DW Amharic
56.4K subscribers
4.14K photos
984 videos
69 files
15.7K links
ይህ የዶይቼ ቬለ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው። ትኩስ ዜና፣ በአበይት ፖለቲካዊ፣ ኤኮኖሚያዊ፤ ማኅበራዊ እና ባሕላዊ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩር ትንታኔ ያቀርባል።
Download Telegram
ሰላም ጤና ይስጥልን ውድ አድማጮች። እንደሁሌው አንድ ሰዓት ላይ የሚጀምረው የዛሬው ሥርጭታችን ከዓለም ዜና በኋላ በሚቀርበው የዜና መፅሔታችን
ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያውያን ሕብረት
በኮምቦልቻና አካባቢው በኤሌክትሪክ ማስተላለፊያዎች የተፈጸመው ስርቆት
በማዕከላይ ኢትዮጵያ ክልል የኤች አይ ቪ ኤይድስ ስርጭት አሳሳቢ ደረጃ መድረሱን
ህወሓት ያወጣው መግለጫ የሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ተካተዋል።
ሳምንታዊ ዝግጅቶች ማሕደረ ዜናና ስፖርትም ሰዓታቸውን ጠብቀው ይቀርባሉ። እንድትከታተሉን ከወዲሁ በአክብሮት እንጋብዛለን።
Live stream started
Live stream finished (58 minutes)
በአማራ ክልል የተከሰተ የነዳጅ እጥረት አሽከርካሪዎችንእግር ተወርች አስሯቸዋል። ዶይቼ ቬለ ያነጋገራቸው አንድ አሽከርካሪ እንደሚሉት በባሕር ዳር ነዳጅ ለመቅዳት እስከ አራት ቀናት
ለመጠበቅ ተገደዋል። በክልሉ ዋና ከተማ የነዳጅ የችርቻሮ ዋጋ 108 ብር ቢሆንም 120 ብር እንደሚከፍሉ ሌላ አሽከርካሪ አስረድተዋል።እንዲያም ሆኖ በማደያዎች ነዳጅ እንደገባ አልቋል የሚል ምላሽ ይሰጣቸዋል። የክልሉ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ በበኩሉ በነዳጅ ግብይት ሥርዓት ላይ በርካታ ህገወጥነት ቢኖርም በህገወጦች ላይ እርምጃ
እየተወሰደ እንደሆነ ይገልፃል፡፡ https://p.dw.com/p/4t7t4?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
አስተያየት ለመስጠት ይኽን ቦት ይጠቀሙ 👉🏾
@dwamharicbot
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል እየጨመረ የመጣው የኤችአይቪ ሥርጭት አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን የክልሉ ጤና ቢሮ አስታወቀ። ባለፉት ሰባት ወራት ብቻ ምርመራ ከተደረገላቸው ሰዎች መካከል 6.7 በመቶ በደማቸው ኤችአይቪ ተገኝቶባቸዋል። የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው “የቫይረሱ ሥርጭት ሳናውቀው ችግር ውስጥ እያስገባን ይገኛል” ብለዋል። https://p.dw.com/p/4t7G8?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
አስተያየት ለመስጠት ይኽን ቦት ይጠቀሙ 👉🏾
@dwamharicbot
የህወሓት ሊቀ-መንበር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል በፕሪቶሪያ በተፈረመው ግጭት የማቆም ሥምምነት ላይ የአፍሪካ ኅብረት አሸማጋዮች በአፋጣኝ ተሰብስበው እንዲወያዩ ጥሪ አቀረቡ። በዶክተር ደብረፅዮን የሚመራው ህወሓት የኢትዮጵያ ፌደራል መንግስቱ የፕሪቶርያው የሰላም ስምምነት እየጣሰ በተናጠል አዋጆች፣ ደንቦች እና መመርያዎች እያወጣ ይገኛል ሲል ወቅሷል። https://p.dw.com/p/4t7c7?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
አስተያየት ለመስጠት ይኽን ቦት ይጠቀሙ 👉🏾
@dwamharicbot
በአማራ ክልል በኃይል ተሸካሚ የብረት ምሰሶ ላይ በተፈጸመ ሥርቆት ደሴ፣ ኮምቦልቻ እና ወልዲያን በመሳሰሉ ከተሞች የኤሌክሪክ አገልግሎት መቋረጡን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የአካባቢው ኃላፊ ለዶይቼ ቬለ ተናገሩ። አብዛኛው ደቡብ ወሎ እንዲሁም በተወሰኑ የሰሜን ወሎ እና የሰሜን ሸዋ ዞኖች አካባቢዎች አገልግሎቱ ተቋርጧል። ፋብሪካዎች ሥራቸው ተስተጓጉሏል። https://p.dw.com/p/4t7l5?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
አስተያየት ለመስጠት ይኽን ቦት ይጠቀሙ 👉🏾
@dwamharicbot
የኢትዮጵያ ፀረ አበረታች ቅመሞች ባለሥልጣንና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ቀደም ሲል በዋናነት ለትራክና ለሜዳ ውድድሮች ትኩረት ይሰጥ የነበረ ቢሆንም ፣ ከ2017 የውድድር ዘመን ጀምሮ ግን በየትኛውም የአለማችን ክልፍል በሚደረጉ ማናቸውም ውድድሮች ላይ ምርመራና ቁጥጥር ማድረግ አስገዳጅ መሆኑን ተናግረዋል። https://p.dw.com/p/4t7bO?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
አስተያየት ለመስጠት ይኽን ቦት ይጠቀሙ 👉🏾
@dwamharicbot
የሙጃህዲያን ኢ-ኻሊቅ (MEK)ና የቡድኑ ምክር ቤት መሪዎች ኢራን በ1967 ከአሜሪካ ባገኘችዉ ድጋፍ የጀመረችዉን የኑክሌር መርሐ ግብርን ወደ ኑክሌር ቦምብ መስሪያነት ለመቀየር ናታንዝና አራክ ዉስጥ በድብቅ እያብላላች መሆኑን ለዓለም አረዱ።ወይም አበሰሩ።ነሐሴ 2003፤ ዋሽግተን። https://p.dw.com/p/4t86p?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
አስተያየት ለመስጠት ይኽን ቦት ይጠቀሙ 👉🏾
@dwamharicbot
የኢትዮጵያ መንግሥት ተግባራዊ ለሚያደርገው የኮሪደር ልማት ፕሮጀክት ሰዎችን በግዳጅ ማፈናቀል በአፋጣኝ እንዲያቆም አምነስቲ ኢንተርናሽናል ጠየቀ። አምነስቲ መንግሥት “በግዳጅ መፈናቀልን ለመከላከል ቁልፍ የሕግ እና የአሠራር ሥርዓቶች ባለማዘጋጀቱ የተጎጂዎችን ሰብአዊ መብቶች ጥሷል” የሚል ድምዳሜ ላይ ደርሷል።

https://p.dw.com/p/4t8xO?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
በአማራ ክልል ያለው የነዳጅ እጥረት አሁንም የክልሉ ችግር ሆኖ መቀጠሉን አሽከርካሪዎች እየተናገሩ ነው፡፡ በባሕር ዳር ከተማ በየግዜው ነዳጅ ለመቅዳት ረጃጅም የተሽከርካሪ ሰልፎች በከተማዋ ነዋሪዎች እንቅስቃሴዎች ላይ ጫና እየፈጠር እንደሆነ አስተያየት ሰጪዎች ይናገራሉ፡፡ የክልሉ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ በበኩሉ በነዳጅ ግብይት ሥርዓት ላይ በርካታ ህገወጥነት ቢኖርም በህገወጦች ላይ እርምጃ እየተወሰደ እንደሆነ ይገልፃል፡፡
የቪድዮ ዘገባ፤ ዓለምነው መኮንን
የዶይቸ ቬለ የዩቲዩብ ገጻችን ይከተሉ! ለባለንጀራዎም ያጋሩ!
ውድ አድማጮቻችን የተለያዩ መገናኛ አውታሮችን በመጠቀም አድማሳችንን በማስፋት ዝግጅቶቻችንን በዩቲዩብም ማቅረብ ጀምረናል ። የአዲሱና የትክክለኛው የዶይቸ ቬለ ዩቲዩብ ገጽ አባል በመሆን ዝግጅታችንን ተከታተሉ ። በትክክለኛው በዚህ የዩቲዩብ አድራሻችን፦ https://www.youtube.com/channel/UC3-RNH75BEZslJLEoIAxa2A
አባል ይሁኑ ። ለወዳጆቻችሁም ያጋሩ ።
ሰላም ጤና ይስጥልን ውድ አድማጮች። በዛሬው ሥርጭታችን ከዓለም ዜና በኋላ በሚቀርበው የዜና መፅሔታችን
የመንግሥት የኢኮኖሚ ዕድገት መረጃ እና የሚሰጡ አስተያየቶች
ኢትዮጵያ ለአደጋ ስጋት ምላሽ ፈንድ የሚውል ገቢ፤ ከግለሰቦች እና ከሰራተኞች ደመወዝ እንዲሰበሰብ የሚያስገድደውን ረቂቅ አዋጅ ስራ ላይ ለማዋል እየሰራች ነው መባሉን፡፡
የፍልስጤምና የአውሮፓ ህብረት የፖለቲካ ውይይት የሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ተካተዋል።
ሳምንታዊ ዝግጅቶች ጤናና አካባቢ እንዲሁም አውሮፓና ጀርመን ሰዓታቸውን ጠብቀው ይቀርባሉ። እንድትከታተሉን ከወዲሁ በአክብሮት እንጋብዛለን።
Live stream started
ወይዘሮ ካላስ በጋዛ ለደረሰው ውድመትና እልቂት ሀዘናቸውን በመግለጽ እስራኤል ወደ ጋዛ እርዳታ እንዳይገባ መክልከሏን በጥብቅ አውግዘዋል፤ “ ወደጋዛ እርዳታ እንዳይገባ መከልከሉን በጥብቅ እናወግዛለን። እስራኤል እርዳታ ያለምንም ችግር ወደ አክባቢው እንዲገባ ማድረግ ይኖርባታል” በማለት ህብረቱ ከፍልስጤቴም ህዝብ ጋር ያለውን አንድነት ገልጸዋል https://p.dw.com/p/4tAS2?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
አስተያየት ለመስጠት ይኽን ቦት ይጠቀሙ 👉🏾 @dwamharicbot
የኢትዮጵያ የፕላን እና ልማት ሚኒስትር ፍፁም አሰፋ ሰሞኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበትት ለመንግሥት የካቢኔ አባላት የሀገሪቱን የዘጠኝ ወራት የምጣኔ ሐብት የሥራ አፈፃፀም ሲያቀርቡ መንግሥት የያዘውን የ8.4 በመቶ የኡኮኖሚ ዕድገት ውጥን ሊያሳካ የሚችልበት ያሏቸው አመላካቾችን ዘርዝረዋል https://p.dw.com/p/4tABU?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
አስተያየት ለመስጠት ይኽን ቦት ይጠቀሙ 👉🏾 @dwamharicbot
በቅርቡ ለዝርዝር ዕይታ ለፓርላማ ቋሚ ኮሚቴ የተመራው ረቂቅ አዋጁ፤ የመንግስት እና የግል ተቋማት ከሚሰጧዋቸው የተለያዩ አገልግሎቶች “ለአደጋ ስጋት ምላሽ ፈንድ” የሚውል ገቢ እንዲሰበስቡ ያስገድድዳል። https://p.dw.com/p/4tAdn?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
አስተያየት ለመስጠት ይኽን ቦት ይጠቀሙ 👉🏾 @dwamharicbot
የአማራ ክልል ህብረተሰብ ጤና ተቋም ዋና ዳይሬክተር አቶ በላይ በዛብህ ሰሞኑን በሰጡት መግለጫ በሽታው ባሕር ዳር ከተማ አስተዳደርን ጨምሮ በአማራ ክልል 3 ወረዳዎች መከሰቱንና ከ1ሺህ 400 በላይ ሠዎች በበሽታው መያዛቸውን ተናግረዋል፡፡ https://p.dw.com/p/4t9Er?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
አስተያየት ለመስጠት ይኽን ቦት ይጠቀሙ 👉🏾 @dwamharicbot
የሚያዝያ 7 ቀን 2017 የዓለም ዜና
·
በአማራ ክልል ከመንግሥት የሚዋጉታጣቂ ኃይሎች “ችግሮችን ለመፍታት ወደ ውይይት እንዲመጡ” የአማራ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ጥሪ አቀረበ። ምክር
ቤቱ ጥሪውን ያቀረበው የመንግሥት የጸጥታ አስከባሪዎች ከፋኖ ታጣቂዎች የሚያደርጉት ውጊያ ሁለተኛ ዓመቱን ሊደፍን በተቃረበበት ወቅትነው።
·
በደቡብ ሱዳን እየተባባሰ በመጣውግጭት ካለፈው መጋቢት ወዲህ ከ200 በላይ ሰዎች መገደላቸውን እና ከ125,000 በላይ የሚገመቱ ሰዎች መፈናቀላቸውን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታወቀ። ድርጅቱ ዛሬ
ማክሰኞ ባሰራጨው መግለጫ ከአየር በተፈጸመ ድብደባ ብቻ ከ180 በላይ ሰዎች መገደላቸውን፤ ከ250 በላይ መቁሰላቸውን ይፋ አድርጓል።
· ሶማሊያ ከ56 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ለምርጫ
ድምጽ ሰጪዎችን መመዝገብ ጀመረች። ዛሬ የተጀመረው የድምጽ ሰጪዎች ምዝገባ መንግሥታት የሚያወጧቸውን ሕግጋት የሚያሟሉ ዜጎችን የመምረጥመብት ወደሚያረጋግጥ ዓለም አቀፍ አሠራር ሶማሊያን አንድ እርምጃ የሚያቀርብ ነው።
·
በሱዳን አስገድዶ መድፈር እንደ ጦርሥልት ጥቅም ላይ እየዋለ እንደሚገኝ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስጠነቀቀ። ዛሬ ሁለተኛ ዓመቱን የደፈነው የሱዳን ጦርነት እንዲቆም
የአፍሪካ ኅብረትን ጨምሮ የዓለም ሀገራት ጥሪ አስተላልፈዋል።
· እስራኤል በጋዛ ሠርጥ በሚገኘው የኩዌት
የመስክ ሆፒታል ደጃፍ በፈጸመችው የአየር ጥቃት አንድ የሕክምና ባለሙያ ሲገደሉ በርካቶች ቆሰሉ። ጥቃቱ የተፈጸመው በመቶ ሺሕዎችየሚቆጠሩ ሰዎች በተበታተኑ የድንኳን መጠለያዎች በሚኖሩበት ሙዋሲ የተባለ አካባቢ ነው።
·
አልጄሪያ አስራ ሁለት የፈረንሳይዲፕሎማቶች ለማባረር ያሳለፈችው ውሳኔ መዘዝ እንደሚኖረው የፈረንሳይ ውጪ ጉዳይ መሥሪያ ቤት አስጠነቀቀ። እርምጃውን "አሳዛኝ" ያሉት የፈረንሳይ ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር
ዦን ንዌል ባሮ ሀገራቸው የአልጄሪያን ውሳኔ በዝምታ እንደማታልፍ ዛሬ ማክሰኞ ተናግረዋል።
ዜናውን ለማድመጥ የድምጽ ማዕቀፉን ይጫኑ
https://p.dw.com/p/4tAyZ?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
አስተያየት ለመስጠት ይኽን ቦት ይጠቀሙ 👉🏾 @dwamharicbot