DW Amharic
56.3K subscribers
4.16K photos
988 videos
69 files
15.8K links
ይህ የዶይቼ ቬለ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው። ትኩስ ዜና፣ በአበይት ፖለቲካዊ፣ ኤኮኖሚያዊ፤ ማኅበራዊ እና ባሕላዊ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩር ትንታኔ ያቀርባል።
Download Telegram
የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ኢትዮጵያ ዉስጥ የወጣው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ላይ ማሻሻያ መደረጉን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ። በማሻሻያው መሰረት በተለያዩ ምክንያቶች ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩ ዜጎችን ቀብር ሥነ ስርዓት አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ 50 ሰዉ በተገኘበት መፈጸም እንደሚቻል የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ መናገራቸዉ ተመልክቶአል። የአስክሬን የላቦራቶሪ ውጤት ከመምጣቱ በፊት የቀብር ሥነ ሥርዓት መፈጸም አይቻልም የሚለው መመሪያ መሻሻሉንም ዶክተር ሊያ ተናግረዋል።
በሌላ በኩል ከውጭ የሚገቡ ሰዎች በተለይም ወደ ሃገር ከገቡ በኋላ ባለፉት ሦስት ቀናት ውስጥ ከመጡበት ሃገር ተመርምረው ነጻ መሆናቸውን የሚያሳይ መረጃ ይዘው ከመጡ ናሙና ተወስዶ በቤታቸው 14 ቀናት እንዲቆዩ ይደረጋልም ተብሏል። ከኮሮና ተኅዋሲ ነጻ መሆናቸውን የሚያረጋገጥ ሪፖርት ይዘው ለማይመጡ መንገደኞች ደግሞ ናሙናቸው ተወስዶ ለሰባት ቀናት በለይቶ ማቆያ እንዲቆዩ እንደሚደረግም ተገልፆአል። ከዚህ ቀደም ለ14 ቀናት የነበረው አስገዳጅ የለይቶ ማቆያ ወደ 7 ቀናት ዝቅ መደረጉን የሃገር ዉስጥ የመገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። ኢትዮጵያ ዉስጥ ባለፉት 24 ሰዓታ ተጨማሪ 116 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸkል፤ የ 7 ሰዎች ህይወት ደግሞ አልፏል። በዓለም የኮሮና መረጃ መዘርዝር መሰረት 4070 ሰዎች በኮሮና መያዛቸዉ ተረጋግጦአል 72 ሰዎች በኮሮና ሕይወታቸዉ አልፎአል ፤ 934 ሰዎች ደግሞ ከኮሮና ካመጣባቸዉ ሕመም አገግመዋል።
ጀርመን እና ናሚቢያ በቅኝ ግዛት ዘመን ናሚቢያ ዉስጥ ለተፈጸሙት ወንጀሎች የጀመሩት ድርድር በሚቀጥለዉ ዓመት እንደሚጠናቀቅ ተገለፀ። ሁለቱ ሃገራት በቅኝ ግዛት ዘመን የነበረዉን ወንጀል ይቅርታ ለመጠየቅ ብሎም ካሳ ለመክፈል የሚያደርጉትን ድርድር ከጀመሩ ዓመታት ማስቆጠሩ ይታወቃል። በጉዳዩ ላይ ጀርመንን ወክለዉ የሚደራደሩት ቡድን መሪ ሩፕሬሽት ፖሌንዝ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ድርድሩ በሚቀጥለዉ የጎርጎረሳዉያን 2021 ዓመት በጀርመን የምክር ቤት ምርጫ ከመደረጉ በፌት ይጠናቀቃል ብለዉ እንደሚያምኑ ተናግረዋል። ጀርመን በሚቀጥለዉ ዓመት ቢዘገይ እስከ ጥቅምት ወር የምክር ቤት ምርጫን እንደምታካሂድ የወጣዉ መዘርዝር ያሳያል። ከጎርጎረሳዉያኑ 1904 እስከ 1908 ዓመት በዝያን ወቅት ጀርመን - ደቡብ ምዕራብ አፍሪቃ ተብላ በምትጠራዉ በዛሬዋ ናሚቢያ የጀርመን ቅኝ ገዥ ጦር በአስር ሺህ የሚቆጠሩ የናሚቢያ ተወላጆችን በተለይ የሄሬሮ እና ናማ ጎሳዎችን መግደላቸዉ በታሪክ ተፅፎአል። በጎርጎረሳዉያኑ 2017 ዓ. ም በዝያን ጊዜዉ የጀርመን ቅኝ ገዢ ጦር በናሚቢያ ሕዝብ ላይ ለተፈፀመዉ ጭፍጨፋ የጀርመን መንግሥት ለተበዳይ ወገኖች ካሳ እንዲከፍል ሲሉ የሄሬሮ እና የናማ ጎሳ ተወካዮች በኒው ዮርክ ዩኤስ አሜሪካ ክስ መመስረታቸው የሚታወስ ነዉ።
ባለፈዉ ሳምንት ዩናይትድ ስቴትስ አትላንታ ዉስጥ አንድ ጥቁር አሜሪካዊን ተኩሶ የገደለ አሜሪካዊ ፖሊስ በቁጥጥር ስር ዋለ። ጌራት ሮልፍ የተባለዉ ይህ የ 27 ዓመት አሜሪካዊ ፖሊስ ጆርጅያ ዉስጥ በሚገኝ እስር ቤት ዉስጥ እንሚገኝ የወጣዉ ዘገባ ያመለክታል። ባለፈዉ ሳምንት ጌሪታ ሮልፍ የተባለዉ የቀድሞ የፖሊስ ባልደረባ ጥቁር አሜሪካዊዉን ሬሻርድ ብሩክስን በጥይት ተኩሶ የመታዉ በቁጥጥር ስር አልዉልም ብሎ ለማምለጥ ሲሞክር ነዉ ተብሎአል። ከሮልፍ ጋር የነበረ ሌላ የፖሊስ ባልደረባ በግድያዉ ወቅት አብሮ ስለነበር በቁጥጥር ስር ከዋለ በኋላ ማስያዣ ገንዘብ ከፍሎ ከእስር መዉጣቱ ተዘግቦአል።
ቻይና ሁለት ካናዳዉያንን በስለላ ወጀል ከሰሰች። ሁለቱ የካናዳ ዜጎች በስለላ ወንጀል ተከሰዉ በእስር የተያዙት ከአንድ ዓመት ከሰባት ወር በፊት ነዉ። እንደ ፈረንሳዩ ፤ አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘገባ አንዱ ቻይና ዉስጥ ዲፕሎማት የነበረ፤ አንዱ ካናዳዊ ደግሞ በንግድ ሥራ ላይ የተሰማራ ነበር። ሁለቱ የካናዳ ዜጎች ቻይና ዉስጥ ከታሰሩ በኋላ፤ ካናዳ አንዲት ቻይናዊት፤ የአንድ ትልቅ ድርጅት ስራ አስክያጅን አስራለች። ይሁንና ቻይና ዜጋዋ ካናዳ ዉስጥ የታሰረችዉ በበቀል ነዉ ስትል ድርጊቱን እያወገዘች ነዉ። ካናዳ የታሰረችዉ ቻይናዊት ሜንግ ቮንዡ በዩናይትድ ስቴትስ ማዕቀብ ከተጣለባት ኢራን ጋር ሕግን በመጣስ የፈፀመችዉ ሥራ አለ በመባል ዩናይትድ ስቴትስ የእስር ማዘዣ የቆረጠችባት የቻይና ዜጋ ናት ተብሎአል። ይህ በቻይና እና በካናዳ የተቀሰቀሰዉ አተካራ በሁለቱ ሃገሮች መካከል ያለዉን የዲፕሎማሲ ግንኙነቱን እንዳያሻክረዉ አስግቶአል።
ኬንያ በአብላጫ ድምፅ የተመድ የፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤት የተለዋጭ አባልነት መቀመጫ አገኘች። ትናንት ምሽት ኒዮርክ ውስጥ በተከፈተው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ በተካሄደው የድምጽ አሰጣጥ ስርዓት ላይ ኬንያ እና ጅቡቲ ከምስራቅ አፍሪቃ ሃገራት የቀረቡ እጩ ሃገራት ነበሩ። በመንግሥታቱ ዋና ጽ/ቤት በተካሄደዉ በሁለተኛ ዙር ድምጽ አሰጣጥ ኬንያ ከ193 አባል ሀገራት የ129 ን ድጋፍን አግኝታ የሁለት ዓመት የተለዋጭ አባልነት መንበር ፀድቆላታል። የኮሮና ተኅዋሱ ስርጭትን ለመቆጣጠር ድምፅ አሰጣጡ ከፍተኛ የደኅንነት መመርያዎችን ተግባራዊ ያደረገም ነበር ተብሎአል። ከአራት ዓመታት በፊትም ኢትዮጵያ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ ያልሆነ አባልነት ተመርጣ ነበር። በወቅቱም ኢትዮጵያ 185 ድምፅን በማግኘት ነበር አፍሪቃ ወክላ ተለዋጭ አባል መሆንዋ ይታወሳል።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት መስራች አባል የሆነችው ኢትዮጵያ በታሪኳ ውስጥ ሦስት ጊዜ የምክር ቤቱ ቋሚ ያልሆነ መቀመጫን ማግኘትዋ የሚታወቅ ነዉ።
በአማራ ክልል በአንዳንድ አካባቢዎች ያለእድሜ ጋብቻ አስገድዶ መደፈር ቁጥሩ መጨመሩ ተነገረ። ይህ የሆነዉ የኮሮና ተኅዋሲ ቁጥጥርን ለመግታት ከቤት አትዉጡ አልያም ፤ የትምህርት ቤት መዘጋትን ተከትሎ ነዉ ተብሎአል። የአማራ ክልል ሴቶች፣ ህፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ ምክትል ኃላፊ ወ/ሮ ሰላማዊት ዓለማየሁ ለዶቼ ቬለ በሰጡት ቃለ-ምልልስ የኮሮና ቫይረስን ተከትሎ የትምህርት ቤቶችን መዘጋት ምክንያት በማድረግ በርካታ ያለእድሜ ጋብቻዎች በክልሉ መታየታቸዉ አሳሳቢ ነዉ፡፡ ምክትል ኃላፊዋ ባለፉት 3 ወራት ከ1300 በላይ ያለ እድሜ ጋብቻ ጥቆማ ደርሶዋቸዋል።
ችግሩ በዋናነት በደቡብ ጎንደር፣ ምስራቅ ጎጃምና ሰሜን ወሎ ዞኖች መበራከቱን ወ/ሮ ሰላማዊት ዓለማየሁ አብራርተዋል፡፡ ድርጊቱን ለመከላከል ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ እየተሰራ እንደሆነም ምክትል ቢሮ ኃላፊዋ አመልክተዋል፡፡
በታላቁ የሕዳሴ ግድብ ላይ የሚደረገው የሶስትዮሽ ውይይት ከስምምነት ባይደርስ እንኳ በተያዘለት ጊዜ ግድቡን በውሃ ከመሙላት የሚያግዳት ነገር እንደሌለ ኢትዮጵያ አስታወቀች። ግድቡን በውሃ ለመሙላት በተያዘለት የጊዜ ቀጠሮ መሰረት ከቀጣዩ ወር ጀምሮ እንደሚከናወን የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ ገዱ አንዳርጋቸው ተናግረዋል። በግድቡ አስተዳደር እና የውሃ ልቀት ላይ ለአንድ ሳምንት ሲደረግ የነበረው የሶስትዮሽ ውይይት ያለውጤት መጠናቀቁን ተከትሎ « ግድቡን በውሃ ለመሙላት ስምምነት ላይ መድረስ ለእኛ አስገዳጅ አይደለም »ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ መናገራቸውን አሶሽየትድ ፕረስ ዘግቧል። ከታችኛው የተፋሰሱ ሃገራት ጋር ከስምምነት ለመድረስ በብርቱ እየጣሩ መሆኑን እና የተፈለገው ውጤት አለመገኘቱንም አቶ ገዱ ገልጸዋል። «ያ ደግሞ የግድቡን ግንባታ የጊዜ ሰሌዳ የሚያፋልስ ነገር እንዲፈጠር አንፈቅድም» ብለዋል። ያልተቋጨው የሶስቱ ሃገራት ውይይት በግብጽ እና በሱዳን በኩል በጠቅላይ ሚንስትር ደረጃ ከፍ ብሎ እንዲመከርበት የሚጠይቅ ሃሳብ ቢቀርብም ኢትዮጵያ ከዚህ በላይ ገፍታ መሄድ እንደማትፈልግ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ገዱ አንዳርጋቸው አስረግጠው ተናግረዋል። እንደ የአሶሽየትድ ፕረስ ዘገባ በግድቡ ላይ የሚደረግ ውይይት ውጤት አልባ መሆን በተለይ ኢትዮጵያ እና ግብጽን ምናልባትም «ሃገራዊ ጥቅማችንን ለማስከበር» በሚል ወደ ሃይል እርምጃ ሊያመሩ ይችሉ ይሆናል የሚል የባለሞያዎች ግምት እንዳለ ጽፏል። ኢትዮጵያ ግድቡን በውሃ ለመሙላት የዝናቡ ሁኔታ እየታየ ከአራት እስከ ሰባት አመት ባለው ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ አቅዳለች።
«መንግስት እና ሸማቂ ሀይሎች ልዩነታቸውን በድርድር ይፍቱ»ምሁራን እና የሀገር ሽማግሌዎች
በምዕራብ ኦሮሚያ በመንግስት እና ሸማቂ ሀይሎች መከላከል በሚፈጠሩት ግጭቶች ምክንያት ለችግር መጋለጣቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች በተለያዩ ጊዜያት ሲገልጹ ቆይተዋል፡፡ መንግስትም ሆነም መንግስትን የሚቃወሙ የፖለቲካ ድርጅቶች ልዩነታቸውን በውይይት መፍታት አለባቸው ብለዋል።https://p.dw.com/p/3e5uf?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
ኢትዮጵያ የታላቁን ሕዳሴ ግድብ የውሃ ሙሌት ተግባራዊ ለማድረግ በያዘችው እቅድ ላይ የተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ጥበቃ ምክር ቤት ጣልቃ እንዲገባ ግብጽ ጠይቃለች። ግብጽ ዛሬ ለጸጥታው ጥበቃ ምክር ቤት ባስገባችው አቤቱታ «የግድቡ ሙሌት ተግባራዊነት የውሃ አቅርቦቴ ላይ ስጋት ደቅኖብኛል » ስትል ጠይቃለች። የግብጽ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር «በቅን ልቦና ላይ የተመሰረተ» ያለውን ውይይት በሶስቱ ሃገራት መካከል ተደርጎ ከስምምነት እስኪደረስ ምክር ቤቱ ጫና ያሳርፍ ዘንድ መጠየቁን የጀርመን ዜና ምንጭ ዘግቧል። ሃገራቱ ከመጨረሻ ስምምነት ለመድረስ ኢትዮጵያ የፖለቲካ ቁርጠኝነት አላሳየችም በማለትም ግብጽ መክሰሷን ዘገባው ጠቅሷል። እንደ የአሶሽየትድ ፕረስ ዘገባ ደግሞ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር በበኩሉ ግብጽ ጉዳዩን ወደ ጸጥታው ጥበቃ ምክር ቤት መውሰዷ ተቀባይነት የለውም ብሏል። በናይል ወንዝ የ85 በመቶ የውሃ ምንጭ ድርሻ የኢትዮጵያ ሆኖ ሳለ በእንግሊዝ የኮሎኒ ዘመን ስምምነት ግብጽ ዘመናትን የተሻገረ በውሃው የመጠቀም የአንበሳውን ድርሻ ይዛ ቆይታለች።
የኮሮና ወረርሽኝ ባሳደረው ቀውስ በኬኒያ የሚኖሩ በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ስደተኛ ቤተሰቦች ለምግብ ድጋፍ ፈላጊነት መጋለጣቸውን አለማቀፉ የስደተኞች መርጃ ተቋም አስታወቀ። ተቋሙ እንዳለው በኬንያ የጎዞ ዕገዳ መጣሉን ተከትሎ የተፈጠረው ማህበራዊ ቀውስ በርካታ ኢትዮጵያውያንን ስራ አጥ አድርጓቸው ለዕርዳታ ፈላጊነት ዳርጓዋል ብሏል። ከ40,000 በላይ ኢትዮጵያውያን በኬኒያ እንደሚገኙ የገለጸው ድርጅቱ አብዛኞቹ በመደበኛ መንገድ የሚኖሩ ባለመሆናቸው በወረርሽኙ ምክንያት ለተፈ,ጠረው ማህበራዊ ቀውስ መንግስት የሚሰጠውን ድጎማ ማግኘት የማይችሉ መሆናቸውን በስደተኞች መርጃ የምስራቅ እና የአፍሪካ ቀንድ ሃገራት ዳይሬክተር መሐመድ አበዲኬር ተናግረዋል። ይህንኑ ተከትሎ ድርጅቱ መሰረታዊ የምግብ እና መድኃኒት አቅርቦት መጀመሩን ኦል አፍሪካ ዘግቧል።። የሰብዓዊ አገልግሎት ተግባራት ላይ የተሰማሩ ድርጅቶች እና መንግስታት በወረርሽኙ ምክንያት ለቀውስ የተጋለጡ ወገኖችን ለመደገፍ በሚደረግ ጥረት ውስጥ ተሳታፊ እንዲሆኑም ነው መሐመድ አብዲ ኬር የጠየቁት።
በኢትዮጵያ በአንድ ቀን በ399 ሰዎች ላይ የኮሮና ተሕዋሲ መገኘቱን የጤና ሚኒስቴር እና የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታወቁ። በተህዋሲው የተያዙ ሰዎች ቁጥርም 4,469 ደርሷል። በዕለቱ ከበሽታው ጋር በተገናኘ የሞተ ሰው እንደሌለም ዕለታዊ ሪፖርቱ አመልክቷል። በተህዋሲው ከተያዙት ውስጥ አንዱ የውጭ ሃገር ዜጋ ነው። በተህዋሲው የተያዙት 204 ሴቶች እና 195 ወንዶች መሆናቸው ተመልክቷል። 135 ከሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ለይቶ ማቆያ ማዕከል እና 132 ሰዎች ደግሞ ከደወሌ እና ጋሊሌ ለይቶ ማቆያ ውስጥ የነበሩ ሰዎች ሲሆኑ ሰዎቹ ከየት እንደመጡ ሪፖርቱ ያለው ነገር የለም። ቀሪዎቹ 86 ሰዎች ከአዲስ አበባ ከተማ ፣ 18 ሰዎች ከአማራ ክልል፣ 14 ሰዎች ከድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ፣ 9 ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል፣ 2 ሰዎች ከትግራይ ክልል እንዲሁም አንድ አንድ ሰዎች በደቡብ ፣በሶማሌ እና በጋምቤላ ክልሎች ተገኝተዋል። በዕለቱ ሌሎች 95 ሰዎች ከበሽታው አገግመው መውጣታቸውም ታውቋል። በዚህም ባጠቃላይ ከህመሙ አገግመው የወጡ ሰዎች ቁጥር 1,122 ደርሷል።
የኤርትራውያኑ የተራዘመ ጥበቃ በጀርመን
ምንም ያኽል የለውጥ ተስፋ ቢደረግም ኤርትራ አኹንም አምባገነን ተደርጋ ነው የምትወሰደው። እንዲያም ኾኖ ስደተኞች ቤተሰቦቻቸውን ወደ ጀርመን ማምጣት ሲፈልጉ ከኤርትራ ባለስልጣናት ጋር ግንኙነት መፍጠር አለባቸው። ለብዙዎች ታዲያ ይኽ እጅግ አስቸጋሪ ነው።https://p.dw.com/p/3e4Ii ?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
የኮሮና ወረርሽኝ ባሳደረው ቀውስ በኬኒያ የሚኖሩ በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ስደተኛ ቤተሰቦች ለምግብ ድጋፍ ፈላጊነት መጋለጣቸውን አለማቀፉ የስደተኞች መርጃ ተቋም አስታወቀ። ተቋሙ እንዳለው በኬንያ የጎዞ ዕገዳ መጣሉን ተከትሎ የተፈጠረው ማህበራዊ ቀውስ በርካታ ኢትዮጵያውያንን ስራ አጥ አድርጓቸው ለዕርዳታ ፈላጊነት ዳርጓዋል ብሏል። ከ40,000 በላይ ኢትዮጵያውያን በኬኒያ እንደሚገኙ የገለጸው ድርጅቱ አብዛኞቹ በመደበኛ መንገድ የሚኖሩ ባለመሆናቸው በወረርሽኙ ምክንያት ለተፈጠረው ማህበራዊ ቀውስ መንግስት የሚሰጠውን ድጎማ ማግኘት የማይችሉ መሆናቸውን በስደተኞች መርጃ የምስራቅ እና የአፍሪካ ቀንድ ሃገራት ዳይሬክተር መሐመድ አበዲኬር ተናግረዋል። ይህንኑ ተከትሎ ድርጅቱ መሰረታዊ የምግብ እና መድኃኒት አቅርቦት መጀመሩን ኦል አፍሪካ ዘግቧል።። የሰብዓዊ አገልግሎት ተግባራት ላይ የተሰማሩ ድርጅቶች እና መንግስታት በወረርሽኙ ምክንያት ለቀውስ የተጋለጡ ወገኖችን ለመደገፍ በሚደረግ ጥረት ውስጥ ተሳታፊ እንዲሆኑም ነው መሐመድ አብዲ ኬር የጠየቁት።
የኮሮና ወረርሽኝ ወደ ከፋ የወረርሽን ደረጃ መሻገሩን የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ። ወረርሽኙ ከተቀሰቀሰ ጊዜ ጀምሮ በመላው ዓለም በአንድ ቀን ብቻ ከ150,000 በላይ ሰዎች በተህዋሲው መያዛቸውን ዋና ዳይሬክተሩ ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ተናግረዋል። በተህዋሲው ከተጠቁት ውስጥ ግምሽ ያህል የአሜሪካ ሃገራት መሆናቸውን እና የደቡባዊ እስያ ሃገራትም በከፍተኛ ደ,ረጃ መጠቃታቸውን ዶ/ር ቴድሮስ ተናግረዋል። ከደቡባዊ አሜሪካ ሃገራት በተህዋሲው በብርቱ የተጠቃችው ብራዚል በአንድ ቀን ብቻ 50,000 በተህዋሲው የተያዙ ሰዎች ተገኝተውባታል። ቁጥሩ ከእስከ ዛሬው ሁሉ ከፍተኛው ነው ተብሏል። በዚህም በብራዚል በተህዋሲው የተያዙ ሰዎችን ቁጥር ከአንድ ሚሊዮን መሻገሩን የአሶሽየትድ ፕረስ ዘገባ ያመለክታል። ኢትዮጵያ እና ደቡብ አፍሪካ ደግሞ በኮሮና በሽታ ተይዘው የመተንፈሻ መሳርያ ድጋፍ ለሚፈልጉ እና በኦክሲጂን እየታገዙ ህክምናቸውን በመከታተል ላይ ለሚገኙ ህሙማን ዴክሳሜታዞን የተሰኘውን መድኃኒት ለመስጠት መወሰናቸውን አስታውቀዋል። በመላው ዓለም በኮሮና ተህዋሲ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር ከ8.5 ሚሊዮን ሲሻገር በዚሁ በሽታ ጠንቅ የሞቱት ደግሞ እስከ ዛሬ እኩለ ቀን ድረስ ከ454, 000 በላይ ደርሷል።