EBC Ethics Department
418 subscribers
203 photos
11 videos
13 files
23 links
Integrity is our currency to fight corruption
Download Telegram
ሰንደቅ ዓላማን በተመለከተ የተከለከሉ ተግባራት ምንድን ናቸው?
******

በኢፌዴሪ ሕገ-መንግሥት አንቀፅ 3 ከሰፈረው የሰንደቅ ዓላማ ድንጋጌ እንዲሁም በሰንደቅ ዓላማ ማሻሻያ አዋጅ ቁጥር 863/2006 መሠረት ሰንደቅ ዓላማን በተመለከተ የተከለከሉ ተግባራት፦

👉🏽 ሰንደቅ ዓላማው በወጣበት ሰንደቅ (ምሰሶ ወይም ፖል) ላይ ማስታወቂያ መለጠፍ፣ ያለአግባብ ሌሎች ሰንደቅ ዓላማዎች ወይም አርማዎችን ጨምሮ ማውለብለብ ወይም መገልገል

👉🏽 ሰንደቅ ዓላማው ላይ ቃላትን መጻፍ፣ ሌሎች ምልክቶች ወይም አርማዎችን መጠቀም ወይም መገልገል

👉🏽 ሰንደቅ ዓላማውን በአዋጅ በተደነገገው መሠረት የተቀመጡ አርማውን ሳያካትቱ መጠቀም

👉🏽 ሰንደቅ ዓላማው በሚሰቀልበት እና በሚወርድበት ጊዜ ተገቢውን ክብር አለመስጠት

👉🏽 በስብሰባ ወይም በማናቸውም መሰል ክንውኖች ሰንደቅ ዓላማውን የጠረጴዛ ሽፋን አድርጎ መጠቀም

👉🏽 ሕዝብ በተሰበሰበበት ቦታ ሰንደቅ ዓላማውን በጽሑፍ ወይም በቃላት ወይም በድርጊት ወይም በሌላ በማናቸውም አኳኋን ማዋረድ ወይም ጉዳት እንዲደርስበት ማድረግ

👉🏽 የሰንደቅ ዓላማውን ቀለማት ቅደም ተከተል እንዲሁም የብሔራዊ አርማውን መጠን ሳይጠብቁ ማዘጋጀት እና መገልገል

👉🏽 በሰንደቅ ዓላማው አዋጅ ከተጠቀሰው የማውረጃ ጊዜ በላይ (ከፀሐይ መጥለቅ በኋላ) ተሰቅሎ እንዲቆይ ማድረግ እና በሰዓቱ አለመስቀል

👉🏽 ሰንደቅ ዓላማውን የሕንፃ ወይም የሌሎች ቁሳቁሶች መሸፈኛ ማድረግ

👉🏽 ሰንደቅ ዓላማውን በማንኛውም ንግድ ማስታወቂያነት መጠቀም ዋና ዋና የተከለከሉ ተግባራት ናቸው።
👍1
ግብረ-ገብነት ምንድን ነው?
***************
 ግብረ-ገብ ማለት እያንዳንዱ ሰው ከሌሎች ሰዎችና ከራሱ ህይወትና እድገት፣ መብትና ነጻነት፣ ጥቅምና ፍላጎት፣ ክብርና ዓላማ አንፃር ማድረግ የሚገባውን ወይም ማድረግ የማይገባውን ድርጊት፣ መሆን የሚገባው እና የማይገባው ፀባይ የሚገልጽባቸው፣ የሚደነግግባቸው ወይም ብይን የሚሰጥባቸው ፅንሰ ሃሳቦች ናቸው፡፡
 ግብረ-ገብ እያንዳንዱ ሰው “እኔ ለሌሎች ሰዎች መስጠት የሚኖርብኝ እሴት ምን መሆን አለበት?” ብሎ ራሱን እንዲጠይቅ የሚያደርግ ነው፡፡
 በመልካም ግብረ-ገብ የታነፀ ሰራተኛ ወደ ስራው ሲሄድ ዛሬ አገልግሎት ፈልገው ለሚመጡ አገልግሎት ፈላጊዎች በምን ግብረ-ገባዊ እሴት በተሞላው አገልግሎት ማስተናገድ አለብኝ ብሎ የሚያስብ ነው፡፡
 አገልጋይነቱ በተገልጋዮች ፊት ዘንድ እርካታ ፈጥሮ ከአገልግሎት ፈላጊዎቹ የሚያገኘው ምስጋና ለነገ ማንነቱ ስንቅ ይሆነዋል፡፡
 የሰው ልጅ ሁለት ውጫዊ እና ውስጣዊ ማንነት ይኖረዋል፡፡ ውጫዊ ማንነቱ በአብዛኛው የሚገለፀው በውጫዊ ተክለ ሰውነቱ፣ በአለባበሱ፣ በአነጋገሩ፣ በአኗኗሩ፣ በፀባዩ፣ በሥራውና በመሳሰሉት ተግባራት ነው፡፡
 ውስጣዊ ማንነቱ ባህሪውን፣ እውቀቱን፣ አስተሳሰቡን፣ እምነቱን፣ ምኞቱን፣ ስሜቱንና እሴቱን አጠቃሎ ይይዛል፡፡ ይህ ማንነት ግን ለእርሱና በእርሱ ብቻ የሚኖር ነው፡፡ አንዱ የሌላውን ውስጣዊ ማንነት መረዳት አስቸጋሪ ነው፡፡
 ሰው ህይወቱን የሚመራው በአብዛኛው በውስጣዊ ማንነቱ ነው፡፡ ከዚህ አኳያ በመንግስት ተቋማት ውስጥ ያሉ ሰራተኞች ማንነትም እንዲሁ መንታ ነው፡፡
 አንዳንዶች አለቆቻቸውን ሲያዩ ታታሪ የሚመስሉ በውስጣቸው ግን አልማጭ የሆኑ ሰራተኞች እንደሚኖሩ ይታመናል፡፡ እንደነዚህ አይነት ሰዎች ደግሞ ውስጣዊ ማንነታቸው በግልጽ ስለማይታወቅ የሚያደርሱትም ጉዳት ከፍተኛ ይሆናል፡፡
👉🏽ለዚህ ነው ውስጣዊ ህይወትን በግብረ-ገብ ማነፅ፣ በስነ-ምግባር መፈተሽና ማፅዳት የሚያስፈልገው፡፡
ሙስና መኖሩን የሚያመላክቱ ዋናዋና ማሳያዎች
**********************
ሙስና በተለያዩ መንገዶች ሊገለፅ ይችላል ፡፡ ሙስና በባህሪው ተለዋዋጭ ውስብስብ
ቢሆንም ሙስና መኖሩን የሚያመላክቱ ዋናዋና ማሳያዎች የሚከተሉት ናቸው:-
1. የግልፀኝነት ጉድለት
ግልፅ ያልሆነ የውሳኔ አሰጣጥ ሂደቶች ሲኖሩ
መረጃዎችን ለህዝብ ወይም ለባለድርሻ ተደራሽ ያለማድረግ ችግሮች ሲበራከቱ
2 የጥቅም ግጭት ሲፈጠር
የግል ፍላጎትን ከሙያ ፍላጎቶች የሚጋጭበት ሁኔታዎች ሲፈጠሩ
3 ስልጣንን አለአግባብ መጠቀም
ውሳኔ ሰጪ አካላት ለግል ጥቅማቸው ስልጣንን አለአግባብ ሲጠቀሙ ሙስና ሊከሰት ይችላል፡፡
4 መመሪያዎችን ችላ ማለት
ከመመሪያ ውጪ የሚሰሩ ስራዎች ሲበራከቱ
5 ከመጠን ያለፈ ዋጋ ወይም ያልተለመደ ቅናሾች
በድንገት የዋጋ ጭማሪ ወይም ከገበያ ዋጋ ጋር የማይጣጣሙ ግዢዎች ሲፈፀሙ፡፡
6 የሙስና ተጠቋሚዎችን ቅሬታ ችላ ማለት
ሪፖርት የተደረጉ ስጋቶችን ችላ ማለትና የሙስና ጠቋሚዎችን ከለላ ችላ ማለት፡፡
7 የተጠያቂነት ማነስ
ደካማ የተጠያቂነት ስርዓት ሲኖር
8 የክትትል ማነስ
ደካማ የውስጥና የውጪ ክትትልና ቁጥጥር ሲኖር
የሙስና ምልክቶችን ለይቶ በማወቅና ምልክቶችን በመቅረፍ መልካም አስተዳደር በማስፈን የሙስና
መከላከል ሚናችንን እንወጣ፡፡
Ethics Department
2👍1
Registrant Form ..doc
37 KB
ይህ የአስመዘጋቢ መረጃ ተሞልቶ በዚህ ቴሌግራም ይላክ ፡፡
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ዲጂታል የሀብት ምዝገባ ሲስተም , Video
Forwarded from TG Goshu
EBC ASSET REGISTRATION SYSTEM በሚለው ቴሌግራም ቻናል በዚህ ሊንክ https://t.me/+CfNQmFU-eDo1NjRk
😁1
1