በውጫሌ በተቀሰቀሰ ግጭት ቢያንስ አራት ሰዎች ተገደሉ
በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን ውጫሌ ከተማ ትናንት ከሰዓት በኋላ በተቀሰቀሰ ግጭት ቢያንስ አራት ሰዎች መገደላቸውን እና በርካቶች መቁሰላቸውን የዐይን ምስክሮች ተናገሩ፡፡ ግጭቱ የተፈጠረው በከተማይቱ ወጣቶች እና ፖሊሶች መካከል ነው።
ነዋሪዎች እንደሚሉት፣ የከተማይቱ ወጣቶች “የአካባቢያችን መሬት ለመንግስት ሰራተኞች ለቤት መስሪያ መሰጠት የለበትም” በሚል ሲቃወሙ ነበር። የዓይን ምስክሮች ለዶይቼ ቬለ እንደነገሩት በግጭቱ በጥይት ተመትተው የሞቱ ወጣቶች እስከ ስድስት ይደርሳሉ። አንድ የዓይን እማኝ በከተማይቱ ካለ ፖሊስ ጣቢያ በተተኮሰ ጥይት ሶስት ሰዎች ተመትተው መሞታቸውን ተመልክቼያለሁ ብለዋል። እኚሁ ምስክር አምስት ሰዎች እንደቆሰሉ ገልጸዋል። በግጭቱ ስድስት ሰዎች መሞታቸውን የሚናገሩት ሌላው የውጫሌ ከተማ ነዋሪ የቁስለኞቹን ቁጥር 12 ያደርሱታል።
ትናንት ከግጭቱ በኋላ የአማራ ክልል ልዩ ኃይል ወደ አካባቢው በመግባት የማረጋጋት ሥራ ማከናወኑን እና ዛሬ ከተማይቱ መረጋጋቷን ነዋሪዎች ተናግረዋል። የአራት ሟቾች የቀብር ስነስርዓት በዛሬው ዕለት መከናወኑንም ገልጸዋል፡፡
የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ አበረ አዳሙ ስለ ግጭቱ በስልክ ተጠይቀው በሰጡት ምላሽ ጉዳዩን የሚያጠና ቡድን ወደቦታው መንቀሳቀሱን ተናግረው ለጊዜው ዝርዝር መረጃ እንደሌላቸው ለዶይቼ ቬለ ገልጸዋል፡፡
(ዘገባ፦ ዓለምነው መኮንን - ከባህር ዳር)
👉🏾 @dwamharicbot

የሀዋሳ ፍርድ ቤት የሲዳማ ግጭት ዘጠኝ ተጠርጣሪዎች በዋስትና እንዲፈቱ ወሰነ
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ ፍርድ ቤት አንደኛ ወንጀል ችሎት በሲዳማ ዞን የተለያዩ አካባቢዎች ተከስቶ የነበረዉን ሁከት ቀስቅሰዋል በሚል ተጠርጥረው የተያዙ ዘጠኝ ግለሰቦች በዋስ እንዲፈቱ ወሰነ።
ፍርድ ቤቱ ዛሬ በዋለው ችሎት በዋስ እንዲፈቱ ከወሰነላቸዉ ተጠርጣሪዎች መካከል የሲዳማ ሚዲያ ኔትዎርክ ዋና ስራ አስኪያጅ ጌታሁን ደጉዬ ፣ ምክትላቸው ታሪኩ ለማ እና የእዚሁ ጣቢያ የቦርድ አባል የሆኑት በላይ ባልጉዳ ይገኙበታል።
ፖሊስ በተጠርጣሪዎቹ ላይ ቀሪ የምስል፣ የድምፅ፣ የሰነድ እና የሰው ማስረጃዎችን ለማሰባሰብ ተጨማሪ የ14 ቀናት የጊዜ ቀጠሮ እንዲሰጠው ፍርድ ቤቱን ጠይቆ ነበር። ፍርድ ቤቱ ግን እስከአሁን አራት የጊዜ ቀጠሮዎች መሰጠታቸውንና መርማሪ ፖሊስም በማስረጃ አሰባሰብ ሂደት አከናወንኩ ያላቸው ስራዎች ተመሳሳይ መሆናቸውን በመጥቀስ የቀረበውን ተጨማሪ የ14 ቀናት የጊዜ ቀጠሮ ዉድቅ አድርጎታል ።
ፍርድ ቤቱ ተጠርጣሪዎቹ እያንዳንዳቸው የ50 ሺህ ብር ዋስትና በማቅረብ ጉዳያቸውን ውጭ ሆነው እንዲከታተሉ ወስኗል። ተጠርጣሪዎቹ ለነሀሴ 14 ቀን 2011 ዓ.ም. እንዲቀርቡም አዟልም።
(ዘገባ፦ ሸዋንግዛው ወጋየሁ - ከሀዋሳ)

👆 በዩኒቨርሲቲ መግቢያ የፈተና ውጤት ላይ የሚቀርቡ ቅሬታዎች ቀጥለዋል
በመቶዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎች እና ወላጆች በ12ኛ ክፍል የዩኒቨርሲቲ መግቢያ የፈተና ውጤት ላይ ያላቸውን ቅሬታ ለማቅረብ ዛሬ አዲስ አበባ በሚገኘው የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ቅጽር ግቢ በር ላይ ተሰባስበው ነበር። ቅሬታ አቅራቢዎቹ ከኤጀንሲው የሚሰጣቸውን ቅጽ ሞልተው ከዚያው ከበር ላይ እንዲመልሱ ተደርገዋል።
በኤጀንሲው የተዘጋጀው የቅሬታ መቀበያ ቅጽ የተማሪዎችን ሙሉ አድራሻ፣ በ2011 ዓ. ም. የትምህርት ዘመን በሁሉም የትምህርት አይነቶች ያስመዘገቡትን ውጤት ዝርዝር እና የሚያመለክቱት ፍሬ ሀሳብ የሚሞላበት ክፍት ስፍራን የያዘ ነው። ካለፈው ሰኞ ጀምሮ ለቅሬታ አቅራቢያዎች መታደሉ የተገለጸው ይህ ቅጽ በኤጀንሲው ድረ ገጽም ላይ ለአመልካቾች ቀርቧል።
ዛሬ ከማለዳው ጀምሮ ቅሬታቸውን ለማቅረብ አምስት ኪሎ ወደሚገኘው የኤጀንሲው ዋና መስሪያ ቤት ያመሩ ተማሪዎች ውጤቱ ዳግም እንዲመረመር ጠይቀዋል። ዶይቼ ቬለ ያነጋገራቸው ተማሪዎች “በፍጹም ያልጠበቅነው ውጤት ነው የተመዘገበው፤ ውጤቱ ሙሉ በሙሉ እንደገና ሊታይ ይገባል” ብለዋል። ከድምር ሰባት መቶ ውጤት ውስጥ ከ30 በታች ያመጣ ተማሪ መኖሩን በማሳያነት ጠቅሰዋል።
የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ አርአያ ገብረእግዚአብሄር ችግር የተስተዋለበት የስኮላስቲክ አፕቲቲዩድ የትምህርት አይነት ብቻ መሆኑን ለዶይቼ ቬለ ገልጸዋል። ይህም ቢሆን “የፈተና ኮድ 21 እና 22 ላይ ብቻ የተከሰተ” መሆኑን የጠቀሱት አቶ አርአያ “ውጤቱ እንደገና ታይቶ እና ታርሞ መጠናቀቁን” አስረድተዋል። አዲሱ ውጤትም ዛሬ ከሰዓት አሊያም ነገ ይፋ ይደረጋል ብለዋል።
ከምሽቱ አንድ ሰዓት በሚጀምረው የራዲዮ ስርጭታችን በዚህ ጉዳይ ላይ ሰፋ ያለ ዘገባ ስለሚኖረን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን።
(ዘገባ እና ፎቶ፦ ሰለሞን ሙጬ - ከአዲስ አበባ)

👆የድሬዳዋ ሪፈራል ሆስፒታል ለዩኒቨርስቲ ተሰጠ
የቪዲዮ ዘገባ፦ በ2002 ዓ.ም ግንባታው ተጀምሮ ዛሬም ድረስ ያልተጠናቀቀው የድሬዳዋ ሪፈራል ሆስፒታል ለድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ ተሰጠ። ሆስፒታሉ ዛሬ በተካሄደ ስነ ስርዓት ወደ ዩኒቨርስቲው እንዲተላለፍ የተደረገው የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ በወሰነው መሰረት ነው።
የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የሆስፒታሉን ቀሪ የግንባታ ስራዎችን አጠናቅቆ የህክምና ማስተማርያና እና ምርምር ማዕከል እንደሚያደርገው በዛሬው የርክክብ ስነ ስርዓት ተገልጿል። የርክክብ ሰነዱን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አህመድ መሀመድ ቡህ እና የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ያሬድ ማሞ ተፈራርመዋል።
ዶ/ር ያሬድ ዩኒቨርስቲው የሆስፒታሉን ቀሪ ስራዎችን ለማጠናቀቅ 200 ሚሊዮን ብር በጀት መመደቡን ተናግረዋል። በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ የግንባታ ስራውን እንደሚያጠናቅቅም ገልጸዋል።
በ324 ሚልዮን ብር በጀት ግንባታው ሲከናወን መቆየቱ የተገለጸው የድሬዳዋ ሪፈራል ሆስፒታል ሲጠናቀቅ ከሶስት መቶ በላይ አልጋዎች እና የተለያዩ የህክምና ማዕከላት ይኖሩታል። ሆስፒታሉ ወደ ዩኒቨርስቲው እንዲዛወር መደረጉ ለከተማይቱ እና አጎራባች አካባቢ ነዋሪዎች በተመጣጣኝ ዋጋ የተሻለ የህክምና አገልግሎት መስጠት የሚችል ተቋም ያደርገዋል ተብሏል።
(ቪዲዮ፦ መሳይ ተክሉ - ከድሬዳዋ)

👆በማልታ ከባህር የተረፈው ኢትዮጵያዊ 14 ሰዎች መሞታቸውን ተናገረ
ከቀናት በፊት በአነስተኛ ጀልባ ላይ ከአስክሬን ጋር የተገኘው ኢትዮጵያዊ ስደተኛ አብረውት የነበሩ 14 ስደተኞች በምግብ እና ውኃ እጥረት ማለቃቸውን ተናገረ። ከሟቾቹ ስደተኞች ውስጥ ኢትዮጵያውያን እንደሚገኙበትም ገልጿል።
ሞሃመድ አደም ኦጋ የተባለው የ38 ዓመቱ ኢትዮጵያ ስደተኛ በሜዴትራንያን ባህር ላይ ትንሳፈፍ ከነበረች አነስተኛ ጀልባ ላይ በነፍስ አድን ሰራተኞች የተገኘው ባለፈው ማክሰኞ ነበር። የማልታ ጦር ሰራዊት ሞሃመድ በጀልባው ላይ እንዳለ ከሞተ ስደተኛ አጠገብ ተንበርክኮ የሚያሳይ ምስል ካሰራጨ በኋላ ጉዳዩ ለቀናት መነጋገሪያ ሆኖ ቆይቷል።
በአሳሳቢ ሁኔታ ላይ እንደነበር የተነገረለት ሞሃመድ በማልታ ወዳለ ሆስፒታል ከተወሰደ በኋላ ህይወቱ ተርፋለች። ኢትዮጵያዊው ስደተኛ በሆስፒታል አልጋ እንዳለ ታይምስ ኦፍ ማልታ ለተሰኘው የሀገሬው ጋዜጣ እንደተናገረው እርሱ እና አብረውት የነበሩት ስደተኞች ለ11 ቀናት በባህር ላይ ቆይተዋል።
በአቅራቢያቸው ያልፉ ለነበሩ መርከቦች እና ሂሊኮፕተሮች የድረሱልን ጥሪ ቢያሰሙም ምላሽ አለማግኘታውንም ስደተኛው ገልጿል። “‘እርዱን! እርዱን’ እያልን እንጮኽ ነበር። እጃችንንም አውለብለብናል። ሆኖም አልፈውን ነው የሄዱት” ሲል ለጋዜጣው አስረድቷል።
“ምግብ አልነበረንም። ውኃም፤ ነዳጅም የለም። ከዚያ የባህሩን ውኃ መጠጣት ጀምርን። ከአምስት ቀን በኋላ ሁለት ሰዎች ሞቱ። ከዚያ በየቀኑ ሁለት ሰዎች ይሞቱ ነበር” ሲል ብቸኛው ተራፊ አስከፊው የሜዲትራንያን የባህር ላይ ጉዞው እንዴት እንደነበር ገልጿል። በባህር ላይ ህይወታቸውን ካጡት መካከል አንዲት ጋናዊ ነፍሰ ጡር ሴት እንደምትገኝበትም ተናግሯል። ከጋናውያን ሌላ ኢትዮጵያውያን እና ሶማሊያውያን ስደተኞች አብረውት እንደነበሩ አብራርቷል።
በስተመጨረሻ ከእርሱ ጋር የቀረው ሶማሊያዊ ስደተኛ ለመሞት ዝግጁ እንደሆነ ገልጾ ሁሉንም ነገር ወደ ባህር ይወረውር ነበር ብሏል ሞሃመድ። ሶማሊያዊው ስልክ እና የአቅጣጫ መጠቆሚያ ጂፒኤስ ጭምር ወደ ባህር ውስጥ መጨመሩን የሚያስታውሰው ስደተኛው ኢትዮጵያዊ “መሞት ከፈልግህ በራስህ ሙት። እኔ መሞት አልፈልግም” የሚል ምላሽ እንደሰጠው ገልጿል።
ከሊቢያ የተነሳው ሞሃመድ ጓደኞቹ ወደሚገኙበት ጀርመን ለመድረስ አልሞ ይጓዝ እንደበር አስረድቷል። ኢትዮጵያዊውን ስደተኛ በመጀመሪያ ከባህር ላይ ያገኙት ፍሮንቴክስ የተሰኘው የአውሮፓ ህብረት የድንበር መስሪያ ቤት ቃኚዎች ናቸው። ቃኚዎቹ ለማልታ ጦር ሰራዊት ሁኔታውን ደውለው ካሳወቋቸው በኋላ የሞሃመድ ህይወት ሊተርፍ ችሏል።

👆በዩኒቨርሲቲ መግቢያ የፈተና ውጤት ላይ የቀረቡ ቅሬታዎች
የቪዲዮ ዘገባ፦ የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ይፋ ያደረገው የ12ኛ ክፍል የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ቅሬታ ማስነሳቱን ተከትሎ ኤጀንሲው ካለፈው ሰኞ ጀምሮ የቅሬታ መቀበያ ቅጽ በመስጠት ቅሬታዎችን እየተቀበለ ይገኛል። በኤጀንሲው ዋና መስሪያ ቤት በአካል መገኘት ቅሬታቸውን ሲያቀርቡ ያገኘናቸው ተማሪዎች ውጤቱ ዳግም እንዲመረመር ጠይቀዋል። ከተለያየ የሃገሪቱ አካባቢዎች የመጡት ወላጆች “የተጠበቀው ቀርቶ ያልተጠበቀው መከሰቱ እንዳሳዘናቸው” ገልጸዋል። መንግስት ትውልድ የደከመበትን ይህንን ጉዳይ በጥሞና እንዲያጤነውም ጠይቀዋል።
የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ አርአያ ግብረእግዚአብሄር ችግር የተስተዋለበት የስኮላስቲክ አፕቲትዩድ የትምህርት አይነት ብቻ መሆኑን ተናግረዋል። ይህም የፈተና ኮድ 21 እና 22 ላይ ብቻ የተከሰተ በመሆኑ እንደገና ታይቶ እና ታርሞ መጠናቀቁን ገልጸዋል። አዲሱ ውጤት ዛሬ አልያም ነገ ይፋ እንደሚደረግ የጠቆሙት ዋና ዳይሬክተሩ ይህን ተከትሎም “ቢያንስ ከተፈታኞች መካከል በግማሽ ያህሉ የተማሪዎች ውጤት ላይ ለውጥ ይኖራል” ብለዋል።
ይሁንና በሁሉም ትምህርቶች ውጤት ላይ እየቀረበ ያለው ቅሬታ ተገቢ ያልሆነ በመሆኑ ተቀባይነት የለውም ብለዋል። “አሁን ተማሪዎች በአካል እየመጡም ይሁን በድረ ገጽ እያቀረቡት ያለው ቅሬታ ኤጀንሲው ችግር አለበት ካለው አይነት በላይ በመሆኑ ቅሬታ ማቅረባቸው ትርጉም አይኖረውም ማለት ነው ወይ?” ስንል አቶ አርአያን ጠይቀናቸዋል። “አዎ! ከንቱ ድካም ነው። በሌሎች ትምህርቶች ላይ የተስተዋለ ችግር የለም። የሚስተካከልም ነገር አይኖርም” ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።
(ቪዲዮ እና ዘገባ፦ ሰለሞን ሙጬ - ከአዲስ አበባ)

ዋና ዋና ዜናዎቹ
በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን አምባሰል ወረዳ ውጫሌ ከተማ ትናንት ወጣቶች ከፖሊስ ጋር ተጋጭተው የሰው ሕይወት ማለፉን እማኞች ተናገሩ። ዶቼ ቬለ ያነጋገራቸው የዓይን ምስክሮች እንደሚሉት በጥይት ቢያንስ አራት ሰዎች ሞተዋል ከ6 በላይም ተጎድተዋል።
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ ፍርድ ቤት አንደኛ ወንጀል ችሎት በሲዳማ ዞን የተለያዩ አካባቢዎች ተከስቶ የነበረዉን ሁከት ቀስቅሰዋል በሚል ተጠርጥረው የተያዙ ዘጠኝ ግለሰቦች በዋስ እንዲፈቱ ወሰነ። ፖሊስ መረጃ ለማሰባሰብ በተጨማሪ የጠየቀውን የ14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ፍርድ ቤቱ አልተቀበለውም።
ካምፓላ ላይ የተካሄደው ሦስተኛው የኢትዮጵያ እና የዩጋንዳ የጋራ ሚኒስትሮች ኮሚሽን ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ስምምነት በመፈራረም ዛሬ ተጠናቀቀ። ስምምነቱ በዲፕሎማሲያዊ ጉዳዮች፤ ተፈላጊዎችን አሳልፎ በመስጠት፣ በጋራ የሕግ ድጋፍ ፣ እና የመጓጓዣ ሰነድ አገልግሎትን እንደሚያጠቃልል የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ በትዊተር ባሰራጩት መላክት ጠቅሰዋል።
ኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፑብሊክ ውስጥ የኢቦላ ተሐዋሲ ወረርሽኝ ወደ ሦስተኛ ክፍለ ሀገር መዛመቱ ተነገረ።
https://p.dw.com/p/3O2SO?maca=amh-RED-Telegram-dwcom

Deutsche Welle
የነሐሴ 10 ቀን 2011 ዓ,ም የዓለም ዜና
የሱዳን ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች እና የተቃዋሚ መሪዎች ስልጣን ለመጋራት የሚያስችላቸውን ስምምነት በይፋ ተፈራራሙ። ስምምነቱ በሲቪል የሚመራ የሽግግር መንግስት ለመመስረት መንገድ ይጠርጋል ተብሎለታል። በስምምነት ስነ ስርዓቱ ላይ የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድን ጨምሮ የኬንያው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ እና የደቡብ ሱዳን አቻቸው ሳልቫ ኪር ተገኝተዋል።
👉🏾 @dwamharicbot
👉🏾 @dwamharicbot
የደቡብ የመን ተገንጣዮች በአገሪቱ ሁለተኛ ከተማ ከፕሬዝዳንት አብድረቦ መንሱር ሐዲ ታማኞች በመንጠቅ ተቆጣጥረዋቸው የቆዩ ቁልፍ የመንግሥት ሕንፃዎችን በዛሬው ዕለት ጥለው መውጣታቸውን አንድ ከፍተኛ ባለስልጣን አስታወቁ። የደቡብ የሽግግር ምክር ቤት ተብሎ የሚጠራው ተገንጣይ ቡድን ደጋፊዎች ከፕሬዝዳንቱ ዋና ፅህፈት ቤት፣ የከፍተኛ ፍርድ ቤት፣ የማዕከላዊ ባንክ እና የኤደን ዋና ሆስፒታል ሕንፃዎች ለቀው መውጣታቸውን የፕሬዝዳንት አብድረቦ መንሱር ሐዲ መንግሥት የማስታወቂያ ምኒስትር ሙዓማር አል-ኢርያኒ አስታውቀዋል።
ኢርያኒ እንዳሉት በተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች የሰለጠኑት ኃይሎች ከአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ሕንፃ እና በኤደን ከሚገኝ የነዳጅ ማጣሪያ ለቀው እንዲወጡ ዝግጅት እየተደረገ ነው። የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች የሳዑዲ መራሹ ጥምረት ዋና አጋር ብትሆንም በደቡባዊ የመን ያላትን ተደማጭነት ለማጠናከር እና ቁጥጥሯን ለማጥበቅ ደቡብ የመንን ለመገንጠል የሚሻው የደቡብ ሽግግር ምክር ቤት ኃይሎችን ማሰልጠኗን እና ማስታጠቋን የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዘግቧል። ለሽግግር ምክር ቤቱ ታማኝ የሆኑት ታጣቂዎች የቀድሞዋ ሉዓላዊ ደቡብ የመን መቀመጫ የነበረችውን የኤደንን ከተማ የተቆጣጠሩት ባለፈው ሳምንት 40 ሰዎች ከተገደሉበት ጦርነት በኋላ ነበር።
ሳዑዲ መራሹ ግብረ-ኃይል ታጣቂዎቹ ከተማይቱን መቆጣጠራቸውን አውግዞ ድርድር ለማድረግ ይቻል ዘንድ በቁጥጥራቸው ስር ያደረጓቸውን ቦታዎች ጥለው እንዲወጡ ጥሪ አቅርቦ ነበር። የሐዲ መንግሥት ተገንጣዩቹ ከተቆጣጠሯቸው ቦታዎች ለቅቀው ካልወጡ አልደራደርም ብሎ ቆይቷል።
የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዘጋቢዎች ታጣቂዎቹ ለቅቀዋቸው በወጡ አካባቢዎች የሳዑዲ አረቢያ እና የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ወታደራዊ ተሽከርካሪዎች መመልከታቸውን ዘግበዋል። ሳዑዲ መራሹ ጥምር ኃይል ቦታዎቹ ለአብድረቦ መንሱር ሐዲ መንግሥት ተላልፈው እንደሚሰጡ አስታውቋል። ወታደራዊ የጦር ሰፈሮችን ጨምሮ በርካታ ቦታዎች አሁንም በተገንጣዮቹ እጅ እንደሚገኙ የዘገበው የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ከሳዑዲ መራሹ ኃይል ጋር በተደረገ ስምምነት ቀሪዎቹም ይለቀቁ እንደው የታወቀ ነገር የለም ብሏል። ደቡብ የመን ከሰሜኑ ጋር እስከተቀላቀለችበት የጎርጎሮሳዊው 1990 ዓ.ም. ድረስ ሉዓላዊ አገር ነበረች። 👉🏾 @dwamharicbot

የሱዳን ወታደራዊ የሽግግር ምክር ቤት እና የተቃውሞ መሪዎች በሲቪል የሚመራ አስተዳደር የሚያቋቁሙበትን የሥልጣን ክፍፍል ስምምነት ዛሬ በኻርቱም ከተማ ተፈራረሙ። ስምምነቱን የተፈራረሙት የሽግግር ምክር ቤቱ ምክትል ሊቀ-መንበር ሉቴናንት ጄኔራል መሐመድ ሐምዳን ዳጋሎ እና ጥምረት ለነፃነት እና ለውጥ የተባለው የተቃዋሚዎች ስብስብ ተወካይ አሕመድ ራባይ ናቸው።
የኢትዮጵያው ጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አሕመድ፤ የግብጹ አቻቸው ሙስጠፋ ከማል ማዶቢ፣ የኬንያው ፕሬዝዳንት ኡኹሩ ኬንያታ እና የደቡብ ሱዳኑ አቻቸው ሳልቫ ኪር ሚያርዲት በዛሬው መርሐ ግብር ላይ ተገኝተዋል።
ስምምነቱ ሲፈረም በአዳራሹ የነበሩትን ጨምሮ በኻርቱም ጎዳናዎች፤ በዳርፉር እና በከሰላ ግዛቶች ሱዳናውያን ደስታቸውን በሆታ ገልጸዋል። የተቃውሞው መሪ መሐመድ ናጂ አል-ሳም «ከሶስት አስርት አመታት ጭቆና እና ሙስና» በኋላ በሱዳን ታሪክ አዲስ ምዕራፍ ተበስሯል ሲሉ አድንቀዋል። ከእንግዲህ ዋንኛው ትኩረት በሁሉም የሱዳን ክፍሎች ከሚገኙ አማፂያን ጋር በመሆን «ፍትኃዊ እና አጠቃላይ ሰላም» ማምጣት እንደሆነም ተናግረዋል። የቀድሞ የሱዳን ጠቅላይ ምኒስትር እና የዑማ ፓርቲ መሪ ሳዲቅ አል-ማሓዲ በበኩላቸው ዛሬ ፊርማ የተፈረመው የሥልጣን ክፍፍል ሥምምነት ፍትኃዊ ምርጫ እስከሚካሔድ በሚዘልቀው ዴሞክራሲያዊ ለውጥ የመጀመሪያው እርምጃ መሆኑን ተናግረዋል።
በስምምነቱ መሰረት 40 ሚሊዮን ዜጎች ያሏትን አገር የሚመራ ሉዓላዊ ምክር ቤት በወታደሮቹ እና በተቃዋሚዎች ጥምረት ይመሰረታል። የሽግግር መንግሥቱን የሚመራው ይኸው ሉዓላዊ ምክር ቤት አስራ አንድ አባላት የሚኖሩት ሲሆን ስድስት ሲቪል ፖለቲከኞች እና አምስት ወታደራዊ መኮንኖችን በአባልነት ይይዛል።
አዲስ የሚመሰረተው የሽግግር መንግሥት አባላት ማንነት በነገው ዕለት ይታወቃል ተብሎ ይጠበቃል። ተቃዋሚዎቹ በተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት ያገለገሉት የምጣኔ-ሐብት ባለሙያ አብደላ ሐምዶክን ጠቅላይ ምኒስትር አድርገው ለማጨት ማሰባቸውን ሬውተርስ ከሁለት ቀናት በፊት ዘግቧል። 👉🏾 @dwamharicbot