Ethiopian Association of Civil Engineers
4.99K subscribers
393 photos
14 videos
46 files
226 links
Channel for Ethiopian Association of Civil Engineers members to updated current construction issues, information and opportunities
Download Telegram
In celebration of World Engineering Day on March 4th #WorldEngDay2021, WFEO invites you to submit a video before Feb. 12th, to showcase contributions that #YoungEngineers are making towards a more #sustainable, #resilient, and #inclusive world

More info https://bit.ly/3iyYliL

#Agenda2030 #GlobalGoals #SDGs #ClimateAction #Engineering #WomenInSTEM
የሀዘን መግለጫ
የማህበራችን አባል የሆኑት ፕሮፌሰር ንጉሴ ተበጀ (Fellow Engineer) ከዚህ አለም በሞት መለየት ማህበሩ የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን እየገለጸን
በማህበራችን ከ1990 ዓ.ም ጀምሮ ማህበሩን በመመስረትና ከመደበኛ አባልነት እስከ የስራ አስፈፃሚ ቦርድ በመሆኑ ያገለገሉ ሲሆን ህይወታቸው እስካለፈበት ቀን ድረስ ማህበሩን ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ በዕውቀትና በገንዘብ ሲደግፉ የቆዩ ሲሆን የኢትዮጵያ ሲቪል መሐንዲሶች ማህበርም የተሰማውን ልባዊ ሐዘን እየገለፀ ነገ በቀን 14/05/2013 ዓ.ም ላይ በቅዱስ ዮሴፍ ቤተክርስትያን ከቀኑ 6፡00 በሚፈፀመው የቀብር ስነስርዓት ላይ በሚደረገው የሽኝት መርሃ ግብር ላይ የማህበሩ አባላት በመገኘት ሐዘናችሁን እንድትገልፁ እናሳውቃለን፡፡
ፕሮፌሰር ንጉሴ ተበጀ (Fellow Engineer) በታማኝነት እና በስነምግባር በሞያቸው አገራቸው ሲያገለግሉ የነበሩ መሆናቸውን ማህበሩ ይመሰክራል::
የኢትዮጵያ ሲቪል መሐንዲሶች ማህበር
Condolence

On behalf of the Ethiopian Association of Civil Engineers we want to express our deepest and most sincere condolences to the family and friends of Prof. Nigussie Tebeje (Fellow engineer) and EACE Community.
May his soul Rest in Peace
Ethiopian Association of Civil Engineers
Asemahagn Worku:
💚💛
ሀገራችን ትልቅ ሰው አጣች!
በኢትዮጰያ የእስትራክቸራል ምህድስና ረገድ ግንባር ቀደም ከሆኑ ምሁሮች አንዱ ነበሩ። መልካም ሰው ነበሩ!
ነብሳቸውን በአፀደ ገነት ያኑርልን ለቤተሰቦቻቸውም መፅናናት ይስጥልን።
--------------------------------------------
©ጌጡ ተመስገን
የስትራክቸራል ምህንድስና ሊቅ
ንጉሴ ተበጀ (ኤመሪተስ ፕሮፌሰር)
1937-2013

ንጉሴ ተበጀ በ1937 ዓ.ም በወርሃ ጥቅምት በስድስተኛው ቀን በዕለተ ሰኞ ተወለደ፡፡ የትውልድስፍራው በቀድሞ መጠሪያው በቤጌምድር ጠቅላይ ግዛት በደብረ ታቦር አውራጃ ልዩ ስሙ ፈረስ ሜዳ በተባለው ቦታ ነው፡፡

ወላጅ አባቱ ፓስተር ተበጀ ጉዳዬ የተቃወቁ የሰባተኛ ቀን አድቬንቲስት ቤተክርስቲያን አገልጋይ የነበሩ ሲሆን ወላጅ እናቱ ወይዘሮ ደብሬ ቦጋለ ደግሞ ልጆቻቸውን በቤት ተንከባክበው የሚያሳድጉ የቤት እመቤት ነበሩ፡፡

ወላጆቻቸው ካፈሯቸው ከሦስት ወንድሞቹና ከአራት እህቶቹ መካከል እርሱ ለቤተሰቡ የመጀመሪያ ልጅ ሲሆን ያደገው ጥሩ ፍቅር ባለበት ቤተሰብ ውስጥ ነው፡፡

ንጉሴ ተበጀ ትምህርት የጀመረው ገና በልጅነት ዕድሜው ሲሆን እስከ አምስተኛ ክፍል በቀነናና በአቃቂ የአድቬንቲስት ሚሲዮን ትምህርትቤት ተማረ፡፡ አባቱ በቤተክርስቲያን አገልግሎት ወደ ጎንደር ሲዛወሩ እርሱም ወደ ደብረታቦር በመሄድ በቀጥታ ሰባተኛ ክፍል ገብቶ የተማረ ሲሆን ስምንተኛ ክፍልን እንደቨረሰ ወደ ኩየራ አድቬንቲስት ሚሰዮን ትምህርት ቤት ተዛውሮ ከዘጠነኛ እስከ አስራ አንደኛ ክፍል ትምህርቱን ተከታተለ፡፤ከዚያም የአስራ ሁለተኛ ክፍል ትምህርቱን በመድሐኒያለም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አጠናቋል፡፤ገና ከልጅነት እድሜው ትምህርት ለመቀበል ብሩህ አዕምሮ ስለነበረው በትምህርቱ የላቀ ውጤት ያመዘግብ የነበረ ሲሆን በአጠቃላይ ከትምህርት ቤቱ አንደኛ የሚወጣባቸው በርካታ ጊዜያት ነበሩ፡፡

ከዚያም በልጅነት እድሜው የነበረውን የህክምና ሙያ የማጥናት ፍላጎቱን በመተው በቀዳማዊ ኃይለ ስላሴ ዩኒቨርስቲ (በአሁኑ መጠሪያ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ )ገብቶ የሲቪል ምህንድስና ሙያ በመከታተልበ1957 ዓ.ም ከዩኒቨርስቲው ብቸኛው ወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ በመሆን የባችለር ኦፍ ሳይንስ ዲግሪው አግኝቷል፡፡በዩኒቨርስቲው ጥቂት አመታት ከስራ በኋላ በአገነው የከፍተኛ ትምህርት እድል በመተቀም ወደ አሜሪካን አገር አቅንቶ በፔንስልቬኒያ ግዛት ከሊሀይ ዩኒቨርሲቲ የሁለተኛ ዲግሪ ትምህርቱን የተከታተለ ሲሆን በ1961 ዓ.ም በማተር ኦፍ ሳይንስ ዲግሪ ተመርቋል፡፡ባስመዘገበው የላቀ ውጤት በዩኒቨርስቲው የሶስተኛ ዲግሪ ትምህርቱን በመቀጠል በ27 ጫመቱ በ1964 ዓ.ም የዶክሬትሬት ዲግሪውን አግኝቷል፡፡

ከወጣትነት እድሜ አንስቶ በጉልምስናና ከዚያም በኋላ ባለው የህይወት ዘመን ለሀገርና ለወገን የሚጠቅም ብሎም ለትውልድ የሚተርፍ በርካታ ተግባራትን በመፈፀም በምህንድስናው የሙያ ዘርፍ የፕሮፌሰርነትን ማዕድ ለማግኘትና ”አንቱ“ ለመባል በቅቷል፡፡
ኤመሪተስ ፕሪፌሰር ንጉሴ ተበጀ ያገለገሉበት የስራ ልምዳቸውን በተመለከተ፣
 ከ1957 እስከ 1959 ለሁለት አመታት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በመምህርነት፣
 ከ1959 እስከ 1965 ለስድስት አመታት በአሜሪካ አገር በሊሀይ ዩኒቨርስቲ የምርመራ ስራ በረዳትነት እና የድህረ ዶክትሬት ምርምር ስራ፣
 ከ1965 እስከ 1967 በፈረንሳይ አገር በፓሪስ በሲ.ቲ.አይ.ሲ.ኤም(CTICM) ድርጅት በስትራክቸራል መሀንዲስነት ፣

 ከ1967 እስከ 1983 ለአስራ ሰባት አመታት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በመምህርነት ያገለገሉ ሲሆን በእነዚህ ጊዜያትም ለአምስት ተከታታይ ዓመታት የቴክኒዮሎጂ ፋካልቲ የሲቪል ኢንጅነሪንግ የትምህርት ክፍልን በኃላፊነት የመሩ ሲሆን በሌለ ተጨማሪ አምስት አመታት ቤኒበርስቲው የቴክኒዮሎጂ ፋካልቲ ዲንነት ተመድበው ኃላፊነታቸውን በብቃት ተወጥተዋል፣

 ከ1983 እስ 2013 ራሳቸው ባቋቋሙት አክመ(ACME) ዲዛይነርና ኮንሰልታንት በተሰኘ ድርጅት በስራ አስኪያጅነት አገልግለዋል፡፡

ያከናወኑትን የሳይንሳዊ ምርመር ስራቸውን በተመለከተ በአለም አቀፍ ደረጃ በሚታተሙ ጆርናሎች በጠቅላላው ከሃያ ሁለት በላይ ሳይንሳዊ የምርምር ጽሁፎችን ያዘጋጀና ለህትመት ያበቁ ሲሆን ለአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የመማሪያነት የሚያገለግሉትን ጨምሮ በሙያቸው ስምንት የተለያዩ መጽኃፍትን በሀገር ውስጥና በውጭ አገር አሳትመዋል፡፤ ከዚህም በተጨማሪ የሀገራችንን የህንፃ ስታንዳርድ የሥራ ህግጋትና ማሻሻያዎችን ስድስት ቅጾች አዘጋጅተዋል፡፡ከዩኒቨርስቲው መምህርነት ፣በድህረ ምርቃ ፕሮግራም በፈታኝነትና ከምርምር ስራች ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ከሀገራቸው ተጨማሪ በአሜሪካ በፈረንሳይ፣በኡርንዳ፣በታንዛኒያና በደቡብ ሱዳን ተዘዋውረው ሰርተዋል፡፡

በህንፃ ዲዛይንና የማማከር ስራን በሚመለከት ከአርባ በላይ ለሚሆኑ ከአምስት እስከ ሰላሳ ሶስት የሚደርሱ ወለል ያላቸውን ህንፃዎች የስትራክቸር ዲዛይንና የማማከር ስራዎችን አከናውነዋለው፡፡ ከነዚህ መካከል የአዋሽ ባንክና ኢንሹራንስ፣የንብ ባንክ፣የአማራ የገንዘብና ብድር ተቋም፣ የራምዳ ሆቴል፣ የማርዮት ሆቴል፣ ዬንኮማድ፣ የጌት ኮሜርሻል፣ የመቀሌ ስታዲዮምና የአዳማ ስታድዮም ለአብነት ተጠቃሽ ናቸው፡፡

የድልድይ ዲዛይኖችንና የማማከር ስራዎችን በተመለከተ ካከናወኗቸው በርካታ ስራዎች መካከል ከሞጆ ሀዋሳ ፈጣን መንገድ፣ ከሳውላ ማጂ፣ ከሞጣ ደብረ ታቦር፣ ከካሳ በር አዋሽ አርባ፣ ከጎንደር ሁመራ፣ ከጌዶ ነቀምትና ከገዋሌ ሚሌ የመንገድ ስራዎች ሲከናወኑ ለሚሰሩ ድልድዮች የሙያ ድርሻቸውን ማበርከታቸው ተጠቃሾች ናቸው፡፡ በተለይም በአባይና የግልገሌ ጊቤ ሁለት ሳይት 146 ቶን ያህል ተሸከርካሪዎቻችን የመሸከም አቅም የነበረውን ድልድይ ወደ 213 ቶን እንዲሻሻል በማድረግ ረገብ ከፍተኛ አስተዋፆኦ አድርገዋል፡፡

ከውኃየስትራክቸር ስራ ጋር በተያያዘም ከ300 ሜትር ኪዮብ መያዝ የሚችል የኮንክሪት የውኃ ታንከር ስራዎች በአቃቂ፣ በቃሊቲና በጎተራ አካባቢ ዲዛይነሮች ሰርተዋል፡፡የመተላለፊያ መንገዶችን በሚመለከትም በመዲናችን በአዲስ አበባ ሳር ቤት፣ በኦሎምፒያ፣ በወሎ ሰፈር፣ በሩዋንዳና በመሷለኪያ አካባቢ ያሉ የመንገድ መተላለፊያዎች የእርሳቸው የሙያ አስተዋፅኦና አሻራ ያረፋባቸው ስራዎች ናችው፡፡

በዲዛይንና በማማከር ካበረከቱት አስተዋፅኦ በተጨማሪ ለትላልቅ ህንፃዎች የዲዛይን ተጫራቾች መረጣ በሚካሄድበት ወቅት በውድድር ሂደት ላይ በሙያቸው የዳኝነት ስራ ተሳታፊ በመሆን የድርሻቸውን የተወጡ ሲሆን በዚህም ታሳታፊ ከነበሩባቸው ማካከል የህብረት ባንክ፣ የህብረት ኢንሹራንስ፣ የንብ ባንክና ኢንሹራንስ፣ የቅዱስ ሚካኤል ቤተ-ክርስትያንና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስትይንና የመሰብሰቢያ አዳራሽ ግንባር ቀደም ተጠቃሾች ናቸው፡፡ ከግንባታ ስራ ጋር በተያያዘም በተለያዩ ወቅቶች በግንባታ አሰሪዎችና በአገር ውስጥና የውጭ አገር ተቋራጮች መካከል አለምግባባት ሲከሰት በሙያቸው በግልግል ዳኝነት በመሳተፍ ስምንት ለሚደሱ ጉዳዮች አለመግባባቶችና ጋጭቶች ዕልባት እንዲያገኙ አድርገዋል፡፡
በመስራችነትና በአባልነት አስተዋፅኦ ያደረጉባቸውን የሙያ ማህበራትን በሚመለከት የኢትዮጲያ ሲቪል ኢንጅነሮች ማህበር፣ የአሜሪካ ሲቪል ኢንጅነሮች፣ በአሜሪካ የትልልቅ ሕንፃዎች ካውንስል፣ የኢተርናሽናል የድልድይና ስትራክቸራል ኢንጅነሮች ማህበር፣ የአፍሪካ ኔቶርክ ሳይንቲፊክ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት እንዲሁም ዘዴ ጆርናል የኢትዮጵያ ኢንጅነሮችና አርክቴክቶች ማህበር ይገኙበታል፡፡

እኚህ የስትራክቸራል ምህንድስና ምሁር ባከናወኑት የላቀ ተግባር በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር ከፍተኛ ሽልማትና እውቅና የተበረከተላቸው ሲሆን ከእነዚህም የሚከተሉት ዋንኛዎቹ ናቸው፡፡

 በዩንቨርስቲ መምህርነት፣ በስተራክቸራል ምህንድስና ሙያ ባደረጉት ከፍተኛ የምርመራ ስራና ለሀገሪቱ በአበረከቱት ከፍተኛ የምርመራ ስራና ለሀገሪቱ በአበረከቱት ከፍተኛ አስተዋጻኦ ምክንያት በ1981 ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የመጀመሪያው የሲቪል ምህንድስና የሙሉ ፕሮፌሰርነት መአረግ ሰጥቷቸዋል እርሳቸው የሙሉ ፕሮፌሰርነት ያገኙበት ወቅት ዩኒቨርስቲው ይህንን መዕረግ መስጠት በጀመረበት በጥቂቱ አመታት ውስጥ በመሆኑ በወቅቱ በአገሪቱ በዚህ ማዕረግ ይጠሩ ከነበሬ ጥቂት ምሁራን መካከል በመጀመሪያዎቹ ረድፍ የሚገኙ ናቸው፡፡
 በ1994 ከኢትዮጲያ ሳይንትፊክ ሶሳይት የፋክሊቲ የሳይንስ አሸናፊ ሆነዋል፡፡

 በ2005 ከአሜሪካ ኮንክሪት ኢንስትቱይት የኢትዮጵያ ቻፕተር በዲዛይንና በኮንክሪት ኮንስትራክሽን ስራ የህይወት ዘመን የላቀ አስተዋፅኦ የእውቅና ተሸላሚ ሆነዋል፡፡
 በ2009 የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የኢዩቤልዩ ሽልማት አግኝተዋል

 እንዲሁም በ2009 በኢትዮጵያ በሳይንስ ረገድ ላደረጉት ከፍተኛ አስተዋፅኦ የበጎ ሰው ተሸላሚ ሆነዋል
 ኤመሪተስ ፕሮፌሰር ንጉሴ በተለይ በሚከተለው ጉዳዮች ስማቸው ጎልቶ በመውጣት በብዙዎች ዘንድ አድነቆትና ክብርን ያተረፉ ናቸው

 በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በቅድመ ምረቃና በድህረ ምረቃ የትምህርት መርሀ ግብር ለበርካታ አመታት በማስተማር በጥናትና ምርምር ስራ በመሳተፍና የማመሪያ መጻህፍትን በማሰተም እውቀታቸውን ለሌሎችም በማጋራት በርካታ ምሁራንን ማፍራታቸው ፤

 የታላላቅ የድልድይና ግንባታ ስራዎችን በማቀድ በማማከርና ችግሮችን በመፈታት የነበራቸው አስተዋፅዖ ከፍተኛ መሆኑ በዚህም ረገድ በተለይም በተደጋጋሚ ከሚታወሱባቸውና እንደ እንደ አስረጂነት ከሚተቀሰው መካከል በ1998 ዓ.ም የአባይ ድልድይን ለመገንባት የሚያገለግል ከባድ ማሽን ሲያጓጉዙ የነበሩ ሁለት ከፍተኛ የጭነት ተሸከረካሪዎች የአባይ ድልድይ ጋር ሲደርሱ ድልድዩ እነዚህን ማዙፍ ማሽነሪ የጫኑ ተሸከርካሪዎች የማሳለፍ አቅም ስለመኖሩ ለመወሰን ባለመቻሉ ዕውቀት ችግሩን ሊፈታው መቻሉ ነው፡፡

ከሙያቸው ውጪ የነበራቸውን የማህበራዊ ተሳትፎና የግል ህይወት በሚመለከት የቀድመሞ መንግስት ከፖለቲካና ከፓርቲ የአባልነት ተሳትፎ ውጪ ያሉ ጥቂት የሥነ ጥበብና የልዩ ልዩ ሙያ ባለቤት የሆኑ ታዋቂ ሰዎች በኢትዮጵያ ህዝባዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ብሔራ ሸንጎ እንዲገቡ ባደረገበት ወቅት እርሳቸውም በሞያቸው በነበራቸው ታዋቂነት ተመርጠው የብሄራዊ የመማክርት ጉባኤ ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

የግል ህይወታቸውንና አኗኗራቸውንና በሚመለከት ኤመሪተስ ፕሮፌሰር ንጉሴ በስነ ጥበብ ረገድ ከዘመናዊ የሙዚቃ መሳሪያዎች መካከል ፒያኖ መጫወት የሚችሉ ሲሆን በተለይ በወጣትነት የሚያውቋቸው ይመሰክሩላቸዋል፡፡ የስዕል ጥበብ አፍቃሪ በመሆናቸውም በሀገራች ከእውቅ ሰዓሊያን ጋር ቅርበት የነበራቸው ሲሆን የእነርሱን የጥበብ ስራዎች በመግዛት የስነ ጥበብ ባለሙያዎችን የሚያበረታቱ ነበሩ፡፡በቋንቋ ረገድም ከአማርኛና ከእንግሊዘኛ በተጨማሪ የፈረንሳይ ቋንቋ የሚያውቁ ነበሩ፡፡

የእረፍት ጊዜያቸውን በሚመለከት ገና ከዩኒቨርስቲ መምህርነት አነስቶ በቋሚነት ቴኒስ ስፖርት መጫወትን ያዘውትሩ የነበረ ሲሆን ከአቅም በላይ ካልሆነ በስተቀር ከጨዋታ ሜዳ የማይታጡ ነበሩ፡፡ከሚቀርቧቸው ወዳጆቻቸው ጋር እየተገናኑ ስለማህበራዊና የተለያዩ ጉዳዮች መጫወት የሚያደስታቸው ሲሆን ይህም ከነበረባቸው የሥራ ውጥረት ፋታ በማግኘት የሚዝናኑበት መንገድ ነው፡፡ ከተወሰኑ የቅርብ ወዳጂቻቸው ጋርም የጓደኛሞች ማህበር በማቋቋም በመደበኛነት የሚገናኙ ሲሆን ይህም ለእርሳቸው አስደሳችና ከፍተኛ ቦታ የሚሰጡት ጉዳይ ነበር፡፡ ምንም እንኳን እሳቸው ከብዙዎች ጋር በሚያደርጉት ግንኙነት ቁም ነገር ላይ እጂ ጨዋታ የሚያውቁ መስለው ባይታዩም ከዚህ በተቀራኒው ከቅርም ወዳጆቻቸው ጋር ሲሆኑ ተጫዋችና ተግባቢ ሰው ነበሩ፡፡
ከዚህ በተጨማሪ በትርፍ ጊዜያቸው የተለያዩ ማህበራዊና ታሪክ ላይ የሚያተኩሩ መጽሐፍትማንበብና በቤታቸው ሆነው የአገር የአለም ዘቀፍ ዜናዎችን አስተማሪና አዝናኝ ታሪካዊና ዶክመንተሪ ልፊሞችን ፣የአውሮፓ የእግር ኳስ የአለም የሜዳ ቴኒስ ውድድሪችን መከታታል ያደስታቸው ነበር፡፡

የቤተሰብ ሕይወታቸውን በሚመለከት ከወይዘሮ አይናበባ አመኑ ጋር ትዳር መስርተው ላለፉት 30 አመታት በትዳር ኖረዋል፡፡በዚህም ወቅት ከአብራካቸው ሁለት ወንዶችና ሁለት ሴቶች ልጆች አፍርተው የአራት ልጆች አባት በመሆን ለቤተሰባቸው ተገቢውን ፍቅርና ክብካቤ በማሳት ልጆቻቸውን ለቁምነገር አድርሰዋል፡፡

በአጠቃላይ ኤመሪተስ ፕሮፌሰር ንጉሴ ተበጀ በሰስትራክቸራል ምህንድስና ዘርፍ በሀገራችን የተከበሩ ስመጥር ባለሞያ፣ የሞያ እገዛቸውን ለሚሹ ለማናቸውም አካላት ምክራቸውንና እውቀታቸውን ሳይሰስቱ በፈቃደኝነት የሚያጋሩ ሁሌም የሚያምኑበትን መፈፀማቸውን እንጂ ለታይታ ዝናና ክብር ለማግኘት የማይጣጣሩና ለዚህም ቦታ የማይሰጡ ፣የመርህ ሰው ፣በማናቸውም ረገድ ሰላማዊ ግንኙነት የሚሹና በቀጥታ በሚመለከታቸው ጉዳይ ላይ ማተኮር እንጂ በማይመለከታቸው ጉዳይ ላይ ጣልቃ መግባት የማይፈልጉ፣በቅርብ ወዳጆቻቸው ዘንድ ተግባቢና ተወዳጅ የሆኑመ አብረዋቸው ላደጉት ወንድሞቻቸውና እህቶታቸው ልዩ ፍቅር ያላቸው የራሳቸውን ቤተሰብ በፍቅርና በልዩ ክብካቤ የሚመሩ ተወዳጅና ተከባሪ ናቸው፡፡

ኤመሪተስ ፕሮፌሰር ንጉሴ ተበጀ ባደረባቸው ህመም በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር ሕክክና ሲከታተሉ ከዮዩ በኋላ ጥር 12 ቀን 2013 ዓ በአዲስ አበባ ከተማ በቅዱስ ዮሴፍ ቤተክርስቲያን ተፈጽሟል፡፡

በደረሰብን መሪር ሀዘን በቅርብ በመገኘትና በተለያየ መንገድ ላጽናናችሁን ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡

ከቤተሰቦቻቸው!
It has been 10 years since the first #UNESCO #Engineering #Report was released… and a lot has changed.

The second UNESCO Engineering Report - scheduled for release on #WorldEngineeringDay - will point to the 2030 Agenda for Sustainable Development as presenting a blueprint for action and explain how #engineers are now at the forefront to deliver on the #SustainableDevelopmentGoals, using their scientific knowledge and experience to turn innovative ideas into #sustainability projects for the benefit of all.

bit.ly/WorldEngDay for more info. #WorldEngineeringDay #WED2021 #WFEO #UNESCO #UNSDG
#WFEO #EACE1962
@eaceg @ecethiopia2 @eacec
የሀዘን መግለጫ
የኢንጅነር ተኮላ ገ/መድህን የቀብር ስነ ስርዓት ረቡዕ የካቲት 17 ቀን በቅድስት ስላሴ ቤ/ክ ከቀኑ በዘጠኝ ሰዓት ይፈጸማል።
Forwarded from Abebe Bellete
Our former executive member, Eng. Tekola G/Medhin passed away. His burial is on 24 Feb. 2021 at 3:00pm , St. Selassie Church.
Condolence
Ethiopian Association of Civil Engineers
Our former executive member, Eng. Tekola G/Medhin passed away. His burial is on 24 Feb. 2021 at 3:00pm , St. Selassie Church
On behalf of the Ethiopian Association of Civil Engineers we want to express our deepest and most sincere condolences to the family and friends of Eng. Tekola G/Medhin (Fellow engineer) and EACE Community.
May his soul Rest in Peace
የሀዘን መግለጫ
የማህበራችን አባል የሆኑት ኢንጂኔር ታደሰ ኃ/ሥላሴ ተክለ (Fellow Engineer) ከዚህ አለም በሞት መለየት ማህበሩ የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን እየገለጸን
በማህበራችን ከ1990 ዓ.ም ጀምሮ ማህበሩን በመመስረትና ከመደበኛ አባልነት እስከ የስራ አስፈፃሚ ቦርድ በመሆኑ ያገለገሉ ሲሆን ህይወታቸው እስካለፈበት ቀን ድረስ ማህበሩን ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ በዕውቀትና በገንዘብ ሲደግፉ የቆዩ ሲሆን የኢትዮጵያ ሲቪል መሐንዲሶች ማህበርም የተሰማውን ልባዊ ሐዘን እየገለፀ የቀብር ስነስርዓት ላይ በሚደረገው የሽኝት መርሃ ግብር ላይ የማህበሩ አባላት በመገኘት ሐዘናችሁን እንድትገልፁ እናሳውቃለን፡፡
በታማኝነት እና በስነምግባር በሞያቸው አገራቸው ሲያገለግሉ የነበሩ መሆናቸውን ማህበሩ ይመሰክራል::
የኢትዮጵያ ሲቪል መሐንዲሶች ማህበር
#Condolence
On behalf of the Ethiopian Association of Civil Engineers we want to express our deepest and most sincere condolences to the family and friends of eng. Taddese Haile Silase (Fellow engineer) and EACE Community.
May his soul Rest in Peace
Ethiopian Association of Civil Engineers
የኢንጂኔር ታደሰ ኃ/ሥላሴ ተክለ አጭር
የህይወት ታሪክ
የካቲት 22 ቀን 2013 ዓ/ም
ኢንጂኔር ታደሰ ኃ/ሥላሴ ተክለ ከእናታቸው ከወ/ሮ እልፍነሽ ወልደመድህን እና ከአባታቸው ከአቶ ኃ/ሥላሴ ተክለ በቀድሞ አርሲ ክ/ሀገር ዶዶታ ወረዳ ሊጋባ ከተማ ጥቅምት 14 ቀን 1933 ዓ/ም ተወለዱ፡፡
እደሜያቸው ለትምህርት ሲደርስ በአካባቢው ት/ቤት ትምህርት በመከታተል ላይ እያሉ፤ በ1940 ዓ/ም ክቡር ትዕዛዝ ወልደ ጊዩርጊስ ወልደ ዮሐንስ ወደ አዲስ አበባ አምጥተው በተፈሪ መኮንን ት/ቤት አስገብተው እየከፈሉላቸው እንዲማሩ አድርገዋል፡፡ እዚያው ት/ቤት አዳሪ በመሆን እስከ 12 ክፍል ድረስ ትምህርታቸውን ተከታትለዋል፡፡
በመቀጠል በቀዳማዊ ኃ/ሥላሴ ዩኒቨርስቲ በ1953 ዓ/ም የምህድስና ኮሌጅ በመግባት በ1957 ዓ/ም ትምህርታቸውን አጠናቅቀው ተመርቀዋል፡፡ በት/ቤት በነበሩበት ጊዜ ጀምሮ በነበራቸው የአገር ፍቅር የተነሳ በወቅቱ በነበረው ""ተምሮ ማስተማር" በሚባል ፕሮግራም ቀዳሚ ተሳታፊ ነበሩ፡፡
ከቀኃሥ ዩኒቨርስቲ እንደተመረቁ፣ ልምድ ለማግኘት በቀን ሙያተኛነት በመቀጠር፤ አሁን ዋናው ፖስታ ቤት ያለበት ህንጻ በሚገነባበት ጊዜ አገልግሎት አበርክተዋል፡፡ በዚህ ፕሮጀክት ላይ እየታዩ ደረጃ በደረጃ እስከ ፕሮጀክቱ ዋና መሐንዲስነት ድረስ አገልግለዋል፡፡
በመቀጠል ታደሰ ኃ/ሥላሴ ኮንስትራክሽን በሚል የራሳቸውን አቋቁመው ነበር፡፡ ድርጅቱን በማሳደግ ከኢንጂኔር ብርሃነ አባተ ጋር በመሆን በርታ ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበርን አቋቋመዋል፡፡ አገር በቀል የሆኑ ተቋራጮች ሲመሠረቱ ከቀደምቶቹ አንዱ በመሆን፤ በርታ ኮንስትራክሽን በተለያዩ የመንገድ ሥራዎች ለምሳሌ ፡- ብቸና ሞጣ፣ ጅማ ጭዳ፣ ሰርዶ አፍዴራ፣ ጋሸና ላሊበላን ገንብተዋል፡፡ ፋብሪካም ገንብተዋል ለምሳሌ፡- የሐረር ቢራ ፋብሪካ፣ ሜታ ቢራ ፋብሪካ፣ ለቱሪስት መዳረሻ የሚሆኑ ታሪካዊ ቦታዎች ውስጥ በባህር ዳር "ጣና ሐይቅ" በጎንደር "ጎሃ" በላሊበላ "ሮሃ" በአክሱም "የሃን" በሒልተን ሆቴል ደረጃ የሆኑ አራት ሆቴሎችን ገንብተዋል፡፡ በሰፋፊ የመስኖ ሥራ ተግባራትም ተሳትፈዋል፣ለምሳሌ የአሚባራ መስኖ ፕሮጀክት፡፡
ኢንጂኔር ታደሰ ኃሥላሴ ስለ አገር ልማት የነበራቸው ህልም ከፍ ያለ ነበር፡፡ በተለያዩ መድረኮች ለአገር ልማት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ሊያደርጉ የሚችሉ ሃሳቦችን አቅርበዋል፤ ያገባኛል የሚሉ ወገኖችም በሃሳባቸው ዙሪያ እንዲወያዩ አድርገዋል፡፡ በተጨማሪ ኢንጂነር ታደሰ ኃሥላሴ ስለ አገር ልማት ጽሑፎችን ለሕዝብ በተደጋጋሚ አበርክተዋል፡፡ እንዲሁም በዚሁ ጥረት በህዝብ ሚዲዎች ብዙ ገለጣዎችን አከናውነዋል፡፡
ኢንጂኔር ታደሰ ኃ/ሥላሴ ያቀርቧቸው የነበራቸው የልማት አስተያየቶች ላይ ተመርኩዞ በ2011 ዓ/ም በተመሠረተ የመሐንዲሶች የጥናት ቡድን፡ በ2050 ኢትዮጵያ በልማት የት ልትደርስ ትችላለች በሚል በተዘጋጀ መድረክ እውቅና ተሰጥቷቸው ተሸልመዋል፡፡
ኢንጂኔር ታደሰ ኃ/ስላሴ በጣም ግልጥና በጣም ቅን ግለሰብ ነበሩ፡፡ እሳቸውን መሰል ቅን ሰው ማግኘት ያዳግታል፡፡ ኢንጂነር ታደሰ ኃ/ሥላሴ ሚያዝያ 1967 ዓ/ም ከወ/ሮ ሂሩት አማረ ጋር ትዳር መሥርተው ለ46 ዓመት እስከ እለተሞታቸው ድረስ በፍቅር አብረው ኖረዋል፡፡
ኢንጂኔር ታደሰ ኃ/ሥላሴ ባደረባቸው ሕመም ምክንያት በሕክምና ሲረዱ ቆይተው በተወለዱ በ80 ዓመታቸው የካቲት 22 ቀን 2013 ዓ/ም በሞት ተለይተውናል፡፡ ቀብራቸው የካቲት 23 ቀን 2013 ዓ/ም በአራዳ መናገሻ ቅዱስ ጊዩርጊስ ቤተ ከርስቲያን ይፈፀማል ፡፡
የኢትዮጵያ ሲቪል መሐንዲሶች ማህበር
👍2
WFEO Committee on Disaster Risk Management & Colegio de Ingenieros del Perú organize the #Webinar Towards #Resilient #Societies The #Engineering contribution
9 March 19.00 Lima Time

Registration https://lnkd.in/dss7SDH
Zoom link https://lnkd.in/dQxgnTe

#GlobalGoals #SustainableDevelopment #SDG11 #WorldEng#sustainability #WorldEngDay2021 #Engineers4SDGs #Engineer World Engineering Day #SDGs #Engineering #Agenda2030 #GlobalGoals #sustainability
የስራ ልምምድ ፕሮግራም ምዝገባ (Internship Program Application)

የኢትዮጲያ ሲቪል መሃንዲሶች ማህበር ከፖለቲካ ነጻ የሆነ እና ለትርፍ ያልተቋቋመ የሙያ ማህበር ሲሆን ዋና አላማውም በሀገሪቱ የሲቪል ምህንድስና ሙያን ማሳደግ፤ ማጎልበት፤ የሲቪል ምህንድስና ትምህርትን እና የምርምር ስራዎችን እንዲበረታቱ ማድረግ ነው፡፡

ማህበሩ ከተለያዩ የኮንስትራክሽን ዘርፍ ላይ ከተሰማሩ ድርጅቶች እና ተቋማት ጋር በመተባበር ከዩኒቨርስቲ ተመርቀው ስራ ያላገኙ እና አሁን ባለው የኮሮና ቫይረስ እና ሌሎች ምክንያቶች ስራ ላይ ለማይገኙ አባላቶቹ እስከ አንድ አመት ድረስ የሚቆይ የስራ ልምምድ ፕሮግራም አዘጋጅቷል። የስራ ልምምድ ፕሮግራሙ በአገሪቱ በሚገኙ የተለያዩ የህንፃ፣ የመንገድ፣ የድልድይ፣ የውሃ፣ የግድብ፣ የፓርክ ግንባታ እና የመሳሰሉት ፕሮጀክቶች ላይ ሲሆን ፍላጎቱ ያላችሁ የማህበሩ አባላት በማህበሩ ድህረ ገፅ (EACE Internship Application) በመግባት መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን። ፕሮግራሙ ላይ ለመሳተፍ የማህበሩ አባል መሆን አስፈላጊ ነው፡፡ በተጨማሪም ምዝገባው በድህረ ገጹ ብቻ የሚካሄድ መሆኑን እንገልጻለን።

በምዝገባ ወቅት ወደ አካውንትዎ ለመግባት የአባልነት መታወቂያ ቁጥርዎንና የይለፍ ቃልዎን (password) ይጠቀሙ፡፡ የይለፍ ቃልዎን (password) የማያውቁት ከሆነ “Forgot Your Password?” የሚለውን ሊንክ በመጠቀም አዲስ ማውጣት ይችላሉ፡፡ ለተጨማሪ መረጃ በኢሜል አድራሻችን eaceregister@gmail.com ይላኩልን፡፡
የኢትዮጲያ ሲቪል መሃንዲሶች ማህበር, 2013 ዓ.ም
https://eacecivil.org/announcements/9
#EACE1962
@eaceg @ecethiopia2 @eacec @ECFEt
1
https://www.youtube.com/watch?v=As6A4C_rV8k EACE contribution/role on MInistry of Transport Ten year plan Addressed issues includes Job creation for professionals (Civil Engineer) all over the country, Fair Wage(ተመጣጣኝ ክፍያ), Construction Quality, Projects should be contracted based on engineering estimation and market value, continuous professional development, the design engineer must free from any influencing while design routes, depth.... should be based on engineering parameters and science only, consultants and contractors should hire all the relevant engineers necessary for the project and they should avoid the practice of delivering projects with one or two engineers only...