ናይሮቢ-የሶማሊያና የኬንያ ዉዝግብ
የኬንያዉ ፕሬዝደንት ኡሑሩ ኬንያታ ናይሮቢ ለሚገኙ የዉጪ ዲፕሎማቶች መግለጫ በሚሰጡበት ስብሰባ ላይ የሶማሊላንድ ባንዲራ ለመታየቱ ኬንያ ይቅርታ ጠየቀች።የኬንያታን መግለጫ ለመከታተል ተገኝተዉ የነበሩት በኬንያ የሶማሊያ አምባሳደር መሐመድ አሕመድ ኑር፣ የሶማሊላንድ «ባላንጣቸዉ» በስፍራዉ መገኘታቸዉን ሲያዩ ስስብሰባዉን ረግጠዉ ወጥተዋል።የሶማሊያ መንግስትም ተቃዉሞዉን ለኬንያ አስታውቋል።የኬንያ ዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር ዛሬ ባሰራጨዉ የይቅርታ መልዕክት ግን የሶማሊላንድ አምባሳደር በስብሰባዉ ላይ ስለመገኘታቸዉ የጠቀሰዉ ነገር የለም።የይቅርታዉ ደብዳቤ፣ በስብሰባዉ ላይ «የሶማሊላንድ ባንዲራ በመታየቱ ለተፈጠረዉ ቅሬታና ሐፍረት ከልብ ይቅርታ እንጠይቃለን» ነዉ የሚለዉ።የሁለቱ ተጎራባች ሐገራት አዲስ አለመግባባት የተከሰተዉ የኬንያ ፕሬዝደንት ኡሁሩ ኬንያታ አዲስ በተመረጡት በሶማሊያዉ ፕሬዝደንት ሐሰን ሼኽ ማሕሙድ በዓለ ሲመት ላይ በቅርቡ ተገኝተዉ ዓመታት ያስቆጠረዉን ዉዝግብ ለማስወገድ ከተስማሙ በኋላ መሆኑ ነዉ።በግዛት ይገባኛልና በሶማሊላንድ ዕዉቅና ሰበብ የሚወዛገቡት ሶማሊያና ኬንያ እንደ ጎርጎሪያኑ አቆጣጠር በ2020 ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸዉን አቋርጠዉ ነበር።ሶማሊያ ከኬንያ ጫት መግዛትዋን አቋርጣም ነበር።ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸዉን ባለፈዉ ነሐሴ ዳግም ሲጀምሩ፤ ሰሞኑን ደግሞ የጫቱን ንግድ ለመቀጠል ተስማምተዋል።

ጋምቤላ-ዉጊያና መረጋጋት
የኢትዮጵያ መንግስትና የአማፂያን ኃይላት ትናንት ሲዋጉባት የዋለችዉ የጋምቤላ ከተማ ዛሬ መረጋጋት እንደሰፈነባት የጋምቤላ ክልል መስተዳድርና የከተማዋ ነዋሪዎች አስታወቁ።የኢትዮጵያ መንግስት ኦነግ ሸኔ የሚለዉና የጋምቤላ ነፃ አዉጪ ግንባር (ጋነግ) ሸማቂዎች ትናንት ማለዳዉን በከተማይቱ ላይ በቅንጅት ጥቃት ከፍተዉ እንደነበር የክልሉ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ በፌስ ቡክ ገፁ ዘግቦ ነበር።ከተማይቱን ለመያዝና ላለማስያዝ በአማፂያኑና በመንግስት ፀጥታ ሐይሎች መካከል ለተከታታይ ሰዓታት ዉጊያ ሲደረግ ነዉ የዋለዉ።አንዳንድ የከተማዋ ነዋሪዎች ለዶይቼ ቬሌ እንደተናገሩት ታጣቂዎቹ ጀጀቤ የተባለውን የከተማውን ክፍል ተቆጣጥረውም ነበር፡፡በዉጊያዉ ከሁሉም ወገን የሰዉ ሕይወት መጥፋቱና ሰዉ መጎዳቱንም ነዋሪዎች አስታዉቀዋል።ይሁንና የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኡሞድ ኡጁሉ በተለይ ለዶይቼ ቬሌ በስልክ በሰጡት አስተያየት በዉጊያዉ ስለደረሰዉ ጉዳት በዝርዝር መግለፅ አልፈለጉም።አቶ ኡሞድ ለባሕርዳሩ ወኪላችን ለዓለምነዉ መኮንን እንደነገሩት ጋምቤላ ዛሬ እየተረጋጋች፣ የመንግስት የፀጥታ ኃይላትም የተደበቁ አማፂያንን ለመያዝ እያሰሱ ነዉ።የከተማይቱ ነዋሪዎች እንደሚሉት ግን ዛሬ የተኩስ ድምፅ ባይሰማም፣ የአገልግሎት መስጪያ ተቋማት እስከ ዛሬ ከቀትር በኋላ ድረስ እንደተዘጉ ነዉ።

የሰኔ 8 ቀን 2014 ዓ/ም የዓለም ዜና በድምጽ
ርዕሶቹ
የትግራይ ክልልን የሚቆጣጠረው ሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሃት “ተአማኒ፣ ገለልተኛ እና መርህ ላይ የተመሰረተ የሰላም ሂደት” ላይ ለመሳተፍ ዝግጁ መሆኑን አስታወቀ። ህወሃት ባለፈዉ ሰኞ ተፅፎ ትናንት ባሰራጨው ግልፅ ደብዳቤ ድርድሩ « ከዚህ በፊት በተያዘለት ዕቅድ መሰረት » የኬኒያ ፕሬዚደንት የሚመሩት እና ሌሎች ዓለማቀፍ ተቋማት በተገኙበት በኬኒያ እንዲሆን ፍላጎት እንዳለው ገልጿል።
የኢትዮጵያ መንግስትና የአማፂያን ኃይላት ትናንት ሲዋጉባት የዋለችዉ የጋምቤላ ከተማ ዛሬ መረጋጋት እንደሰፈነባት የጋምቤላ ክልል መስተዳድርና የከተማዋ ነዋሪዎች አስታወቁ።
የኬንያዉ ፕሬዝደንት ኡሑሩ ኬንያታ ናይሮቢ ለሚገኙ የዉጪ ዲፕሎማቶች መግለጫ በሚሰጡበት ስብሰባ ላይ የሶማሊላንድ ባንዲራ በመታየቱ ኬንያ ይቅርታ ጠየቀች።
ብሪታኒያ ፤ ትናንት ማክሰኞ ምሽት ወደ ርዋንዳ ልታጓጉዛቸው የነበሩ ተገን ጠያቂዎችን የጫነ አውሮፕላን የአውሮጳ ፍርድ ቤት ጣልቃ ከገባ በኋላ ሰርዛለች። የአውሮጳ ፍርድ ቤት ተገን ጠያቂዎቹን ወደ ርዋንዳ ማባረር « ሊቀለበስ የማይችል ብርቱ ጉዳት ያደርሳል» ሲል አስጠንቅቋል።
በእስራኤል እና ሳዑዲ አረቢያ መካከል መደበኛ ግንኙነት ይደረግ ዘንድ በቀጣዩ ወር ሳዑዲአረቢያን ለመጎብኘት ካቀዱት የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ብዙ እንደሚጠብቁ የእስራኤሉ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ያኢር ላፒድ ተናገሩ።
https://p.dw.com/p/4Cklx?maca=amh-RED-Telegram-dwcom ማድመጥ ይቻላል። አስተያየት ለመስጠት፣ ጥቆማ ለማድረስ ይኽን ቦት ይጠቀሙ 👉🏾 @dwamharicbot

Deutsche Welle
የሰኔ 8 ቀን 2014 ዓ/ም የዓለም ዜና
ጋምቤላ ዛሬ በአንጻራዊ ሰላም ስለመዋሏ
የጋምቤላ ክልል መንግሥት ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ በተለይ ለዶይቼ ቬሌ በስልክ ዛሬ በከተማዋ መረጋጋት ተፈጥሯል፣ የፀጥታ ኃይሉ ደግሞ የአሰሳ ሥራ እየሰራ እንደሆነ አብራርተዋል፡፡ https://p.dw.com/p/4CkR5?maca=amh-RED-Telegram-dwcom ማድመጥ ይቻላል። አስተያየት ለመስጠት፣ ጥቆማ ለማድረስ ይኽን ቦት ይጠቀሙ 👉🏾 @dwamharicbot

የጋምቤላ ክልል መንግሥት ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ በተለይ ለዶይቼ ቬሌ በስልክ ዛሬ በከተማዋ መረጋጋት ተፈጥሯል፣ የፀጥታ ኃይሉ ደግሞ የአሰሳ ሥራ እየሰራ እንደሆነ አብራርተዋል፡፡
ስለሰላም ድርድሩ የህወሐት መግለጫ
የኤርትራ መንግሥት ሠራዊት የትግራይ ግዛት ከሆኑ አካባቢዎች አሁንም አለመውጣቱ እና በአዋሳኝ አካባቢዎች ተደጋጋሚ የከባድ መሳሪያ ድብደባ እየፈፀመ መሆኑ የገለፁት ዶክተር ደብረፅዮን፣ የኤርትራ ሠራዊት ከያዘው የትግራይ ግዛት እንዲወጣ እና ከትንኮሳዎች እንዲቆጠብ ጥሪ አቅርበዋል። https://p.dw.com/p/4CkPQ?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
👉🏾 @dwamharicbot

የኤርትራ መንግሥት ሠራዊት የትግራይ ግዛት ከሆኑ አካባቢዎች አሁንም አለመውጣቱ እና በአዋሳኝ አካባቢዎች ተደጋጋሚ የከባድ መሳሪያ ድብደባ እየፈፀመ መሆኑ የገለፁት ዶክተር ደብረፅዮን፣ የኤርትራ ሠራዊት ከያዘው የትግራይ ግዛት እንዲወጣ እና ከትንኮሳዎች እንዲቆጠብ ጥሪ አቅርበዋል።
የፌደራል መንግሥት ከህወሓት ጋር ይደረጋል ያለው ድርድር
በሰሜን ኢትዮጵያ ሰላም እንዲሰፍን ከተፈለገ ሊደረግ የታቀደው ድርድር ሁሉንም ተፋላሚ ኃይሎች ያካተተ ሊሆን እንደሚገባ ተጠቁሟል፡፡ ስለቀጠለውና ምናልባትም በሰላም ሊቋጭ ይችላል ስለተባለው ጦርነት አስተያየታቸውን ያከሉት አንድ የፖለቲካል ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ባለሙያ ድርድሩ እንዲሳካ እውነት ላይ ሊመሰረት ይገባዋልም ይላሉ፡፡https://p.dw.com/p/4Ckm4?maca=amh-RED-Telegram-dwcom

በሰሜን ኢትዮጵያ ሰላም እንዲሰፍን ከተፈለገ ሊደረግ የታቀደው ድርድር ሁሉንም ተፋላሚ ኃይሎች ያካተተ ሊሆን እንደሚገባ ተጠቁሟል፡፡ ስለቀጠለውና ምናልባትም በሰላም ሊቋጭ ይችላል ስለተባለው ጦርነት አስተያየታቸውን ያከሉት አንድ የፖለቲካል ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ባለሙያ ድርድሩ እንዲሳካ እውነት ላይ ሊመሰረት ይገባዋልም ይላሉ፡፡
ጉድለት የተጫነው የ2015 የኢትዮጵያ በጀት
የኢትዮጵያ መንግሥት ለ2015 ያዘጋጀው በጀት 231.4 ቢሊዮን ብር የተጣራ ጉድለት ያጋጥመዋል ተብሎ እንደሚገመት የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አሕመድ ሽዴ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተናግረዋል። ይኸን ለመሙላት መንግሥታቸው 224.5 ቢሊዮን ብር ከአገር ውስጥ፤ 6.9 ቢሊዮን ብር ከውጪ አገር ለመበደር እንዳቀደ የገንዘብ ሚኒስትሩ አስረድተዋል። https://p.dw.com/p/4Ckab?maca=amh-RED-Telegram-dwcom

የኢትዮጵያ መንግሥት ለ2015 ያዘጋጀው በጀት 231.4 ቢሊዮን ብር የተጣራ ጉድለት ያጋጥመዋል ተብሎ እንደሚገመት የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አሕመድ ሽዴ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተናግረዋል። ይኸን ለመሙላት መንግሥታቸው 224.5 ቢሊዮን ብር ከአገር ውስጥ፤ 6.9 ቢሊዮን ብር ከውጪ አገር ለመበደር እንዳቀደ የገንዘብ ሚኒስትሩ አስረድተዋል።
በጅማ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የተሰራው የአፈር መመርመሪያ በአፈሪቃ ደረጃ ተሸላሚ ሆነ
ከ85 በመቶ በላይ የሚሆነው ህዝቧ በግብርና በሚተዳደርባት ኢትዮጵያ የአፈር ምርምር ጥናት የሚካሄድባቸው ማዕከላት ጥቂት መሆናቸውን መረጃዎች ያሳያሉ።ይህንን ችግር ለመፍታት ይመስላል የጅማ ዩንቨርስቲ ተማሪዎች ተንቀሳቃሽ የአፈር መመምመሪያ መሳሪያ ሰርተዋል።ይህ ቴክኖሎጅም በአፍሪቃ ደረጃ በቅርቡ ተሸላሚ ሆኗል። https://p.dw.com/p/4Ckgy?maca=amh-RED-Telegram-dwcom

ከ85 በመቶ በላይ የሚሆነው ህዝቧ በግብርና በሚተዳደርባት ኢትዮጵያ የአፈር ምርምር ጥናት የሚካሄድባቸው ማዕከላት ጥቂት መሆናቸውን መረጃዎች ያሳያሉ።ይህንን ችግር ለመፍታት ይመስላል የጅማ ዩንቨርስቲ ተማሪዎች ተንቀሳቃሽ የአፈር መመምመሪያ መሳሪያ ሰርተዋል።ይህ ቴክኖሎጅም በአፍሪቃ ደረጃ በቅርቡ ተሸላሚ ሆኗል።
ስለትናንቱ የጋምቤላ እና ምዕራብ ኦሮሚያ ፀጥታ ችግር የመንግስት ምላሽ
ዶ/ር ለገሰ በምእራብ ኦሮሚያም በተመሳሳይ መንግስት የፀጥታ ኃይሎች እርምጃ መውሰዱን ነው የገለጹት። https://p.dw.com/p/4Ckqh?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
👉🏾 @dwamharicbot
ዶ/ር ለገሰ በምእራብ ኦሮሚያም በተመሳሳይ መንግስት የፀጥታ ኃይሎች እርምጃ መውሰዱን ነው የገለጹት። https://p.dw.com/p/4Ckqh?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
👉🏾 @dwamharicbot
Deutsche Welle
ስለትናንቱ የጋምቤላ እና ምዕራብ ኦሮሚያ ፀጥታ ችግር የመንግስት ምላሽ
ዶ/ር ለገሰ በምእራብ ኦሮሚያም በተመሳሳይ መንግስት የፀጥታ ኃይሎች እርምጃ መውሰዱን ነው የገለጹት፡
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ዛሬ ሰኔ 8 ቀን 2014 ዓ/ም የደራሲና መምህርት መስከረም አበራን የዋስትና መብት ተጠብቆ ከእስር እንድትፈታ መወሰኑን ጠበቃዋ ሄኖክ አክሊሉ ለዶይቼ ቬለ ተናገሩ።
ዛሬ የዋለው የጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በፖሊስ የቀረበውን የመስከረም አበራ የዋስትና ውሳኔ ይሻርልኝ ጥያቄ ውድቅ በማድረግ ከትናንት በስትያ ሰኞ ሰኔ 6 ቀን 2014 ዓ/ም መስከረም አበራ በ30 ሺህ ብር ዋስትና ከእስር እንድትፈታ የተሰጠውን ውሳኔ አፅንቶታል። ባለፈው ሰኞ ሰኔ 6ቀን 2014 ዓ/ም መስከረም አበራ፤ በ30 ሺህብር ዋስትና ከእስር እንድትለቀቅ የስር ፍርድ ቤት የወሰነ ቢሆንም ፖሊስ ውሳኔው ይቀልበስልኝ ሲል ይግባኝ ጠይቆበት ነበር። የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ትናንት ማክሰኞ ሰኔ 7 2014 ዓ/ም ፖሊስ ያቀረበውን የይግባኝ አቤቱታ የተመለከተው ፍርድ ቤት ይግባኙን ውድቅ በማድረግ የዋስትና ውሳኔውን አፀንቶት ነበር። ነገር ግን ፖሊስ እንደገና ሰበር ሰሚ ፍርድቤትን ይግባኝ በመጠየቁ የፍርድ ቤቱ በውሳኔ ተግባራዊ ሳይሆን መቅረቱን የአዲስ አበባዋ ወኪላችን ሃና ደምሴ ዘግባለች።
በደራሲና መምህር መስከረም አበራ የዋስትና ውሳኔ ላይ ፖሊስ ያቀረበው አቤቱታ ውድቅ ሲሆን የዛሬው የጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ውሳኔ ለሁለተኛ ግዜ ነው ።
የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ " ሁከት እና ብጥብጥ በማነሳሳት " ወንጀል ተጠርጥራ ግንቦት 11 2014 ከቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ተይዛ ከአንድ ወር በላይ በእስር ላይ ቆይታለች።
ምስል፤ ከመስከረም አበራ የፌስ ቡክ ገጽ የተወሰደ

-ጋምቤላ ከተማ ዉስጥ ባለፈዉ ማክሰኞ በመንግስትና በአማፂያን ኃይላት መካከል በተደረገ ዉጊያ 40 ያክል ሰዎች መገደላቸዉና ሌሎች ከ40 በላይ ሰዎች መቁሰላቸዉ ተነገረ።ከተማይቱ መረጋጋትዋ ቢነገርም የመንግስት መስሪያ ቤቶችና አገልግሎት መስጪያ ተቋማት የወትሮ ስራቸዉን በቅጡ አልጀመሩም።
-የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ግጭት ቀስቅሰዋል ወይም በየግጭቱ ተሳትፈዋል ያላቸዉን ከ9 መቶ በላይ ሰዎች አሰረ።ተጠርጣሪዎቹ የገዚዉ ፓርቲ አባላት፣ የፖሊስ መኮንኖችና የመንግስት ሰራተኞችን ይጨምራል።
-በተጋመሰዉ የግሪጎሪያኑ 2022 ዓመት በሚሊዮን የሚቆጠር ሕዝብ መሰደድና መፈናቀሉን የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች መርጃ ኮሚሽነር (UNHCR) አስታወቀ።የኮሚሽነሩ የበላይ ፊሊፖ ግራንዲ ምዕራባዉያን መንግስታት ለዩክሬን ስደተኛ ያሳዩትን ርሕራሔና ደግነት ለሌሎች ችግረኞች መንፈጋቸዉን ተችተዋል።https://p.dw.com/p/4CpGB?maca=amh-RED-Telegram-dwcom @dwamharicbot

ዜና፣ ሰኔ 9፣2014
የሰኔ 10 ቀን፣ 2014 ዓ.ም የዓለም ዜና
አርዕስተ ዜና
*በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን ሽርካ ወረዳ ታጣቂዎች በመንግስት የፀጥታ አካላት እና አስተዳዳሪዎች ላይ በከፈቱት የጦር መሣሪያ ጥቃት የወረዳው አስተዳዳሪ እና የወረዳው የፖሊስ ምክትል አዛዥ መገደላቸው ተገለጠ።
*ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ባለፈው ማክሰኞ በዳኞች ላይ የሰጡት አስተያየት የአማራ ክልል ዳኞችን እንዳስቆጣ የክልሉ ዳኞች ማኅር ዐስታወቀ። ማኅበሩ የማስተካከያ ንግግር እንዲደረግም ጠይቋል።
*የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን፦ አንድ ተማሪን ሲደበድቡ በማኅበራዊ መገናኛዎች በተሰራጨ ተንቀሳቃሽ ምስል ላይ የታዩ አራት የፖሊስ አባላቱን በቁጥጥር ሥር አውሎ ምርመራ እያጣራ መሆኑን ዐስታወቀ።
*መአከላዊ የሶማሊያ ከተማ በኾነችው ባህዶ ውስጥ የአልሸባብ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት ቢያንስ 30 ሰዎች መገደላቸውን የጀርመን ዜና አገልግሎት(dpa) ዘገበ።
ዜናው በዝርዝር
*በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን ሽርካ ወረዳ ታጣቂዎች በመንግሥት የፀጥታ አካላት እና አስተዳዳሪዎች ላይ በከፈቱት የጦር መሣሪያ ጥቃት የወረዳው አስተዳዳሪ እና የወረዳው የፖሊስ ምክትል አዛዥ መገደላቸው ተገለጠ። ግድያው ባለፈው እሑድ ሰኔ 05 ቀን፣ 2014 ዓ.ም. በወረዳው ጋሌማ በተባለ ደናማ አከባቢ ጠዋት በግምት ከ3 እስከ 4 ሰዓት ገደማ መፈፀሙን ለደህንነታቸው ሲባል ስማቸውን ያልገለጡ ነዋሪ ለዶይቼ ቬለ (DW) ተናግረዋል። እንደ ነዋሪው አስተያየት፦ የወረዳው አስተዳዳሪን ጨምሮ የፖሊስ ኮሚሽን ምክትል አዛዡ ከወረዳው ከተማ ጎቤሳ የተወሰኑ የፖሊስ አባላትን አስከትለው የአርሲ ብሔራዊ መካነ-አራዊት አካል ወደ ሆነው ጋሌማ ሲያመሩ ነው ጥቃቱ በታጣቂዎች የተከፈተው። በጥቃቱም የወረዳው አስተዳዳሪ፣ የወረዳው ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል አዛዥ እና አንድ የሚሊሻ አባል መገደላቸውን ነው ነዋሪው የገለጹት።
«የወረዳው አስተዳዳሪን ጨምሮ የፖሊስ ኮሚሽን ምክትል አዛዡ ባለፈው ከዚህ የሔዱት ዘመቻ ተብሎ ነው። ዝምብ ብሎ ፖሊሶች እና ቀለል ያለ ኃይል ይዘው ነው የኼዱት። ጋሌማ ውስጥ ድንኳን ተጥሏል ተብሎ ከዚህ በፊት መረጃ ደርሷቸዋል።»
ነዋሪው እንዳሉት በዕለቱ ታጣቂዎች ሰዎች አግተዋል፤ የጦር መሣሪያና ገንዘብ ዘርፈዋል። የወረዳው ፖሊስ አዛዥ ዘመዱ ኃይሉ የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ እና የፖሊስ ምክትል አዛዥ በጥቃቱ መገደላቸውን ለዶይቼ ቬለ አረጋግጠዋል፡፡
«በታጣቂዎች እና በሰላም አስከባሪዎች መካከል የሰው ሕይወት አልፏል። ይህ መኾኑ የታወቀ ነው። በሺርካ ወረዳ እና በሳቡሬ ድንበር ላይ ነው። ቦታው ደግሞ አስቸጋሪ ነው። የሌሎችም የወደቁ ሰዎች ሬሳ ይኖራል ብለን እናስባለን።»
የአርሲ ዞን ሺርካ ወረዳ ዋና ከተማ ጎቤሳ ከአዲስ አበባ 264 ኪ.ሜ ገደማ ርቀት ላይ ስትገኝ፤ ከበቆጂ ከተማ ደግሞ 35 ኪ.ሜ. ትርቃለች። ነዋሪዎቹ ከዚህ ቀደም ታጣቂዎች በአከባቢው እንደማይንቀሳቀሱና መሰል የፀጥታ ስጋትም ሲያዩ የመጀመሪያቸው መሆኑን ለአዲስ አበባው ዘጋቢችን ሥዩም ጌቱ ተናግረዋል።
*ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ባለፈው ማክሰኞ በዳኞች ላይ የሰጡት አስተያየት የአማራ ክልል ዳኞችን እንዳስቆጣ የክልሉ ዳኞች ማሕበር ዐስታወቀ። የተሰጠው አስተያየት በኅብረተሰቡ ዘንድ የተሳሳተ ግንዛቤ የሚያስጨብጥ በመሆኑ በአስቸኳይ እንዲታረም ሲል ማኅበሩ ባወጣው መግለጫ ጠይቋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ባለፈው ማክሰኞ ከተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ሲመልሱ ዳኞችን በተመለከተ የሰጡት ጥቅል አስተያየት በርካታ የክልሉን ዳኞች በእጅጉ እንዳበሳጨ በመግለጫው ተመልክቷል። የአማራ ክልል ዳኞች ማሕበር ምክትል ሊቀመንበር አቶ ብርሃኑ አሰፋ የጠቅላይ ሚንሥትሩ ንግግር ማስተካከያ እንደሚያሻው ተናግረዋል።
«እንግዲህ ዳኞች አንደኛ ደረጃ ሌቦች በሚል ተገልጠዋል። የዚህ አይነት ደረጃን ለማውጣት ጥናት እና ማስረጃ የሚጠይቅ ነው። ምናልባት በሳቸው በኩል ምን አይነት ጥናት እና ማስረጃ ይዘው እንደሆነ ባናውቅም ይህንን ታሳቢ አድርገው የተነገረው ንግግር ፍርድ ቤቶችም ላይ ዳኞችም ላይ የሚፈጥረው ትልቅ ተጽእኖ አለ። ንፁህ እና ምሥጉን ዳኞች ሞራል የሚነካ ነው፤ የሚያሸማቅቅ ነው። ማስተካከያ ንግግር እንዲያደርጉ ነው ጥያቄ ያቀረብነው።»
አንዳንድ ስነምግባር የጎደላቸው ዳኞች እንደሚኖሩ ያመለከቱት የማሕበሩ ምክትል ፕረዚደንት የተሰጠው አስተያየት በንፅህናና በእውነት ለኅሊናቸው የሚሠሩ ዳኞችን ሞራል የነካ ነው ሲሉም ተችተዋል። ያም ሆኖ ዳኞች በተባለው ነገር ሳይረበሹና ሳይበሳጩ ጉዳዩ በሥራቸው ምንም ተፅዕኖ ሳይፈጥር በተለመደው ሁኔታ ተግባራቸውን እንደሚያከናውኑ መግለጣቸውን የባሕር ዳር ወኪላችን ዓለምነው መኮንን ዘግቧል።
*የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን፦ አንድ ተማሪን ሲደበድቡ በማኅበራዊ መገናኛዎች በተሰራጨ ተንቀሳቃሽ ምስል ላይ የታዩ አራት የፖሊስ አባላቱን በቁጥጥር ሥር አውሎ ምርመራ እያጣራ መሆኑን ለዶይቸ ቬለ (DW) ገለጠ። ሰኔ 8 ቀን፣ 2014 ዓ.ም በጉለሌ ክ/ከተማ ድል በር 2ኛ ደረጃ ት/ት ቤት ክፍል ውስጥ ለስንብት በተደረገ ዝግጅት አንድ ተማሪ ርችት በመተኮሱና ሌሎች ተማሪዎች ላይ መደናገጥ በመፈጠሩ አራት የፖሊስ አባላት ተማሪውን ተከታትለው በመያዝ የድብደባ ወንጀል እንደፈፀሙበት የከተማው ፖሊስ ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ምክትል ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ ተናግረዋል።
«ያደረገው ጥፋት ትክክል አይደለም። ተማሪውም ቢሆን ሌሎች ተማሪዎች እየተማሩ የሌሎች ተማሪዎችን ኹኔታ ማደናቀፍ አይጠበቅበትም። ግን [ፖሊሶቹ]የወሰዱት ርምጃ ከህግ ውጪ የኾነ፤ ሁላችንንም ያስከፋ መረጃ ነው። ስለዚህ የፖሊስ አባላቱን በቁጥር ስር የማዋል ሥራ ነው የተሠራው። አራት የፖሊስ አባላት ናቸው እዚያ ቦታ ላይ ሥራውን ሲሠሩ የነበሩት። እና በዚያ በሥራ መሀል ለተፈጠረው ችግር አራቱንም ፖሊሶች በቁጥጥር ስር አድርገን ምርመራ እያደረግን ነው ያለነው።»
በፖሊስ በርካታ ውጤታማ ሥራዎች ቢሰሩም ሕገ ወጥ ተግባር የሚፈፅሙ አንዳንድ ፖሊሶች ሊያጋጥሙ እንደሚችሉ ሆኖም በአጥፊዎች ላይ ርምጃ እንደሚወሰድ ኃላፊው ገልፀዋል። በማኅበራዊ የመገናኛ አውታሮች የተለቀቀው ተንቀሳቃሽ ምስል ውስጥ የፖሊስ የደንብ ልብስ የለበሱ ፖሊሶች የተማሪ ደንብ ልብስ የለበሰ ተማሪን በቆመጥ ደጋግመው ሲነርቱት፤ በጫማ እየረጡ ሲመቱትም በግላጭ ያሳያል። በከተማዋ መሰል ድርጊቶች በፖሊሶች ሲፈፀሙ ተደጋግሞ ታይቷል።