DW Amharic
56.4K subscribers
4.14K photos
984 videos
69 files
15.7K links
ይህ የዶይቼ ቬለ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው። ትኩስ ዜና፣ በአበይት ፖለቲካዊ፣ ኤኮኖሚያዊ፤ ማኅበራዊ እና ባሕላዊ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩር ትንታኔ ያቀርባል።
Download Telegram
የባሕርዳር ስታዲዮም ግንባታ
የባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲዮምን ለማጠናቀቅ ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ 2ኛው ዙር ግንባታ ዛሬ ከፍተኛ የክልልና የፌደራል መንግስት ባለስልጣናት በተገኙበት ተጀምሯል፡፡የአማራ ክልል ስፖርትና ወጣቶች ቢሮ ኃላፊ አቶ ርዚቅ ሙሳ በስርዓቱ ላይ እንደተናገሩት ስታዲዮሙ ግንባታዉ ሳይጠናቀቅም በርካታ ጨዋታዎችን አስተናግዷል።
ስታዲዮሙ የካፍ ደረጃ ማሟላት ባለማሟላቱ ታላላቅ ጨዋታዎችን እንዳያስተናግድ በመታገዱ ብሔራዊ ጨዋታዎችን ማስተናገድ አልቻለም ብለዋል፡፡ በመሆኑም የክልሉ መንግስት 700 ሚሊዮን፣ ከህብረተሰቡ 74 ሚሊዮን ብር፣ ከሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ 300 ሚሊዮን ብር በተደረገ ድጋፍ ቀሪ ስራዎችን ለማከናወን ዛሬ ስራው መጀመሩን ኃላፊው ተናግረዋል፡፡
ኮንትራክቱን የወሰደው የሜድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ሥራ አስፈፃሚ አቶ ጀማል አህመድ በበኩላቸው ተቋማቸው ለፕሮጀክቱ ማስፈፀሚያ 300 ሚሊዮን ብር መለገሱን ጠቁመው ጠቅላላ ስራውን በአንድ ዓመት ውስጥ ለማጠናቀቅ ቃል ገብተዋል፡፡
የኢፌድሪ ባህልና ስፐርት ሚኒስትር አቶ ቀጀላ መርዳሳ ስታዲዮሙ ተጠናቅቆ በተሟላ ሁኔታ አገልግሎት እንዲሰጥ መስሪያ ቤታቸው ጠንክሮ እንደሚሰራ በስነስርዓቱ ላይ ገልጠዋል፡፡
የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ይልቃል ከፋለም የክልሉ መንግስት ሁሉንም የተጀመሩ ፕሮጀክቶች ዳር እንዲደርሱ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን አመልክተው፣ ለስታዲዮሙ መጠናቀቅ ግን ልዩ ክትትል እንደሚደረግለት አመልክተዋል፡፡
በዛሬው የሁለተኛው ግንባታ ማስጀመሪያ ስነስርዓት ላይ የኢፌድሪ ባህልና ስፕርት ሚኒስቴር ከፍተኛ ባለስልጣናት፣ የኢፌድሪ መከላከያ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር አብርሐም በላይ፣ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ጀኔራል ዳይሬክተር ተመስገን ጥሩነህና ሌሎች የክልልና ፌደራል ከፍተኛ
ዩናይትድ ስቴትስ ለየሠላም ስምምነቱ ገቢራዊነት ትጥራለች-ቃል አቀባይ

የኢትዮጵያ ፌደራዊ መንግስትና ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ባለፈዉ ሳምንት የተፈራረሙትን ግጭት የማቆም ስምምነት ገቢር ለማድረግ የሚደረገዉን ንግግርና ጥረት ዩናይትድ ስቴትስ እንደምትደግፍ የሐገሪቱ ዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር አስታወቀ።የአሜሪካ ዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ ኔድ ፕራይስ ትናንት ለጋዜጠኞች እንደነገሩት ፕሪቶሪያ-ደቡብ አፍሪቃ ላይ የተፈረመዉን ስምምነት ገቢር ለማድረግ የኢትዮጵያ መንግስትና የህወሓት ባለስልጣናት ናይሮቢ ኬንያ ዉስጥ የሚደርጉትን ዉይይት የአሜሪካዉ ልዩ መልዕክተኛ ማይክ ሐማር በቅርብ እየተከታተሉ ነዉ።ይሁንና የልዩ መልዕክተኛዉ ሚና ከታዛቢነት የዘለለ እንዳልሆነ ቃል አቀባዩ አስታዉቀዉ፣ ዋና አደራዳሪዉ የአፍሪቃ ሕብረት መሆኑን ገልፀዋል።ቃል አቀባይ ፕራይስ አክለዉ እንዳሉት ሁለቱ ወገኖች ፕሪቶሪያ ላይ የተፈራረሙት ስምምነት በራሱ «በጣም ጠቃሚ» ነዉ።የሁለቱ ወገኖች ባለስልጣናት በአፍሪቃ ሕብረት መሪነት ናይሮቢ-ኬንያ ዉስጥ የሚያደርጉት ዉይይት ግጭት የማስወገዱን ስምምነት ገቢራዊነት፣የጋራ አጣሪና ተቆጣጣሪ ስልትን መቀየስና የወታደራዊ-ለ-ወታደራዊ (የጦር አዛዦች) ዉይይትን እንደሚያካትት ቃል አቀባዩ አስታዉቀዋል።ዩናይትድ ስቴትስ ዉይይቱን መታዘቧንና ሒደቱን የሚመራዉ የአፍሪቃ ሕብረት «አጋር መሆኗን ትቀጥላለች» እንደ ቃል አባይ ኔድ ፕራይስ መግለጫ።የጦር አዛዦቹን ንግግር ጨምሮ ስምምነቱ ከታለመለት ግብ እንዲደርስ የማድረጉ «ኃላፊነት ግን የሁለቱ ወገኖች ነዉ» አሉ ቃል አቀባዩ። ናይሮቢ ኬንያ ዉስጥ የተያዘዉ የሁለቱ ወገኖች የጦር አዛዦች ንግግር እስካሁን ስለደረሰበት ነጥብ በግልፅ የተነገረ ነገር የለም። ይሁንና ንግግሩ ዛሬ ወይም ነገ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል።
የወለጋ ዉጊያ ቀጥሏል
የኢትዮጵያ መንግስት ጦርና የኦሮሞ ነፃ አዉጪ ጦር ወለጋ ዉስጥ በገጠሙት ዉጊያ በርካታ ሰዎች መገደላቸዉን የአካባቢዉ ነዋሪዎች አስታወቁ።የአሜሪካዉ ዜና አገልግሎት አሶስየትድ ፕሬስ (AP) የዓይን እማኞችን ጠቅሶ እንደዘገበዉ ምስክሮቹ «አነስተኛ አዉሮፕላን» በማለት በገለፁት የአየር ጥቃት በታገዘዉ ዉጊያ በአስር የሚቆጠሩ ሰላማዊ ሰዎች ተገድለዋል።መንግስት ኦነግ-ሸኔ በሚል ስም በአሸባሪነት የፈረጀዉ አማፂ ቡድን የምስራቅ ወለጋ ዞን ዋና ከተማ ነቀምትን ባለፈዉ ዕሁድ ጧት ይዟት ነበር።ይሁንና የመንግስት ጦር የዚያኑ ዕለት ከተማይቱን መልሶ ተቆጣጥሯታል።የኦሮሞ ነፃ አዉጪ ጦር ቃል አቀባይ ኦዳ ቱርቢ በበኩላቸዉ ጦራቸዉ ነቀምት ከተማ ዉስጥ ታስረዉ የነበሩ 120 የፖለቲካ እስረኞችን አስለቅቋል ብለዋል።ወለጋ ዉስጥ በተለይም ምዕራብ ወለጋ ዉስጥ በቀጠለዉ ዉጊያ ምክንያት መንገዶች በመዘጋታቸዉ ወደ በኒ ሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ ከተማ አሶሳ የፍጆታ ሸቀጥ መግባት ማቆሙን የከተማዋ ነዋሪዎች አስታዉቀዋል።ከተማይቱ ዉስጥ የሚገኘዉ ሸቀጥ ዋጋም በጅጉ መጨመሩን ነዋሪዎቹ ገልፀዋል።የቤኒሻንል ጉሙዝ ክልል የሰላም ግንባታና የጸጥታ ቢሮ ምክትል ኃላፊ ሙሳ ሀሙድም አሶሳ ዉስጥ የፍጆታ ዕቃዎች እጥረትና የዋጋ ንረት መኖሩን አምነዋል።አቶ ሙሳ ለአሶሳዉ ወኪላችን ለነጋሳ ደሳለኝ እንደነገሩት የፍጆታ ዕቃዎችና የሰብአዊ ርዳታዎች በሌላ መንገድ ወደ ክልሉ እንዲገቡ እየተደረገ ነው፡፡
የዕዉቁ ድምፃዊ የዓሊ ቢራ የቀብር ሥርዓት በድሬዳዋ ከተማ
ቪዲዮ፣ መሳይ ተክሉ
የኢዮጵያ ኃይላት ስምምነቱን እንዲያከብሩ ኬንያና ደቡብ አፍሪቃ ጠየቁ
የኢትዮጵያ ፈደራዊ መንግስትና ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ባለፈዉ ሳምንት የተፈራረሙትን ስምምነት ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ እንዲያደርጉ የደቡብ አፍሪቃና የኬንያ መሪዎች ጠየቁ።ናይሮቢን የሚገበኙት የደቡብ አፍሪቃዉ ፕሬዝደንት ሲሪያል ራማፎዛና የኬንያዉ አስተናጋጃቸዉ ዊሊያም ሩቶ ዛሬ በጋራ እንዳስታወቁት የኢትዮጵያ ተፋላሚ ኃይላት ግጭት ለማቆም መስማማታቸዉን ያደንቃሉ።ይሁንና ሁለቱ መሪዎች እንዳሉት ኢትዮጵያ ዉስጥ ዘላቂ ሰላም ለማስፋን ተፈራራሚ ኃይላት ስምምነታቸዉን ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ማድረግ አለባቸዉ።የኢትዮጵያ መንግስትና የህወሓት ተወካዮች ሁለት ዓመት ያስቆጠረዉን ጦርነት በሰላም ለመፍታት የተስማሙት ደቡብ አፍሪቃ ዉስጥ ለዘጠኝ ቀናት ከተደራደሩ በኋላ ነዉ።የሁለቱ ወገኖች የጦር አዛዦች ደግሞ ስምምነቱ ገቢራዊ ስለሚሆንበት፣ በተለይም የህወሓት ተዋጊዎች ትጥቅ ስለሚፈቱበት ስልት ካለፈዉ ሰኞ ጀምሮ ናይሮቢ-ኬንያ ዉስጥ እየተነጋገሩ ነዉ።የንግግሩ ዉጤት በይፋ አልተነገረም።የደቡብ አፍሪቃና የኬንያ ፕሬዝደንቶች አንድናቆትና ጥያቄ የተሰማዉም የሁለቱ ወገኖች ንግግር ዉጤት በሚጠበቅበት ወቅት ነዉ።የደቡብ አፍሪቃ ፕሬዝደንት በኬንያ ለመጀመሪያ ጊዜ ያደረጉት ጉብኝት ዋና ዓላማ በሁለቱ ሐገራት የንግድ፣ የዜጎች ዝዉዉርና የቪዛ ጉዳይ ለመወያየት ነዉ።ሁለቱ መሪዎች የኬንያ ዜጎች ደቡብ አፍሪቃን ለዘጠና ቀናት ያሕል ያለ መግቢያ ቪዛ እንዲጎበኙ ተስማምተዋል።የደቡብ አፍሪቃ ዜጎች ከዚሕ ቀደምም ያለ ቪዛ ኬንያን መጎብኘት ይችሉ ነበር።
የባሕርዳር ስታዲዮም የግንባታ ማስጀመሪያ ሥርዓት

የባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲዮም ሁለተኛ የግንባታ ምዕራፍ ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ ዛሬ ተጀምሯል፡፡ የአማራ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ርዚቅ ሙሳ ዛሬ ግንባታው ሲጀመር እንዳሉት የአማራ ክልላዊ መንግስተ 700 ሚሊዮን ብር የመደበ ሲሆን ከህብረተሰቡ 74 ሚሊዮን ብር መገኘቱን ተናግረዋል፡፡ የሜድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ሥራ አስፈፃሚ አቶ ጀማል አህመድ በበኩላቸው ተቋማቸው ለስታዲዮሙ ግንባታ 300 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አድርጓል፡፡
ግንባታው በአንድ ኣመት ውስት እንደሚጠናቀቅ የግንባታው ተቋራጭ ሜድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ስራ አስፈፃሚ አቶ ጀማል ተናግረዋል፡፡
የኢፌድሪ ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ቀጀላ መርዳሳ ሚኒስቴር መስሪ ቤታቸው ስታዲዮሙ ፍፃሜ እንዲገኝ አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል፡፡
ቪዲዮ፣ ዓለምነው መኮንን (ከባህር ዳር)
የጥቅምት 30 ቀን 2015 ዓም የዶቼቬለ ዐርዕስተ ዜና

በኦሮምያ ክልል የምስራቅ ወለጋ ዞን ዋና ከተማ ነቀምቴ በኩል ወደ ጊምቢ መንዲና አሶሶ ከተሞች በሚወስዱት መንገዶች የመጓጓዣ አገልግሎት በመቋረጡ ለተለያዩ ችግሮች መዳረጋቸውን ነዋሪዎች ለዶቼቬለ ተናገሩ። ነጆና መንዲ ከተሞች ባንክን ጨምሮ ሌሎች ማኅበራዊ አገልግሎት ሰጭ ተቋማት በመዘጋታቸው ወደ ኦሶሳና ካማሺ ከተማ የፍጆታ እቃዎች እየገቡ እንዳልሆነ ተናግረዋል።

ኬንያውያን ከመጪው ጎርጎሮሳዊው 2023 ዓም አንስቶ፣ ያለቪዛ ደቡብ አፍሪቃ መግባት እንደሚችሉ ተዘገበ። በአሶስየትድ ፕሬስ ዘገባ መሠረት በሁለቱ ሀገራት ስምምነት ኬንያውያን በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ያለ ቪዛ ደቡብ አፍሪቃ ውስጥ ለ90 ቀናት መቆየት እንዲችሉ ተፈቅዷል።

በአሜሪካን ፕሬዝዳንት የስልጣን ዘመን እኩሌታ ላይ በሚካሄደው ምርጫ ዘንድሮ ዴሞክራቶች በአንዳንድ አካባቢዎች ባልተጠበቀ ሁኔታ የበላይነት ቢያገኙም ሪፐብሊካኖች ግን የሀገሪቱን የሕግ መምሪያ ምክር ቤት ሳይቆጣጠሩ አይቀርም የሚል ትንበያ ወጥቷል። ትናንት በተካሄደው ምርጫ ለህግ መወሰኛ ምክር ቤት የተሰጠው ድምጽ ቆጠራ ደግሞ እስካሁን የሁለቱም ውጤት ተቀራራቢ ነው።

ሙሉውን ዜና ለማዳመጥ የድምጽ ማዕቀፉን ይጫኑhttps://p.dw.com/p/4JHrn?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
👉🏾 @dwamharicbot
አርዕስተ ዜና

-የኢትዮጵያ መንግስትና የህወሓት ባለስልጣናት ናይሮቢ-ኬንያ ዉስጥ የሚያደርጉት ንግግር ዛሬም መቀጠሉ ተነገረ።የንግግሩን ሒደት የሚከታተሉ ባለስልጣናት እንዳሉት ትናንት ያበቃል ተብሎ የነበረዉ ንግግር ባንድ ቀን ተራዝሟል።የግግሩ ዉጤት ግን በሚስጥር እንደተያዘ ነዉ።

-የኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ መንግስት ጦርና M23 የተባለዉ አማፂ ቡድን ምስራቃዊ ኮንጎ ዉስጥ የገጠሙት ዉጊያ እንደቀጠለ ነዉ።ኬንያ በበኩሏ የኮንጎ ጦርን የሚያግዝ ሠራዊት ለማዝመት ወሰነች።

-ኢራን ፀረ-ሚሳዬል ሚሳዬል የማይበግረዉ ሐይፐርሶኒክ ሚሳዬል መስራትዋን አንድ የሐገሪቱ የጦር ጄኔራል አስታወቁ።ሚሳዬሉ የኑክሌር አረር መሸከም የሚችል፣ከድምፅ ፍጥነት አምስት እጥፍ የሚምዘገዘግ ነዉ።የዓለም የአቶሚክ ተቆጣጣሪ ድርጅት መግለጫዉን «አስጊ» ብሎታል።https://p.dw.com/p/4JLnQ?maca=amh-RED-Telegram-dwcom@dwamharicbot