ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ አንደኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን ዛሬ በአዲስ አበባ እንዳያካሒድ መከልከሉን አስታወቀ። ፓርቲው በዋና ከተማዋ በሚገኘው ጋምቤላ ሆቴል ጠቅላላ ጉባኤውን ለማካሔድ ፈቃድ አግኝቶ እንደነበር ምክትል ፕሬዝደንቱ አቶ አምሀ ዳኘው ተናግረዋል። የሆቴሉ ምክትል ሥራ አስኪያጅ "ከእናንተ በፊት ከኦሮሚያ ፖሊስ መጥተው ስብሰባው እዚህ እንዳይካሔድ ብለው አስፈራርተውኛል" የሚል ምላሽ እንደሰጧቸው አቶ አምሀ ጠቅላላ ጉባኤው እንደማይካሔድ ከተረጋገጠ በኋላ ከሆቴሉ ደጃፍ ከፓርቲው አመራሮች ጋር ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት ተናግረዋል።
ከአቶ አምሀ በተጨማሪ ሌሎች የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ አመራሮች ለተስተጓጎለው ጠቅላላ ጉባኤ "የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ እና የደህንነት ኃይሎች ከፍተኛ ጫና" አድርገዋል እያሉ ሲከሱ ተደምጠዋል።
ፓርቲው ጠቅላላ ጉባኤውን እንዳያካሒድ የገጠመው እንቅፋት ከኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ በኩል ውግዘት ገጥሞታል። የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ ጠቅላላ ጉባኤ እንዳይካሔድ መደረጉ ከተረጋገጠ በኋላ ኢዜማ ባወጣው መግለጫ "የመድብለ-ፓርቲ ሥርዓትን ለማምጣት የሚደረገውን ጥረት የሚያከስም ዓይን ያወጣ ህገ ወጥ-ተግባር" በማለት አውግዟል። ባለፈው የካቲት 26 ቀን 2015 እናት ፓርቲ ጠቅላላ ጉባኤውን በቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ አዳራሽ ለማድረግ ሲሞክር “ከመንግሥት የመጣ” በተባለ “ትዕዛዝ” መከልከሉን አስታውቆ ነበር። 👉🏾 @dwamharicbot

የሱዳን የሽግግር ሉዓላዊ ምክር ቤት ፕሬዝደንት ጄኔራል አብዱል ፋታኅ አል-ቡርኻን እና ምክትላቸው ብርጋዴየር ጄኔራል መሐመድ ሐምዳን ዳጋሎ (ሔሜቲ) የአገሪቱን ጸጥታ የሚከታተል የጋራ ኮሚቴ ማቋቋማቸውን አስታወቁ። ኮሚቴው የአገሪቱን መደበኛ ኃይሎች፣ ጉዳዩ የሚመለከታቸው የመንግሥት ተቋማት እና ታጣቂ ቡድኖች እንደሚያካትት የሱዳን መንግሥት የሚቆጣጠረው ሱና (SUNA) የዜና ወኪል ዘግቧል። ሁለቱ ወታደራዊ ሹማምንት ውሳኔውን ያሳለፉት ትላንት ቅዳሜ በኻርቱም ባደረጉት ስብሰባ ነው።
ባለፈው ጥቅምት ከተካሔደው እና ጄኔራል አብዱል ፋታኅ አል ቡርኻን ከመሩት መፈንቅለ-መንግሥት በኋላ ሁለቱ ሹማምንት የሚመሩት ወታደራዊ መንግሥት ብርቱ ተቃውሞዎች ሲገጥሙት ቆይቷል። ጄኔራል አብዱል ፋታኅ አል ቡርኻን እና ብርጋዴየር ጄኔራል መሐመድ ሐምዳን ዳጋሎ (ሔሜቲ) ባለፈው መስከረም የሱዳን የሽግግር ሉዓላዊ ምክር ቤት መሪ እና የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር በሲቪል ፖለቲከኞች እንዲመረጡ መወሰናቸውን ቢያስታውቁም እስካሁን የታየ ነገር የለም። 👉🏾 @dwamharicbot

የሳዑዲ አረቢያው ግዙፍ የነዳጅ እና ጋዝ አምራች ኩባንያ አራምኮ ባለፈው አንድ ዓመት ብቻ 161 ቢሊዮን ዶላር ማትረፉን ይፋ አደረገ። የአራምኮ ዋና ሥራ አስፈጻሚ እና ፕሬዝደንት አሚን ሐሰን ናስር ዛሬ እሁድ ባወጡት መግለጫ የኩባንያው ዓመታዊ ትርፍ በጎርጎሮሳዊው 2021 ከነበረበት 110 ቢሊዮን ዶላር በዚህ ዓመት በ46.5 በመቶ ከፍ ማለቱን ገልጸዋል። ኩባንያው ባለፈው ዓመት በቀን የሚያመርተው ድፍድፍ ነዳጅ 11.5 ሚሊዮን በርሜል ደርሷል። ከአራት ዓመታት በኋላ ወደ 13 ሚሊዮን በርሜል ከፍ የማድረግ ዕቅድ አለው።
የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በበረታበት እና የነዳጅ ዋጋ ባሽቆለቆለበት የጎርጎሮሳው 2020 አራምኮ ያገኘው ገቢ 49 ቢሊዮን ዶላር ነበር። ኩባንያው 161 ቢሊዮን ዶላር ያተረፈው በሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት ምክንያት በዓለም ገበያ የኃይል ቀውስ በበረታበት ዓመት ነው። በጦርነት ሰበብ በሩሲያ ላይ በተጣሉ ማዕቀቦች ሳቢያ በምዕራባውያን አገራት ገበያ የሚቀርበው የሩሲያ ነዳጅ እና ጋዝ ምርት እጅግ የተገደበ ነበር። በዓለም ገበያ የነዳጅ ዋጋ ማሻቀብ በሳዑዲ አረቢያ እና በአሜሪካ መካከል ያለውን ግኑኝነት አሻክሮት ቆይቷል። 👉🏾 @dwamharicbot

ሞዛምቢክ በወር ለሁለተኛ ጊዜ ከሕንድ ውቅያኖስ በሚነሳ በኃይለኛ ወጀብ ተመታች። ማዕከላዊ ሞዛምቢክን የመታው፤ ከፍተኛ ዝናብ፣ ኃይለኛ ንፋስ እና ጎርፍ ያስከተለ ወጀብ በጥንካሬውም ሆነ በተከሰተበት የጊዜ ልዩነት ከዚህ ቀደም ከታዩት ሁሉ የከፋው ነው ተብሏል። በሞዛምቢክ የአንድ አመቱ ዝናብ ባለፉት አራት ሣምንታት ብቻ መጣሉን ሬውተርስ ዘግቧል። እስካሁን አንድ ሰው መሞቱ ቢረጋገጥም የመገናኛ አገልግሎቶች እና የኤሌክትሪክ አቅርቦት በወጀቡ በመቋረጣቸው እስካሁን የደረሰው የጉዳት መጠንም ይሁን የሞቱ ሰዎች ብዛት በትክክል አይታወቅም።
ኃይለኛው ወጀብ ቅዳሜ ለሊቱን ያረፈው በሞዛምቢክ በስተምስራቅ ከሕንድ ውቅያኖስ ዳርቻ በምትገኘው ክሊማነ የተባለች ከተማ ነው። በከተማዋ የሚገኙ ጉይ ታይለር የተባሉ በተባበሩት መንግሥታት የሕጻናት መርጃ ድርጅት (UNICEF) ባልደረባ "ንፋሱ ለሊቱን ሙሉ በጣም ጠንካራ ነበር። ብዙ ውድመት ደርሷል። ዛፎች ተገንድሰዋል፤ ጣሪያዎች ተገንጥለዋል" ሲሉ በስልክ ለሬውተርስ ሁኔታውን አስረድተዋል።
የአካባቢው ነዋሪዎች ትምህርት ቤቶች፣ አብያተ-ክርስቲያናት እና መጋዘኖችን ጨምሮ በጊዜያዊ መጠለያዎች እንዲሸሸጉ ተመክረዋል። በወጀቡ ሳቢያ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ሰዎች ሰብዓዊ ቀውስ ሊገጥማቸው እንደሚችል በአገሪቱ የሚንቀሳቀሱ የግብረ ሰናይ ድርጅቶች ሥጋት አላቸው። ባለፈው ወር በተከሰተ ተመሳሳይ ወጀብ በሞዛምቢክ እና በማዳጋስካር 27 ሰዎች ሲሞቱ 171,000 ሰዎች ችግር ላይ ወድቀዋል። 👉🏾 @dwamharicbot

የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝደንት ሲሪል ራማፖሳ ከከብት ማርቢያቸው ግማሽ ሚዮን ዶላር ገደማ ሲሰረቅ ለፖሊስ አላመለከቱም በሚል ከገቡበት ቅሌት ነጻ ወጡ። የሙስና ጉዳዮችን የሚከታተለው "የሕዝብ ጠባቂ" የተባለ የደቡብ አፍሪካ መንግሥት ተቋም በቅሌቱ የፕሬዝደንቱ እጅ እንደሌለበት ባደረገው ምርመራ የመጀመሪያ ውጤት ማረጋገጡን የአገሪቱ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል። የፕሬዝደንቱ ቃል አቀባይ ቪንሰንት ማግዌንያ ራማፖሳ የምርመራውን የመጀመሪያ ውጤት እንደተቀበሉ አረጋግጠዋል።
የፕሬዝደንቱን ስም ሊያጠለሽ ያሰጋው ቅሌት የተቀሰቀሰው ባለፈው ሰኔ ከፕሬዝደንቱ ከብት ማርቢያ ከሚገኝ መኖሪያ ቤት ከሶፋ ውስጥ ተሸሽጎ የነበረ 500 ሺሕ ዶላር ገደማ መሰረቁ ከተረጋገጠ በኋላ ነው። ገንዘቡ ለአንድ ሱዳናዊ ከብት ተሸጦ የተገኘ መሆኑን የገለጹት ራማፖሳ ስርቆቱን ለፖሊስ አላመለከቱም የሚል ውንጀላ ቀርቦባቸው ነበር። ተቺዎቻቸው ጉዳዩ በፕሬዝደንትነታቸው የጥቅም ግጭት ጭምር አለበት የሚል ክስ አቅርበዋል።
የሕዝብ ጠባቂ የተባለው ተቋም ምርመራ የመጀመሪያ ውጤት ግን ራማፖሳ ጉዳዩን ለፕሬዝዳንታዊ ጥበቃ ጓድ ኃላፊ ማመልከታቸውን አረጋግጦ ነጻ አውጥቷቸዋል። የፕሬዝዳንታዊ ጥበቃ ጓድ ኃላፊው በአንጻሩ ጉዳዩን በቀጥታ ለፖሊስ ከማመልከት ይልቅ የራሳቸውን ምርመራ በመጀመር ተገቢ ያለ ሆነ እርምጃ መውሰዳቸውን የተቋሙ ሪፖርት አትቷል። ራማፖሳ የሙስና ጉዳዮችን በሚከታተለው መስሪያ ቤት የመጀመሪያ ውጤት እፎይታ ቢያገኙም የአገሪቱ ፖሊስ የሚያደርገው ምርመራ ገና አልተጠናቀቀም። 👉🏾 @dwamharicbot

የመጋቢት 03 ቀን 2015 የዓለም ዜና
• ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ አንደኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን ዛሬ በአዲስ አበባ እንዳያካሒድ መከልከሉን አስታወቀ። ፓርቲው በዋና ከተማዋ በሚገኘው ጋምቤላ ሆቴል ጠቅላላ ጉባኤውን ለማካሔድ ፈቃድ አግኝቶ እንደነበር ምክትል ፕሬዝደንቱ አቶ አምሀ ዳኘው ተናግረዋል። የሆቴሉ ምክትል ሥራ አስኪያጅ "ከእናንተ በፊት ከኦሮሚያ ፖሊስ መጥተው ስብሰባው እዚህ እንዳይካሔድ ብለው አስፈራርተውኛል" የሚል ምላሽ እንደሰጧቸው አቶ አምሀ ጠቅላላ ጉባኤው እንደማይካሔድ ከተረጋገጠ በኋላ ከሆቴሉ ደጃፍ ከፓርቲው አመራሮች ጋር ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት ተናግረዋል። ኢዜማ በመንግሥት ተደረገ የተባለውን ክልከላ "የመድብለ-ፓርቲ ሥርዓትን ለማምጣት የሚደረገውን ጥረት የሚያከስም ዓይን ያወጣ ህገ ወጥ-ተግባር" በማለት አውግዟል።
• የሱዳን የሽግግር ሉዓላዊ ምክር ቤት ፕሬዝደንት ጄኔራል አብዱል ፋታኅ አል-ቡርኻን እና ምክትላቸው ብርጋዴየር ጄኔራል መሐመድ ሐምዳን ዳጋሎ (ሔሜቲ) የአገሪቱን ጸጥታ የሚከታተል የጋራ ኮሚቴ ማቋቋማቸውን አስታወቁ። ኮሚቴው የአገሪቱን መደበኛ ኃይሎች፣ ጉዳዩ የሚመለከታቸው የመንግሥት ተቋማት እና ታጣቂ ቡድኖች እንደሚያካትት የሱዳን መንግሥት የሚቆጣጠረው ሱና (SUNA) የዜና ወኪል ዘግቧል።
• ሞዛምቢክ በወር ለሁለተኛ ጊዜ ከሕንድ ውቅያኖስ በሚነሳ በኃይለኛ ወጀብ ተመታች። ማዕከላዊ ሞዛምቢክን የመታው፤ ከፍተኛ ዝናብ፣ ኃይለኛ ንፋስ እና ጎርፍ ያስከተለ ወጀብ በጥንካሬውም ሆነ በተከሰተበት የጊዜ ልዩነት ከዚህ ቀደም ከታዩት ሁሉ የከፋው ነው ተብሏል። በሞዛምቢክ የአንድ አመቱ ዝናብ ባለፉት አራት ሣምንታት ብቻ መጣሉን ሬውተርስ ዘግቧል። እስካሁን አንድ ሰው መሞቱ ቢረጋገጥም የመገናኛ አገልግሎቶች እና የኤሌክትሪክ አቅርቦት በወጀቡ በመቋረጣቸው እስካሁን የደረሰው የጉዳት መጠንም ይሁን የሞቱ ሰዎች ብዛት በትክክል አይታወቅም።
• የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝደንት ሲሪል ራማፖሳ ከከብት ማርቢያቸው ግማሽ ሚዮን ዶላር ገደማ ሲሰረቅ ለፖሊስ አላመለከቱም በሚል ከገቡበት ቅሌት ነጻ ወጡ። የሙስና ጉዳዮችን የሚከታተለው "የሕዝብ ጠባቂ" የተባለ የደቡብ አፍሪካ መንግሥት ተቋም በቅሌቱ የፕሬዝደንቱ እጅ እንደሌለበት ባደረገው ምርመራ የመጀመሪያ ውጤት ማረጋገጡን የአገሪቱ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።
• የሳዑዲ አረቢያው ግዙፍ የነዳጅ እና ጋዝ አምራች ኩባንያ አራምኮ ባለፈው አንድ ዓመት ብቻ 161 ቢሊዮን ዶላር ማትረፉን ይፋ አደረገ። የአራምኮ ዋና ሥራ አስፈጻሚ እና ፕሬዝደንት አሚን ሐሰን ናስር ዛሬ እሁድ ባወጡት መግለጫ የኩባንያው ዓመታዊ ትርፍ በጎርጎሮሳዊው 2021 ከነበረበት 110 ቢሊዮን ዶላር በዚህ ዓመት በ46.5 በመቶ ከፍ ማለቱን ገልጸዋል። ኩባንያው ባለፈው ዓመት በቀን የሚያመርተው ድፍድፍ ነዳጅ 11.5 ሚሊዮን በርሜል ደርሷል።
የዕለቱን ዜና ለማድመጥ የሚከተለውን መስፈንጠሪያ ይጫኑ፦ https://p.dw.com/p/4OZW3?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
አስተያየት ለመስጠት፣ ጥቆማ ለማድረስ ይኽን ቦት ይጠቀሙ 👉🏾 @dwamharicbot

DW.COM
የመጋቢት 03 ቀን 2015 የዓለም ዜና | DW | 12.03.2023
ኢትዮጵያ ውስጥ ዓመታትን የተሻገረው የፖለቲካ አለመረጋጋት በህዝቡ ላይ ያስከተለው ስጋት ከዕለት ወደ ዕለት እየጠናበት በመሄድ ላይ ነው። በአወዛጋቢ ፖለቲካዊ ትርክትና ግልጽ ባልሆነው የፖለቲካ መርህ በየጊዜው ቅርጻቸውን የሚቀያይሩት ሀገራዊና አካባቢያዊ ጉዳዮች በሚቀሰቅሱት ውዝግብ ሕይወት እየተቀጠፈ፤ በርካቶች ለጉዳት እና እስር እየተዳረጉ ነው። https://p.dw.com/p/4OWy0?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
አስተያየት ለመስጠት፣ ጥቆማ ለማድረስ ይኽን ቦት ይጠቀሙ 👉🏾 @dwamharicbot
አስተያየት ለመስጠት፣ ጥቆማ ለማድረስ ይኽን ቦት ይጠቀሙ 👉🏾 @dwamharicbot
DW
መረጋጋት የተሳነው የፖለቲካ አውድ
ኢትዮጵያ ውስጥ ዓመታትን የተሻገረው የፖለቲካ አለመረጋጋት በህዝቡ ላይ ያስከተለው ስጋት ከዕለት ወደ ዕለት እየጠናበት በመሄድ ላይ ነው። በአወዛጋቢ ፖለቲካዊ ትርክትና ግልጽ ባልሆነው የፖለቲካ መርህ በየጊዜው ቅርጻቸውን የሚቀያይሩት ሀገራዊና አካባቢያዊ ጉዳዮች በሚቀሰቅሱት ውዝግብ ሕይወት እየተቀጠፈ፤ በርካቶች ለጉዳት እና እስር እየተዳረጉ ነው።
የሰኞ መጋቢት 4 ቀን 2015 ዓም ዐርዕስተ ዜና
ስደተኞችን ጭና ባለፈው ቅዳሜ ከሊቢያ የተነሳች አንዲት ጀልባ ሜዴትራንያን ባህር ላይ ሰጥማ ከተሳፋሪዎቹ 30ው የደረሱበት እንዳልታወቀ የኢጣልያ የባህር ጠረፍ ጠባቂ አስታወቀ። ከስደተኞች 17ቱ ከሊቢያ የባህር ክልል በሕይወት መትረፋቸውንና የጠፉት ፍለጋም መቀጠሉንም ተገልጿል።
ባለፈው ቅዳሜና እሁድ ሞዛምቢክንና ማላዊን ለሁለተኛ ጊዜ የመታው ፍሪዲ የሚል ስም የተሰጠው ወጀብ በማላዊ ብቻ ቢያንስ 60 ሰዎችን ገደለ። ማዕከላዊ ሞዛምቢክን ባለፈው ቅዳሜ የመታው ወጀቡ የቤቶችን ጣሪያዎች ነቃቅሏል። በተለይ ክዊሊማነ የተባለችው ወደብ ዙሪያ ከባድ ጎርፍ ጉዳት አድርሷል።
ኢራን በቅርብ ጊዜው ፀረ-መንግስት ተቃውሞ ለታሰሩ ከ22ሺህ በላይ ሰዎች ይቅርታ ማድረጓን ዛሬ አስታወቀች። ኢራን ዛሬ ይቅርታ አደረጉላቸው ያለቸው እስረኞች ቁጥር የኢራን ሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ቡድን ከዘገበው የበለጠ ነው።
ሙሉውን ዜና ለማዳመጥ ከታች የሚገኘውን የድምጽ ማዕቀፍ ይጫኑ
https://p.dw.com/p/4Ocm3?maca=amh-RED-Telegram-dwcom

የዓለም ዜና፤መጋቢት 4 ቀን 2015 ዓ.ም. | DW | 13.03.2023
በኢትዮጵያ ውስጥ "በመንግሥትም ሆነ በተቃውሞ ጎራ የተሰለፉ የልዩነት ፖለቲካ አራማጅ" ያላቸው ኃይሎች በሚያሳድሩት መጓተት እና ፍጭት በሀገሪቱ "የሥጋት ድባብና አጠቃላይ የማኅበረ - ፖለቲካ ምስቅልቅል የመጨረሻው ደረጃ ላይ ደርሷል" የሚል ሥጋቱን የኢትዮጵያ ዜጎች ለማሕበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) ገለጸ።
"በየቀኑ በሚፈጠሩ ውጥንቅጦች እና የሚፈለፈሉ አጀንዳዎች" ሕዝብ የሥነ ልቦና ጫና ውስጥ እንደገባ ፓርቲው ትላንት ሰኞ ባወጣው መግለጫ አትቷል።
ኢዜማ በመግለጫው በስም የጠቀሰው ፓርቲ ወይም ግለሰብ ባይኖርም "የብሔር ፖለቲከኞች"ያላቸው ኃይሎች "አጠቃላይ ሀገራዊ ቀውስ እንዲፈጠር ያለ እረፍት እየሰሩ ይገኛሉ" ሲል ወንጅሏል።
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ መንግሥት "በጉያው አቅፎ" እዚህ አድርሷቸዋል የሚላቸውን "በሃሰት ትርክት የተሞሉ፣ በጥላቻ የሰከሩ ለተቀረው ኢትዮጵያዊ ቀርቶ እንወክለዋለን ለሚሉት ህዝብ እንኳን ግልጽና የጠራ መዳረሻ ያላስቀመጡ አክራሪ ኃይሎችን በግልጽ ሊፋለማቸውና፣ ከመዋቅሩ ሊመነጥራቸው" እንደሚገባ ኢዜማ ጥሪ አስተላልፏል።
"እኩልነት ላይ የቆመ የፖለቲካ ሥርዓት መገንባት" ኢትዮጵያ ከገባችበት ችግር መውጫ መፍትሔ ነው ያለው ኢዜማ ሀገር እንዳትፈርስ በሚያግባቡ መሰረታዊ የሀገር ህልውና ጉዳዮች ላይ አብሮ ለመስራት ለሁሉም አካል ጥሪ አስተላልፏል። 👉🏾 @dwamharicbot

በመቀመጫውን በፓሪስ ያደረገ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት ጅቡቲ አንድ ተመራማሪውን አስራ ወደ ኢትዮጵያ እንደላከችበት ከሰሰ። ፌዴሬሽን ለሰብዓዊ መብቶች የተባለው ድርጅት ምክትል ፕሬዝደንት ወደ ጅቡቲ ተመልሰው እንዳይገቡ መከልከላቸውን ተቋሙ አስታውቋል። አሌኪስ ዴስዋኢፍ የተባሉት የድርጅቱ ምክትል ፕሬዝደንት በጅቡቲ ሁለት ቀን ካሳለፉ በኋላ ትላንት ሰኞ ከሆቴላቸው በበጸጥታ ኃይሎች ተወስደው ወደ ኢትዮጵያ ለመብረር በተዘጋጀ አውሮፕላን እንደተጫኑ ፌዴሬሽን ለሰብዓዊ መብቶች ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
በመግለጫው መሠረት የምክትል ፕሬዝደንቱን ማስታወሻ ደብተሮች፣ የእጅ ስልክ እና ሲም ካርድ የነጠቁት ፖሊሶች ለእርምጃው የሰጡት ማብራሪያ የለም። ለተመሳሳይ ሥራ ወደ ጅቡቲ ያቀኑ የድርጅቱ ሌላ ባልደረባ ባለፈው እሁድ ወደ አገሪቱ መግባት ተከልክለው ወደ ቱርክ መላካቸውን የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ አስታውቋል። ደስዋኢፍ ግን በጅቡቲ በነበራቸው የሁለት ቀናት ቆይታ ከሰብዓዊ መብቶች ድርጅቶች ተወካዮች፣ የሰራተኛ ማኅበራት፣ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች፣ ከውጭ አገሮች ዲፕሎማቶች እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሠራተኞች ተገናኝተው ነበር። 👉🏾 @dwamharicbot

በደቡባዊ ሶማልያ ዛሬ ማክሰኞ በተፈጸመ ጥቃት አምስት ሰዎች ሲገደሉ የአካባቢውን አስተዳዳሪ ጨምሮ አስራ አንድ ሰዎች ቆሰሉ።
ከሞቃዲሾ 450 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ባርዴራ ፈንጂ የተጫነ ተሽከርካሪ የመንግሥት ባለሥልጣናት ወደሚገኙበት የእንግዳ ማረፊያ ጥሶ በመግባት መንጎዱን ሑሴን አዳን የተባሉ የፖሊስ መኮንን ለአሶሼትድ ፕሬስ ተናግረዋል።
የፖሊስ መኮንኑ "ፍንዳታው የሕንፃውን አብዛኞቹን ክፍሎች ያወደመ ሲሆን አምስት የጸጥታ አስከባሪዎች ሕይወታቸው አልፏል" ሲሉ አስረድተዋል። የግዛቲቱ አስተዳዳሪ አሕመድ ቡሌ ጋረድን ጨምሮ አስራ አንድ ሰዎች ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸዋል። ሞሐሙድ ሳኔይ የተባሉ የአይን እማኝ በጥቃቱ እንደደረሰው ያለ ትልቅ ፍንዳታ ሰምተው እንደማያውቁ ተናግረዋል። ሞሐሙድ ሳኔይ እንዳሉት ፍንዳታው "አካባቢውን እንደ ርዕደ መሬት አንቀጥቅጦታል።"
ላለፉት አስራ አምስት ዓመታት በሁለት እግሩ መቆም ከተሳነው የሶማሊያ ማዕከላዊ መንግሥት ውጊያ የገጠመው አል-ሸባብ እንዲህ አይነት ጥቃቶች ሲፈጽም ቆይቷል። በአሜሪካ አየር ኃይል እና በአፍሪቃ ኅብረት ሰላም አስከባሪዎች የሚታገዘው የሶማሊያ ጦር ባለፉት ወራት በአክራሪው አል-ሸባብ ላይ በከፈተው ዘመቻ ሰፋፊ ግዛቶች መቆጣጠሩ የሚዘነጋ አይደለም። 👉🏾 @dwamharicbot

የሩሲያ የታችኛው ምክር ቤት አባላት ቅጥረኛ ወታደሮችን የሚተቹ ግለሰቦችን እስከ 15 ዓመታት በሚደርስ እስር የሚቀጣ ሕግ ዛሬ ማክሰኞ አጸደቁ። ሕጉ እንደ ቫግነር ያሉ እና ከሩሲያ ጦር ጎን ለጎን በዩክሬን ጦርነት ቅጥረኛ ወታደሮች ያሰማሩ "በጎ ፈቃደኛ ቡድኖች" ላይ ትችት የሚሰነዝሩትን የሚቀጣ ነው።
"ከዛሬ ጀምሮ የአገራችንን እና የዜጎቻችንን ደህንነት ለመጠበቅ ሕይወታቸውን አደጋ ላይ የሚጥሉ ሰዎች ከትንኮሳ እና ከውሸት ይጠበቃሉ" ሲሉ የሩሲያ የታችኛው ምክር ቤት ሊቀ-መንበር ቭያቼስላቭ ቮሎዲን ተናግረዋል። ሕጉ ሥራ ላይ ለመዋል መጀመሪያ በሩሲያ የላይኛው ምክር ቤት ለጥቆም በፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን መጽደቅ ይኖርበታል።
ሕግ አውጪዎቹ ሩሲያ ዩክሬንን ከወረረች በኋላ ተቺዎችን ለመቅጣት የወጡ ሕግጋትንም የበለጠ ጠበቅ አድርገዋል። የሩሲያ ወታደሮች እና ከመደበኛው ጦር ጎን ለጎን የሚዋጉ "በጎ ፈቃደኞችን" በሚያጣጥሉ ላይ ይፈረድ የነበረው የአምስት ዓመታት እስር ወደ ሰባት ከፍ ተደርጓል። ስለ ሩሲያ ወታደሮች "የሐሰት መረጃ ማሰራጨት" በአንጻሩ በ15 ዓመታት እስር ያስቀጣል። በሩሲያ በቅጥረኝነት መሥራት ወንጀል ቢሆንም በታችኛውም ምክር ቤት የቀረበው ሕግ ግን ጸድቋል። 👉🏾 @dwamharicbot

የበርሊን ፖሊስ የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ከነገ ረቡዕ እስከ አርብ በከተማዋ ከሚጎበኟቸው ቦታዎች ተያያዥነት ያላቸውን አካባቢዎችን በስፋትእንደሚዘጋ አስታወቀ። የአገራቸውን የፍትኅ ሥርዓት ለመቀየር ጥረት የጀመሩት እና በእስራኤል ብርቱ ተቃውሞ የገጠማቸው ኔታንያሁ የጀርመን ዋና ከተማን ሲጎበኙ ጥብቅ የጸጥታ ጥበቃ ይደረጋል።
ኔታንያሁ በበርሊን ከመራሔ-መንግሥት ኦላፍ ሾልስ እና ከፕሬዝደንት ፍራንክ ቫልተር ሽታይንማየር የሚገናኙባቸው ቦታዎች ከፍተኛ ጥበቃ ከሚደረግላቸው መካከል ናቸው።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚጎበኙት በበርሊን የሚገኝ የሆሎኮስት መታሰቢያ አካባቢ ሙሉ በሙሉ የሚዘጋ ይሆናል። በሚዘጉት አካባቢዎች ተቃውሞ ማድረግ የሚፈቀደውም እጅግ በተገደበ መጠን እንደሚሆን የጀርመን ዜና አገልግሎት ዘግቧል።
የጀርመን ፕሬዝደንት ፍራንክ ቫልተር ሽታይንማየር በኔታንያሁ ማሻሻያ ሳቢያ በእስራኤል የተቀሰቀሰው ተቃውሞ እንደሚያሳስባቸው ከገለጹ የዓለም መሪዎች መካከል ናቸው። የኔታንያሁ ተቺዎች ማሻሻያው በሕግ አውጪው እና በሕግ ተርጓሚው መካከል ላለው የሥልጣን ክፍፍል ሥጋት አድርገው ይመለከቱታል።
የአገሪቱን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሥልጣን ነጥቆ "ክነሰት" ተብሎ ለሚጠራው ምክር ቤት የሚሰጠው የኔታንያሁ እና ወግ አጥባቂዎቹ ማሻሻያ "የእስራኤልን ዴሞክራሲ ያበቃል" የሚል ሥጋት ፈጥሯል። ኔታንያሁ ከጽህፈት ቤታቸው ወደ አውሮፕላን ማረፊያ የሚወስዱ መንገዶች በተቃዋሚዎች ተዘግተው ከተሽከርካሪ ይልቅ በሔሊኮፕተር ለመጓዝ ተገደው ነበር።👉🏾 @dwamharicbot

ፕሬዝደንት ሐሰን ሼይክ መሐሙድ "የሶማልያ እና የኢትዮጵያን የሁለትዮሽ ግንኙነት እና ስልታዊ አጋርነት ለማጠናከር ቁርጠኛ" መሆናቸውን አስታወቁ። ፕሬዝደንቱ ይኸን ቁርጠኝነታቸውን የገለጹት በኢትዮጵያ የሶማሊያ አምባሳደር ሙክታር ሞሐመድ ዋሬ የሹመት ደብዳቤ በተቀበሉበት ወቅት እንደሆነ የሶማልያ መንግሥት የሚቆጣጠረው ሱና የዜና ወኪል ዘግቧል።
ፕሬዝደንት ሐሰን ሼይክ መሐሙድ ለሥራ ጉብኝት ከተጓዙበት አስመራ ወደ ሞቃዲሾ የተመለሱት በዛሬው ዕለት ነው። ፕሬዝደንቱ በአስመራ ከኤርትራው አቻቸው ኢሳያስ አፈወርቂ ተገናኝተው "የጋራ ጠቀሜታ ባላቸው የቀጠናው ጉዳዮች" ላይ መወያየታቸውን የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገብረመስቀል በተረጋገጠ የትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ገልጸዋል። 👉🏾 @dwamharicbot