DW Amharic
56.4K subscribers
4.14K photos
984 videos
69 files
15.7K links
ይህ የዶይቼ ቬለ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው። ትኩስ ዜና፣ በአበይት ፖለቲካዊ፣ ኤኮኖሚያዊ፤ ማኅበራዊ እና ባሕላዊ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩር ትንታኔ ያቀርባል።
Download Telegram
Live stream finished (1 hour)
የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ርዕሠ-ሊቀነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ዛሬ ጠዋት በ88 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በአጸደ ሥጋ ተለዩ።
ርዕሠ ሊቀነ ጳጳስ ፍራንሲስ እንደ ጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር ከ2021 ጀምሮ በተለያዩ ሕመሞች ሲሰቃዮ የነበረ ሲሆን በተለይ በዘንድሮዎ ዓመት ለረዥም ጊዜ በሆስፒታል ተኝተው በሕክምና ሲረዱ ቆይተዋል።
ይሁንና ፍራንሲስ ትላን የትንሳኤ በዓልን አስመልክተው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ብቅ ብለው ለእምነቱ ተከታዮች መልካም ትንሳኤ የሚል አጭር መልዕክት አስተላልፈዋል። በሕመም ላይ የሰነበቱት ፍራንሲስ ወንበር ላይ ተቀምጠው በተወካያቸው በኩል ባስተላለፉት መልዕክት "ያለ የእምነት ነጻነት፣ የአስተሳሰብ ነጻነት እና ሐሳብን የመግለጽ ነጻነት እንዲሁም የሌሎችን አመለካከት ከማክበር ውጪ ሰላም አይኖርም" ብለዋል። የ88 ዓመቱ ፍራንሲስ "አሳሳቢ" ያሉትን ጸረ-ሴማዊነት እና የጋዛን አሳዛኝ እልቂት አውግዘዋልም።
የሊቃጳጳሱ ሞትን ተከትሉ የተለያዩ ኃይማኖት ተቋማት፣ መንግስታት፣ ድርጅቶችና ማሕበራት የሐዘን መልዕክታቸውን እያስተላለፉ ሲሆን የጣልያኗ ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ «ዓለማችን ታላቅ ሰው አጣች» ሲሉ የሐዘን መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
ርዕሠ-ሊቀነ ጳጳሳት ፍራንሲስ በፎቶ
የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ርዕሠ-ሊቀነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ዛሬ ጠዋት በ88 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።
ርዕሠ ሊቀነ ጳጳስ ፍራንሲስ እንደ ጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር ከ2021 ጀምሮ በተለያዩ ሕመሞች ሲሰቃዮ የነበረ ሲሆን በተለይ በዘንድሮዎ ዓመት ለረዥም ጊዜ በሆስፒታል ተኝተው በሕክምና ሲረዱ ቆይተዋል።
ፍራንሲስ በ 2013 ለመጀመሪያ ጊዜ ይፋዊ ስራ ሲጀምሩ እራሳቸውን ከ‹‹ከምድር ዳርቻ›› ብለው የገለፁት ጳጳሱ የመጀመሪያ ይፋዊ ስራቸው በማኅበረሰብ ዘንድ የተገለሉትን መጎብኘት ነበር።
ይህ ሁሉ ከባህሪያቸው ጋር የሚስማማ ነበር። ጳጻሱ ከቀደምቶቹ መሪዎች በተለየ ከቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ከፍ ብሎ በሚገኘው ሐዋርያዊ ቤተ መንግሥት ወደሚባለው ቦታ አልሄዱም። ይልቁንም በጵጵስና ዘመናቸው በሙሉ በቫቲካን የእንግዳ ማረፊያ ውስጥ በሁለት ክፍሎች ውስጥ ከሰራተኞች እና እንግዶች ጋር ነበር የኖሩት።
በጎርጎሪያኑ 2013 ርዕሰ ሊቃነጳጳስ ሆነው የተመረጡት አርጀንቲናዊው የቀድሞው ጆርጅ ማሪዮ ቤርጎሊዮ የአሁኑ ሊቀጳጳስ ፍራንሲስ ፤ለስደተኞች እና ቤት ለሌላቸው ሰዎች በመቆም እንዲሁም ለአየር ንብረት እና ለአካባቢ ጥበቃ ይታገሉ ነበር።
ፎቶዎች፤ ከማህደራችን
Live stream started
የመከላከያ ሰራዊት ወሰድኩ ያለው ወታደራዊ እርምጃዎች
መከላከያ በመግለጫው ሚያዚያ 11 ቀን 2017 ዓ.ም. በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ባሶና ወረዳ “ፅንፈኛ” በሚል በተጠቀሱ ታጣቂዎች ላይ በተወሰደ ወታደራዊ እርምጃ፤ ከ50 በላይ ታጣቂዎች መገደላቸው ተብራርቷል። በጎጃምም በአንድ ቀን ብቻ ከ300 በላይ ታጣቂዎችን መገደላቸው ገልጿል፡፡
https://p.dw.com/p/4tMtW ?maca=amh-RED-Telegram-dwcom አስተያየት ለመስጠት ይኽን ቦት ይጠቀሙ @dwamharicbot
ስለ አዲስ አበባ "ኮሪዶር" ልማት የመንግሥት፣ የተነሺዎች እና የመብት ድርጅት አስተያየት
እድር፣ እቁብ፣ ማኅበር ኢትዮጵያዊያን በየአካባቢያቸው በጋራ ተሳስረው የሚኖሩባቸው የአኗኗር ቁልፍ መስጋብሮች ናቸው። ከካዛንችስ የተነሱ ነዋሪዎች ይህ እንደተጠበቀላቸው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሲናገሩ የገርጂ አካባቢዎቹ ቤታቸውን ያጡት ግን የገጠማቸው በተቃራኒው እንደሆነ ይገልጻሉ።
https://p.dw.com/p/4tN9n ?maca=amh-RED-Telegram-dwcom አስተያየት ለመስጠት ይኽን ቦት ይጠቀሙ @dwamharicbot
አዲሱ የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ካቢቤና ተቃውሞው
በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራ የህወሓት ክንፍ የጀነራል ታደሰ ወረደ አዲሱ ካቢኔ አካታች አይደለም በማለት ተችቷል። በአቶ ጌታቸው የሚመራው የህወሓት ክንፉ እንዳለው አዲሱ የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት ጀነራል ታደሰ ወረደ፥ ለአንድ ቡድን ብቻ በማዳላት አካታች ያልሆነ ካቢኔ መስርተዋል ያለ ሲሆን ይህ እንዲስተካከልም ጥሪ አቅርቧል።
https://p.dw.com/p/4tNLY ?maca=amh-RED-Telegram-dwcom አስተያየት ለመስጠት ይኽን ቦት ይጠቀሙ @dwamharicbot