ዶይቸ ቬለን | DW AMHARIC NEWS🇪🇹
2.95K subscribers
2.46K photos
76 videos
2 files
335 links
ይህ የዶይቼ ቬለ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው። ትኩስ ዜና፣ በአበይት ፖለቲካዊ፣ ኤኮኖሚያዊ፤ ማኅበራዊ እና ባሕላዊ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩር ትንታኔ ያቀርባል

DW AMHARIC NEWS IS A GLOBAL NEWS AND INFORMATION CHANNEL FROM A GERMAN INTERNATIONAL BROADCASTER DEUTSCHE WELLE (DW)
Download Telegram
የኮሮና ክትባት በአመት ውስጥ እውን ሊሆን ይችላል!

በአውሮፓ ለሚዘጋጁ የክትባት መድኃኒቶች ፍቃድ የሚሰጠው የአውሮፓ ህብረት ኤጀንሲ ተስፋ የተጣለበት የኮሮና ቫይረስ ክትባት በቀጣዩ አንድ ዓመት ውስጥ እውን ሊሆን እንደሚችል አስታውቋል - #AlAin

@dwamharic_news @dwamharicnewsbot
የኤርትራ ልዑክ በካርቱም ከፕሬዚዳንት አል ቡርሃን ጋር ተወያየ

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዑስማን ሳሌህን እና የፕሬዝዳንቱን ከፍተኛ አማካሪ የማነ ገብረአብን ያካተተው የኤርትራ ልዑክ በካርቱም ከሱዳን ሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤት ፕሬዚዳንት አል ቡርሃን ጋር መወያየታቸውን የኤርትራ የኢንፎርሜሽን ሚኒስትር የማነ ገብረመስቀል በይፋዊ የትዊተር ገጻቸው ገልጸዋል፡፡

ልዑኩ የኮሮና ወረርሽኝን በጋራ መከላከልን ጨምሮ የሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ የትብብር ጉዳዮችን በተመለከተ ከፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የተላከውን ደብዳቤ ለአል ቡርሃን አስረክቧል። አል ቡርሃንም ለሱዳን የቀረበች ካሏት ኤርትራ ለተላከላቸው ደብዳቤ አመስግነው ተቀብለዋል።

የሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ግንኙነትን ይበልጥ ለማሳደግ ጠንከር ያሉ እርምጃዎችን በእርግጥ መውሰድ እንደሚያስፈልግም ነው ቡርሃን የገለጹት። በሱዳን እየተካሄዱ ስላሉ የለውጥ ሂደቶችም ለልዑኩ አስረድተዋል። ዛሬና ትናንት በአዲስ አበባ የኢትዮ ሱዳን ከፍተኛ የፖለቲካ ምክክር መድረክ መካሄዱ የሚታወስ ነው።

#AlAin
@dwamharic_news @dwamharicnewsbot
የዓለም የካርበን ልቀት መጠን በ 7 ፐርሰንት ሊቀንስ ይችላል ተባለ

የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል በተጣለው የእንቅስቃሴ ገደብ ምክንያት የአለም የካርበን ልቀት በ7 ፐርሰንት ሊቀንስ አንደሚችል ኜቸር ክላይሜት ቼንጅ ላይ የታተመውን ጥናት ጠቅሶ ሮይተርስ ዘግቧል፡፡

ጥናቱን ያካሄዱት የአውሮፓ፣ የአሜሪካና የአውስትራሊያ የሳይንቲስቶች ቡድን ሲሆን የ62 ሀገራትን፣ የ50 የአሜረካ ግዛቶችን፣ የ30 የቻይና ግዛቶችንና የስድስት የኢኮኖሚ ዘርፎችን ካርበን ልቀት እለታዊ የኤሌክትሪክ ፍጆታቸውን ተጠቅሞ በመተንተን መሆኑን ገልጿል፡፡

በፈረንጆቹ 2019 ዓለም 100 ሚሊዮን ቶን ካርበን ጋዝ በየቀኑ ወደ አካባቢ ለቃ ነበር፡፡ በፈረንጆቹ 2020 በሚያዚያ ወር ወደ 83 ሚሊዮን ቶን ዝቅ ማለቱን ይሄው ጥናት አመልክቷል፡፡

#AlAin
@dwamharic_news @dwamharicnewsbot
አጫጭር መረጃዎች ፦

- በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክያት የተዘጋው የአሜሪካ እና የካናዳ ድንበር እስከ ሰኔ 14/2012 ዓ/ም ድረስ ተዘግቶ እንደሚቆይ ጠ/ሚ ጀስቲን ትሩዶ ገልፀዋል።

- 2ተኛ ቀኑን ባስቆጠረው የWHO 73ኛ ዓመታዊ የቪዲዮ ጉባዔ ላይ የተሳተፉ አባል ሃገራት ድርጅቱ /WHO/ እና በስሩ ያሉ ኤጀንሲዎች ለኮሮና ወረርሽኝ የሰጡት ምላሽ በገለልተኛ አካል እንዲጣራ ተስማምተዋል - #AlAin

- የቻይና ሳንቲስቶች የኮቪድ-19ኝን የሚያቆም መድሀኒት አግኝተናል እያሉ ነው። ወረርሽኙን ክትባት ያቆመዋል ተብሎ ይገመት ነበር የሚሉት የቻይና ላብራቶሪ ተመራማሪዎች የኮሮናን ስርጭት በፍጥነት የማቆም ኃይል ያለው መድሀኒት እያዘጋጀን ነው ብለዋል - https://telegra.ph/EthioFM-05-19

- በህንድ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ከ100,000 በላይ ሆኗል። የሟቾች ቁጥር ከ3,000 በላይ ሆኖ ተመዝግቧል።

- በብራዚል የኮሮና ቫይረስ እየበረታ ነው፤ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከUK፣ ከጣልያን፣ ከፈረንሳይ በልጧል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 261,567 ደርሷል።

- በጣልያን ባለፉት 24 ሰዓት 162 ሰዎች ሞተዋል፤ 813 ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

- በማዳጋስካር ሁለተኛው (2) ሞት በትላትናው ዕለት ምሽት ተመዝግቧል። በሌላ በኩል በሀገሪቱ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 326 ደርሰዋል።

@dwamharic_news @dwamharicnewsbot
#DrMikeRyan

የዓለም ጤና ድርጅት የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ተጠቂዎች ቁጥር እየቀነሰባቸው ባሉ ሀገራት ቫይረሱን ለመከላከል የተጣሉ እገዳዎች በቶሎ የሚነሱ ከሆነ ወረርሽኙ ለሁለተኛ ጊዜ ወረርሽኙ ከፍተኛ ደረጃ ይደርሳል ሲል #አስጠንቅቋል፡፡

የድርጅቱ የአስቸኳይ ጊዜ ጉዳዮች ኃላፊ ዶ/ር ማይክ ርያን አለም በመጀመሪያው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ሞገድ ውስጥ ነች፤ ምንም እንኳን በብዙ ሀገራት በቫይረሱ የመያዝ መጠን እየቀነሰ ቢሆንም በማእከላዊና በደቡብ አሜሪካ እየጨመረ ነው ብለዋል፡፡

እንደ ዶክተር ማይክ ርያን ከሆነ ወረርሽኞች ሁሌም ወቅታዊ ናቸው ፤ በዚህ አመት የመጀመሪያው ሞገድ ያቆመባቸው ሀገራት እንደገና ይመለሳል ብለዋል፡፡ ቫይረሱን ለመከላከል የተጣሉ ክልከላዎች ቶሎ የሚነሱ ከሆነ ቫይረሱ በፍጥነት ሊስፋፋ የሚችልበት እድል እንዳለ ገልጸዋል - #AlAin

@dwamharic_news @dwamharicnewsbot
#DrMikeRyan

የዓለም ጤና ድርጅት የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ተጠቂዎች ቁጥር እየቀነሰባቸው ባሉ ሀገራት ቫይረሱን ለመከላከል የተጣሉ እገዳዎች በቶሎ የሚነሱ ከሆነ ወረርሽኙ ለሁለተኛ ጊዜ ወረርሽኙ ከፍተኛ ደረጃ ይደርሳል ሲል #አስጠንቅቋል፡፡

የድርጅቱ የአስቸኳይ ጊዜ ጉዳዮች ኃላፊ ዶ/ር ማይክ ርያን አለም በመጀመሪያው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ሞገድ ውስጥ ነች፤ ምንም እንኳን በብዙ ሀገራት በቫይረሱ የመያዝ መጠን እየቀነሰ ቢሆንም በማእከላዊና በደቡብ አሜሪካ እየጨመረ ነው ብለዋል፡፡

እንደ ዶክተር ማይክ ርያን ከሆነ ወረርሽኞች ሁሌም ወቅታዊ ናቸው ፤ በዚህ አመት የመጀመሪያው ሞገድ ያቆመባቸው ሀገራት እንደገና ይመለሳል ብለዋል፡፡ ቫይረሱን ለመከላከል የተጣሉ ክልከላዎች ቶሎ የሚነሱ ከሆነ ቫይረሱ በፍጥነት ሊስፋፋ የሚችልበት እድል እንዳለ ገልጸዋል - #AlAin

@dwamharic_news @dwamharicnewsbot
በቺሊ 6 ነጥብ 8 ሬክተር ስኬል የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ ደረሰ!

በሰሜናዊ ቺሊ 6 ነጥብ 8 ሬክተር ስኬል የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ መድረሱን የጀርመን የጂኦ ሳይንስ ማዕከል አስታወቀ፡፡ አደጋው የ145 ኪሎ ሜትር ጥልቀት እንዳለውም ማዕከሉ ገልጿል፡፡

የአሜሪካ የጂኦሎጂካል ሰርቬይ የመሬት መንቀጥቀጡ ከሳን ፔድሮ ዴ አታካማ በስተደቡብ ምዕራብ በኩል እንደተነሳ አስታውቋል፡፡ በአደጋው እስካሁን የደረሰ ጉዳት ሪፖርት እንዳልተደረገ ሲጅቲኤን ዘግቧል፡፡

በቺሊ ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱ የሚታወስ ሲሆን እ.ኤ.አ በ1960 የተከሰተውና 9 ነጥብ 5 ሬክተር ስኬል የተመዘገበው ግን ከሁሉም ከፍተኛው ሆኖ በታሪክ ተመዝግቧል፡፡

#AlAin
@dwamharic_news @dwamharicnewsbot
#UPDATE

ፈረንሳይ የሩዋንዳ የዘር ጭፍጨፋ ተጠርጣሪውን ፍሊሲያ ካቡጋን አሳልፋ ለመስጠት ተስማማች።

የፈረንሳይ ፍርድ ቤት ፍሊሲያ ካቡጋ ለመንግስታቱ ድርጅት ዓለም አቀፍ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ተላልፎ እንዲሰጥ ወስኗል - #AlAin

@dwamharic_news @dwamharicnewsbot
ደቡብ አፍሪካ ለቀጣዮቹ ሶስት ሳምንታት አርብ አርብ ጥቁር እንዲለበስ ጥሪ አቀረበች!

መሪው የደቡብ አፍሪካ ፓርቲ ኤ.ኤን.ሲ የዛሬዋን ዕለተ አርብ ጥቁር ቀን በሚል ጆርጅ ፍሎይድ እንዲታሰብ አወጀ፡፡ መታሰቢያ ስነ ስርዓቱ ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎዛ በሚያደርጉት ንግግር በይፋ እንደሚጀመር ያስታወቀው ፓርቲው ደቡብ አፍሪካውያን ለቀጣዮቹ ሶስት ሳምንታት አርብ አርብ ጥቁር በመልበስ ከአሜሪካ ህዝብ ጎን መቆማቸውን እንዲያሳዩ ጥሪ አቅርቧል፡፡ #AlAin

@dwamharic_news @dwamharicnewsbot
ፈረንሳይ ባዘጋጀችው 1000 የአፍሪካ ስራ ፈጣሪዎች ውድድር 11 ኢትዮጵያውያን አሸነፉ

ውድድሩ በአፍሪካ-ፈረንሳይ ጉባዔ 2020 ዋና ጸሃፊ እና ዲጂታል አፍሪካ ትብብር የተዘጋጀ ሲሆን በመጠጥ ውሃ እና ሳኒቴሽን፣በኢነርጂ ልማት እና በሌሎችም ዘርፎች የተሰማሩ በርካታ አፍሪካዊ ስራ ፈጣሪ ወጣቶች ተሳትፈውበታል፡፡

ስራ ፈጣሪዎቹ ከአህጉሪቱ 53 ሃገራት የተውጣጡ ሲሆኑ ውድድሩን ካሸነፉ 1 ሺ ስራ ፈጣሪዎች መካከል 11ዱ ኢትዮጵያውያን መሆናቸውንም የፈረንሳይ ኤምባሲ የውድድሩን አዘጋጆች ጠቅሶ አስታውቋል፡፡ አሸናፊዎቹ ገንዘብን ጨምሮ የተለያዩ የሙያና የስልጠና ድጋፎችን ያገኛሉ እንደ አዘጋጆቹ ገለጻ፡፡

28ኛው የአፍሪካ-ፈረንሳይ ጉባዔ ባሳለፍነው ሳምንት በፈረንሳይ ቦርዶ ከተማ ሊዘጋጅ እቅድ ተይዞለት የውድድሩ አሸናፊዎች ጉባዔውን እንዲታደሙ ግብዣ ተደርጎላቸውም ነበር፡፡ ሆኖም በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት ሳይሳካ ቀርቷል፡፡

#AlAin
@dwamharic_news @dwamharicnewsbot
#GERD

የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ስለሺ በቀለ (ዶ/ር ኢንጂነር) በ2014 ዓ/ም ኃይል ማንጨት የሚጀምሩ 11 ተርባይኖች ተከላ በቀጣዩ አመት እንደሚካሄድ መናገራቸውን አል አይን / #AlAin / ዘግቧል።

ሚኒስትሩ በህንድ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ባዘጋጀው ዌቢናር (የኦንላይን ቨርቹዋል ውይይት) ለተሳተፉ አምባሳደሮች እና ምሁራን የግድቡን የድርድር ሂደቶች እና ቀጣይ ስራዎችን በተመለከተ ሰፊ ማብራሪያን ሰጥተዋል፡፡

በቀጣይ ዓመት ኃይል እንደሚያመነጩ የሚሞከሩትን ሁለት ተርባይኖች ውሃ ማስተላለፊያ ‘ፔንሰቶኮች’ እና ‘ቦተም አውትሌት’ ለማጠናቀቅ ይሰራል ያሉት ሚኒስትሩ የተርባይኖቹንና የኤሌክትሪክ ስራዎቹን ማጠናቀቅ እንደሚጠበቅም ገልጸዋል፡፡

ውሃው ሳይቋረጥ እንዲያልፍ፣ የግድቡ ከፍታ ወደ 590 ሜትር እንዲያድግ ከማድረግ እና ተጨማሪ 13 ነጥብ 4 ቢሊዬን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ ከመያዝ ባለፈ በ2014 ዓ/ም ኃይል ማንጨት የሚጀምሩ 11 ተርባይኖች ተከላ እንደሚካሄድም ነው ያስረዱት፡፡

@dwamharic_news @dwamharicnewsbot
ኢትዮጵያ በሁለተኛነት በተፈለፈለው የአንበጣው መንጋ እየተቸገረች ነው

ኬንያ የበርሃ አንበጣን ለማጥፋት በሚያስችል አቋም ላይ እንደምትገኝ የዓለም የምግብና የግብርና ድርጅት (ፋኦ) አስታውቋል፡፡ በመንጋው ከተጠቁ 29 የሃገሪቱ አካባቢዎች 20ዎቹ ነጻ መሆናቸውን ነው የተነገረው፡፡ ሀገሪቱ በቀጣዩ ሦስት ሳምንታት ሙሉ በሙሉ ከመንጋው ነጻ ልትሆን እንደምትችል ተገምቷል፡፡

የድርጅቱ የምስራቅ አፍሪካ መከላከል (ሬዚሊዬንት) ቡድን መሪ ሲሪል ፌራንድ በናይሮቢ በሰጡት መግለጫ ኢትዮጵያ በሁለተኛነት በተፈለፈለው የአንበጣው መንጋ እየተቸገረች እንደምትገኝ የተናገሩ ሲሆን ከኬንያ በፈለሰው መንጋ በከፊል መቸገሯንም ገልጸዋል፡፡ - #AlAin

@dwamharic_news @dwamharicnewsbot
#UPDATE

በወላይታ ዞን በተለይም በተከሰተው ሁከት በትንሹ የ8 ሰዎች ህይወት ማለፉን አል ዐይን ዘግቧል።

ስማቸው እንዲገለፅ ያልፈለጉ የዞኑ ባለስልጣን እንዳረጋገጡት በሶዶ ከተማ ትናንት ለተቃውሞ አደባባይ በወጡ ሰልፈኞ ላይ በፀጥታ ሀይሎች በተወሰደ እርምጃ የ4 ሰዎች ህይወት አልፏል።

በተመሳሳይ በቦዲቲ ከተማ 4 ሰዎች መገደላቸውን ስማቸው እንዲገለፅ ያልፈለጉት ባለስልጣኑ ተናግረዋል።

ከሞቱት በተጨማሪ በርካታ ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸው ሆስፒታል መግባታቸውንም ገልፀዋል።

በደቡብ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ በተሰጠ መግለጫ በተፈጠረው ሁከት አንድ ሰው ብቻ እንደተገደለ ነው የተገለፀው #AlAin

@dwamharic_news @dwamharicnewsbot
#UPDATE

የፌደራል ስነምግባርና ጸረ-ሙስና ኮሚሽን ሀብታቸውን ለማስመዝገብ ፍቃደኛ ያልሆኑ 184 ባለስልጣናት በወንጀል እንዲከሰሱ ስም ዝርዝራቸውን ለፌደራል ፖሊስ መስጠቱን ለአል ዐይን ገልጿል፡፡

ሀብትና ንብረታቸውን ማስመዝገብ ያለባቸው የመንግስት ሹመኞች በተደጋጋሚ እንዲያስመዘግቡ ቢጠየቁም ለማስመዝገብ ፍቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል ብሏል ኮሚሽኑ፡፡

ባለስልጣናቱ ሀብታቸውን እንዲያስቀምጡ ያስቀመጠው ቀነ ገድብ ባለፈው ሀምሌ 30 ለሁለተኛ ጊዜ በማለፉ ምክንያት ተጠያቂ እንዲሆኑ ማድርጉን ኮሚሽኑ ገልጿል፡፡

በቀነገደቡ ማስመዝገብ ያልቻሉ አንድ መቶ ሰማንያ አራት (184) የፌደራና የአዲስ አባባ መገኘታቸውንና እነሱም በህግ ይጠየቃሉ ብሏል ኮሚሽኑ፡፡ ኮሚሽኑ የባለስልጣናቱን ስም ዝርዝር ግን ይፋ አላደረገም - #AlAin

@dwamharic_news @dwamharicnewsbot
በሱዳን ጎርፍ እያስከተለ ያለው ጉዳት መቀጠሉን የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ገለጹ!

የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሃምዶክ ዛሬ በትዊተር ገጻቸው የዘንድሮው የጎርፍ አደጋ ከፍተኛ ዉድመት ያስከተለ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በክረምቱ በተከሰተ የጎርፍ አደጋ የሟቾች ቁጥር 89 መድረሱን የሀገሩስጥ ጉዳዮች ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል፡፡ ከዚህም ባለፈ ከ18 ሺ በላይ ቤቶች ሲወድሙ ተጨማሪ 32,000 ያህል ቤቶች ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡

ዘንድሮ የዓባይ ወንዝ መጠን ከአውሮፓውያኑ 1912 ወዲህ በሱዳን ያልተገመተ ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረሱን የሀገሪቱ የመስኖ እና የዉሃ ኃብት ሚኒስቴር ገልጿል፡፡ #AlAin

@dwamharic_news @dwamharicnewsbot
ሱዳን በጎርፍ ምክንያት የሶስት ወር የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አዋጀች!

የሰዱን የጸጥታና የመከላከያ ምክርቤት እስካሁን ለ99 ሰዎች ሞት ምክንያት በሆነው ጎርፍ ምክንያት ለሶስት ወር የሚቆይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጇን አስታወቀች፡፡

የሱዳን ሰራተኛና ማህበራዊ ልማት ሚኒስትር እንዳሉት ከሞት በተጨማሪ ጎርፉ በ46 ሰዎች ላይ ጉዳት ማድረሱንና ከግማሽ ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ዜጎችን መጉዳቱናከ100ሺ በላይ ቤቶችን ማውደሙን የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል፡፡

በሱዳን በዚህ አመት የተመዘገበው የዝናብ መጠን በፈረንጆቹ 1946ና 1988 ተመዝግቦ የነበረውን ክበረ ወሰን መስበሩን ሚኒስትር ሌና ኢል ሸክ ተናግረዋል፡፡ ምክርቤቱ በፈረንጆቹ 2020 ጎርፉ እያደረሰ ያለውን ጉዳት ለመቀነስ ኮሚቴ አቋቁሟል፡፡ #AlAin

@dwamharic_news @dwamharicnewsbot
በሱዳን መንግስት እና በአማጺያን መካከል የመጨረሻ የሰላም ስምምነት ተፈረመ!

የሱዳን የሽግግር መንግስትና የሪቮሉሽናሪ ግምባር ጥምረት የመጨረሻውን የሰላም ስምምት የተለያዩ ከአለም አቀፍ ማህበረሰብ፤ከአፍሪካና ከሱዳን የተውጣጡ ተወካዮች በታደሙበት በደቡብ ሰዱን ተፈራርመዋል፡፡

ስምምነቱ በዋነኝነት በፀጥታ ፣ በመሬት ባለቤትነት ፣ በሽግግር ፍትህ ፣ በስልጣን ማጋራት እና በጦርነት ምክንያት ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው የተሰደዱ ሰዎችን መልሶ ማቋቋም ላይ ያተኮረ ነው፡፡

በተጨማሪም የአማጺ ኃይሎችን ማፍረስ እና ተዋጊዎቻቸውን ወደ ብሔራዊ ጦር ስለማቀላቀልም ይመለከታል፡፡ በፈረንጆቹ 2003 አማጺያን መሳሪያ ካነሱ በኋላ በዳርፉር ብቻ በተካሄደው ውጊያ 300ሺ ያህል ሰዎች ለህልፈት መዳረጋቸውን የሲጂቲኤን ዘገባ ያሳያል፡፡

በፊርማ ስነ ስርአቱ የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሃምዶክ፣የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ መሐማት፣ የኢትዮጵያ፣ የጅቡቲ፣ የሶማሊያ፣የቻድ ፕሬዚዳንቶች ፤ የግብጽ ጠቅላይ ሚኒስትርና ሌሎችም ባለስልጣናት ተገኝተዋል፡፡

#AlAin
@dwamharic_news @dwamharicnewsbot