EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
125K subscribers
15.7K photos
112 videos
79 files
9.81K links
Ethiopian Broadcasting Corporation (EBC)
Download Telegram
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የኮሪደር ልማት ስራ ሂደት ላይ ከአዲስ አበባ አስተዳደር አመራሮች ጋር ተወያዩ
******************

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የኮሪደር ልማት ስራ ሂደት ምን ደረጃ ላይ እንዳለ ከአዲስ አበባ አስተዳደር አመራሮች እና የኮሪደር ልማት ስራ መሪዎች ጋር ተወያዩ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማሕበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት፤ ከአንድ ወር በፊት የኮሪደር ልማት ስራ ሂደት ምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ አጠቃላይ ግምገማ ማድረጋቸውን ገልጸዋል።

ከአዲስ አበባ አስተዳደር አመራሮች እና የኮሪደር ልማት ስራ መሪዎች ጋር በድጋሚ በመገናኘት በስራዎቹ ርምጃ ዙሪያ ጥልቀት ያለው ውይይት ማድረጋቸውንም ጠቅሰዋል።

እነኚህ ስራዎቻችን የግንባታ ብቻ ጉዳዮች አይደሉም፤ ይልቁንም ከተማችንን ወደ ላቀ ምቹ፣ ንቁ እና ዘላቂ የመኖሪያ ከባቢ የመለወጥ ጥረቶች ናቸው ሲሉም አክለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው።

ሥነ-ውበትን በማሳደግ፣ አረንጓዴነትን በማስፋት ብሎም መሰረተ ልማትን በማሻሻል የህዝባችንን ጤና መጠበቅ ብቻ ሳይሆን የስራ ዕድሎችንም እየፈጠርን ነው ብለዋል።

በጋራ እነዚህ ጥረቶቻችን የአዲስ አበባን አጠቃላይ ይዞታ በማላቅ እውነትም ለሁሉም ነዋሪዎቿ ፍላጎቶች የተመቸች ያደርጓታል ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ።
ሰሙነ ሕማማት ምንድን ነው? እንዴትስ ይታሰባል?
****************

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን ምዕመናን ከሚጾሙት ሰባቱ የአዋጅ አጽዋማት መካከል ዐቢይ ጾም አንዱ ነው፡፡ "ዐቢይ" የሚለው ቃል ትልቅ የሚል ትርጉም ያለው ሲሆን፣ ይህ ጾምም በሁለት ምክንያቶች ትልቅ ጾም እንደሆነ የቤተ-ክርስቲያኒቱ ሊቃውንት ይናገራሉ፡፡ አንደኛው ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱ ጾሞ አርአያ በመሆን ያበረከተው ጾም መሆኑ ሲሆን፣ ሌላው ደግሞ ጾሙ ለረጅም ጊዜ ማለትም ሐምሳ አምስት ቀናት የሚጾም ረጅም ጾም መሆኑ ትልቅ ያሰኘዋል፡፡

ጾሙ የሁዳዴ ጾምም ይባላል "ሁዳድ" ሰፊ የመንግሥት እርሻ ወይም ማንኛውም በመንግሥት ትዕዛዝ በብዙ ሕዝብ የሚታረስ እርሻ ነው። ጾሙም ጾመ ሁዳዴ የተባለው ትልቅ እና ረጅም ጊዜ የሚቆይ እንዲሁም ሰውን ለማዳን ሰው በሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ አርአያነት የሚጾም ስለሆነ ነው።

የዐቢይ ጾም 8 ሳምንታት ያሉት ሲሆን፣ በስምንቱም ሳምንታት ያሉ እሁዶች የየራሳቸው ስያሜዎች አሏቸው። የመጀመሪያው እሑድ "ዘወረደ" የሚባል ሲሆን፣ አምላክ ከሰማይ መውረዱን፣ ሰው መሆኑን እና የሰው ልጆችን ለማዳን መከራ መቀበሉን ያወሳል፡፡ ሁለተኛው እሑድ "ቅድስት" ይባላል፤ ስለ ዕለተ ሰንበት ቅድስና ስለሚያወሳ ነው፡፡ የሦስተኛው እሑድ "ምኲራብ" ይባላል፤ በዚህ ሰንበት ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ምኲራብ ገብቶ "ቤቴ የፀሎት ቤት ይባላል እናንተ ግን የወንበዴዎች ዋሻ አደረጋችሁት" በማለት በምኩራብ ውስጥ ንግድ ያጧጡፉ የነበሩትን ያባረረበት ነው፡፡
https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid0Dza4NdKgpoGpBH77cPwD2iQ3z4tbYX7A8HrVe2Yao6vmwp9yRYtxp3cAhf5JugCil
በተሰጠን አቅጣጫ መሰረት የኮሪደር ልማት ስራዎቻችንን በአጭር ጊዜ ውስጥ እናጠናቅቃለን፡- ከንቲባ አዳነች አቤቤ
********************

በተሰጠን አቅጣጫ መሰረት የኮሪደር ልማት ስራዎቻችንን ለህዝባችን በገባነው ቃል መሰረት በአጭር ጊዜ ውስጥ እናጠናቅቃለን ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።

ከንቲባዋ በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት፤ "ዛሬ ከጠቅላይ ሚኒስትራችን ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ጋር የኮሪደር ልማት ስራችን ያለበት ደረጃ ላይ ጥልቅ ግምገማ አካሂደን፤ አጠቃላይ ስራዎቻችን ያሉበት አፈጻጸም ውጤታማ መሆናቸውን አይተናል" ብለዋል።

በከተማዋ የገጠመውን ጊዜያዊ የትራፊክ መጨናነቅ ችግር በዘላቂነት ለመፍታት፤ ከተማዋን የሚመጥን የመንገድ መሰረተ ልማት በመገንባት ላይ መሆኑን ገልጸዋል።

ከንቲባዋ በመልዕክታቸው፤ "ህዝባችን ላሳየው ትዕግስት እና ትብብር በከተማ አስተዳደሩ ስም ላመሰግን እወዳለሁ" ብለዋል።
የኦሮሚያ ሕብረት ስራ ባንክ "ማስተር ካርድ" እና "ኮሚኒቲ ፓስ" የተሰኙ የዲጂታል አገልግሎቶችን በስራ ላይ አዋለ
*********************

የኦሮሚያ ሕብረት ስራ ባንክ "ማስተር ካርድ" እና "ኮሚኒቲ ፓስ" የተሰኙ የዲጂታል አገልግሎቶችን በዛሬው ዕለት በስራ ላይ አውሏል።

ባንኩ አገልግሎቶቹን ከማስተር ካርድ ጋር በመተባበር ነው በስራ ላይ እንዲውሉ ያደረገው።

"ማስተር ካርድ" ለውጭ ሀገር ተጓዦች የታለመ የቅድመ ክፍያ አገልግሎት ሲሆን፤ ተጓዦቹ በሚሄዱበት ሀገር የሚያስፈልጋቸውን ገንዘብ በብር በመክፈል በውጭ ሀገር ተሰልቶ የሚሞላላቸው ይሆናል።
ከዚህም ባሻገር አገልግሎቱ ተጓዦቹ በሄዱበት ሀገር ሁሉ መጠቀም የሚያስችል ነው ተብሏል።

በተጨማሪም ባንኩ በ"ኮሚኒቲ ፓስ" የቀረበ "ኮፕ ፋርም ፓስ" የተሰኘ የዲጂታል አገልግሎት በስራ ላይ አውሏል።

"ፋርም ፓስ" የግብርና ምርት ሂደትን የማሳለጥ እና የአርብቶ አደሮች እና ሕብረት ስራ ማህበራትን ትስስር ያጠናክራል ተብሏል።

በአሚር ጌቱ
ለ2016/17 የምርት ዘመን ከ12 ሚሊየን ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ ከውጭ መጓጓዙ ተገለፀ
***************

ለ2016/17 የምርት ዘመን ከተገዛው የአፈር ማዳበሪያ ውስጥ እስከአሁን ከ12 ሚሊየን ኩንታል በላይ ከውጭ ተጓጉዞ ጂቡቲ ወደብ መድረሱን የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን (ኢግሥኮ) አስታወቀ።

ወደብ ከደረሰው ማዳበሪያ 11 ሚሊየን 79 ሺህ 21 ኩንታል ወደ ሀገር ውስጥ ተጓጉዞ በመሠረታዊ የኅብረት ሥራ ማኅበራት አማካኝነት ለአርሶ አደሮች እየቀረበ መሆኑም ተጠቁሟል።

ትላንት ሚያዝያ 22 ቀን 2016 ዓ.ም 636 ሺህ 600 ኩንታል ኤን ፒ ኤስ ቦሮን የጫነች መርከብ ጂቡቲ ወደብ መድረሷ ተጠቅሷል፡፡

በተመሳሳይ ከ11 ቀናት በኋላ 543 ሺህ ኩንታል ተጨማሪ ኤን ፒ ኤስ ቦሮን የአፈር ማዳበሪያ ወደብ ይደርሳል ተብሎ እንደሚጠበቅም ከኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ክልሉ ከአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ ተጠቃሚነቱን ለማሳደግ በመስራት ላይ ይገኛል - አቶ ጥላሁን ከበደ
*************

በኢትዮጵያ በአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ የገቢ ምርትን 85 በመቶ በአገር ውስጥ ምርት ለመተካት ጥረት በመደረግ ላይ መሆኑ ይታወቀል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥትም በክልሉ ፈጣን ዕድገት በማስመዘገብ ህዝቡን ተጠቃሚ ለማድረግ ትኩረት ከሰጣቸው የልማት ዘርፎች አንዱ የኢንዱስትሪው ዘርፍ ነው።

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ክልሉ ለአምራች ኢንዱስትሪ ልማት እምቅ አቅም ያለው መሆኑን ጠቅሰው፤ በክልሉ ያለውን የመልማት ፀጋ በመለየትና አሟጦ በመጠቀም ከዘርፉ የሚገኘውን ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ማሳደግ አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል።
https://ebc.et/newsdetails.aspx?newsid=6586
ሰሙነ ሕማማት
የሠራተኛው ትግል ከኢንዱስትሪ አብዮት እስከ ሰው ሠራሽ አስተውሎት ስጋት
*************

ኢንዱስትሪ እየተስፋፋ የነበረበት 19ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ሠራተኛው በርካታ የመብት ጥያቄዎችን ያነሳ የነበረበት ጊዜ ነበር፡፡ ከነዚህ ጥያቄዎች መካከልም የተመጣጣኝ ከፍያ፣ የሥራ ሰዓት፣ የመደራጀት እና ሌሎች ይገኛሉ፡፡

በሥራ ላይ በሚደርስ አደጋ ሕይወትን ማጣት፣ አካል መጉደል፣ ለዘላቂ የጤና ችግር መዳረግ እና ሌሎች ለሰው ልጆች ምቹ ያልሆኑ ሁኔታዎች ጥያቄው መሰረታዊ እንዲሆን ማድረጋቸውን የሠራተኛውን ትግል የሚያወሱ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡

ሠራተኞች ትግላቸውን ቀጥለው ምቹ ባልሆነ የሥራ አካባቢ ከ10 እስከ 16 ሰዓታት የነበረው የሥራ ሰዓት 8 ሰዓት ብቻ ሆኖ የሙሉ ቀን ደመወዝ እንዲከፈላቸው መጠየቅ ቢጀምሩም፣ የዘመኑ አሠሪዎቻቸው ግን ለጥያቄው ምላሽ መስጠት አልፈለጉም ነበር፡፡

ይህ የከበርቴዎች ለሠራተኛው ጥያቄ ጆሮ ዳባ ልበስ ማለት ግን ሠራተኞች የበለጠ ተደራጅተው ጥያቄያቸውን እንዲገፉበት አደረጋቸው:: ነገር ግን ቀጣሪዎቹ በማይመች አካባቢ እና የአየር ሁኔታ ውስጥ በቀን ለረዥም ሰዓታት በማሠራት ከፍተኛ ትርፍ ማጋበስ የለመዱ በመሆናቸው በቀላሉ ጥያቄዎቹን ለመመለስ ፈቃደኛ አልሆኑም፡፡

በሠራተኛው እንቅስቃሴ የተበሳጩት እና መጪው ሁኔታ ያሳሰባቸው አሠሪዎች “አድማ ቀስቅሳችኋል፤ ምርታማ መሆን አልቻላችሁም፤ እኛ በምንፈልጋችሁ ሁኔታ እየሠራችሁ ስላልሆነ አንፈልጋችሁም” በማለት በርካታ ሠራተኞችን ከሥራ ማሰናበት ጀመሩ::
https://ebc.et/newsdetails.aspx?newsid=6587