ዶይቸ ቬለን | DW AMHARIC NEWS🇪🇹
2.93K subscribers
2.46K photos
76 videos
2 files
336 links
ይህ የዶይቼ ቬለ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው። ትኩስ ዜና፣ በአበይት ፖለቲካዊ፣ ኤኮኖሚያዊ፤ ማኅበራዊ እና ባሕላዊ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩር ትንታኔ ያቀርባል

DW AMHARIC NEWS IS A GLOBAL NEWS AND INFORMATION CHANNEL FROM A GERMAN INTERNATIONAL BROADCASTER DEUTSCHE WELLE (DW)
Download Telegram
#DrLiaTadesse

የምስራቅ አፍርካ አገራት የልማት በየነ መንግስታት IGAD ለጤና ሚኒስቴር 800 ሺ ብር የሚገመት ለኮቪድ-19 የመከላከያ ቁሳቁሶች ድጋፍ ማድረጉን ዶክተር ሊያ ታደሰ ተናግረዋል።

የተደረገው ድጋፍ በድንበር ላይ ፤ በተፈናቃዮቸ አከባቢ እና በስደተኞች ካምፕ የሚሰራውን የኮሮና ቫይረስ የመከላከል ተግባርን ለማገዝ የሚዉል ነው ተብሏል።

@dwamharicnewsbot @dwamharic_news
#DrMercyMwangangi

በኬንያ የሟቾች ቁጥር 42 ደርሷል ፤ ባለፉት 24 ሰዓት የሁለት (2) ሰዎች ህይወት አልፏል።

በተጨማሪ 1,486 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ ሃያ አንድ (21) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 758 ደርሷል።

በሌላ በኩል በትላንትናው ዕለት 3 ሰዎች ከበሽታው ማገገማቸውን ተከትሎ አጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 284 ደርሷል።

@dwamharic_news
#DrLiaTadesse

ድንበር ተሻጋሪ ሾፌሮች ለኮሮና ቫይረስ ተጋላጭ እንዳይሆኑ አስፈላጊውን ጥንቅቄ ማድረግ እንዳለባቸው የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ አሳስበዋል።

በድንበር አካበቢ የሚኖሩ ማኅበረሰቦች የቫይረሱን ሥርጭት ለመግታት በሚደረገው ጥረት ላይ የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡም ጥሪ አቅርበዋል።

የቫይረሱን ሥርጭት ለመግታት ወደ ኢትዮጵያ የሚያስገቡና የሚያስወጡ በሮች ላይ ከፍተኛ ቁጥጥር እየተደረገ መሆኑንም ጠቅሰዋል።

ነገር ግን በጎረቤት ሀገራት ያለው የቫይረሱ ሥርጭት መጨመሩ ጋር ታያይዞ አሁንም በእነዚህ አካባቢዎች ጥብቅ ቁጥጥር ያስፈልጋል ብለዋል።

በተለይ በሥራ ምክንያት የኢትዮጵያን ድንበር አቋርጠው የሚያሽከረክሩ ሾፌሮች ለኮሮና ቫይረስ ተጋላጭ እንዳይሆኑ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉም አሳስበዋል።

በድንበር አካበቢ ያለውን ቁጥጥር ይበልጥ ለማጠናከር አዳዳስ አሰራሮች እየተተገበሩ መሆኑን ጠቁመው ፤ አሰራሮችን በሚመለከትም በቅርብ ለሕዝብ የተጠናቀረ መረጃ እንደሚሰጥ ቃል ገብተዋል።

በሕገወጥ መንገድ ድንበሮችን ተሻገረው ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ ሰዎችን በለይቶ ማቆያ ለማስገባት ደግሞ የማኅበረሰቡ ትብብር እጅጉን እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።

በመሆኑም የአካበቢው ማኅበረሰብ ይህን ተረድቶ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል።

#ENA

@dwamharic_news
#UPDATE

ጃክሮስ አካባቢ በሚገኘው የአቢሲኒያ ባንክ የረር በር ቅርንጫፍ ላይ ግንቦት 5 ቀን 2012 ዓ.ም. ለግንቦት 6 አጥቢያ የዘረፋ ሙከራ ሙሉ በሙሉ መክሸፉን ባንኩ አስታውቋል፡፡ ቅርንጫፉም የአገልግሎት መስተጓጎል ሳይገጥመው በዛሬው ዕለት ሙሉ የባንክ አገልግሎቱን እየሰጠ ይገኛል ሲል ነው ባንኩ የገለጸው፡፡ ጉዳዩን ፖሊስ እየመረመረው መሆኑን ከማሳወቁ ውጪ ስለዘረፋው ዝርዝር መረጃ አልሰጠም፡፡

@dwamharic_news
ጉራጌ ዞን በመስቃንና ማረቆ መካከል በተፈጠረ ግጭት የ3 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገለጸ፡፡

( በኢትዮ ኤፍ ኤም የቀረበ )

በደቡብ ክልል ጉራጌ ዞን በሚገኙት የመስቃንና ማረቆ ወረዳዎች መካከል በተለያዩ ጊዜያት የሚነሱት ግጭቶች ለሰዎች ህይወት ማለፍ ምክንያት መሆናቸውን ቀጥለዋል፡፡

ከሰሞኑን በዞኑ ሁለት ወረዳዎች መካከል በተነሳ የግለሰቦች ፀብ የ3 ሰዎች ህይወት ማለፉን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ መሃመድ ጀማል ለኢትዮ ኤፍኤም ተናግረዋል፡፡ በአካባቢው ያለው የፀጥታ ሃይልም ፀቡን በጊዜ ማስቆም መቻሉንና በአሁኑ ሰዓትም ዞኑ ሰላማዊ እንቅስቃሴ ላይ እንደሚገኝ ነግረውናል፡፡

የስርቆትና የእርስ በእርስ ትንኮሳዎች እንዲሁም የተለያዩ ምክንያቶች ለማረቆና መስቃን ወረዳዎች የፀብ መነሻ መሆናቸውን የነገሩን አቶ መሃመድ በወረዳዎቹ መካከል በተደጋጋሚ የሚፈጠረውን ግጭት ለማስቆም ጥረቶች ቢደረጉም ችግሩን በዘላቂነት መፍታት ያለመቻሉንም ነግረውናል፡፡

ከዚህ ቀደም በወረዳዎቹ መካከል ሰላምን ለመፍጠር ተደጋጋሚ ወይይቶች ተደርገዋል፤ ለችግሩም ተጠያቂ ናቸው የተባሉ አካላት ለፍርድ እንዲቀርቡ ተደርጓል ያሉን አቶ መሃመድ ችግሩን የሚፈጥሩ ግለሰቦች የአካባቢውን ሰላም ለማስጠበቅ በሆደ ሰፊነት ለማለፍ አለመቻላቸው ፀቡ ዛሬም ድረስ እንዲቀጥል አድርጎታል ብለውናል፡፡

በአሁኑ ሰዓትም በአካባቢው የሚገኘው የፀጥታ ሃይል ሄኔታውን በመቆጣጠር ሰላምን የማስቀጠል ግዴታውን በመወጣት ላይ እንደሚገኝ አቶ መሃመድ ተናግረዋል፡፡

@dwamharic_news
በደቡብ ሱዳን የመጀመሪያው ሞት ተመዘገበ!

በደቡብ ሱዳን ከኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ጋር በተገናኘ የመጀመሪያው #ሞት መመዝገቡ ተሰምቷል።

ከዚህ በተጨማሪ በሀገሪቱ በአንድ ቀን 28 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 231 ደርሰዋል።

@dwamharic_news
ደቡብ ሱዳን ሟቾችን እየደበቀች ነው?

የደቡብ ሱዳን 2 ዶክተሮች ሀገራቸው የኮቩድ-19 ሞቶችን ሪፖርት እያደረገች አይደለም ብለዋል!

ሁለት (2) በኮቪድ-19 ላይ የሚሰሩ ዶክተሮች የሀገሪቱ መንግስት በኮቪድ-19 የሚሞቱ ሰዎችን ሪፖርት እያደረገች አይደለም ሲሉ ለ #SSNN ተናግረዋል።

አንደኛው የህክምና ዶክተር በጁባ ወታደራዊ ሆስፒታል በኮቪድ-19 ላይ የሚሰሩ ሲሆን ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ሳይቀሩ በኮሮና ቫይረስ ሞተዋል ፤ የሀገሪቱ መንግስት ግን ሪፖርት አላደረገም ብለዋል።

ሌላኛው ዶክተር 'የደህንነት የፀጥታ አካላት' ስለመንግስት የስራ ኃላፊዎች የኮቪድ-19 ሞት ለየትኛውም ሚዲያ እንዳትናገሩ ብለውናል ሲል ለSSNN ገልፀዋል ፤ በሀገሪቱ የመጀመሪያው ሞት የተመዘገበው ሚያዚያ ወር ነው የቀድሞው የደቡብ ሱዳን የፍትህ ሚኒስትር ፓውሊኒሆ ዋናዊላ ሁናጎ ሲሞት ነገር ግን መንግስት ሪፖርት አላደረገም ሲሉ ለ#SSNN ተናግረዋል።

@dwamharic_news
10ሺ ስደተኛ ኢትዮጵያዊያን ወደ ሀገራቸው መግባታቸውን ተ.መ.ድ አስታወቀ፡፡

( በኢትዮ ኤፍ ኤም የቀረበ )

እነዚህ ዜጎች በህወጥ መንገድ ወደ መካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ገብተው የነበሩና ወደሌሉች የአፍሪቃ ሀገራት ለመግባት የሞከሩ ስለመሆናቸው ተናግሯል ኤጀንሲው፡፡

ኮቪድ -19 በዓለም አቀፍ ደረጃ ወረርሽኝ መባሉን ተከትሎ ከመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት እና ከሌሉች የአፍሪካ ሀገራት ቢያንስ 10 ሺህ ያልተመዘገቡ ስደተኞች ወደ ኢትዮጵያ መመለሳቸውን ነው የተባበሩት መንግስታት የስደትኞች ኤጀንሲ ለቢቢሲ አፍሪካ የገለጸው፡፡

ከእነዚህ ተመላሾች ውስጥ በመጋቢት ወር ላይ ወደ ደቡብ አፍሪካ በመጓዝ ላይ እያሉ በሞዛቢክ ድንበር ላይ ህይወታቸውን አጥተው ከነበሩት ጋር የነበሩ አስራ አንድ ወጣቶችም ይገኙበታል ተብሏል፡፡

@dwamharic_news @dwamharicnewsbot
#DrLiaTadesse

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 15 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል!

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 3,707 ላቦራቶሪ ምርመራ 15 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 287 ደርሷል።

ቫይረሱ የተገኘባቸው ሁሉም ወንድ ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ እድሜያቸው ከ17 እስከ 38 ዓመት የሆኑ ናቸው።

ቫይረሱ የተገኘባቸው 8 ሰዎች ከአዲስ አበባ ሲሆኑ፣ 2 ሰዎች ከቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል (ጉባ ለይቶ ማቆያ)፣ 1 ሰው ከአፋር ክልል (ሰመራ ለይቶ ማቆያ)፣ 1 ሰው ከአማራ ክልል (መተማ ለይቶ ማቆያ) እና 3 ሰዎች ከሶማሌ ክልል (ጅግጅጋ ለይቶ ማቆያ) ይገኛሉ።

የዕለቱ ታማሚዎች የጉዞ ታሪክና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ያላቸው ግንኙነት ፦

• የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው - 7

• በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያላቸው - 7

• የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ እና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት የሌላቸው - 1

ተጨማሪ መረጃ ፦

በትላትናው ዕለት አራት (4) ሰዎች ከአዲስ አበባ ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን አጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር አንድ መቶ አስራ ሁለት (112) ደርሷል።

@dwamharic_news
@dwamharicnewsbot
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ስለተገኙት 2 ግለሰቦች!

በጤና ሚኒስቴር እንደተገለፀው በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በሁለት (2) ሰዎች ላይ የኮሮና ቫይረስ ተገኝቷል። ቫይረሱ የተገኘባቸው በክልሉ ግንቦት 5/2012 ዓ.ም ከተላኩት 63 ናሙናዎች መካከል ነው።

ሁለቱ (2) ግለሰቦች የ35 እና የ29 አመት ዕድሜ ያላቸው እና #ከሱዳን በጉባ ወረዳ በአልመሀል ቀበሌ በኩል ወደ ኢትዮጵያ የገቡና በፖዌ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ የቆዩ ናቸው።

የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጤና ጥበቃ ቢሮ ሀላፊ ወይዘሮ ፍሬህይወት አበበ በክልሉ የኮሮና ቫይረስ በመገኘቱ ህብረተሰቡ ሳይደናገጥ በጤና ባለሙያዎች የተቀመጡ መመሪያዎችን ተግባራዊ በማድረግ ራሱንና ህብረተሰቡን መታደግ እንዳለበት አሳስብዋል።

@DWAMHARIC_NEWS
@DWAMHARICNEWSBOT
በአዲስ አበባ ጀርመን አደባባይ በተፈጠረ ከባድ የእሳት አደጋ የ5 ሰዎች ህይወት አለፈ።

አደጋው በትናንትናው ዕለት በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለከተማ ወረዳ 2 የእንጨት እና ችቡድ ማምረቻ ድርጅት ላይ መድረሱን የአዲስ አበባእሳትና አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን አስታውቋል። በበዚህ አደጋ የ5 ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን 5 ሰዎች ደግሞ ከባድ ጉዳት አጋጥሟቸዋል ብሏል።

አደጋውን ለመቆጣጠር ከ100 በላይ የእሳት አደጋ መከላከል ሰራተኞች የተሳተፉ ሲሆን የወደመው ንብረት ከባድ በመሆኑ የአደጋው መንስኤ በመጣራት ላይ መሆኑንም ኮሚሽኑ ገልጿል። ትናንት 10 ሰዓት ላይ እንደተከሰተ የተገለጸው ይህ አደጋ ሌሊት 8 ሰዓት ላይ መቆጣጠር እንደተቻለም ተገልጿል።

@dwamharic_news
@dwamharicnewsbot
የኮሮና ክትባት በአመት ውስጥ እውን ሊሆን ይችላል!

በአውሮፓ ለሚዘጋጁ የክትባት መድኃኒቶች ፍቃድ የሚሰጠው የአውሮፓ ህብረት ኤጀንሲ ተስፋ የተጣለበት የኮሮና ቫይረስ ክትባት በቀጣዩ አንድ ዓመት ውስጥ እውን ሊሆን እንደሚችል አስታውቋል - #AlAin

@dwamharic_news @dwamharicnewsbot
#DrRashidAman

በኬንያ የሟቾች ቁጥር አርባ አምስት (45) ደርሷል። ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ የሶስት (3) ሰዎች ህይወት ማለፉ ሪፖርት ተደርጓል።

በተጨማሪ 2,100 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ ሃያ ሶስት (23) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 781 ደርሷል።

@dwamharic_news @dwamharicnewsbot
ዛሬ በቃሊቲ ጉሙሩክ ጣቢያ የድንበር ተሻገር አሽከርካሪዎችና ረዳቶች የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ተጀምሯል!

#FTA

የድንበር አቋራጭ ከባድ የመኪና አሽከርካሪዎች እና ረዳቶች ለወረርሽኙ ካላቸው ተጋላጭነት አንጻር በወደቡ ገቢ ጭነት ሲያራግፉም ሆነ ወጪ ጭነት ሲጭኑ በሚኖረው ሂደት የዘመቻ ስራው በከፍተኛ ጥንቃቄ እየተከናወነ ይገኛል ተብሏል፡፡

ከአሁን በፊትም በወደቡ የሰው ንክኪ በሚበዛባቸው አካባቢዎች እንዲሁም ገቢ ጭነት ይዘው የሚገቡ ተሽከርካሪዎችን የጸረ ተህዋስያን ኬሚካል ርጭት የማካሄድ ፣ ማንኛውም አሽከርካሪና እና ረዳት ወደ ወደቡ ሲገባ እና ጭኖ ሲወጣ የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ማስክ እና የሙቀት ልኬት ማድረግ አስገዳጅ ሆኖ እየተሰራበት እንደሚገኝ ተገልጿል።

ዛሬ ግንቦት 07 ቀን 2012 ዓ/ም ደግሞ ከኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት ጋር በመተባበር በአሽከርካሪዎች እና ረዳቶች ላይ የኮሮና ቫይረስ ምርመራ የተጀመረ መሆኑን የፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን አሳውቋል።

@dwamharic_news @dwamharicnewsbot
በአዲስ አበባ የቱርክ ኤምባሲ በቦሌ ከሚገኘው ስናፕ ፕላዛ የአገልግሎት ማዕከሉ ከግንቦት 10 ጀምሮ የቪዛ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምር አስታውቋል፡፡

የኢትዮጵያ እና የቱርክ ዲፕሎማሲዊ ግኑኝነት1933 ዓ.ም ከተመሰረተበት ጊዜ አንስቶ የንግድ እና ኢንቨስትመንት ትስስራቸው ከ1 ቢሊዮን ዶላር በላይ ደርሷል፡፡

በአሁኑ ወቅት ከ500 በላይ የቱርክ ኩባንያዎች በጨርቃጨርቅ፣ ኬሚካል እና ኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪዎች በመሳተፍ ላይ ሲሆኑ ቱርክ በተለይ በኢትዮጵያ በአዋሽ ኮምቦልቻ የባቡር መስመር ዝርጋታ በመስራት አጋርቷን እያሳየች ትገኛለች ሲል ኢትዮ ኤፍ ኤም ዘግቧል፡፡

@dwamharic_news @dwamharicnewsbot
በአዲስ አበባ የቱርክ ኤምባሲ በቦሌ ከሚገኘው ስናፕ ፕላዛ የአገልግሎት ማዕከሉ ከግንቦት 10 ጀምሮ የቪዛ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምር አስታውቋል፡፡

የኢትዮጵያ እና የቱርክ ዲፕሎማሲዊ ግኑኝነት1933 ዓ.ም ከተመሰረተበት ጊዜ አንስቶ የንግድ እና ኢንቨስትመንት ትስስራቸው ከ1 ቢሊዮን ዶላር በላይ ደርሷል፡፡

በአሁኑ ወቅት ከ500 በላይ የቱርክ ኩባንያዎች በጨርቃጨርቅ፣ ኬሚካል እና ኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪዎች በመሳተፍ ላይ ሲሆኑ ቱርክ በተለይ በኢትዮጵያ በአዋሽ ኮምቦልቻ የባቡር መስመር ዝርጋታ በመስራት አጋርቷን እያሳየች ትገኛለች ሲል ኢትዮ ኤፍ ኤም ዘግቧል፡፡

@dwamharic_news @dwamharicnewsbot