛል።

ቡድኑ በግዛቲቱ የሰብዓዊ አገልግሎት መስጫ ማዕከላት፣ የተለያዩ ሀይማኖቶች በመከባበርና በሰላም አብረው በአካባቢው ሰላም፣ አብሮነትና መከባበር ለማምጣት የሚያከናውኑት ተግባርና የተገኘውን ውጤት ተዟዙረው ጎብኝተዋል።https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid02jwneEJBYA5vqiu3qzjjvVNNNYjaZ37D7kPFsmyK1p3L5Eg6M81xNvY1NajVcbxbZl