DW Amharic
56.4K subscribers
4.14K photos
984 videos
69 files
15.7K links
ይህ የዶይቼ ቬለ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው። ትኩስ ዜና፣ በአበይት ፖለቲካዊ፣ ኤኮኖሚያዊ፤ ማኅበራዊ እና ባሕላዊ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩር ትንታኔ ያቀርባል።
Download Telegram
የቀድሞው የጥረት ኮርፖሬት ሥራ አስፈፃሚ አቶ ምትኩ በየነ ከእስር እንዲፈቱ የሚጠይቅ ሰልፍ በአማራ ክልል በዋግኸምራ ዞን ሰቆጣ ከተማ ተካሔደ። አቶ ምትኩ ክልሉን የሚያስተዳድረው ፓርቲ ንብረት የነበረው ጥረት ኮርፖሬትን በሥራ አስፈፃሚነት ሲመሩ ባልተገባ መንገድ የኮርፖሬሽኑ ገንዘብ እንዲባክን አድርገዋል በሚል ተጠርጥረው በእስር ላይ ይገኛሉ። https://p.dw.com/p/3ZQaA?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የመጀመሪያውን የምርጫ ካርታ በዛሬው ዕለት ይፋ አደረገ። ሲዳማ 10ኛው የኢትዮጵያ ክልል እንዲሆን በሕዝበ-ውሳኔ ቢጸድቅም የሥልጣን ሽግግር ባለመደረጉ ራሱን ችሎ የምርጫ ካርታ ሳይዘጋጅለት ቀርቷል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሁለት ሺሕ ገደማ ባለሙያዎች አሰማርቶ ለካርታው ዝግጅት መረጃ ማሰባሰቡን የቦርዱ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ አስረድተዋል።
ብርቱካን እንዳሉት የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ እስካሁን "547 የምርጫ ክልሎች መኖራቸውን ከመግለፅ ባለፈ በካርታ ይፋ የምርጫ ክልል ኖሮት" አያውቅም።
https://p.dw.com/p/3ZQbP?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
ኢትዮጵያ ውስጥ አዲስ ሶስት ሰዎች በኮሮና ተሐዋሲ መያዛቸውን የሃገሪቱ የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ በትዊተር ገፃቸው አስታወቁ። በተህዋሲው መያዛቸው የተረጋገጡት ሰዎች ሁለት የ 44 እና የ47 ዓመት ጃፓናውያን እና አንድ የ42 ዓመት ኢትዮጵያዊ ናቸው ተብሏል። ሁሉም ሰዎች አዲስ አበባ ውስጥ የሚሰሩ እና ከሁለት ቀን በፊት በሽታው ከተረጋገጠበት አንድ የጃፓን ዜጋ ጋር በቅርበት ይሰሩ እንደነበርም ተገልጿል። በሽታው የተረጋገጠባቸው የመጀመሪያው ታማሚ የጤና ሁኔታም መሻሻል እያሳየ መሆኑ ተገልጿል። ሚኒስቴሩ ከዚሁ ሰው ጋር በተያያዘ ንክኪ የነበራቸው 117 ሰዎችም ተገልለው እንደሚገኙ አስታውቋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ኢትዮጵያ ውስጥ ብዙ ሰዎች የሚሰበሰቡባቸው ዝግጅቶች መካሄዳቸው ቀጥሏል። ዛሬ ብቻ 15 ሺ የሚሆኑ ሴቶች ተካፍለውበታል የተባለው ቅድሚያ ለሴቶች የተሰኘው የሩጫ ውድድር አዲስ አበባ ውስጥ ተካሂዷል።
ተጨማሪ የፌዴራል የሥራ ቋንቋዎች በኢትዮጵያ?
ከሰሞኑ የሚንሥትሮች ምክር ቤት በኢትዮጵያ የሥራ ቋንቋ ከአማርኛ በተጨማሪ አራት ቋንቋዎችም እንዲጨመሩ ወስኖ ለተወካዮች ምክር ቤት መርቷል። ኢትዮጵያ ውስጥ የፌዴራል ተጨማሪ የሥራ ቋንቋ እንዲኾኑ በሚንሥትሮች ምክር ቤት ውሳኔ የተሰጠባቸው፦ ኦሮሞኛ፤ ትግሪኛ፤ ሶማሊኛ እና አፋርኛ ናቸው።https://p.dw.com/p/3ZPFj?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
ከኮሮና ተህዋሲ ጋር በተያያዘ ዩናይትድ ስቴትስ ከአውሮፓ እና ወደ አውሮፓ የሚደረጉ በረራዎች ላይ የጣለችውን እገዳ አሰፋች። ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ እንደገለፁት እገዳው ከዛሬ ጀምሮ ብሪታንያ እና አየርላንድንም ይመለከታል። እነዚህ ሁለት ሀገራት በቅርቡ በ26 የአውሮፓ ህብረት ሀገራት ዘንድ ተግባራዊ መደረግ በጀመረው እገዳ አልተካተቱም ነበር። በሌላ በኩል በህዝብ ግፊት ናሙና የሰጡት ትራምፕ በኮሮና ተህዋሲ አለመያዛቸው ተገልጿል። ትራምፕ እንዲመረመሩ ጫና የተደረገባቸው ፍሎሪዳ ውስጥ ከአንድ በተህዋሲው መያዙ ከተረጋገጠ ሰው ጋር ንክኪ ነበራቸው በሚል ነው። ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ እስካሁን ከ 3000 በላይ ሰዎች በተህዋሲው ተይዘዋል።LA/TG
በኮሮና ተህዋሲ ስርጭት ስጋት ያደረባቸው በርካታ የአፍሪቃ ሀገራት ርምጃቸውን እያጠናከሩ ይገኛሉ። እስካሁን በተህዋሲው 28 ሰዎች መያዛቸውን ያረጋገጠችው ሞሮኮ ማንኛውንም አለም አቀፍ በረራዎችን እንደምታቋርጥ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሯ ዛሬ አስታውቋል።
ግብፅ በኮሮና ተህዋሲ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር መጨመሩን ተከትሎ ትምህርት ቤቶችን እና ዩንቨርስቲዎችን ለሁለት ሳምንት እንደምትዘጋ አስታወቀች። በተህዋሲው የተያዙ ሰዎች ቁጥር ወደ 110 ከፍ ብሏል። የኮሮና ተህዋሲ እስካሁን ባልተረጋገጠባት ሊቢያም ከሰኞ ጀምሮ ድንበሯን እንደምትዘጋ እና የአየር በረራዎችን ለ ሶስት ሳምንታት እንደሚቋረጡ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እውቅና ያገኘው መንግሥቷ አስታውቋል። የሀገሪቱ ሁለቱም ተቀናቃኝ ኃይላት ከነገ ጀምሮ ትምህርት ቤቶች እና ዩንቨርስቲዎች ለሁለት ሳምንታት እንደሚዘጉ ዓርብ ዕለት አስታውቀዋል። የኮሮና ቫይረስ እስካሁን በአፍሪቃ 26 ሀገራት ተረጋግጧል።
መንግስት ኃላፊነቱን እንዲወጣ ኢዜማ ጠየቀ
መንግስት የሀገሪቱን ሰላም የማረጋጋት ኃላፊነቱን እንዲወጣ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ጠይቋል።ኢዜማ ጥሪውን ያቀረበው ሀገር አቀፍ የወጣቶች የሰላም ኮንፍረንስ በአዲስ አበባ ባካሄደበት ወቅት ነው። https://p.dw.com/p/3ZTVI?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
የኮሮና ወረርሽኝን በተሻለ መልኩ ለመግታት እንዲያስችል በሚል ስፔን በዜጎቿ ላይ ሀገርአቀፍ የእንቅስቃሴ እገዳ ጣለች። ከአውሮፓ ጣሊያንን ተከትላ ይህንን እገዳ በጣለችው ስፔን ከ 7700 በላይ ሰዎች በተህዋሲው የተያዙ ሲሆን ከ 1350 በላይ ደግሞ ሞተዋል። 47 ሚሊዮን ገደማ የሚሆኑ ነዋሪዎቿ ከቤት መውጣት የሚፈቀድላቸው ሀኪም ቤት እና ገበያ የመሳሰሉ ለመኖር መሠረታዊ የሆኑ ነገሮችን ለመፈፀም ብቻ ይሆናል። ሌሎች እንደ ጀርመን፣ ፈረንሳይ ፣ ኦስትሪያ የመሳሰሉ ሀገራትም እገዳቸውን እያጠናከሩ ይገኛሉ። ሀገራቱ ምግብ ቤት፣ሲኒማ የመሳሰሉ የመዝናኛ ቦታዎችን መዝጋታቸውን አጠናክረው ቀጥለዋል። ፖላንድ ከእኩለ ሌሊት ጀምሮ ወደ ሀገሯ የውጭ ሀገር ሰዎች እንዳይገቡ ከልክላለች።
«አስቸጋሪ ምርጫዎች» ድራማ፥ ክፍል 2
ይህ «አስቸጋሪ ምርጫዎች» በሚል ርዕስ የሚቀርብላችሁ የወንጀል ተፋላሚዎቹ ተከታታይ ድራማ ሁለተኛ ክፍል ነው። https://p.dw.com/p/3ZTTx?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
የኮሮና ተህዋሲ ስርጭትን ለመግታት ጥብቅ ርምጃ ባስተላለፈችው ፈረንሳይ ዛሬ የአካባቢ ምርጫ ተካሄደ። ምንም እንኳን ፈረንሳይ ከእኩለ ሌሊት አንስቶ ሰዎች እንደልብ እንዳይንቀሳቅሱ እገዳ ብትጥልም በሌላ በኩል 48 ሚሊዮን የሚጠጉ ዜጎቿ የአካባቢ ተወካዮቻቸውን እንዲመርጡ ጥሪ ተደርጎላቸዋል። በዛሬው ምርጫ በርካታ ሰዎች በበሽታው እንዳይያዙ በመስጋት እንዳልተሳተፉ የፈረንሳይ ዜና ምንጭ ዘግቧል። ለሀገሪቱ የፖለቲካ ሂደት ወሳኝ ነበር የተባለው ምርጫ በሀገሪቱ ለወራት የተቃውሞ አመፅ ያስነሳውን የፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮ የጡረታ ማሻሻያን በሚመለከት ፓርቲያቸው ምን አይነት ውጤት እንደሚያገኝ በጉጉት እየተጠበቀ ነበር።
ኢትዮጵያ ለሚቀጥሉት አስራ አምስት ቀናት ትምህርት ቤቶች፣ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችና ትላልቅ ስብሰባዎችን ከለከለች። የአገሪቱ 45 ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ባሉበት ትምህርታቸውን ይቀጥላሉ ተብሏል።
የጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አሕመድ መንግሥት ከውሳኔው የደረሰው አራት ሰዎች በኮሮና ተህዋሲ መያዛቸው ከተረጋገጠ በኋላ ነው። ጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አሕመድ በዛሬው ዕለት በሰጡት መግለጫ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ባሉበት ሆነው አስፈላጊው ክትትል ይደረግላቸዋል ማለታቸውን የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።
የኢትዮጵያ መንግሥት እና የጤና ሚኒስቴር የበሽታውን ስርጭት ለመቆጣጠር እና በተህዋሲው የተያዙ ሰዎችን ለመለየት እና ርምጃ ለመውሰድ ከተለያዩ አጋሮች ጋር እየሠራ መሆኑን የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ እሁድ ዕለት በሰጡት ገልጸዋል። ማህበረሰቡም የበሽታውን ስርጭት ለመግታት የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ አሳስበዋል። የኮሮና ተህዋሲ እስካሁን በ 26 የአፍሪቃ ሀገራት መሰራጨቱ የተረጋገጠ ሲሆን በርካታ ሀገራት የዓለም አቀፍ በረራዎችን እየሰረዙ እና የትምህርት ተቋማትን እየዘጉ ይገኛሉ። በሳምንቱ መጨረሻ በኢትዮጵያ በርካታ ሰዎች የተሰበሰቡባቸው እንደ «ቅድሚያ ለሴቶች» ሩጫ እንዲሁም የብልፅግና ፓርቲ የገቢ ማሠባሰቢያ ዝግጅቶች በሚሊኒየም አዳራሽ ተካሒደዋል። መርሐ ግብሮቹ የተካሔዱት በአአገሪቱ በኮሮና የተያዘ አንድ ሰው መገኘቱ ከተረጋገጠ በኋላ ነው። የኢትዮጵያ መንግሥት የኮሮና ተህዋሲ ስርጭትን ለመቆጣጠር እየወሰደ ያለው ርምጃ በቂ ነው ትላላችሁ? በተህዋሲው ላለመያዝ በግል የምታደርጉት ጥረት ምን ይመስላል? ሀሳባችሁን አጋሩን? 👉🏾 @dwamharicbot
የተከበራችሁ የማህበራዊ የመገናኛ ብዙኃን ተከታታዮቻችን የዓለም አቀፍ ስጋት የሆነው የኮሮና ወረርሽኝን የሚመለከቱ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ስርጭቱን ለመግታት ጠቃሚ የሆኑ መረጃዎችን በየጊዜው እና በፍጥነት የምናጋራችሁ ስለሚሆን ገፃችንን ቶሎ ቶሎ ጎብኙ።
የዓለም የጤና ድርጅት ራስን ከኮሮና ተህዋሲ ለመከላከል ጠቃሚ ነው ያለውን መረጃ እናጋራችሁ።
ቪዲዮው እንደሚያብራራው ራስን እና ሌሎችን ከትህዋሲው ስርጭት ለመጠበቅ እጅን ቶሎ ቶሎ በሳሙና እና በውኃ መታጠብ ያስፈልጋል። ሳል ወይም ማስነጠስ ሲኖርብን አፋችንን በክንዳችን በመሸፈን መሳል ወይም ማስነጠስ ይኖርብናል። ወይም ደግሞ ሶፍት መጠቀም ይቻላል። ሶፍትን ከተጠቀምን በኋላ ወዲያውኑ ክዳን ያለው ቁሻሻ መጣያ ውስጥ መጣል እንጂ በኪስ አቆይተን ደግመን መጠቀም አይመከርም። በተቻለ መጠን ትኩሳት ወይም ሳል ካላቸው ሰዎች ጋር በቅርብ ንክኪ እንዳይኖር መራቅ ያስፈልጋል። ሳል፣ ትኩሳት ወይም የመተንፈስ እክል የገጠመው ሰው በቶሎ የህክምና ጣቢያዎችን ሊያማክር ያስፈልጋል። በተቻለ መጠን እቤት መቆየትም ይመከራል።https://www.youtube.com/watch?v=6Ooz1GZsQ70&feature=youtu.be 👉🏾 @dwamharicbot
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ኢትዮጵያ የኮሮና ተህዋሲ ስርጭትን ለመግታት በሚል ለሚቀጥሉት 15 ቀናት ትምህርት ቤቶች፣ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችና ትላልቅ ስብሰባዎችን መከልከሏን ተከትሎ ተማሪዎች ወደየቤታቸው በመመለስ ላይ ይገኛሉ። በሀዋሳ ያለው ሁኔታ ይህን ይመስላል።
የጀርመን ሉፍታንዛ አየር መንገድ ለጉብኝት እና ለእረፍት ወደ ተለያዩ የዓለም ሃገራት የተጓዙ እና በኮሮና ተኅዋሲ ምክንያት ለእረፍት በሄዱበት ሃገር መንቀሳቀስ ያልቻሉ ወደ 4000 የሚሆኑ ጀርመናዉያንን በልዩ በረራ ወደ ሃገር ለመለሰ እየተዘጋጀ መሆኑን አስታወቀ። የአየር መንገዱ ይፋ ባደረገዉ መግለጫ አብዛኞቹ ጀርመናዉያን ቱሪስቶች የሚገኙት በካሪቢያን እና በካናሪ ደሴቶች ላይ ነዉ፤ ረጅም ጉዞን መርጠዉ በግዙፍ በመርከብ የተለያዩ ሃገራትን አቋርጠዉ ወደ ካሪቢያን እና ካናሪ ደሴቶች እየተጓዙ የነበሩ ጀርመናዉያን ቱሪስቶች ናቸዉ። በሌላ በኩል የኮሮና ተኅዋሲ በዓለም ዙርያ ባሉ ሃገሮች እየተዛመተ በመሆኑ እጅግ ካላስፈለገ በስተቀር ጀርመናዉያን ረጅም ጉዞን ባያደርጉ እንዲሁም በርካት ካለ ሰዉ ጋር ላለመቀላቀል ቢሞክሩ ይመረጣል ሲል የሃገሪቱ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መልክት አስተላልፎአል። በሌላ በኩል ሉፍታንዛን ጨምሮ በርካታ የአዉሮጳ ሃገራት አየር መንገዶች የሚያደርጉትን በረራ እያቋረጡ ነዉ። የጀርመኑ ሉፍታንዛ አየር መንገድ ዛሬ ይፋ እንዳደረገዉ፤ ከነገ ማክሰኞ ጀምሮ የመንገደኞች ረጅም በረራን 10 በመቶ፤ በአዉሮጳ ሃገራት የሚŀd,ርገዉን በረራ ደግሞ 20 በመቶ እንደሚቀንስ አስታዉቋል።
በኢራን በኮሮና ተኅዋሲ ተለክፎ የሚሞተዉ ሰዉ ቁጥር ክፉኛ መጨመሩን የሃገሪቱ የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ። ሚኒስቴር መስርያቤቱ ዛሬ ይፋ እንዳደረገዉ፤ በ 24 ሰዓታት ዉስጥ የሟቾች ቁጥር ከ 724 ወደ 853 አሻቅቦአል። በሃገሪቱ ሳራስ -CoV-2 በተባለዉ ተኅዋሲ የተለከፈዉ ሰዉ ቁጥር ወደ 15 ሺህ መድረሱም ተያይዞ ተዘግቦአል። በኮሮና ተኅዋሲ ስርጭት በርካታ ዜጎች ያለቁባት ኢጣልያ በበኩልዋ «አደገኛ ሳምንት» ስትል ተኅዋሲዉ አሁንም እየተፈታተናት እንደሆነ አሳዉቃለች። በኢጣልያ እስካሁን ከ 1800 በላይ ሰዉ ሞትዋል፤ ከ 20 ሺህ የሚበልጥ ሕዝብ ደግሞ በተኅዋሱw ተለክፎአል። የዓለም የጤና ድርጅት ባወጣዉ መረጃ መሰረት COVID-19- በተባለዉ ተኅዋሲ ከቻይና ለጥቆ ኢጣልያእጅግ በርካታ ሰዉ የሞተባት ሃገር ናት። ኢራን እና ኢጣልያ የተኅዋሲዉን ስርጭት ለመግታት የሚያደርጉትን ትግል ቀጥለዋል። እንድያም ሆኖ በሁለቱም ሃገራት በተኅዋሲዉ የታመሙትን ሰዎች ለመርዳት ያለዉ አቅም ሃገራቱን እየተፈታተነ እንደሆነ ነዉ እየተነገረ ።