DW Amharic
56.4K subscribers
4.14K photos
984 videos
69 files
15.7K links
ይህ የዶይቼ ቬለ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው። ትኩስ ዜና፣ በአበይት ፖለቲካዊ፣ ኤኮኖሚያዊ፤ ማኅበራዊ እና ባሕላዊ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩር ትንታኔ ያቀርባል።
Download Telegram
የኦሬገኑ ድል በኮሎምቢያ ካሌም ይደገም ይኾን? እድሜያቸው ከ20 ዓመት በታች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ምሽቱን ይፎካከራሉ። የእንግሊዝ ብሔራዊ የሴቶች የእግር ኳስ ቡድን የጀርመን አቻውን ባለቀ ሰአት ድል አድርጎ ታሪክ አስመዝግቧል። ሊቨርፑል በኮሙኒቲ ሺልድ የፍጻሜ ግጥሚያ ማንቸስተር ሲቲን ቅዳሜ ድል አድርጎ የፕሬሚየር ሊግ ቁጭቱን ተወጥቶበታል። https://p.dw.com/p/4Eym3?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
DW Amharic
ከጉራጌ ክልል በስተቀር በክልሉ የሚገኙ 10 የዞን እና 6 የልዩ ወረዳ ምክር ቤቶች ባካሄዷቸው ጉባኤዎች አሁን ያለውን የደቡብ ክልል በሁለት ክልላዊ መስተዳድር ለማዋቀር ያስችላል የተባለውን ውሳኔ አሳልፈዋል፡፡ የሀዋሳው ወኪላችን ሸዋንግዛው ወጋየሁ በምክር ቤቶቹ ውሳኔ ዙሪያ የዞኖቹን ነዋሪዎችና የማህበረሰብ አንቂዎችን አስተያየት ያሰባሰበበትን ዘገባ ልኮልናል፡፡ https://p.dw.com/p/4Ey5m?maca=amh…
ሁለቱ የኦሮሞ ተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች ከአሜሪካ የምስራቅ አፍሪካ ልዩ መልእክተኛ ማይክ ሐመር ጋር ስላደረጉት ውይይት ለዶይቼ ቬለ የተናገሩት የኦፌኮ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና፤ የብሔራዊ ውይይት ጅማሮ፣ ስለ ሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት የተፋላሚዎች ይዞታ እና አሁናዊ የኦሮሚያ ክልል ሁኔታ በውይይቱ ከተነሱ አበይት ጉዳዮች ነበሩ ብለዋል፡፡ https://p.dw.com/p/4EyYv?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
በትግራይ ክልል የመብራት፣ የቴሌኮም አገልግሎት፣ የባንክ እና ሌሎች መሠረታዊ አገልግሎቶች በፍጥነት ወደነበረበት እንዲመለሱ ሲሉ ዩናይትስ ስቴትስ እና የአውሮፓ ህብረት ከፍተኛ ልዑካን በጋራ ባወጡት መግለጫ አስታወቁ ። ዛሬ መቀሌ የነበሩት የአውሮጳ ህብረት የአፍሪቃ ቀንድ ልዩ ተወካይ አኔተ ቬበር እና አዲሱ የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ማይክ ሀመር ባወጡት የጋራ መግለጫ እንደ ትግራይ ክልል ሁሉ በግጭቱ የተጎዱ አጎራባች የአፋር እና አማራ ክልሎች ሰብዓዊ አገልግሎቶችን ማግኘት እንዳለባቸው አሳስበዋል። ከዚህም ሌላ « በግጭቱ የተሳተፉ ሁሉም አካላት ከጥላቻ ንግግር እና ተንኳሽ ንግግሮች እንዲቆጠቡ» በጋራ ባወጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ጠይቀዋል። በመግለጫው እንደተጠቀሰው ቬበርና ሃመር ወደ ኢትዮጵያ የተጓዙት በኢትዮጵያ ፌደራል መንግስት እና ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) መካከል በአፍሪካ ህብረት አስተባባሪነት ድርድር እንዲጀመር ለማበረታታት ነው።
በአማራ ክልል ምሥራቅ ጎጃም ዞን ደጀን ወረዳ ሰሞኑን በተከሰተው የድንጋይ ናዳ የአንድ ሰው ህይወት ከመጥፋቱ በተጨማሪ ሁለት ህፃናት መቁሰላቸውን የወረዳው አስተዳደር አስታወቀ፡፡አደጋው የደረሰው ሐምሌ 24 ቀን 2014 ዓ.ም ከምሽቱ 3 ሰዓት በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት እንደሆነ አስተዳደሩ ገልጿል።
የደጀን ወረዳ አስተዳደር ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሐይማኖት ካሳ ለዶይቼ ቬሌ በስልክ እንደተናገሩት በደረሰው የታላላቅ አለቶች ናዳ በወረዳው ቦረቦር ሸንቻ ቀበሌ፣ ልዩ ስሙ “ጎበዝ አንባ” 3 ቤቶች ከነሙሉ ንብረታቸው ሲወድሙ 2 ቤቶች ደግሞ በከፊል ተጎድተዋል። በአደጋው የአንድ አባወራ ህይወት ሲያልፍ ሁለት ህፃናት ደግሞ ቆስለዋል” ብለዋል፡፡
“በሐይለኛ ዝናብ አጠቃላይ ቋጥኙ መጥቶ ወደታች በመውረዱ በ3 ቤቶች ጉዳትና የአንድ ሰው ህይወት ጥፋት አድርሷል፣ የቆሰሉ ሰዎች ለጊዜው ሁለት ህፃናት ቀላል ቁስለት ገጥሟቸዋል፣ ያው የሟቹ ልጆች”
ወረዳ አስተዳደሩ ተጨማሪ ናዳዎች ይደርሳሉ በሚል ሥጋት ነዋሪዎችን ወደ ሌላ ቦታ እያዛወረ አንደሆነ አመልክቷል። አደጋው በእንስሳት፣ በአዝመራና በሌሎች ቋሚ ተክሎች ላይም ጉዳት ማድረሱን አቶ ሐይማኖት ተናግረዋል፡፡ አጠቃላይ የጉዳት መጠኑ ግምት እየተጠና መኾኑን የጽሕፈት ቤት ኃላፊው አመላክተዋል።
በአካባቢው ተመሳሳይ ናዳዎች ከዚህ ቀደምም እንደነበሩ ለባህር ዳሩ ወኪል አለምነው መኮንን የገለፁት አቶ ሐይማኖት እንደ አሁኑ የከፋ ባይሆንም ዋና ዋና ጎዳናዎች በናዳ ይዘጉ እንደነበር አስረድተዋል።
የኢትዮጵያ ሚቲዮሮሎጂ ኢንስቲትዩት በያዝነው ወር በአማራ ክልል ጎርፍ የሚያስከትል ከባድ ዝናብ አልፎ አልፎ እንደሚከሰት አስጠንቅቋል፡፡
አዲሱ የሶማሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር ፣የቀድሞ የአልሸባብ ቡድን ተባባሪ መስራች እና ቃል አቀባይ ሙክታር ሮቦውን በአዲስ ካቢኔያቸው ውስጥ ሾሙ። የጠቅላይ ሚኒስትር ሀምዛ አብዲ ባሬ ርምጃ ከአአሸባብ ጋር የሚደረገውን ትግል ለማጠናከር ይረዳል ወይም የጎሳ ግጭትን ሊያስፋፋ ይችላል ተብሎ ይፈራል። በአንድ ወቅት አሜሪካን ሮቦውን አሳልፎ ለሰጣት 5 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር እሰጣለሁ ብላ ነበር። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቴሌቪዥን እንደተናገሩትበጎርጎሮሳዊው 2013 ከአሸባብ የተገነጠሉት ሮቦው የሃይማኖት ሚኒስትር ሆነው ተሾመዋል። የሚኒስትሮቹ ሹመት ግን በሀገሪቱ ምክር ቤት መጽደቅ ይኖርበታል። ሙክታር ሮቦው በቀድሞው የሶማሊያ መንግስት በሶማሊያ ደቡብ ምዕራብ ክልል ዘመቻ ሲያደርጉ ከተነሳ ህዝባዊ ተቃውሞ ጋር በተያያዘ ታህሳስ 2018 ዓም እስር ቤት ገብተው ነበር። በወቅቱ ቢያንስ 11 ሰዎች በፀጥታ ኃይሎች ተገድለዋል።
የሶማሊያውን ሽምቅ ተዋጊ ቡድን አሸባብን በገንዘብ ትደግፋለች የተባለች አንዲት ኔዘርላንዳዊት የሦስት ዓመት እስራት ተበየነባት። ዩናይትድ ስቴትስ አሌክሳንድሪያ የሚገኘው ፍርድ ቤት ሰኞ ዕለት በ38 ዓመቷ ፋርሂያ ሀሰን ላይ የፈረደው ቅጣት አቃቤ ህግ ከጠየቀው በአምስት ዓመት ያነሰ ነበር። ከኔዘርላንድስ ወደ አሜሪካን የተወሰደችው ፋርሂያ ለአሸባብ የቁሳቁስ ድጋፍ ለመስጠት በማሴር ተከሳ በዚህ በጎርጎሮሲያኑ ዓመት መጀመሪያ ላይ ነበር ዩናይትድ ስቴትስ ፍርድ ቤት የቀረበችው ። እንደ አቃቤ ህግ ገለፃ ኔዘርላንዳዊቷ በኦንላይ ተገናኝተው ገንዘብ ሳከባሰቡ 15 ሴቶች አንዷ ናት። ሴቶቹም በየጊዜው አነስተኛ መጠን ያለው ገንዘብ ሶማሊያ እና ኬንያ ያሉ የአሸባብ ታጣቂዎችን ለመደገፍ ገንዘብ ያሰባስቡ ነበር ተብሏል። ፋርሂያ በሦስት ዓመት ውስጥ ወደ 300 የአሜሪካን ዶላር ለግሳለች ያለው አቃቤ ሕግ ክፍያዎቹን ለመከታተል ፈተና እንደነበረው አስታውቋል።
ትውልደ ሶማሊያዊቷ የ6 ልጆች እናት ፋርሂያ ሀሰን በአሥራዎቹ የዕድሜ ክልል በነበረችበት ወቅት ነበር በኔዘርላንድስ ጥገኝነት አግኝታ ትኖር የነበረው። ለመጀመሪያ ጊዜ የተከሰሰችው እጎአ በ2014 ቢሆንም ለሰባት ዓመታት ያህል ለፍርድ ወደ አሜሪካ እንዳትላክ ተሟግታለች። ጠበቃዎቿ ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር ምንም ነገር የሌላት አንዲት ኔዘርላንዳዊት ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ የምትዳኝነት ምክንያት የለም ሲሉ ጠበቃ ቆመውላት ነበር። ፋርሂያ በሰኞው ችሎት የአልሸባብ ደጋፊ እንዳልሆነች ነገር ግን ለሶማሊያ ህዝብ የርዳታ ገንዘብ ትሰጥ እንደነበር ተናግራለች።
ከመጠን ያለፈ የፖሊስ የኃይል ርምጃን ተጠያቂ አለማድረግ እሁድ ለሚካሄደው የኬንያ ምርጫ ስጋት ይሆናል ሲሉ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ተናገሩ። ኬንያ ውስጥ ከዚህ ቀደም በተካሄዱ ምርጫዎች ከምርጫ አስቀድሞ ፣ በምርጫ ወቅት እና በኋላ ብዙ ሁከቶች ተፈጥረዋል ሲል የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ ድርጅት ሂዩማን ራይትስ ዎች ዛሬ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል። ፖሊስ ከዚህ ቀደም ከመጠን ያለፈ የኃይል ርምጃ ተጠቅሟል፣ ከዚህም ጋር በተያያዘ ለፍርድ የቀረቡ ፖሊሶች ጥቂት ናቸው ያለው ሂዩማን ራይትስ ዎች የኬንያ መንግስት ፖሊስን ተጠያቂ አለማድረግ እና የፖለቲካ ጣልቃ ገብነት ማስቆም አለበት ሲል አሳስቧል።
ለእሁዱ ምርጫ በእጩነት የቀረቡት የ 77 ዓመቱ ራይላ ኦዲንጋ እና ተፎካካሪያቸው የ 55 ዓመቱ ዊሊያም ሩቶ ናቸው። የምርጫው ውጤት ተቀራራቢ ይሆናል ተብሎ መገመቱ በራሱ የረብሻውን ስጋት ጨምሯል። እጎአ በ2007 እና 2008 በተካሄደው ምርጫ በተነሳ ሁከት ከአንድ ሺህ በላይ ሰዎች ሞተዋል። ከዚያን ጊዜ በኋላ የተካሄዱ ምርጫዎች በሙሉ ረብሻ ያከሉ ነበሩ። በ 2017 በተካሄደው ምርጫ ሂዩማን ራይትስ ዎች 104 ሰዎች በፖሊሶች እና በታጣቂ ኃይሎች መገደላቸውን አስታውሷል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ በመጨረሻዎቹ የስልጣን ዘመናቸው ከወትሮው በተለየ በስራ ተወጥረዋል ሲል የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ ()ዘግቧል። ኤ ኤፍ ፒ ኬንያታ በምሥራቅ አፍሪካ ሰላም ለማስከበር፣ የሶማሊያን ውጥረት ለማቀዝቀዝ፣ በኮንጎ ቀውስ ጣልቃ በመግባት ሱዳን እና ኢትዮጵያን ለማደራደር በማዘጋጀት ከወትሮው በተለየ በስራ ተጠምደዋል ብሏል።
የአልቃይዳ መሪ አይማን አል ዛዋሂሪ አፍጋኒስታን ውስጥ በአሜሪካ ሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃት መገደሉን ዩናይትድ ስቴትስ አስታወቀች።የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የተሳካ ያሉት ይኽው ጥቃት የዩናይትድ ስቴትስ ጠላቶች ሁሉ ግልጽ መልዕክት ነው ሲሉ ዋሽንግተን ውስጥ ተናግረዋል ። የሀገራቸው የስለላ ድርጅት ሲአይ ኤ የኦሳማ ቢን ላደን ተተኪ የተባለውን አል ዛዋሂሪ በያዝነው በጎርጎሮሳዊው 2022 ካቡል አፍጋኒስታን ውስጥ እንዳለ እንደተደረሰበት እና ከሳምንት በፊት፣ በአል-ዛዋሂሪ ላይ "ርምጃ" እንዲወሰድ መፍቀዳቸውን የተናገሩት ባይደን ጥቃቱ መድረሱን ማረጋገጣቸውንም ገልጸዋል። « ከቤተሰቦቹ መካከል አንዳቸውም አልተጎዱም። በሰላማዊ ሰዎች ላይም ምንም ጉዳት አልደረሰም። አሁን ይህን ዜና ለአሜሪካ ህዝብ የማካፍለው የተልእኮውን ስኬት ከፈጸሙ የፀረ ሽብር ማህበረሰብ እና ከፍተኛ ጥረት ካደረጉ ቁልፍ አጋሮች ካረጋገጥኩ በኋላ ነው።»
ግብፅ ሀገር የተወለደው አል ዛዋሂሪ አይማን እጎአ መስከረም 11 ቀን 2001 ዓ ም ኒውዮርክ ዩናይትድ ስቴትስ ከተፈፀመው የሽብር ጥቃት ጀርባ እጁ እንዳለ ይታመናል። እንደ ዩናይትድ ስቴትስ ገልፃ ቢን ላደንን የተካው የአልቃይዳ መሪ የተገደለው እሁድ ጠዋትነው። 71 ዓመቱ ነበር። ዩናይትድ ስቴትስ በጥብቅ የምትፈልገውን ይህ ሰው ያለበትን ቦታ ለጠቆመ 25 ሚሊዮን ዶላር እንደምትሰጥ አስታውቃ ነበር።
የዩናይትድ ስቴትስ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ ናንሲ ፔሎሲ በእስያ ጉዟቸው ታይዋንን የሚጎበኙ ከሆነ ዩናይትድ ስቴትስ “ዋጋ ትከፍላለች” ስትል ቻይና ዛሬ አስጠንቅቃለች። ፔሎሲ በይፋ ወደ ታይዋን መጓዛቸውን ባያረጋግጡም የዩናይትድ ስቴትስ እና ታይዋን መገናኛ ብዙኃን ይህንን እየዘገቡ ይገኛሉ። የቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ሀው ቹንይንግ ቤጂንግ ላይ ዛሬ በሰጡት መደበኛ ጋዜጣዊ መግለጫ እንደተናገሩት “የቻይናን ሉዓላዊ የፀጥታ ጥቅሞች ለማዳከም አሜሪካ ለምትወስደው ርምጃ ኃላፊነቱን ትወስዳለች» ብለዋል። ፔሎሲ በርግጥ ታይዋንን የሚጎበኙ ከሆነ ከ 25 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የጎነኙ ከፍተኛ የአሜሪካ ባለስልጣን ይሆናሉ። ቻይና ታይዋንን የራሷ አንድ አካል አድርጋ የምታይ ሲሆን ታይዋን ግን ራሷን እንደ ነፃ እና ዲሞክራሲያዊት ሀገር አድርጋ ታያለች። የፔሎሲ የታይዋን ጉብኝትን በተመለከተ ዩናይትድ ስቴትስ ቤጂንግን ለማስቆጣት ሆን ብላ ያደረገችው ነው ስትል ሩሲያ ዛሬ ለቻይና ድጋፏን አሳይታለች። ፔሎሲ ዛሬ ማሌዢያ ኩዋላ ላምፑርን ጎብኝተው ከማሌዢያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኢስማኢል ሳብሪ ጋር እንደተገናኙ የፈረንሳይ ዜና ምንጭ ዘግቧል። የታይዋን የዜና ምንጮች እንደዘገቡት ናንሲ ፔሎሲ ዛሬ ማምሻውን ታይዋን ይገባሉ።
የአውሮፓ ሕብረትና የአሜሪካ ልኡካን በመቐለ

የሕወሓት ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ ለጋዜጠኞች እንዳሉት ውይይቱ መግባባት ላይ የተደረሰበት ነው ብለዋል።https://p.dw.com/p/4F48j?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
የአሜሪካ እና የአውሮፓ ህብረት ልዩ መልእክተኞች የአዲስ አበባ እና መቀለ ቆይታ በፖለቲከኞች እይታ

የትዴፓ ምክትል ሊቀመንበር አቶ መስፍን ደሳለኝ ለሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት የሰላም እልባት ማግኘት “አሁን ተደራዳሪዎች ጋ ባለው ድባብ የመሳካት እድሉ አጠያያቂ ነው” ይላሉ፡፡https://p.dw.com/p/4F56O?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
በደቡብ ክልል ሕዝበ ውሳኔ እንዲካሄድ መጠየቁን

በፖለቲካ ፖርቲዎቹ መግለጫና በዞን ምክር ቤቶቹ ውሳኔ ዙሪያ አስተያየታቸውን የተጠየቁት የሀዋሣ ዩኒቨርስቲ የሕግ መምህርና ተመራማሪ ረዳት ኘሮፎሰር ሽመልስ አሻግሬ አራቱ አገራዊ ፓርቲዎች ያነሱት ጥያቄ ተገቢ ብለውታል ፡፡ https://p.dw.com/p/4F4SM?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
የሲፒጄ መግለጫ እና የባለሙያዎች አስተያየት

ከህዳር 4 ቀን 2020 ጀምሮ ቢያንስ 63 ጋዜጠኞች እና የመገናኛ ብዙኃን ሠራተኞች መታሰራቸውን ሲፒጄ ዘግቧል። ከነዚህም ውስጥ ስምንቱ እስከ ትናንት ድረስ በእሥር ላይ መሆናቸውን ጠቅሷል።https://p.dw.com/p/4F4cx?maca=amh-RED-Telegram-dwcom