DW Amharic
56.4K subscribers
4.14K photos
984 videos
69 files
15.7K links
ይህ የዶይቼ ቬለ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው። ትኩስ ዜና፣ በአበይት ፖለቲካዊ፣ ኤኮኖሚያዊ፤ ማኅበራዊ እና ባሕላዊ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩር ትንታኔ ያቀርባል።
Download Telegram
ደቡብ አፍሪቃ አስትራዜንካ ስተባለዉ የኮሮና መከላከያ ክትባት ዝርዝር መረጃ እስከምታገኝ ክትባቱን ጥቅም ላይ እንደማታዉል ገለፀች። ደቡብ አፍሪቃ ይህን የገለፀችዉ ብሪታንያ እና በስዊድን የመድሃኒት አምራች ኩባንያ የሚመረተዉ አስትራዜንካ የኮnŀ መከላከያ ክትባት ምሁራን እና ተመራማሪዎች እንዴት ጥቅም ላይ መዋል እንዳለበት ገና ምክር ላይ በመሆናቸዉ ነዉ ስትል ምክንያትዋን ሰጥታለች። ደቡብ አፍሪቃ ስለዚህ የኮሮና መከላከያ ክትባት ምሁራኑ አጠቃቀሙ ላይ ተማክረዉ ዉሳኔዉን እስኪሲጨርሱ ድረስ እንደምትጠብቅ ነዉ ያሳወቀችዉ። ከዚህ ቀደም ሲል የአስትራዚንካ የኮሮና ክትባት አምራች ኩባንያ፤ የመከላከያዉ ክትባት አይነት በደቡብ አፍሪቃ ለታየዉ የኮሮና ተኅዋሲ አይነት ጠንካራ የሆነ ፍቱነት እንደሌለዉ አሳዉቆ ነበር ተብሎአል።
የአውሮጳ ህብረት ኤርትራ ወታድሮቿን ከትግራይ ክልል እንድታስወጣ አሳሰበ:: ሕብረቱ ከዚሕ ቀደም ቀደም ዩናይትድስቴትስ የስጠችውን ተመሳሳይ ማሳሰቢያ በመደገፍ የኤርትራ ወታደሮች በትግራይ ዉስጥ መግባትበአካቢዉ ግጭት እንዲባባስ ምክንያት ሆኗል ሲል ወቅሷል::የኢትዮጵያና የኤርትራ መንግስታት <<የኤርትራ ወታደሮችበትግራዩ ጦርነት አልተሳተፉም >> ሲሉ የቀረበባቸውን ክስ በየፊናቸው ሲያስተባብሉ ቆይተዋል:: አሁንም የኤርትራው የማስታወቂያ ሚንስትር የማነ ገብረ መስቀል የአዉሮጳ ሕብረትን ማሳሰቢያ አጣጥለዋል::
የአውሮጳ ህብረት ባወጣው መግለጫ እንዳለው የኤርትራ ወታደሮች ጣልቃ ገብነትን በተመለከተ የኢትዮጵያ መንግሥት ባለስልጣናት የሚሰጧቸው የማስተባበያ አስተያየቶች እርስበእርሳቸው የሚጣረሱ ናቸዉ ብሏል:: ህብረቱ አያይዞም በትግራይ ክልል እየታየ ያለው ሰብአዊ ቀውስ የተለየ ትኩረት ሊያገኝ ይገባል ብሏልም የኢትዮጵያ መንግሥት ያልተገደበ የሰብአዊ እርዳታ እንዲቀርብ ሁኔታዎችን እንዲያመቻችእና ለሰላማዊ ሰዎች እና ለስደተኞች ጥበቃ እንዲያደርግ ጠይቋል:: የኖርዌያውያን ስደተኞች ጉዳይ ምክር ቤት እንዳለው <<በትግራይ ክልል ኤርትራዉያን ስደተኞች በሠፈሩበት መጠለያ ጣቢያ ውስጥ ለስደተኞቹ አገልግሎት ይሰጡ የነበሩ ህንጻዎች እና ሌሎች ቁሳቁሶች ወድመዋል::>> በተያያዘ 20,000 ስደተኞችን እንደያዘ በተነገረለት ሽመልባ ለተሰኘ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ ሰብአዊ ድጋፍ ማድረስ አልተቻለምብሏል:: የኢትዮጵያ መንግሥት በአካባቢው የህወሃት ታጣቂዎች የደፈጣ ውግያ በመጀመራቸው ለሁለቱየመጠለያ ጣቢያዎች አስፈላጊውን እርዳታ ለማድረስ መቸግሩን የሀገሪቱ የስደተኞች መርጃ ኤጄንሲአስታውቋል::
በኢትዮጵያ ወደ ሰሜንና ሰሜን ምዕራብ አንዳንድ ከተሞች ተቋርጦ የነበረው የአየር በረራ ተጀመረ!
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ተፈጥሮ ሰሞኑን ተፈጥሮ ነበር ባለው አስቸጋሪ የአየር ሁኔታ ምክንያት ተቋርጦ በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል በሚገኙ አብዛኞቹ ከተሞች የአየር በረራ ማቋረጡን አስታውቆ ነበር ። ነገር ግን ዛሬ እንደተሰማው ከአዲስ አበባ ባህርዳር፣ ጎንደር እና ላሊበላ የአየር በረራ ትናንት መጀመሩን አየር መንገዱና ተሳፋሪዎች ገልፀዋል፡፡
አንድ የአየር መንገዱ ባልደረባ ለዶይቼ ቬለ እንደተናገሩት ሰሞኑን ተፈጥሮ በነበረው ጭጋጋማ የአየር ሁኔታ ምክንያት ከአርብ ከሰኣት ጀምሮ ከአዲስ አበባ ባህር ዳር፣ ጎንደርና ላሊበላ ይደረጉ የነበሩ በረራዎች ተቋርጠው ቆይተዋል፡፡ ይሁን እንጂ የአየር ሁኔታው የተሰተካከለ በመሆኑ እሁድ ወደ ላሊበላ በረራ መጀመሩን፣ ባህርዳርና ጎንደር ደግሞ ትናንት ሰኞ የበረራ አገልግሎት መቀጠሉን ገልፀዋል፡፡
አንድ ከአዲስ አበባ ወደ ባህር ዳር ለመምጣት ሲጠባበቁ የነበሩ የአየር መንገዱ ደንበኛ ትናንት በረራ መጀመሩ ከአየር መንገዱ ተነግሯቸው በነበረው የበረራ መስተጓጎል በተፈጠረ ወረፋ በረራቸው ተዛውሮ ዛሬ ባሕር ዳር መግባታቸውን ለዶይቼ ቬለ በስልክ ተናግረዋል፡፡
የዶይቼ ቬለ ዘጋቢ እንዳረጋገጠውም ከትናንትና ጀምሮ በባህር ዳር አውሮፕላን ማረፊያ አውሮፕላኖች እየተነሱ ሲያርፉ ነበር፡፡
ሆኖም ያለው የአየር ሁኔታ ሞቃታማነቱን እየጨመረ ስለሚሄድ በቅርቡ ተመሳሳይ የአየር ሁኔታ ለውጥ ሊኖር እንደሚችል በኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ አጀንሲ የባህር ዳር ቅርንጫፍ የትንበያና ትንተና ቡድን አስተባባሪ አቶ ጥላሁን ውቤ የትንበያ ሪፖርቶችን ጠቅሰው ተናግረዋል፡፡
የሱዳኑ ጠቅላይ ሚንስትር አብደላ ሀምዶክ 7 የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎችን በአዲሱ ካቢኔያቸው ውስጥ ማካተታቸው ተነገረ።ጠቅላይ ሚንስትሩ ባለፈው እሁድ የቀድሞዎቹን የካቢኔ አባላት ሚንስትሮችን ከበተኑ በኋላ ተቃዋሚዎችን ያካተቱበትን አዲሶቹን ሚንስትሮች ይፋ አድርገዋል። የተቃዋሚዎችን በካቢኔ አባላት ውስጥ ያካተቱት አብደላ ሀምዶክ ባለፈው ጥቅምት ወር የተደረሰው የሰላም ስምምነት አንድ አካል እንደሆነም ተዘግቧል።አካታች ነው በተባለለት በአዲሱ የሀምዶክ መንግስት ውስጥ ሁለት ሚንስትሮች ከወታደራሩ ቡድን መውሰዳቸውም ነው የተገለጸው። ነጻነት ለለውጥ የተሰኘው ኃይል ስብስብ አባላት የሆኑ እና የኦማር አልበሽርን መንግስት ገዝግዘው በመጣል ውስጥ ትልቅ ሚና ነበራቸው የተባለላቸው ሰዎች የአዲሱን መንግስት አብዛኛውን የካቢኔ ሚንስትርነት ወንበር ይዘዋል።በሹመቱ ውስጥ ከተካተቱት የሱዳን የመጨረሻው በዴሞክራሲያዊ መንገድ ጠቅላይ ተመርጠው የነበሩት ጠቅላይ ሚንስትር ሳዲቅ አል መሃዲ ሴት ልጅ መርዬም ሳዲቅ አል መሃዲ የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሆነው ተሾመዋል። የአብደላ ሀምዶክ አዲሱ መንግስት ሱዳን ወደ ዴሞክራሲያዊ መንገድ ለምታደርገው ጉዞ ሊያግዛት እንደሚችል ዘገባዎች ያመለክታሉ።
ኢትዮጵያ እስከተያዘው የጎርጎርሳውያኑ 2021 መጨረሻ አንድ አምስተኛውን ህዝቧን የኮቪድ 19 ክትባት ለመከተብ ዝግጅት እያደረገች መሆኗን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ። ሚኒስቴሩ እንዳለው እስከ የፊታችን ሚያዝያ ወር የምትረከበውን 9 ሚሊዮን ጸረ ተህዋሲውን ክትባት ማዘዟን ሚንስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ ተናግረዋል። በዚህም እስከ የጎርጎርሳውያኑ የ2021 መጨረሻ ድረስ 20 በመቶ የሚሆነውን የሕብረተሰብ ክፍል ክትባቱን ተደራሽ ለማድረግ እየሰሩ መሆናቸውን ሚኒስትሯ ለሮይተርስ የዜና ምንጭ ገልጸዋል። ሀገሪቱ «የጸረ ተህዋሲውን ክትባት በእርዳታ ማግኘት በሚያስችላት ሁኔታ ላይ ስትሰራ ነበር» ያሉት ሚንስትሯ ነገር ግን ክትባቱን ኮቫክስ በተባለው እና ከዓለም የጤና ድርጅት ጋር በመሆን ደሃ ሀገራት ክትባቱን በፍትሃዊነት እንዲያገኙ በሚሰራ ጥምረት በኩል በኩል ለማግኘት ጥረት በማድረግ ላይ መሆናቸውን አስታውቀዋል። ነገር ግን በኮቫክስ በኩል ይቀርባል የተባለው ክትባት የትኛው እንደሆነ ዶ/ር ሊያ ያሉት ነገር የለም ። ኢትዮጵያ የጸረ ተህዋሲውን ክትባት በግዢ ለማቅረብ 328 ሚሊዮን ዶላር ወይም 13 ቢሊዮን ብር እንደሚያስፈልጋት መንግስታዊው የዜና ምንጭ ኢዜአ ዘግቧል። በኢትዮጵያ 142,000 ሰዎች በኮሮና ሲያዙ 2100 የሚሆኑት ደግሞ ከኮሮና ጋር በተያያዘ ህይወታቸውን አጥተዋል። የተቀረው ዓለም ክትባቱን በዘመቻ መስጠት በጀመረበት በዚህ ጊዜ አፍሪቃ 1,3 ቢሊዮን ለሚሆነው ህዝቧ ክትባቱን ለማድረስ ብርቱ ጥረት ይጠይቃታል ተብሏል። በአህጉሪቱ የተሻለ አቅም ያላቸው ብቻ ክትባቱን ማግኘት መጀመራቸውን ዘገባው አመልክቷል።
የእነ አቶ ጃዋር ሞሐመድ የርሃብ አድማ

በማረሚያ ቤት በርሃብ አድማ ላይ የሚገኙት ፖሊቲከኞች እራሳቸውን እየሳቱ መሆኑን ቤተሰቦቻቸው እና ከጠበቆቻቸው አንዱ ለዶቼ ቨለ ተናገሩ::
https://p.dw.com/p/3p7qC?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
አስተያየት ለመስጠት፣ ጥቆማ ለማድረስ ይኽን ቦት ይጠቀሙ 👉🏾 @dwamharicbot
የሀዋሳ ሀይቅን ለመታደግ የሚደረግ ዘመቻ

የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር በደለል ሙላት የተነሳ ህልውናው በአደጋ ላይ የሚገኘውን የሀዋሳ ሀይቅ ለመታደግ ያስችላል ያለውን የአካባቢ ጥበቃ ዘመቻ በይፋ መጀመሩን አስታወቀ።
https://p.dw.com/p/3p7qe?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
አስተያየት ለመስጠት፣ ጥቆማ ለማድረስ ይኽን ቦት ይጠቀሙ 👉🏾 @dwamharicbot
የአዉሮጳ ሕብረትና ትግራይ

የአዉሮጳ ሕብረት ባለስልጣናት ትግራይ ዉስጥ የተከሰተዉ ሰብአዊ ቀዉስና ባካባቢዉ ሊያስከትል የሚችለዉ ተፅዕኖ እንደሚያሳስባቸዉ አስታወቁ። የሕብረቱ የዉጪ ግንኙነት ኃላፊ፣የአስቸኳይ ርዳታ ኮሚሽነር እና የዓለም አቀፍ ትብብር ኮሚሽነር በጋራ ባወጡት መግለጫ የርዳታ ድርጅቶች ወደ ትግራይ ክልል በሰፊዉ መግባት እንዲችሉ የኢትዮጵያ መንግሥት ይፈቅድ ዘንድ ጠይቀዋል።
https://p.dw.com/p/3p82x?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
አስተያየት ለመስጠት፣ ጥቆማ ለማድረስ ይኽን ቦት ይጠቀሙ 👉🏾 @dwamharicbot
የፌደራል መንግስትና የተቃዋሚ ፖለቲከኞች በመቀሌ

የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት፣ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች፣ የኃይማኖት አባቶችና የሐገር ሽማግሌዎች ሰሞኑን በተከታታይ የትግራይን ርዕሠ-ከተማ መቀሌን ጎብኝተዋል።
https://p.dw.com/p/3p7zs?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
አስተያየት ለመስጠት፣ ጥቆማ ለማድረስ ይኽን ቦት ይጠቀሙ 👉🏾 @dwamharicbot
የትግራይ ወቅታዊ ሁኔታ

ትናንት መቀሌ የገቡት የኢትዮጵያ የተለያዩ የኃይማኖት መሪዎችና የሐገር ሽማግሌዎችም እዚያዉ መቀሌ ዉስጥ ከክልሉ ጊዚያዊ አስተዳደር ባለሙያዎችና ከከተማዋ የተወሰኑ ነዋሪዎች ጋር ተነጋግረዋል።
https://p.dw.com/p/3p7s5?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
አስተያየት ለመስጠት፣ ጥቆማ ለማድረስ ይኽን ቦት ይጠቀሙ 👉🏾 @dwamharicbot
ጀርመን ኢትዮጵያዉያንን መመለስዋን ቀጥላለች

ጀርመን ኢትዮጵያዉያን ስደተኞችን ወደ ሃገራቸዉ መጠረዝዋን ቀጥላለች። በጀርመን ተቃዋሚ ፖለቲከኞች እና የሰብዓዊ ጉዳይ አቀንቃኞች ይህን የጀርመን መንግሥትን ርምጃ እያወገዙ ነዉ።
https://p.dw.com/p/3p843?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
አስተያየት ለመስጠት፣ ጥቆማ ለማድረስ ይኽን ቦት ይጠቀሙ 👉🏾 @dwamharicbot
ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችና የኮሮና ወረርሽኝ

በየዓመቱ በጎርጎሪዮስ የዘመን ቀመር የካቲት 6 የሴት ልጅን ግርዛ ፈጽሞ ለማጥፋት የሚደረገው ጥረት በዓለም ደረጃ ይታሰባል። ኢትዮጵያ እስከ 2025 ዓ,ም ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቱን ለማስቆም ብታቅድም ተግባራዊነቱ ግን እያነጋገረ ነው። በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ምክንያትም በአዳጊና አዋቂ ሴቶች ላይ የሚፈጸሙት ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች መባባሳቸው ተሰምቷል።
https://p.dw.com/p/3p8D2?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
አስተያየት ለመስጠት፣ ጥቆማ ለማድረስ ይኽን ቦት ይጠቀሙ 👉🏾 @dwamharicbot
ዜናው በዝርዝር

*የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) 25 ተጨማሪ ሠራተኞቹ ትግራይ ክልል ውስጥ እንዲንቀሳቀሱ ከኢትዮጵያ መንግሥት ፍቃድ ማግኘቱን ዐስታወቀ።ፈቃዱን አስመልክቶም፦ የዓለም አቀፍ ድርጅት ዋና ፀሐፊ የአንቶኒዮ ጉተሬሽ ቃል አቀባይ ሽቴፋን ዱዦሪክ፦ የርዳታ ሠራተኞች ትግራይ ክልል ውስጥ በተቀላጠፈ መልኩ ርዳታ ማቅረብ እንዲችሉ «የመጀመሪያው ርምጃ ነው» ብሏል። የኢትዮጵያ መንግሥት ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር ያከናወናቸውን ቀና ያሉትን ቊርጠኝነት ቃል አአቀባዩ በመግለጫቸው አውስተዋል። በአሁኑ ወቅት 60 የሚጠጉ የተባበሩት መንግሥታት እና ሌሎች መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የሰብአዊ ድጋፍ አቅራቢ ሠራተኞች ወደ ትግራይ ለመንቀሳቀስ አዲስ አበባ ሆነው እንደሚጠብቊም ቃል አቀባዩ ጠቅሰዋል። የዓለም ምግብ ድርጅት (WFP)የኢትዮጵያ መንግሥት፦ «ወደ ትግራይ የሚገቡ እና የሚሠራጩ የርዳታ ጭነቶችን» በተመለከተ «ባለሥልጣናቱን እና የርዳታ ድርጅቶቹን ለማገዝ» አቀረበ ያለውን ጥያቄም መቀበሉንም ዐስታውቀዋል። ከዚያም ባሻገር የዓለም ምግብ ድርጅቱ እስከ አንድ ሚሊዮን ለሚጠጉ ዜጎች ትግራይ ውስጥ አስቸኳይ የምግብ ርዳታ ለማቅረብ መስማማቱንም ጠቊመዋል። አምነስቲ ኢንተርናሽናል በበኩሉ የኢትዮጵያ መንግሥት ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ተጨማሪ ሠራተኞች ፈቃድ መስጠቱን አስመልክቶ ዛሬ ባወጣው መግለጫ፦ መንግሥት ቃሉን እንዲጠብቅ ጠይቋል። የኢትዮጵያ መንግሥት እና አጋሮቹ ቀደም ሲል 1,8 ሚሊዮን ለሚጠጋ ነዋሪ ትግራይ ውስጥ ርዳታ ማድረሳቸውን የዓለም ምግብ ድርጅት ኃላፊ ዳቪድ ቤያስሌይ ማወደሳቸውን የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚንሥቴር ዛሬ በሰጠው ሳምንታዊ መግለጫ ገልጧል። በሁለት የመጠለያ ጣቢያዎች የሚገኙ 26,000 ኤርትራውያን ስደተኞችም የምግብ ርዳታ እና የአልሚ ምግብ እንደታደላቸው አክሎ ጠቅሷል።

*ሦስት የአውሮጳ ኅብረት ኮሚሽነሮች ትናንት በጋራ ባወጡት መግለጫ፦ ትግራይ ክልል ውስጥ ግጭት እያባባሱ የሚገኙ ያሏቸው የኤርትራ ወታደሮች ከኢትዮጵያ እንዲወጡ ጥሪ አቀረቡ።ዩናይትድ ስቴትስ የኤርትራ ወታደሮች ከትግራይ እንዲወጡ ከዚሕ ቀደም ያደረገችዉን ጥሪ ሕብረቱ እንደሚደግፍ ኮሚሽነሮቹ አስታዉቀዋል። የኤርትራ ወታደሮች ግፍ ይፈጽማሉ፣ ግጭት እና ኹከት እንዲባባስም ሰበብ ሆነዋል ብሏል የኅብረቱ ሦስት ኮሚሽነሮች የጋራ መግለጫ። መግለጫውን የሰጡት የኅብረቱ የውጭ ግንኙነት ኃላፊና የኮሚሽኑ ምክትል ፕሬዚደንት ጆሴፍ ቦሬል፤ የአስቸኳይ ርዳታ ኮሚሽነር ጃኔዝ ሌናርቺች እና የዓለም አቀፍ ትብብር ኮሚሽነሯ ጁታ ኡርፒላይነን ናቸው።ትግራይ ክልል ውስጥ እየታየ ያለው «አስከፊ» የሰብአዊ ቀውስ እና በአካባቢው ሊያደርስ የሚችለው ተጽዕኖ ያሳሰባቸው መሆኑን አክለው ገልጠዋል። የሰብአዊ ርዳታው መዳረስ በትግራይ ክልል እና በአጎራባች አካባቢዎች የአፋር እና የአማራ ክልሎችም የሰብአዊነት መርኆችን፣ ገለልተኝነትን፣ ሰብአዊነትን፣ ለማንም ባልወገነ እና ነጻ በሆነ መልኩ ሊረጋገጥ እና ሊፈቀድ ይገባል ብለዋል።

*የሩስያ ውጭ ጉዳይ ሚንሥትር ሠርጌ ላቭሮቭ፦ የኢትዮጵያ መንግሥት ትግራይ ክልል ውስጥ የሰብአዊ ተግዳሮትን ለመወጣት የሚያደርገውን ጥረት የሩስያ ፌዴሬሽን ዕውቅና እንደሚሰጥ ገለጡ። የሩስያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ ይህን ያሉት ከኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ እና ምክትል ሚንሥትር ደመቀ መኮንን ጋር ትናንት በስልክ ከተወያዩ በኋላ ነው። በውይይቱ ወቅትም አቶ ደመቀ በትግራይ ክልል ውስጥ ስላለው መልሶ ግንባታ እና ማቋቋም ለሠርጌ ላቭሮቭ ማብራራታቸው ተጠቊሟል። ትግራይ ውስጥ የሰብአዊ ድጋፍ ኹኔታ ስኬታማ በሆነ መልኩ መቀጠሉን ማብራራታቸውንም ውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ገልጧል። ሠርጌ ላቭሮቭ የኢትዮጵያ መንግሥት ትግራይ ክልል ውስጥ ያለውን የሰብአዊ ተግዳሮትን በተመለከተ የሚያደርገውን ጥረት እንደሚረዱ መንግሥታቸውም በዚህ ጉዳይ ኢትዮጵያን መርዳቱን ለመቀጠል ምንጊዜም ዝግጁ መሆኑን ጠቊመዋል። ሩስያ አባል የሆነችበት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታው ጥበቃ ምክር ቤት ባለፈው ሳምንት በትግራይ ጉዳይ በዝግ መምከሩ የሚታወስ ነው።

*ኢትዮጵያ እስከ ሚያዝያ ወር ድረስ 9 ሚሊዮን የኮሮና ተሐዋሲ መከላከያ ክትባት ብልቃጦችን ለማስገባት ማቀዷ ተገለጠ። የትኞቹ አይነት ክትባቶች እንደሆኑ ግን አለመገለጡን ሮይተርስ የዜና ምንጭ ዘግቧል። ኢትዮጵያ ክትባቶቹን ለማስገባት ግዢ የፈጸመችው በቀጥታ ሳይሆን ክትባቶችን ለሁሉም ሃገራት ለማዳረስ የዓለም ጤና ድርጅት እና አጋሮቹ በተቋቋመው ኮቫክስ ከተሰኘው ተቋም መሆኑም ተጠቅሷል። ኮቫክስ በጣምራ የሚመራው ደሃ ሃገራት ክትባቶች እንዲዳረሣቸው ይንቀሳቀሳል በተባለው ጋቪ ጥምረት ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ እስካሁን ከ142 ሺህ በላይ ሰዎች ተመርምረው 2,154 ሰዎች ሕይወታቸው ማለፉን የጤና ሚንሥትር መረጃ ይጠቊማል። ኮቫክስ ክትባት አቅራቢ ተቋም በሚቀጥሉት ስድስት ወራት ቢያንስ 330 ሚሊዮን የክትባት ብልቃጦችን ለደሃ ሃገራት ለማቅረብ አቅዷል። ለደሃ ሃገራት ይቀርባሉ ከተባሉት የክትባት ብልቃጦች መካከል 240 ሚሊዮን የሚደርሰው የህንድ ተቋም ከሚያመርተው አስትራዜኔካ-ኦክስፎርድ የሚገኝ መሆኑን ሮይተርስ ዘግቧል። ቀሪው 96 ሚሊዮን ከአስትራዜኔካ መሆኑ ተጠቊሟል። አውራፓውያን የሚረባረቡበት ፕፋይዘር ባዮንቴክ ክትባት ግን 1,2 ሚሊዮን ብቻ ነው ለድሃ ሃገራት ሊሰጥ የታሰበው። ደቡብ አፍሪቃ አስትራዜንካ ስተባለዉ የኮሮና መከላከያ ክትባት ዝርዝር መረጃ እስከምታገኝ ክትባቱን ጥቅም ላይ እንደማታዉል መግለጿ ትናንት ተዘግቧል።

*በደብረ ማርቆስ ከተማ በተነሳ የእሳት ቃጠሎ 10 የሚሆኑ የሉካንዳ ቤቶች መቃጠላቸውን የከተማይቱ ፖሊስ አስታወቀ፡፡ የፖሊስ ጽ/ቤቱ ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር አጃናው አዲስ ለዶይቼ ቬለ እንደተናገሩት ከንጋቱ 12 ሠዓት ተኩል አካባቢ በከተማዋ ቀበሌ 01 በተነሳው ቃጠሎ 10 ሉካንዳ ቤቶች ሙሉ በሙሉ ወድመዋል፡፡ እሳቱ ወደሌሎች አካባቢዎች እንዳይስፋፋ የከተማው ወጣቶች ተቆጣጥረውታል ብለዋል፡፡ የጉዳቱ መጠን እየተጠና ሲሆን በቅርቡም በተመሳሳይ ሁኔታ በከተመው የሸቀጦች መሸጫ ላይ ቃጠሎ ተከስቶ ከ20 በላይ አነስተኛ ሱቆች ከነንብረታቸው መውደማቸውን አስታውሰዋል።

*ምሥራቅ አፍሪቃን ከዚህ ቀደም ከታየው የበረታ የበረሃ አንበጣ ወረርሽኝ ሊያጠቃት እንደሚችል ጀርመን አኸን ከተማ የሚገኘው ሚዜሬዎር የተሰኘው የርዳታ ተቋም አስጠነቀቀ። ከአንድ ዓመት በፊት ከታየው የባሰ ነው የተባለለት ሁለተኛ ዙሩ መጠነ ሰፊ የበረሃ አንበጣ መንጋ ኢትዮጵያ፣ ሶማሊያ እና ኬንያ ውስጥ ከፍተኛ የሰብል ጥፋት ሊያደርስ መሆኑ አሳስቦኛል ብሏል ርዳታ ድርጅቱ። መንጋው ከፍተኛ የሰብል ጥፋት አድርሶ ረሐብ ሊቀሰቅስም ይችላል ሲል ሚዜሬዎር አስጠንቅቋል። የኦለም ምግብ ድርጅት (FAO) በበኩሉ የበረሃ አንበጣ መንጋው ወደ ኡጋንዳ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ኤርትራ እና ጅቡቲ ድረስ ሊሠራጭ ይችላልም ብሏል።
*በምያንማር የተቃውሞ ሰልፈኞች ላይ ፖሊስ አስለቃሽ ጢስ እና የፕላስቲክ ጥይቶችን በመተኮስ ጉዳት ማድረሱ ተገለጠ። የምያንማር መንግሥት ቴሌቪዥን ፖሊስ ተቃዋሚ ሰልፈኞችን ለመበተን በተንቀሳቀሰበት ወቅት ጉዳት ስለደረሰባቸው ሰልፈኞች ዛሬ ዘግቧል። የምያንማርን ሲቢላዊ መንግስት አስወግዶ ሥልጣን የያዘዉን ወታደራዊ ኹንታ የሰጠዉን ማስጠንቀቂያ በመጣስ ተቃዋሚዎች የጀመሩት ሰልፍ አራተኛ ቀኑን አስቆጥሯል። ዛሬ በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ የተቃውሞ ሰልፈኞች አደባባይ መውጣታቸው ተዘግቧል። ሰልፈኞች በወታደራዊ ኹንታው ከሥልጣናቸው የተወገደዉ የሐገሪቱ መንግሥት ወደ ሥልጣን እንዲመለስ እየጠየቊ ነው።

የዓለም ዜናውን ሙሉ ዘገባ በድምጽ እዚህ 👉🏾https://p.dw.com/p/3p8F6?maca=amh-RED-Telegram-dwcom ማድመጥ ይቻላል።
አስተያየት ለመስጠት፣ ጥቆማ ለማድረስ ደግሞ ይኽን ይጠቀሙ 👇🏽 @dwamharicbot
በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ለማካሄድ የምርጫ ቦርድ የጊዜ ገደብ ቢያስቀምጥም የፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫ እንቅስቃሴ ሲደረጉ ብዙ አይስተዋልም። የምርጫ ቦርድ እስከ ምርጫ ክልል ድረስ በመውረድ ጽህፈት ቤቶችን የማዋቀር ስራ ከክልሎች ጋር በመተባበር እያከናወነ መሆኑን አስታውቆ ነበር። የምርጫ ቦርድ እያደረኩ ነው ከሚለው ዝግጅት አንጻር በፖለቲካ ፓርቲዎች ዘንድ እንደ የምርጫ ዓመት የጎላ እንቅስቃሴ እንደማይታይ በርካቶች ይናገራሉ። ሰሞኑን ገዢው የብልጽግና ፓርቲን የሚደግፉ ሰላማዊ ሰልፎች በአብዛኞቹ የሀገሪቱ ክፍል እየተካሄዱ ነው። መንግስት« ህግ የማስከበር ዘመቻ » ካለዉ የትግራይ ጦርነት በኋላ ከትግራይ ክልል ውጭ በተቀረው የሀገሪቱ ክፍል ምርጫው መደረጉ የማይቀር ይመስላል። ነገር ግን በሀገሪቱ አሁንም ያልተመለሱ ጥያቄዎች እንዳሉ በስፋት ይነገራል። ከሱዳን ጋር የተፈጠረው ውጥረት ፣ታዋቂ ፖለቲከኞች መታሰር እና በሀገሪቱ በአንዳንድ አካባቢዎች ሲደረጉ የነበሩ ግጭቶች መፍትሔ አለማግኘታቸዉ የምርጫዉን ዝግጅትና ሒደት ላለማወካቸዉ ዋስትና የለም የሚሉ አሉ።የናንተስ አስተያየት ምድነዉ? ምርጫውን በተመለከተ? በየአካባቢያችሁ ያሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች እንቅስቃሴስ ምን ይመስላል? ሀሳባችሁን አጋሩን።
የኢትዮጵያ መንግስት የአውሮጳ ሕብረት «በትግራይ ክልል ሰብዓዊ ቀውስ እየደረሰ ነው» በማለት ያወጣውን መግለጫ ነቀፈዉ።የኢትዮጵያ ዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር እንደሚለዉ የሕብረቱ መግለጫ መንግሥት በክልሉ እያቀረበ ያለውን የሰብዓዊ ርዳታ ግምት ውስጥ ያላስገባ ነው።የአውሮጳ ሕብረት ትናንት ባወጣው መግለጫ የኤርትራ ወታደሮች ትግራይ ዉስጥ መግባት እና በክልሉ እየተፈጠረ ያለው የሰብዓዊ ቀውስ አሳስቦኛል ብሎ ነበር።የኢትዮጵያ የውጪ ጉዳይ ሚንስቴር ለሕብረቱ መግለጫ በሰጠዉ መልስ "መንግሥት በአካባቢው የሕግ ማስከበር ስራን ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ሕብረቱ የሚያወጣው መግለጫ ሚዛናዊነቱን ያልጠበቀ እና ተገቢነት የሌለው ነው" ሲል ወቅሷል። የአውሮጳ ሕብረት ትናንት እውጥቶ በነበረው መግለጫው የኢትዮጵያ መንግሥት የሰብዓዊ ድጋፍ አቅራቢያዎች ያለ ገደብ እንዲንቀሳቀሱ እና ለስደተኞችና ለሰላማዊ ሰዎች ጥበቃ እንዲያደርግ ጠይቋል።የመንግስታቱ ድርጅት 25 የዕርዳታ አቅራቢ ሰራተኞች ወደ ትግራይ ክልል እንዲገቡ ከኢትዮጵያ መንግስት ፈቃድ ማግኘቱን አስታዉቋል።የውጪ ጉዳይ ሚንስቴር <<የሰብአዊ ድጋፍ አቅርቦቱ በበርካታ የትግራይ ክልል ተደራሽ እንዲሆን መንግሥት እየሰራ ነው>> ብሏል::
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት መረጃ እንደሚያሳየው በትግራይ ክልል የተከሰተውን ጦርነት ተከትሎ 4.5 ሚሊየን ሕዝብ አስቸኳይ የሰብዓዊ እርዳታ ያስፈልገዋል :: ነገር ግን የኢትዮጵያ መንግሥት በክልሉ የተረጂዎችን ቁጥር ከ2.5 ሚልዮን እንደማያልፍ ሲገልፅ ቆይቷል::
ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ጉዳፍ ጸጋይ በ1,500 ሜትር የቤት ውስጥ ሩጫ አዲስ የአለም ክብረወሰን አስመዘገበች:: እትሌቷ በሀገሯ ልጅ ገንዘቤ ዲባባ ተይዞ የነበረውን ክብረ ወሰን በሁለት ሰከንዶች በማሻሻል 3:53:09 በሆነ ጊዜ በመግባት ነው አሸናፊ የሆነችው:: በፈረንሳይዋ የሌቪን ከተማ ትናንት ማምሻውን በተደረገው የቤት ውስጥ የሩጫ ውድድር ሌሎች ኢትዮጵያውያንም አሸናፊዎች ሆነዋል:: አትሌት ለምለም ሀይሉ በ3,000 ሜትር ርቀት አሸናፊ ስትሆን በወንዶች ተመሳሳይ ርቀት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከ1ኛ እስከ 4ኛ ተከታትለው በመግባት እሸናፊዎች ሆነዋል:: ውድድሩን ጌትነት ዋለ 1ኛ በመውጣት አሸንፏል::
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ብልጽግና ፓርቲ በክልሉ መተከል ዞን ለተፈጠረው ሰብአዊ ቀውስ በይፋ ይቅርታ ጠየቀ:: ፓርቲው ካለፈው እሁድ ጀምሮ ሲያካሂድ የነበረውን ኮንፈረስ ዛሬ ካጠናቀቀ በኃላ በማህበራዊ ትስስር ገጹ የአቋም መግለጫ አውጥቷል፡፡
በመግለጫው "በሠላምና መረጋጋት ዕጦት ስትጠቀስ ማስተዋል በእጅጉ አሳዝኖናል፡፡በንፁሃን ዜጎቻችን ላይ የደረሰው ሞትና መፈናቀል ልብ ሰባሪ መቼም እና የትም መደገም የሌለበት አሳዛኝ ድርጊት በመሆኑ መላ የክልላችንን ኗሪዎች ይቅርታ እየጠየቅን በተግባር ለመካስ መዘጋጀታችንን እናረጋግጣለን" ብሏል፡: ነገር ግን በክልሉ የደረሰው ሰብአዊ እና ቁሳዊ ጥፋት ዝርዝርን በተመለከተ እንዲሁም ለተጎጂዎች ሊደረግ ስለሚገባ ዝርዝር የካሳ ሁኔታ ፓርቲው ያለው ነገር የለም:: ከዚህ ቀደም በዞኑ ለሚፈጠሩ ችግሮ የተለያዩ ምክንያቶች ሲሰጡ የቆዩ ሲሆን የክልሉ መንግስት በክልሉ የሚንቀሳቀሱ ተቋዋሚ ፓርቲዎችን እና ግብጽን ተጠያቂ ሲያደረጉ ነበር፡፡