DW Amharic
56.5K subscribers
4.13K photos
984 videos
69 files
15.7K links
ይህ የዶይቼ ቬለ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው። ትኩስ ዜና፣ በአበይት ፖለቲካዊ፣ ኤኮኖሚያዊ፤ ማኅበራዊ እና ባሕላዊ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩር ትንታኔ ያቀርባል።
Download Telegram
ከወጣቶች ዓለም፤የኢትዮጵያዊያን ወጣቶች የሥጋት ኑሮ በደቡብ አፍሪካ
የደቡብ አፍሪካ መንግሥት ለኢትዮጵያዊያንም ሆነ ለሌሎች አገር ስደተኞች ጥበቃ ለማድረግ ፍላጎት የለውም የሚለው መልካሙ “ ተበድያለሁ ብለህ ክስ ለመመሥረት ብትሞክር እንኳን ተከታትለው ሊገድሉህ ይችላሉ ፡፡ አሁን እኛ ማድረግ የምንችለው በኮሚቴያችን አማካኝነት ኢትዮጵያዊያን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ምክር መስጠት እና ወቅታዊ መረጃዎችን ማጋራት ነው “
https://p.dw.com/p/4tI5J ?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ባሸነፉበት በቤጂንግ የተካሔደ የግማሽ ማራቶን ሩጫ ቻይና ሰው መሰል ሮቦቶች አወዳደረች። በቤጂንግ ዛሬ ቅዳሜ የተካሔደው ኢ-ታውን ሒውማኖይድ ሮቦት ግማሽ ማራቶን በዓለም የመጀመሪያው እንደሆነ ተነግሮለታል። በውድድሩ 10,000 ሰዎች እና 21 ሰው መሰል ሮቦቶች ተሳትፈዋል። https://p.dw.com/p/4tJYj?maca=amh-RED-Telegram-dwcom አስተያየት ለመስጠት ይኽን ቦት ይጠቀሙ @dwamharicbot
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የትንሳኤን በአልን ለማክበር በደቡብ ዞን ሀይቅ መካነ ኢየሱስ በሚገኙ የሀገር ዉስጥ ተፈናቃዮች በመጠለያ ጣቢያ እየተደረገ ያለዉ ዝግጂት ዛሬ እና ከአመታት በፊት ለወግ ማዕረግ በበቁበት፤ ልጅ ወልደዉ ለመሳም በቻሉበት ፤ ቤት ንብረት ባፈሩበት የተፈናቀሉበት ስፍራ ምን ይመስላል ሲል ዶቼ ቬለ ሁኔታዉን ተመልክቷል።
ቪዲዮ ዘገባ ፤ ኢሳያስ ገላው (DW) ፤ ደሴ
Live stream started
በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በሚሰጠው ልዩ ትርጉምና እሴት ትልቁን ስፍራ የሚይዘው የትንሳኤ በዓል እጅጉን የሚጠበቅ የራሱ የሆነ ድባብ አለው፡፡ በዚህ በዓል የሩቅ ቤተዘመድ ከቅርቡ፣ ልጅ ከቤተሰቡ እና ወዳጅ ከዘመዱ ብዙ ርቀት ተጉዘውም ቢሆን መገናኝት፤ ለበዓሉም ቤት ያፈራውን አብሮ መቋደስ ወግ ባህል የሆነ ነውና በበርካቶች ይናፈቃል፡፡ https://p.dw.com/p/4tJaU?maca=amh-RED-Telegram-dwcom አስተያየት ለመስጠት ይኽን ቦት ይጠቀሙ @dwamharicbot
ኢትዮጵያ ውስጥ ዕለታዊ ተግባራት የሆኑ ያሏቸው "መለያየት፣ መጣላት ብሎም እርስ በርስ መገዳደል" እንዲወገዱ እና "በዕርቅ፣ በይቅርታና በውይይት" እንዲፈቱ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን ፓትርያርክ ብፁዕ አቡነ ማትያስ ጥሪ አደረጉ። https://p.dw.com/p/4tJe3?maca=amh-RED-Telegram-dwcom አስተያየት ለመስጠት ይኽን ቦት ይጠቀሙ @dwamharicbot
የትንሳኤን በአልን ለማክበር በደቡብ እና ሰሜን ወሎ ዞን በሚገኙ የሀገር ዉስጥ ተፈናቃዮች በመጠለያ ጣቢያቸዉ እያደረጉት ያለዉ ዝግጅት ዛሬ እና ከአመታት በፊት ለወግ ማዕረግ ባበቁበት ልጅ ወልደዉ ለመሳም በቻሉበት ቤት ንብረት ባፈሩበት የተፈናቀሉበት ስፍራ ምን ይመስል ይሆን? https://p.dw.com/p/4tJUt?maca=amh-RED-Telegram-dwcom አስተያየት ለመስጠት ይኽን ቦት ይጠቀሙ @dwamharicbot
የሚያዝያ 11 ቀን 2017 ዓ/ም የአድማጮች ማኅደር ዝግጅት https://p.dw.com/p/4tJUy?maca=amh-RED-Telegram-dwcom አስተያየት ለመስጠት ይኽን ቦት ይጠቀሙ @dwamharicbot
የሰው አካል ገበያ እና ዝውውር በርካታ ሚሊዮን ዶላሮች ፈሰስ ተደርገዉበት ፤ ጨካኝ እና ዓለማቀፍ የሰው አካል አዘዋዋሪዎችን ማሳተፉ በርግጥ ጉዳዩ ለኬንያ እና ኬንያውያን ብቻም ሳይሆን ለመላው አፍሪቃ አስደንጋጭ ሆኗል። https://p.dw.com/p/4tIUU?maca=amh-RED-Telegram-dwcom አስተያየት ለመስጠት ይኽን ቦት ይጠቀሙ @dwamharicbot
የታንዛንያ ብሔራዊ የምርጫ ኮሚሽን ዋነኛው የተቃዋሚ ፓርቲ ቻዴማ መጪው ዓመት ጥቅምት ወር በሚደረገው አጠቃላይ ምርቻ እንዳይሳተፍ አግዷል። ለፓርቲው ከምርጫ ውድድሩ መታገድ የምርጫ የስነ ምግባር ደንቡን ተቀብሎ አለመፈረሙ በምክንያትነት ተጠቅሷል። https://p.dw.com/p/4tIU0?maca=amh-RED-Telegram-dwcom አስተያየት ለመስጠት ይኽን ቦት ይጠቀሙ @dwamharicbot
ባለፈው ክፍል ጀምበሬ እና ራሒም የጀምበሬን ወላጅ አባት ፍለጋ እንደጀመሩ ሰምተናል። የወንድማማች ልጆቹ በመጀመሪያው ፍለጋቸው አንድ ያወቁት ነገር ነበር። እምነት በበኩሏ በትምህርት ቤቶች መካከል የሚደረገው የውድድር ሃሳብ በሌላ ተፎካካሪ ጥቅም ላይ እንደዋለ ተረድታለች። እንዴት ሆነ? ተከታዩ ክፍል “አንድ ምስል ከ ሺ ቃላት ይበልጣል” በሚል ርዕስ እነሆ ቀርቧል። https://p.dw.com/p/4nuq9?maca=amh-RED-Telegram-dwcom አስተያየት ለመስጠት ይኽን ቦት ይጠቀሙ @dwamharicbot
Live stream finished (1 hour)
የሚያዝያ 11 ቀን2017 የዓለም ዜና


· · የኢትዮጵያ የጸጥታ አስከባሪዎች በአዲስ ስታንዳርድ ሚዲያ ቢሮ እና በተቋሙ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሠራተኛ የመኖሪያ ቤት ብርበራ ማካሔዳቸውን ጃኬን አሳታሚ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ አስታወቀ። ሐሙስ ዕለት በተካሔደው ብርበራ ሦስት ሠራተኞችታስረው መፈታታቸውን ስምንት ላፕቶፖች፣ ሁለት ዴስክ ቶፕ ኮምፒውተሮች እና ስምንት ሞባይል ስልኮችን ጨምሮ ልዩ ልዩ ቁሳቁሶች በጸጥታ አስከባሪዎች መወሰዳቸውን በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ፈቃድ የተሰጠው አሳታሚ ትላንትአርብ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
· በመጪው ግንቦት በይፋ መራኄ-መንግሥት ይሆናሉ ተብለው የሚጠበቁት ፍሬድሪሽ ሜርስ የጀርመንን ኢኮኖሚ ለማዘመን
ቃል ገቡ። ሜርስ "ዓላማችን ግልጽ ነው። ጀርመን በኢኮኖሚ ጠንካራ፣ ደሕነቷ የተረጋገጠ፣ ፍትኃዊ እናየበለጠ ዘመናዊ መሆን አለባት" ብለዋል።
·
የሩሲያው ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን ነገ የሚከበረውን የፋሲካ በዓል ምክንያት በማድረግ በዩክሬን በሚካሔደው ጦርነት በተናጠልተኩስ አቁም አወጁ። የዩክሬን ፕሬዝደንት ቮሎዶሚር ዜሌንስኪ ግን የሩሲያው ፕሬዝደንት "በሰዎች ሕይወት ለመጫወት እየሞከሩ ነው" ሲሉ በታወጀው የአጭር ጊዜ የተኩስ አቁም እምነት እንደሌላቸው የሚጠቁም አስተያየት ሰጥተዋል።
·
በኢራን እና በአሜሪካ መካከል ኑክሌርን በተመለከተ የሚካሔደው ድርድር "ወደፊት እየተራመደ" መሆኑን የኢራን ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አርጋቺ ተናገሩ። የሁለቱ ሀገሮች ተወካዮችዛሬ ቅዳሜ በጣልያን ዋና ከተማ ሮም ከተገናኙ በኋላ "ድርድሩ ወደፊት እየተራመደ
ነው ማለት እችላለሁ" ያሉት አማን አርጋቺ "አሁን በተለያዩ መርኆች እና ዓላማዎች ረገድ ከጥሩ መግባባት ላይ ደርሰናል" ሲሉ ለሀገራቸው ቴሌቭዥን ጣቢያ ተናግረዋል።
· ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ባሸነፉበት በቤጂንግ የተካሔደ የግማሽ ማራቶን ሩጫ ቻይና ሰው መሰል ሮቦቶች አወዳደረች። ውድድሩን
ኢትዮጵያውያኑ ኤልያስ ደስታ እና ሐዊ ጉደታ አሸንፈዋል።
ዜናውን ለማድመጥ የድምጽ ማዕቀፉን ይጫኑ https://p.dw.com/p/4tJmR?maca=amh-RED-Telegram-dwcom አስተያየት ለመስጠት ይኽን ቦት ይጠቀሙ @dwamharicbot
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የበዓል ገበያ በወምበራ ወረዳ

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ወምበራ ወረዳ የበዓል ገበያ ደምቆ ውሏል፡፡ ከመተከል ዞን ዋና ከተማ ግልገል በለስ ከተማ በ170 ኪ፡ሜ ገደማ ርቀት ላይ የሚትገኘው ወምበራ ወረዳ ዛሬ የቁም እንስሳት የበሬ ዋጋ ከፍተኛ እስከ 95ሺ፣ በግ ከፍተኛ እስከ 25ሺ ሲሸጥ መዋሉን ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች አመልክተዋል፡፡ ወረዳው ተስማሚ የአየር ንብረት ያለውና በቡና ምርትም የታወቀ ነው፡፡
ቪዲዮ ዘገባ፤ ነጋሳ ደሳለኝ (DW) አሶሳ
Live stream started
እንወያይ፤ የኢትዮጵያ የመናገር ነጻነት ወዴት እያመራ ነው?

በጋዜጠኞችና የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች የሚደርሱ እስርና ወከባዎች በኢትዮጵያ በቋፍ ላይ የነበረውን የፕረስ ነጻነት አደጋ ላይ እንደጣለው የሙያው ባለቤቶችና ተከራካሪዎች በየጊዜው ስጋታቸውን እየገለጹ ይገኝሉ። በሙያው የተሰማሩ ጋዜጠኞች የሙያዊ ክህሎትና የሥነምግባር ችግሮች እንደሚስተዋሉም በመስኩ የተደረጉ ጥናቶች ያመላክታሉ።
https://p.dw.com/p/4tIUv?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
አስተያየት ለመስጠት ይኽን ቦት ይጠቀሙ 👉🏾
@dwamharicbot
የሚያዝያ 12 ቀን2017 የዓለም ዜና

· በዓለም ዙሪያ የክርስትና እምነት ተከታዮች በተለያዩ ሁኔታዎች ውስጥ ሆነው የትንሳኤ በዓልን አከበሩ። ዘንድሮ በኦርቶዶክሳውያን፣
ካቶሊካውያን እና ፕሮቴስታንቶች ዘንድ ፋሲካ የተከበረው በተመሳሳይ ቀን ነው።
· ሩሲያ እና ዩክሬን ትላንት ቅዳሜ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ያወጁትን የተናጠል የተኩስ አቁም በመጣስ እርስ በርስ ተወነጃጀሉ።
·
የእስራኤል ጦር በጋዛ 15 የሕክምና ባለሙያዎች የተገደሉበት ባለፈው ወር የተፈጸመ ጥቃት ላይ በተደረገ ምርመራ በርካታ ሙያዊ ስሕተቶች እና የትዕዛዝ ጥሰቶች መገኘታቸውን ይፋ አደረገ።
·
ከፍራንክፉርት አቅራቢያ በምትገኝ አነስተኛ ከተማ ሁለት ሰዎች ከተገደሉ በኋላ የጀርመን ፖሊስ ተጠርጣሪ በቁጥጥር ሥር ለማዋል ከፍተኛ ዘመቻ እያካሔደነው።
·
በሺሕዎች የሚቆጠሩ አሜሪካውያን ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ እና ፖሊሲዎቻቸውን በመቃወም ኒው ዮርክ እና ዋሽንግተንን ጨምሮ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች አደባባይ ወጡ።
ዜናውን ለማድመጥ የድምጽ ማዕቀፉን ይጫኑ https://p.dw.com/p/4tKrt?maca=amh-RED-Telegram-dwcom አስተያየት ለመስጠት ይኽን ቦት ይጠቀሙ @dwamharicbot
Live stream finished (1 hour)
የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ርዕሠ-ሊቀነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ዛሬ ጠዋት በ88 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በአጸደ ሥጋ ተለዩ።
ርዕሠ ሊቀነ ጳጳስ ፍራንሲስ እንደ ጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር ከ2021 ጀምሮ በተለያዩ ሕመሞች ሲሰቃዮ የነበረ ሲሆን በተለይ በዘንድሮዎ ዓመት ለረዥም ጊዜ በሆስፒታል ተኝተው በሕክምና ሲረዱ ቆይተዋል።
ይሁንና ፍራንሲስ ትላን የትንሳኤ በዓልን አስመልክተው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ብቅ ብለው ለእምነቱ ተከታዮች መልካም ትንሳኤ የሚል አጭር መልዕክት አስተላልፈዋል። በሕመም ላይ የሰነበቱት ፍራንሲስ ወንበር ላይ ተቀምጠው በተወካያቸው በኩል ባስተላለፉት መልዕክት "ያለ የእምነት ነጻነት፣ የአስተሳሰብ ነጻነት እና ሐሳብን የመግለጽ ነጻነት እንዲሁም የሌሎችን አመለካከት ከማክበር ውጪ ሰላም አይኖርም" ብለዋል። የ88 ዓመቱ ፍራንሲስ "አሳሳቢ" ያሉትን ጸረ-ሴማዊነት እና የጋዛን አሳዛኝ እልቂት አውግዘዋልም።
የሊቃጳጳሱ ሞትን ተከትሉ የተለያዩ ኃይማኖት ተቋማት፣ መንግስታት፣ ድርጅቶችና ማሕበራት የሐዘን መልዕክታቸውን እያስተላለፉ ሲሆን የጣልያኗ ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ «ዓለማችን ታላቅ ሰው አጣች» ሲሉ የሐዘን መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
ርዕሠ-ሊቀነ ጳጳሳት ፍራንሲስ በፎቶ
የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ርዕሠ-ሊቀነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ዛሬ ጠዋት በ88 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።
ርዕሠ ሊቀነ ጳጳስ ፍራንሲስ እንደ ጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር ከ2021 ጀምሮ በተለያዩ ሕመሞች ሲሰቃዮ የነበረ ሲሆን በተለይ በዘንድሮዎ ዓመት ለረዥም ጊዜ በሆስፒታል ተኝተው በሕክምና ሲረዱ ቆይተዋል።
ፍራንሲስ በ 2013 ለመጀመሪያ ጊዜ ይፋዊ ስራ ሲጀምሩ እራሳቸውን ከ‹‹ከምድር ዳርቻ›› ብለው የገለፁት ጳጳሱ የመጀመሪያ ይፋዊ ስራቸው በማኅበረሰብ ዘንድ የተገለሉትን መጎብኘት ነበር።
ይህ ሁሉ ከባህሪያቸው ጋር የሚስማማ ነበር። ጳጻሱ ከቀደምቶቹ መሪዎች በተለየ ከቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ከፍ ብሎ በሚገኘው ሐዋርያዊ ቤተ መንግሥት ወደሚባለው ቦታ አልሄዱም። ይልቁንም በጵጵስና ዘመናቸው በሙሉ በቫቲካን የእንግዳ ማረፊያ ውስጥ በሁለት ክፍሎች ውስጥ ከሰራተኞች እና እንግዶች ጋር ነበር የኖሩት።
በጎርጎሪያኑ 2013 ርዕሰ ሊቃነጳጳስ ሆነው የተመረጡት አርጀንቲናዊው የቀድሞው ጆርጅ ማሪዮ ቤርጎሊዮ የአሁኑ ሊቀጳጳስ ፍራንሲስ ፤ለስደተኞች እና ቤት ለሌላቸው ሰዎች በመቆም እንዲሁም ለአየር ንብረት እና ለአካባቢ ጥበቃ ይታገሉ ነበር።
ፎቶዎች፤ ከማህደራችን