DW Amharic
56.4K subscribers
4.14K photos
984 videos
69 files
15.7K links
ይህ የዶይቼ ቬለ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው። ትኩስ ዜና፣ በአበይት ፖለቲካዊ፣ ኤኮኖሚያዊ፤ ማኅበራዊ እና ባሕላዊ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩር ትንታኔ ያቀርባል።
Download Telegram
የሚያዝያ 13 ቀን 2017 ዓ.ም፤ የስፖርት ዝግጅት
በሳምንቱ መጨረሻ በተለያዩ የአለም ክፍሎች በተካሄዱ የጎዳና ላይ ውድድሮች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አሽናፊ ሆነዋል። በቦስተን የ5 ኪሎሜትር ውድድር አትሌት ገላ ሀምበሴ 14 ደቂቃ ከ53 ሰከንድ በመግባት በአንደኝነት አሸናፊ ሆናለች።https://p.dw.com/p/4tNL2?maca=amh-RED-Telegram-dwcom አስተያየት ለመስጠት ይኽን ቦት ይጠቀሙ @dwamharicbot
ማሕደረ ዜና፣የሱዳን ዉድመትና የመከፋፈሏ ሥጋት
ያለመግባባቱ ምክንያቶች ከሩቅ ያሉት በቅኝ ገዢነት ብዙ ጊዜ የሚወቀሱት አዉሮጶች፣ በአረብ ጠላትነት የምትወገዘዉ እስራኤል ወይም አሜሪካኖች አይደሉም።የሱዳንን ሕዝብ «ወንድም» የሚሉት፣ከአብዛኛዉን ሱዳናዊ ጋር ቋንቋ፣ ባሕል፣ ኃይማኖት የሚጋሩት አረቦች እንጂ።ሳዑዲ አረቢያ፣ ግብፅና የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች በጋራ መግለጫዉ ይዘት ላይ አልተስማሙም።
https://p.dw.com/p/4tNM3?maca=amh-RED-Telegram-dwcom አስተያየት ለመስጠት ይኽን ቦት ይጠቀሙ @dwamharicbot
በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቼስኮስ ህልፈት የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን አስተያየት
ሥዩም ጌቱ
የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ-ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ሥርዓተ ቀብር ቅዳሜ ሲፈጸም የጀርመን፣ አሜሪካ፣ ዩክሬንን ጨምሮ በርካታ መሪዎች ይገኛሉ። የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ-ክርስቲያን በዕለቱ መስዋዕተ-ቅዳሴ አዘጋጅታለች። የቤተ-ክርስቲያኒቱ ካርዲናል አቡነ ብርሃነኢየሱስ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳስ ፍራንሲስ “ታላቅ አባት” እንደነበሩ ተናግረዋል።
https://p.dw.com/p/4tPuM?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
አስተያየት ለመስጠት ይኽን ቦት ይጠቀሙ 👉🏾
@dwamharicbot
በዳውሮ ዞን ዲሳ ወረዳ በወባ በሽታ ሰዎች እየሞቱ መሆኑን ነዋሪዎች እና የሕክምና ባለሙያ ገለጹ
ሸዋንግዛው ወጋየሁ
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ዳውሮ ዞን ዲሳ ወረዳ በተቀሰቀሰ የወባ በሽታ የሰዎች ሕይወት እያለፈ እንደሚገኝ የወረዳው ነዋሪዎች እና የሕክምና ባለሙያ ለዶይቼ ቬለ ገለጹ፡፡ ሾታ በተባለ አንድ ቀበሌ ብቻ ባለፈው ሳምንት ምርመራ ከተደረገላቸው 127 ታማሚዎች መካከል 102ቱ በወባ በሽታ የተያዙ መሆናቸው መረጋገጡን የህክምና ባለሙያዎች ተናግረዋል።
https://p.dw.com/p/4tPgM?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
አስተያየት ለመስጠት ይኽን ቦት ይጠቀሙ 👉🏾
@dwamharicbot
በጋምቤላ ከተማ አንድ ጀሪካን የወንዝ ውኃ እስከ 20 ብር እየተሸጠ መሆኑን ነዋሪዎች ገለጹ

ጋምቤላ ባሮ ወንዝ ባጠገቧ እየፈሰሰ የውኃ እጦት በርቶባታል። የክልላዊ መንግሥት መቀመጫ በሆነችው ከተማ ነዋሪዎች እንደሚሉት የወንዝ እና የጉድጓድ ውኃ በጀሪካ እየተቀዳ እስከ 20 ብር ይሸጣል። ችግሩ የተፈጠረው ከባሮ ወንዝ ውኃ የሚገፋበት ፓምፕ በማርጀቱና የውኃ ማስተላለፊያ ቧምቧዎች በመንገድ ግንባታ በመቆረጣቸው እንደሆነ ባለሥልጣናቱ ይናገራሉ።
https://p.dw.com/p/4tPbS?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
አስተያየት ለመስጠት ይኽን ቦት ይጠቀሙ 👉🏾
@dwamharicbot
በምዕራብ ኦሞ ዞን የአባ ሠንጋ በሽታ 7 ሰዎች ገደለ
ሸዋንግዛው ወጋየሁ
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ምዕራብ ኦሞ ዞን በተቀሰቀሰ የአባ ሠንጋ በሽታ ሰባት ሰዎች መሞታቸውን የዞኑ አርብቶ አደር መምሪያ ኃላፊ በለጠ ግርማ ለዶይቼ ቬለ ተናገሩ። ብዛት ያለው የቀንድ ከብት ሐብት ባለበት ምዕራብ ኦሞ ዞን በሽታው የተከሰተው ሱሪ በተባለ ወረዳ በሚገኝ ቀበሌ ነው።
https://p.dw.com/p/4tP08?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
አስተያየት ለመስጠት ይኽን ቦት ይጠቀሙ 👉🏾
@dwamharicbot
በአማራ ክልል የሚደረገዉ ግጭት በተፈጥሮ ሐብት ላይ ያስከተለዉ ጉዳት
ከሰሜኑ ጦርነት ጀምሮ በቀጠለው አለመረጋጋትና ጦርነት ምክንያት ግን ለተፈጥሮ ሀብት የሚደረገው ጥበቃና እንክብካቤ እየተቀዛቀዘ በመምጣቱ አንዳንድ አካባቢዎች እንደገና እየተራቆቱ፣ በውስጣቸው የነበሩ የዱር እንስሳትም በህገወጥ አዳኞች እየተገደሉና እየተሳደዱ መሆኑ በስፋት ይገለፃል፡፡
https://p.dw.com/p/4tOeZ?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
አስተያየት ለመስጠት ይኽን ቦት ይጠቀሙ 👉🏾
@dwamharicbot
የሚያዝያ 14 ቀን 2017 ዓ.ም የዓለም ዜና
የተባበሩት መንግስታት የምግብ ድርጅት በኢትዮጵያ ከግማሽ ሚልዮን ለሚልቁ የተመጣጠነ ምግብ ለሚያስፈልጋቸው እናቶችና ሕጻናት ሲሰጥ የነበረውን የምግብ ርዳታ ሊያቆም መሆኑን አስታወቀ። ድርጅቱ ርዳታውን የሚያቆመው በገንዘብ እጥረት መሆኑን አመላክቷል።


የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ሃይሎች ከካርቱም 800 ኪሎሜትሮችን ርቃ በምትገኘው በዳርፉር ግዛት በፈጸሙት ጥቃት ከ30 በላይ ስቪሎች መገደላቸውን የስቪሎች መከላከያ ኮሚቴ የተባለ ቡድን አስታወቀ። ቡድኑ ለአሶሽየትድ ፕረስ እንዳለው በጥቃቱ ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ስቪሎችም ቆስለዋል።

ትላንት በ88 ዓመታቸው ያረፉት የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳስ ፍራንሲስ የቀብር ሥነሥርዓት በሚቀጥለው ቅዳሜ እንደሚፈጸም የቫቲካን ባለስልጣናት ዛሬ አስታወቁ። የቫቲካን ካርዲናሎች ዛሬ ተሰብስበው በወሰኑት መሰረት የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳቱ የቀብር ሥነስርዓት የሚፈጸመው ሮም በሚገኘው ቅድስት ማሪያ ቤተክርስትያን ነው።

እስራኤል በጋዛ ሰርጥ በፈጸመችው ጥቃት ቢያንስ 14ፍልስጤማውያን መገደላቸውን የጃባልያ ከተማ አስተዳዳሪ ገለጹ። ከሟቾች አብዛኛዎቹ ህጻናትና ሴቶች ናቸው ተብሏል።

ሩስያ በዩክሬይን ያዛፓሪያ ግዛት በፈጸመችው የተመሪ ሚሳይል ጥቃት አንዲት ሴት መገደሏንና 15
መቁሰላቸውን ዩክሬይን አስታወቀች። በጥቃቱ የመኖሪያ ቤቶችን ጨምሮ የስቪል መሰረተ ልማቶች ላይ ጉዳት መድረሱንም ዜናው አክሏል። ሩስያ ለጥቃቱ የተጠቀመችበት «ዘመናዊ» የተባለለት ተመሪ ሚሳይል የዩክሬይን የአየር መከላከያ ምድብተኞች ሚሳይሉን ለማክሸፍ አስቸጋሪ እንደሆነባቸው ሮይተርስ ዘግቧል።
https://p.dw.com/p/4tQBx?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
አስተያየት ለመስጠት ይኽን ቦት ይጠቀሙ 👉🏾
@dwamharicbot
Live stream finished (1 day)
Live stream started
Live stream finished (1 hour)
በኪረሙ ወረዳ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት 15 ሰዎች ተገደሉ
በምስራቅ ወለጋ ዞን ኪረሙ ወረዳ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት የሚሊሻ አባላትን ጨምሮ 15 ሰዎች መገደላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡ በወረዳው ጫቢ ተብሎ በሚጠራ ቦታ በአንድ ሳምንት ልዩነት ሁለት ጊዜ በታጣቂዎች ጥቃት መፈጸሙን አስተያየታቸውን ለዲዳቢሊው የሰጡ ነዋሪዎች አመልክተዋል፡፡
https://p.dw.com/p/4tRv0 ?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
አስተያየት ለመስጠት ይኽን ቦት ይጠቀሙ 👉🏾
@dwamharicbot
የኢትዮጵያ ፖሊስ የአዲስ ስታንዳድርን መረጃ ወይም ዳታ «እወስዳለሁ» አለ
የኢትዮጵያ የፌደራል ፖሊስ ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ የአዲስ ስታንዳደርድ ቢሮን መመዝበሩ አልበቃ ብሎ በወሰዳቸዉ ኮምፒዉተሮችና ሞባይሎች ዉስጥ የሚገኙ መረጃዎችን ለመዉሰድ መዛቱን ዓለም አቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት (CPJ) አጥብቆ ተቃዉሞታል
https://p.dw.com/p/4tSAD ?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
አስተያየት ለመስጠት ይኽን ቦት ይጠቀሙ 👉🏾
@dwamharicbot
የዩናይትድስቴትስ የፌዴራል ፍርድ ቤት ውሳኔ እና የአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ
አሜሪካ የፌደራል ፍርድ ቤት ትናንት በዋለው ችሎት፣ የአሜሪካ ድምፅ እና ሌሎች የዓለምአቀፍ ሚዲያ ተቋማት ከእገዳው በፊት ወደነበሩበት ቁመና እንዲመለሱ አዘዙ። በዚህም መሰረት ጉዳዩ በይግባኝ መታየት ቢቀጥልም እንኳን የመጨረሻ እልባት እስከሚያገኝድረስ አስተዳደራዊ ዕረፍት የተሰጣቸው ቋሚና የኮንትራት ሠራተኞች ወደ ሥራቸው እንዲመለሱ ተወስኗል።
https://p.dw.com/p/4tRUc ?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
አስተያየት ለመስጠት ይኽን ቦት ይጠቀሙ 👉🏾
@dwamharicbot
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ በዓለም መሪዎች ሲታወሱ
ባለፈው ሰኞ የፋሲካ ማግስት የሮማው ሊቀ ጳጳስ ፖፕ ፍራንሲስ በ88 አመታቸው ከዚህ አለም በሞት መለየታቸውን ተክትሎ የበርካታ አገሮችና የአለምቀፍ ድርጅቶች መሪዎች ሀዘናቸውን እየገለጹ ናቸው። የላቲን አሜሪካዋ አርጀንቲና ተወላጅ የሆኑት ፖፐ ፍራንሲስ ከደቡባዊው የዓለማችን ክፍል የወጡ የመጀመሪያው የአለም ካቶሊክ ቢተክርሲቲያን መሪ ነበሩ።
https://p.dw.com/p/4tSQ2 maca=amh-RED-Telegram-dwcom
አስተያየት ለመስጠት ይኽን ቦት ይጠቀሙ 👉🏾
@dwamharicbot
የትራምፕ ታሪፍ የዓለም ኢኮኖሚ ዕድገትን እንዳቀዛቀዘ የአይኤምኤፍ ትንበያ አሳየ
ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ለዓለም ዋና ዋና ኢኮኖሚዎች በጥር የሰጠውን የዕድገት ትንበያ የዶናልድ ትራምፕ ታሪፍ ባስከተለው ውጥረት ምክንያት ከልሷል። ተቋሙ የኢትዮጵያ አጠቃላይ ሀገራዊ ምርት በ6.6% ያድጋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ይፋ አድርጓል። ትንበያው የኢትዮጵያ መንግሥት በ2017 ከሚጠብቀው ኢኮኖሚያዊ ዕድገት በ1.8 በመቶ ዝቅ ያለ ነው።
https://p.dw.com/p/4tSir ?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
አስተያየት ለመስጠት ይኽን ቦት ይጠቀሙ 👉🏾
@dwamharicbot
የሚያዚያ 15 ቀን 2017 ዓ.ም. የዓለም ዜና

የሚያዚያ 15 ቀን 2017 ዓ.ም. አርዕስተ ዜና

በምስራቅ ወለጋ ዞን ኪረሙ ወረዳ ትናንት ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት የሚሊሻ አባላትን ጨምሮ 15 ሰዎች መገደላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡ በጥቃቱ ከባድ መሣሪያዎችም ጥቅም ላይ መዋላቸውንም ለዶቼቬለ ተናግረዋል።
ጅቡቲ ሕገ ወጥ ስደተኞችን በቅርቡ ማባረር እንደምትጀምር አስታወቀች። ስደተኞቹ እስከሚቀጥለው ሳምንት ድረስ ሀገሪቱን ለቀው እንዲወጡ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር አዟል።

የፍልስጤም ፕሬዝዳንት መሐሙድ አባስ ሀማስ ጋዛ ውስጥ የያዛቸውን ታጋቾች በሙሉ እንዲለቅ ጠየቁ። ታጋቾቹን ይዞ መቆየቱ እስራኤል በፍልስጤም ጥቃቷን እንድትቀጥል ሰበብ ሆኗታል ብለዋል።

https://p.dw.com/p/4tSln?maca=amh-RED-Telegram-dwcom 
አስተያየት ለመስጠት ይኽን ቦት ይጠቀሙ 👉🏾
@dwamharicbot
ሕግጋት፣ ደንቦችና መመሪያዎች ብዙ በማይታወቅባቸዉ ወይም በተገቢዉ መንገድ ገቢር በማይደረጉባቸዉ እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ሃገራት የማኅበራዊ መገናኛ ብዙኀን አጠቃቀም አሳሳቢ እየሆነ መምጣቱ እየተነገረ ነው። ማኅበራዊ መገናኛ ዘዴው መረጃዎችን ፈጥኖ በማዳረስ በኩል የሚጫወተው አዎንታዊ ሚና ቢኖረውም ግለሰቦች እንዳሻቸው የሚያስተላልፏቸው «መስመር የሳቱ» መልእክቶች መኖራቸው ይታያል። እንደ ቲክቶክ ባሉ የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች የሚተላለፉ ጥንቃቄ የጎደላቸው «የጥላቻ ንግግሮች»፣ የግለሰቦችን ወይም የቡድናትን ስም የሚያጠለሹ ብሎም የማኅበረሰቡን እሴት የሚንዱ መልዕክቶች መኖራቸዉን የሚገልጹ ወገኖች በማኅበራዊ መገናኛ ብዙሃን የሚተላለፉ መልእክቶች ይዘት ተገቢው ክትትል እንደሚጎላቸው ማመላከቻ ነው ይላሉ።
እርግጥ ነው እንደሜታ(ፌስቡክ) እና ቲክቶክ ያሉ የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች በበርካታ ቋንቋዎች የሚለጠፉ /post/ መረጃዎችን እንደሚከታተሉ ይገልጻሉ። ለምሳሌ ቲክቶክ አማርኛን ጨምሮ ከ70 በላይ በሚሆኑ ቋንቋዎች የሚዘጋጁ ቪዲዮዎች ለብዙኀን ከመድረሳቸው አስቀድሞ እንደሚከታተልና እስካሁንም 92 በመቶ የሚሆኑትን «የተዛቡና የጥላቻ ንግግሮችን» የያዙ ያላቸውን ማንሳቱን ይገልጻል። እንዲህ ላሉ ይዘቶችም ትዕግሥት እንደሌለው አመልክቷል። ሆኖም ግን ለማኅበረሰብ እሴት ቦታ የሌላቸው መደዴ ይዘቶች መሰራጨታቸው አልቀረም። እንደውም አንዳንዶች ተከታዮቻቸውን ለማብዛት ያፈነገጠ አቀራረብ እንደሚጠቀሙ ነው ጉዳዩን የተከታተሉ ምሁራን የሚገልጹት። ለመሆኑ እንደ ሜታ ማለትም ፌስቡክ፤ ቲክቶክ፤ ዩቲዩብ፣ ኤክስ(ትዊተር) ያሉ የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎችን አጠቃቀም እርስዎ እንዴት ይመዝኑታል? ከሥርዓት ውጪ የሆኑ ለሚሏቸው ይዘቶችስ ማረቂያ መፍትሄ የሚሉት ይኖር ይሆን? ሃሳብዎን ያካፍሉን፤ ተወያዩበትም።
አዲሱ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ሰላማዊ እና ዴሞክራሲያዊ የትግል መንገዶችን እየዘጋ ነው ሲሉ በክልሉ የሚንቀሳቀሱ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች አመለከቱ። ዓረና፣ ባይቶና እና የትግራይ ነፃነት ፓርቲ በጋራ በሰጡት መግለጫ አዲሱ የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ሁሉንም ባገለለ መልኩ ካቢኔው አዋቅሯል ሲሉም ወቅሰዋል። ጊዜያዊ አስተዳደሩ «የወታደራዊ አገዛዝ ባህርያት እየታየበት ነው» የሚሉት የተቃዋሚ ፓርቲዎቹ በክልሉ በአንፃራዊነት በተሻለ ሁኔታ እየታየ ቆየ ያሉት አካታች ፖለቲካዊ እንቅስቃሴን ለመቀየር እና ሁሉን ነገር በአንድ አካል ቁጥጥር ስር ለማድረግ ጥረት እየተደረገ ነው ብለዋል። ፓርቲዎቹ አክለውም አዲሱ ጊዜያዊ የክልሉ አስተዳደር በበርካቶች ተሳትፎ ተመስርቶ ከነበረው ምክር ቤት ጋር አብሮ ለመሥራት ፈቃደኛ አለመሆን፤ የዴሞክራሲ ግንባታ ተቋማትን ማፍረስ፤ እንዲሁም የተለየ አስተሳሰብ ያላቸውን አካላት እና የተቃውሞ ፓርቲ አባላትን ማሳደድ መኖሩንም ገልጸዋል። ዶቼ ቬለ በተቃዋሚ ፓርቲዎቹ የቀረቡትን አቤቱታዎች በተመለከተ ከጊዜያዊ አስተዳደሩ ምላሽ ለማግኘት ያደረገው ጥረት አልተሳካም።
ሚሊየን ኃይለ ሥላሴ ከመቀለ
ትናንት በኃይለና የመሬትመንቀጥቀጥ የተመታችው ተርክዬ ዛሬም ተደጋጋሚ መንቀጥቀጥ ኢስታንቡል ላይ እንዳጋጠማት ተገለጸ። የዘርፉ ባለሙያዎችና ተመራማሪዎች ወሁንም ቀጣይ እጅግ ኃይለኛ የመሬት መንቀጥቀጥ ሊከተል እንደሚችል አሳስበዋል። የሀገሪቱ የአደጋ ጊዜ ተቋም ዛሬ ይፋ ባደረገውመረጃ መሠረት ኢስታንቡል ላይ በሬክተር መለኪያ እስከ 4,6 የደረሰ ወደ 300 የሚሆኑ መንቀጥቀጦች ተከስተዋል። የትናንቱ 6,2 የተመዘገበው የመሬት መንቀጥቀጥ ኢስታምቡል ውስጥ ጨምሮ 236 ሰዎችን ለጉዳት ዳርጓል። አንዳንዶቹ የተጎዱት የመሬት መንቀጥቀጡባስከተለባቸው ፍርሀት ከሕንጻዎች በመዝለል ነው። የከተማዋ ባለሥልጣናት እስካሁን ኢስታምቡል ውስጥ የተደረመሰ ፎቅ ስለመኖሩ መረጃ
አልደረሰንም ብለዋል። እንዲያም ሆኖ የከተማ ልማት ሚኒስትሩ ሙራት ኩሩም እንደሚሉት በመሬት መንቀንቀጡ ሊደርስ የሚችለውን አደጋ በመፍራት ከወዲሁከ12 ሕንጻዎች ላይ ነዋሪዎች እንዲወጡ ተደርጓል። ወደቤታቸው መመለስ ያልቻሉና በጊዜያዊ መጠለያ ውስጥ ለሚገኙት ወገኖችም የተርክዬ
ቀይ ጨረቃ እርዳታ እያቀረበ መሆኑ ተነግሯል።
የስነምድር ተመራማሪዎችለተርክዬ መገናኛ ብዙሃን እንደጠቆሙት ቀኑና ጊዜውን በግልፅ ለመናገር ቢያዳግታቸውም በሬክተር መለኪያ ከ7,4 እስከ 7,7 ሊደርስ
የሚችል ኃይለኛ የመሬት መንቀጥቀጥ ሊከሰት እንደሚችል ከወዲሁ ምልክቶች አይተዋል። በዚህም ምክንያት በርካታ ነዋሪዎች ወደ አግያንየባሕር ዳርቻ አካባቢ ለመጓዝ ጥረት እያደረጉ ነው። በዚህም ምክንያት ከኢስታንቡል የሚነሱ በረራዎች በሙሉ ሞልተዋል። ሆቴሎችም
በብዛት ተይዘዋል። የአግያን የባሕር ዳርቻ ከኢስታንቡል 575 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኝ አካባቢ ነው።