ባለሥልጣኑ 14ኛውን የዘር ጥራት ቁጥጥር የምክክር መድረክ እያካሄደ ነው ::
***
(አዳማ ፣የካቲት 19 /2018 ዓ/ም የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን )
የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን 14ኛውን የዘር ጥራት ቁጥጥር የምክክር መድረክ ከATI ፣ ከግብርና ሚኒስቴር ፣ ENP እና FSRP ጋር በመተባበር የክልል የዘር ጥራት ቁጥጥር ባላስልጣን መ/ቤቶች ፣ ከአዲስ አበባ እና ድሬደዋ ከተማ አስተዳደር የሚመለከታቸው አካላት በተገኙበት እያካሄደ ነው ::
በመድረኩ ላይ የተገኙት የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ክቡር አምባሳደር ድርባ ኩማ እንደገለፁት ፤ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ መሰረታዊ ከሆኑ ጉዳዮች አንዱ የተሻሻሉ ዝርያዎችን እና ጥራቱን የጠበቀ ዘር መጠቀም መሆኑን ገልፀዋል ::
የምክክር መድርኩ ዋና ዓላማም እንደ ሀገር በዘር የጥራት ቁጥጥር ስረዓት ላይ የሚታዩ ችግሮችን በጋራ በመወያየት በቀጣይ በቅንጅት በመስራት መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት እንደሆነም ተናግረዋል ::
በዘርፉ ወጥነት ያለው የመረጃ ስረዓት መዘርጋት ውሳኝ መሆኑን ገልፀው ፤ ታማኝነትና ወጥነት ያለው የዘር የመረጃ ልውውጥ ስረዓት እንዲገነባ አየሰራን ነው ብለዋል:
ጠንካራና ወጥነት ያለው የዘር ቁጥጥር ስርዓት በመዘርጋት ህገ-ወጥ የዘር ዝውውርን በመከላከል ለአርሶ አደሩ ጥራት ያለው ዘር እንድደርስ ከሚመለከታቸው እና ከባለድርሻ አካላት በቅንጅትና መስራት አስፈላጊ መሆኑን ገልፀዋል ::
በዘር ጥራት ቁጥጥር ስራ እሴት ሰንሰለት ውስጥ ተዋናይ የሆኑ አካላት ለዘር ጥራት መረጋገጥ ወሳኝ ሚና እንዳላቸውም ተናግረዋል::
ዋና ዳይሬክተሩ አክለውም ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ እንደሀገር ጠንካራ የግብርና ሬጉላቶሪ ተቋም እንዲሆን በትኩረት አየተሰራ ነው ብለዋል ::
በባለስልጣኑ የዕፅዋት ሬጉላቶሪ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ወንዳለ ሀብታሙ (ዶ/ር) በግብርና ስረዓት ውስጥ ምርትና ምርታማነትን ከሚ ያሳድጉ ግብዓቶች ውስጥ አንዱና ዋነኛው ጥራቱን የጠበቀ ዘር ነው ብለዋል ::
የዘር ጥራትን በሚፈለገው ደረጃ ለማስጠበቅ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ሆኖ ለመገኝት አንደ ሀገር በርካታ ስራዎች መከናወናቸውን ገልፀው፤ ወጥነት ያለው የዘር ጥራት ቁጥጥር ስረዓት መዘርጋት ትኩረት የሚሰጠው ጉዳይ መሆኑን በመድረኩ ገልፀዋል ::
በመድረኩ ላይ የክልል የዘር ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣናት የክልላቸውን በዘር ጥራት ቁጥጥር የአፈፃፀም ሪፖርት አቅርበዋል ::
የምክክር መድረኩ ለተከታታይ ሶስት ቀናት የሚቀጥል ይሆናል ::
ዘጋቢ :- መንበረ ሀይሉ
ፎቶ ግራፍ :- ብርቱካን አዲሱ
ጠንካራ የሬጉላቶሪ ስርዓት ለዘላቂ ዕድገት
የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል መረጃዎችን ያግኙ
ዌብሳይት:- http:www.eaa.gov.et
ፌስቡክ:- Ethiopian Agricultural Authority
ቴሌግራም:-eaapr_1234

👍5❤1
እንኳን ለጥቁር ህዝቦች ኩራት ለሆነው ለ130ኛው የዐድዋ ድል በዓል አደረሳችሁ።
ጠንካራ የሬጉላቶሪ ስርዓት ለዘላቂ ዕድገት
‹‹Robust Regulatory System For Sustainable Development>>

👍3