DW Amharic
56.5K subscribers
4.13K photos
984 videos
69 files
15.7K links
ይህ የዶይቼ ቬለ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው። ትኩስ ዜና፣ በአበይት ፖለቲካዊ፣ ኤኮኖሚያዊ፤ ማኅበራዊ እና ባሕላዊ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩር ትንታኔ ያቀርባል።
Download Telegram
Live stream finished (23 hours)
Live stream started
Live stream finished (1 hour)
የሚያዚያ 10 ቀን 2017 የዓለም ዜና
-በመላዉ ዓለም የሚገኙ የክርስትና እምነት ተከታዮች ዛሬ የሥቅለት በዓልን አክብረዉ ዋሉ።በአሉ ቫቲካን ዉስጥ በርዕሰ ሊቃነ-ጳጳሳቱ ሕመም፣ እየሩሳሌም ዉስጥ በጦርነት መሐል ግን የግሪጎሪያንና የዩሊዮስ የቀን አቀጣጠርን በሚከተለዉ ዓለም ሁሉ አንድ ቀን ተከብሯል።----የእስራኤል ጦር ጋዛ ሠርጥ፣ የዩናይትድ ስቴትስ ጦር ደግሞ የመን ዉስጥ በርካታ ሰዎችን ገደሉ።እስራኤል ታጋቾች እንዲለቀቁ ያቀረበችዉን ጥያቄ ሐማስ ዉድቅ አደረገዉ።---የዩክሬንና የሩሲያን ጦርነትን በድርድር ለማስቆም ዩናይትድ ስቴትስ የምታደርገዉ ጥረት ባጭር ጊዜ ዉጤት ካላመጣ ጥረቱን ልታቆም እንደምትችል ዉጪ ጉዳይ ሚንስትሯ አስታወቁ።
https://p.dw.com/p/4tIaO ?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
ሰሙነ ሕማማት እና ያሬዳዊ ዜማ በዕለተ ስቅለት ሲታወስ
በሰሙነ ሕማማት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን የምትጠቀምባቸዉ ያሬዳዊ የዜማ ስልቶች በተለየ መልኩ አገልግሎት ይከወኖባቸዋል በሕማማት ሰሞንም የኢየሱስ ክርስቶስን መከራና ሞት በማሰብ ዕለታቱን ያሳልፋሉ እነኝህ የቅዱስ ያሬድ ዜማዎችም ምእመናኑ የክርስቶስን ህማም እንዲያስቡ የሚያደርጉ ናቸዉ
https://p.dw.com/p/4tI1m ?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
በትግራይ ክልል በተፈጸሙ ወንጀሎች ተጠያቂነት ይረጋገጥ ፤ ቅድሚያ ለሰብአዊ መብቶች
አዲሱ የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር በጦርነቱ ወቅት በትግራይ ለተፈፀመው ወንጀሎች ተጠያቂነት እንዲረጋግጥ እንዲሰራ ቅድሚያ ለሰብአዊ መብቶች የተባለ የመብቶች ተሟጋች ድርጅት ጥሪ አቀረበ። ከዚህ በተጨማሪ በእስር ላይ አሉ ያላቸው የትግራይ ተወላጅ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አባላት እንዲፈታም የፌዴራሉን መንግስት ጠይቋል።
https://p.dw.com/p/4tI5I ?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
አንድ ለ አንድ፣ ኢትዮጵያ «የኃይል እጥረት የለም፣ መብራት ግን ይቆራረጣል» ባለሙያ
የዉሐ ሐብት አስተዳደር፤ የድንበር ተሻጋሪ ወንዞች፣ የሐድሮ ዲፕሎማሲ ባለሙያ አማካሪ ናቸዉ።ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ላይ ያስገነባችዉ ግዙፍ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ የሕዳሴ ግድብ የዓለም ርዕስ በነበረበት ዘመን በኢትዮጵያ የዉኃ ሐብት፣ የመስኖና የኃይል ሚንስቴር የድንበር ተሻጋሪ ወንዞች ጉዳይ ኃላፊ ነበሩ።
https://p.dw.com/p/4tEAE ?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
ከወጣቶች ዓለም፤የኢትዮጵያዊያን ወጣቶች የሥጋት ኑሮ በደቡብ አፍሪካ
የደቡብ አፍሪካ መንግሥት ለኢትዮጵያዊያንም ሆነ ለሌሎች አገር ስደተኞች ጥበቃ ለማድረግ ፍላጎት የለውም የሚለው መልካሙ “ ተበድያለሁ ብለህ ክስ ለመመሥረት ብትሞክር እንኳን ተከታትለው ሊገድሉህ ይችላሉ ፡፡ አሁን እኛ ማድረግ የምንችለው በኮሚቴያችን አማካኝነት ኢትዮጵያዊያን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ምክር መስጠት እና ወቅታዊ መረጃዎችን ማጋራት ነው “
https://p.dw.com/p/4tI5J ?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ባሸነፉበት በቤጂንግ የተካሔደ የግማሽ ማራቶን ሩጫ ቻይና ሰው መሰል ሮቦቶች አወዳደረች። በቤጂንግ ዛሬ ቅዳሜ የተካሔደው ኢ-ታውን ሒውማኖይድ ሮቦት ግማሽ ማራቶን በዓለም የመጀመሪያው እንደሆነ ተነግሮለታል። በውድድሩ 10,000 ሰዎች እና 21 ሰው መሰል ሮቦቶች ተሳትፈዋል። https://p.dw.com/p/4tJYj?maca=amh-RED-Telegram-dwcom አስተያየት ለመስጠት ይኽን ቦት ይጠቀሙ @dwamharicbot
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የትንሳኤን በአልን ለማክበር በደቡብ ዞን ሀይቅ መካነ ኢየሱስ በሚገኙ የሀገር ዉስጥ ተፈናቃዮች በመጠለያ ጣቢያ እየተደረገ ያለዉ ዝግጂት ዛሬ እና ከአመታት በፊት ለወግ ማዕረግ በበቁበት፤ ልጅ ወልደዉ ለመሳም በቻሉበት ፤ ቤት ንብረት ባፈሩበት የተፈናቀሉበት ስፍራ ምን ይመስላል ሲል ዶቼ ቬለ ሁኔታዉን ተመልክቷል።
ቪዲዮ ዘገባ ፤ ኢሳያስ ገላው (DW) ፤ ደሴ
Live stream started
በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በሚሰጠው ልዩ ትርጉምና እሴት ትልቁን ስፍራ የሚይዘው የትንሳኤ በዓል እጅጉን የሚጠበቅ የራሱ የሆነ ድባብ አለው፡፡ በዚህ በዓል የሩቅ ቤተዘመድ ከቅርቡ፣ ልጅ ከቤተሰቡ እና ወዳጅ ከዘመዱ ብዙ ርቀት ተጉዘውም ቢሆን መገናኝት፤ ለበዓሉም ቤት ያፈራውን አብሮ መቋደስ ወግ ባህል የሆነ ነውና በበርካቶች ይናፈቃል፡፡ https://p.dw.com/p/4tJaU?maca=amh-RED-Telegram-dwcom አስተያየት ለመስጠት ይኽን ቦት ይጠቀሙ @dwamharicbot
ኢትዮጵያ ውስጥ ዕለታዊ ተግባራት የሆኑ ያሏቸው "መለያየት፣ መጣላት ብሎም እርስ በርስ መገዳደል" እንዲወገዱ እና "በዕርቅ፣ በይቅርታና በውይይት" እንዲፈቱ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን ፓትርያርክ ብፁዕ አቡነ ማትያስ ጥሪ አደረጉ። https://p.dw.com/p/4tJe3?maca=amh-RED-Telegram-dwcom አስተያየት ለመስጠት ይኽን ቦት ይጠቀሙ @dwamharicbot
የትንሳኤን በአልን ለማክበር በደቡብ እና ሰሜን ወሎ ዞን በሚገኙ የሀገር ዉስጥ ተፈናቃዮች በመጠለያ ጣቢያቸዉ እያደረጉት ያለዉ ዝግጅት ዛሬ እና ከአመታት በፊት ለወግ ማዕረግ ባበቁበት ልጅ ወልደዉ ለመሳም በቻሉበት ቤት ንብረት ባፈሩበት የተፈናቀሉበት ስፍራ ምን ይመስል ይሆን? https://p.dw.com/p/4tJUt?maca=amh-RED-Telegram-dwcom አስተያየት ለመስጠት ይኽን ቦት ይጠቀሙ @dwamharicbot
የሚያዝያ 11 ቀን 2017 ዓ/ም የአድማጮች ማኅደር ዝግጅት https://p.dw.com/p/4tJUy?maca=amh-RED-Telegram-dwcom አስተያየት ለመስጠት ይኽን ቦት ይጠቀሙ @dwamharicbot
የሰው አካል ገበያ እና ዝውውር በርካታ ሚሊዮን ዶላሮች ፈሰስ ተደርገዉበት ፤ ጨካኝ እና ዓለማቀፍ የሰው አካል አዘዋዋሪዎችን ማሳተፉ በርግጥ ጉዳዩ ለኬንያ እና ኬንያውያን ብቻም ሳይሆን ለመላው አፍሪቃ አስደንጋጭ ሆኗል። https://p.dw.com/p/4tIUU?maca=amh-RED-Telegram-dwcom አስተያየት ለመስጠት ይኽን ቦት ይጠቀሙ @dwamharicbot
የታንዛንያ ብሔራዊ የምርጫ ኮሚሽን ዋነኛው የተቃዋሚ ፓርቲ ቻዴማ መጪው ዓመት ጥቅምት ወር በሚደረገው አጠቃላይ ምርቻ እንዳይሳተፍ አግዷል። ለፓርቲው ከምርጫ ውድድሩ መታገድ የምርጫ የስነ ምግባር ደንቡን ተቀብሎ አለመፈረሙ በምክንያትነት ተጠቅሷል። https://p.dw.com/p/4tIU0?maca=amh-RED-Telegram-dwcom አስተያየት ለመስጠት ይኽን ቦት ይጠቀሙ @dwamharicbot
ባለፈው ክፍል ጀምበሬ እና ራሒም የጀምበሬን ወላጅ አባት ፍለጋ እንደጀመሩ ሰምተናል። የወንድማማች ልጆቹ በመጀመሪያው ፍለጋቸው አንድ ያወቁት ነገር ነበር። እምነት በበኩሏ በትምህርት ቤቶች መካከል የሚደረገው የውድድር ሃሳብ በሌላ ተፎካካሪ ጥቅም ላይ እንደዋለ ተረድታለች። እንዴት ሆነ? ተከታዩ ክፍል “አንድ ምስል ከ ሺ ቃላት ይበልጣል” በሚል ርዕስ እነሆ ቀርቧል። https://p.dw.com/p/4nuq9?maca=amh-RED-Telegram-dwcom አስተያየት ለመስጠት ይኽን ቦት ይጠቀሙ @dwamharicbot
Live stream finished (1 hour)
የሚያዝያ 11 ቀን2017 የዓለም ዜና


· · የኢትዮጵያ የጸጥታ አስከባሪዎች በአዲስ ስታንዳርድ ሚዲያ ቢሮ እና በተቋሙ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሠራተኛ የመኖሪያ ቤት ብርበራ ማካሔዳቸውን ጃኬን አሳታሚ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ አስታወቀ። ሐሙስ ዕለት በተካሔደው ብርበራ ሦስት ሠራተኞችታስረው መፈታታቸውን ስምንት ላፕቶፖች፣ ሁለት ዴስክ ቶፕ ኮምፒውተሮች እና ስምንት ሞባይል ስልኮችን ጨምሮ ልዩ ልዩ ቁሳቁሶች በጸጥታ አስከባሪዎች መወሰዳቸውን በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ፈቃድ የተሰጠው አሳታሚ ትላንትአርብ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
· በመጪው ግንቦት በይፋ መራኄ-መንግሥት ይሆናሉ ተብለው የሚጠበቁት ፍሬድሪሽ ሜርስ የጀርመንን ኢኮኖሚ ለማዘመን
ቃል ገቡ። ሜርስ "ዓላማችን ግልጽ ነው። ጀርመን በኢኮኖሚ ጠንካራ፣ ደሕነቷ የተረጋገጠ፣ ፍትኃዊ እናየበለጠ ዘመናዊ መሆን አለባት" ብለዋል።
·
የሩሲያው ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን ነገ የሚከበረውን የፋሲካ በዓል ምክንያት በማድረግ በዩክሬን በሚካሔደው ጦርነት በተናጠልተኩስ አቁም አወጁ። የዩክሬን ፕሬዝደንት ቮሎዶሚር ዜሌንስኪ ግን የሩሲያው ፕሬዝደንት "በሰዎች ሕይወት ለመጫወት እየሞከሩ ነው" ሲሉ በታወጀው የአጭር ጊዜ የተኩስ አቁም እምነት እንደሌላቸው የሚጠቁም አስተያየት ሰጥተዋል።
·
በኢራን እና በአሜሪካ መካከል ኑክሌርን በተመለከተ የሚካሔደው ድርድር "ወደፊት እየተራመደ" መሆኑን የኢራን ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አርጋቺ ተናገሩ። የሁለቱ ሀገሮች ተወካዮችዛሬ ቅዳሜ በጣልያን ዋና ከተማ ሮም ከተገናኙ በኋላ "ድርድሩ ወደፊት እየተራመደ
ነው ማለት እችላለሁ" ያሉት አማን አርጋቺ "አሁን በተለያዩ መርኆች እና ዓላማዎች ረገድ ከጥሩ መግባባት ላይ ደርሰናል" ሲሉ ለሀገራቸው ቴሌቭዥን ጣቢያ ተናግረዋል።
· ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ባሸነፉበት በቤጂንግ የተካሔደ የግማሽ ማራቶን ሩጫ ቻይና ሰው መሰል ሮቦቶች አወዳደረች። ውድድሩን
ኢትዮጵያውያኑ ኤልያስ ደስታ እና ሐዊ ጉደታ አሸንፈዋል።
ዜናውን ለማድመጥ የድምጽ ማዕቀፉን ይጫኑ https://p.dw.com/p/4tJmR?maca=amh-RED-Telegram-dwcom አስተያየት ለመስጠት ይኽን ቦት ይጠቀሙ @dwamharicbot