• የኦሮሞ ፌድራሊስት ኮንግረስ በዚህ አመት ይካሔዳል ተብሎ በሚጠበቀው ምርጫ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥትን ሥልጣን ለመያዝ እንዳቀደ ሊቀ-መንበሩ መረራ ጉዲና ተናገሩ።
• በቡርኪና ፋሶ በዛሬው ዕለት ከመንገድ ዳር የተጠመደ ቦንብ ፈንድቶ ሰባት ሕፃናትን ጨምሮ አስራ አራት ሰላማዊ ሰዎች ተገደሉ።
• ኬንያ በሶስት ግዛቶች የአንበጣ መንጋ ለማጥፋት በአውሮፕላን መድሐኒት መርጨት ጀመረች።
• በምሥራቃዊ ሱዳን በጎሳዎች መካከል ባለፉት ሁለት ቀናት በተፈጠረ ግጭት በትንሹ ዘጠኝ ሰዎች መገደላቸውን የአገሪቱ የለውጥ አራማጆች አስታወቁ።
• ኢራን የሜጀር ጄኔራል ቃሲም ሶሌይማኒ ግድያን ለመበቀል አሜሪካናውያንን ባሉበት እንደምትቀጣ የአገሪቱ ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዥ ዛቱ።
የዕለቱን ዜና ለማድመጥ የሚከተለውን መሥፈንጠሪያ ይጫኑ፦ https://p.dw.com/p/3ViUm?maca=amh-RED-Telegram-dwcom

Deutsche Welle
የዓለም ዜና
ቻይና የኢራንን ጦር አዛዥ የገደለችው አሜሪካ ኃይሏን ያለ አግባብ መጠቀም እንድታቆም አሳሰበች። የቻይናው ውጭ ጉዳይ ምኒስትር ዋንግ ይ ከኢራኑ አቻቸው ባደረጉት የስልክ ውይይት የአሜሪካ ጦር እርምጃ የዓለም አቀፍ ግንኙነት መሠረታዊ ባህልን የሚጣረስ፤ የመካከለኛው ምሥራቅን ውጥረት የሚያባብስ ነው ሲሉ ተናግረዋል። በዕለተ አርብ ማለዳ አሜሪካ በሰው አልባ አውሮፕላን ከፈጸመችው ግድያ በኋላ በመካከለኛው ምሥራቅ የሰፈነው ውጥረት ያሳሰባቸው የጀርመን፤ የቻይናና እና የፈረንሳይ ውጭ ጉዳይ ምኒስትሮች ውይይት አድርገዋል። ኢራን እንደዛተችው የበቀል እርምጃ እንደምትወስድ የሚያምኑ ተንታኞች እና ፖለቲከኞች የሁለቱ አገሮች ፍጥጫ ከመካከለኛው ምሥራቅ ተሻግሮ ዳፋው ለዓለም እንደሚተርፍ አስግቷቸዋል።
@dwamharicbot
@dwamharicbot
ኢራን የሜጀር ጄኔራል ቃሲም ሶሌይማኒ ግድያን ለመበቀል አሜሪካናውያንን ባሉበት እንደምትቀጣ የአገሪቱ ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዥ ዛቱ። በኢራን አብዮታዊ ዘብ የኬርማን ግዛት አዛዥ ጄኔራል ጎላማሊ አቡሐሜዝ በሖርሙዝ ሰርጥ በሚተላለፉ መርከቦች ላይ ጭምር ጥቃት ሊፈጸም እንደሚችል መናገራቸውን ታንሲም የተባለው የአገሪቱ ብዙኃን መገናኛ ዘግቧል።
የአሜሪካ የጦር መርከቦች በሖርሙዝ ሰርጥ እንደሚተላለፉ ያስታወሱት የጦር አዛዡ ኢራን ጥቃት ልትፈፅምባቸው የምትችላቸው ዒላማዎች መለየቷን ተናግረዋል። የጦር አዛዡ እንዳሉት ቴል አቪቭን ጨምሮ በቀጠናው በሚገኙ 35 ዒላማዎች ላይ አገራቸው ጥቃት መፈጸም ትችላለች።
ኢራን ከግዛቷ ውጪ ለምታከናውናቸው ወታደራዊ ዘመቻዎች ኃላፊነት የተጣለበት ቁድስ የተባለ የጦር ኃይል አዛዥ የነበሩት ሶሌይማኒ ትናንት አርብ ማለዳ የተገደሉት በባግዳድ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በአሜሪካ ሰው አልባ አውሮፕላን ድብደባ ነበር።
በጥቃቱ ከኢራን የጠበቀ ቁርኝት እንዳለው የሚነገርለት ሐሽድ አል -ሳቢ የተባለ የኢራቅ ታጣቂ ቡድን አዛዥ ማሕዲ አል -ሙሓንዲስ ከነ ጠባቂዎቻቸው ተገድለዋል። በዛሬው ዕለት በኢራቋ የባግዳድ ከተማ ለሁለቱ የጦር አዛዦች በተካሔደ የሽኝት መርሐ-ግብር "ሞት ለአሜሪካ" የሚል መፈክር ከፍ ብሎ ተሰምቷል።
ግድያው እንዲፈጸም ትዕዛዝ ማስተላለፋቸውን ያረጋገጡት የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሶሌይማኒ "በአሜሪካ ዲፕሎማቶች እና ወታደሮች ላይ የከፋ ጥቃት ለመፈጸም እያሴሩ ነበር" ብለዋል። ፕሬዝዳንቱ የኢራን አብዮታዊ ዘብ እና ሶሌይማኒ ያዙት የነበረው የቁድስ ኃይል በመቶዎች ለሚቆጠሩ የአሜሪካ ወታደሮች ሞት ተጠያቂ ናቸው ብለዋል።
አያቶላ አሊ ኻሜኒን ጨምሮ የኢራን መሪዎች፤ የጦር አዛዦች እና ፖለቲከኞች ግድያውን አውግዘው የአገራቸው በቀል የከፋ እንደሚሆን ዝተዋል።
የኢራን ውጭ ጉዳይ ምኒስትር ዣቫድ ዛሪፍ ራሱን እስላማዊ መንግሥት ብሎ የሚጠራውን ታጣቂ ቡድን፣ አል-ኑስራ እና አልቃዒዳን የመሰሉ አሸባሪ ድርጅቶችን በቀጣናው በመዋጋት ስኬታማ የነበረውን ኃይል አዛዥ መግደል እጅጉን አደገኛ እና የሞኝ ተግባር ነው ሲሉ ኮንነዋል።
የኢራቅ ምክር ቤት ያደርገዋል ተብሎ በሚጠበቀው አስቸኳይ ስብሰባ የአሜሪካ እና አጋሮቿ ወታደሮች ከአገሪቱ ግዛት ለቀው እንዲወጡ ሊጠይቅ ይችላል ተብሎ ይጠበቃል። የአሜሪካ እና የኢራን ፍጥጫ በምዕራባውያኑ ጣልቃ ገብነት እና የርስ በርስ ግጭት ቀውስ ውስጥ የገባችውን ኢራቅ የሌላ ጦርነት አውድማ እንዳያደርጋት ዜጎቿ ሥጋታቸውን እየገለጹ ነው።

በቡርኪና ፋሶ በዛሬው ዕለት ከመንገድ ዳር የተጠመደ ቦንብ ፈንድቶ ሰባት ሕፃናትን ጨምሮ አስራ አራት ሰላማዊ ሰዎች ተገደሉ። በፍንዳታው አራት ሰዎች ክፉኛ መቁሰላቸውን የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዘግቧል። አደጋው የደረሰው ቡርኪና ፋሶ ከማሊ ከምትዋሰንበት ድንበር አቅራቢያ ሶሩ በተባለ ግዛት ነው። በፍንዳታው የነጎደው አውቶቡስ ተማሪዎችን የሚያጓጉዝ ነበር። በፍንዳታው የሞቱት ሕፃናት ከእረፍት ወደ ትምህርት ቤት በመመለስ ላይ ነበሩ።@dwamharicbot
ኬንያ በሶስት ግዛቶች የአንበጣ መንጋ ለማጥፋት በአውሮፕላን መድሐኒት መርጨት ጀመረች። በአውሮፕላን የመድሐኒት ርጭት የተጀመረው ዋጂር፣ መርሳቤት እና ማንዴራ በተባሉ ግዛቶች ነው። የኬንያ መንግሥት እንዳለው የአንበጣ መንጋ ከጎረቤት አገራት ወደ ኬንያ ድንበር መሻገር የጀመረው ከአንድ ሳምንት ገደማ በፊት ነው። የዓለም የምግብ እና የእርሻ ድርጅት እንዳለው በምሥራቅ አፍሪካ የተከሰተው የአንበጣ መንጋ በሶማሊያ እና በኢትዮጵያ ብቻ 70,000 ሔክታር መሬት ላይ የነበረ ሰብል አውድሟል።@dwamharicbot
በምሥራቃዊ ሱዳን በጎሳዎች መካከል ባለፉት ሁለት ቀናት በተፈጠረ ግጭት በትንሹ ዘጠኝ ሰዎች መገደላቸውን የአገሪቱ የለውጥ አራማጆች አስታወቁ።
በፖርት ሱዳን ከተማ የተፈጠረው ግጭት አንድ ሰው በስለት ተወግቶ በሞተበት የግለሰቦች ጠብ መቀስቀሱን የሱዳን የሕክምና ዶክተሮች ኮሚቴ አስታውቋል። ኮሚቴው እንዳለው በቤኒ አመር እና በኑባ ጎሳዎች መካከል በተቀሰቀሰው ግጭት ከ100 በላይ ሰዎች ቆስለዋል። ባለሥልጣናት ግጭቱን ለመቆጣጠር የጸጥታ አስከባሪዎች በከተማዋ አሰማርተዋል። ባለፈው ነሐሴ ወር በዚያው በፖርት ሱዳን በሁለቱ ጎሳዎች ግጭት ከ30 በላይ ሰዎች ተገድለው ነበር። ባለፈው ሳምንት በምዕራብ ዳርፉር የአረብ ዝርያ ባላቸው እና በሌላቸው ጎሳዎች መካከል ሌላ ግጭት ተቀስቅሷል።

የኦሮሞ ፌድራሊስት ኮንግረስ በዚህ አመት ይካሔዳል ተብሎ በሚጠበቀው ምርጫ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥትን ሥልጣን ለመያዝ እንዳቀደ ሊቀ-መንበሩ መረራ ጉዲና ተናገሩ። ፓርቲው በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ አዲሱን ፅህፈት ቤቱን ሲያስመርቅ ባደረጉት ንግግር ፕሮፌሰር መረራ ከተሳካ ኦፌኮ ብቻውን አሊያም ከሌሎች የፖለቲካ ፓርቲዎች ሥልጣን በመጋራት የኦሮሚያ ክልል መንግሥት የማቋቋም ዕቅድ እንዳለው ተናግረዋል።
«ኦፌኮ ከሌሎች የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር እያዘጋጀን ያለንው ስትራቴጂ ቢያንስ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ሥልጣንን መጋራት፤ ከተሳካልን የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥትን ማቋቋም ነው። ነገ እና ከነገ ወዲያ ሕዝባችንን ሲያስሩ እና ሲያሰቃዩ የነበሩትን በክብር ወደ ቦታቸው እንዲመለሱ ማድረግ ይኖርብናል። ከሕዝባችን ጋር ወደ ጀመርንው ትግል መግባት እንፈልጋለን ለሚሉ ደግሞ ወሳኝ ምዕራፍ ላይ እንደመሆናችን መጠን እና የብሔራችን አካል በመሆናቸው ጥሪ እናደርግላቸዋለን። ንስሀ ገብተው መመለስ ከፈለጉ እንኳን ደህና መጣችሁ ብለን እንቀበላቸዋለን። ከሀዲዎች ለነበሩት እና ዛሬም ከሀዲነታቸውን መቀጠል ለሚፈልጉ ሕዝባችንን አሳልፈው ለመስጠት መሬታችንን ለመሸጥ፤ ለማዘረፍ እና ለመዝረፍ ለሚፈልጉ የኦሮሞ አምላክ ይፋረዳችሁ እንላለን» ብለዋል።
በሌላ ዜና ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ የጠራው አስቸኳይ ጉባኤ በመቐለ ከተማ ተጀምሯል። ጉባኤው በኢሕአዴግ ውኅደት ላይ የመጨረሻ ውሳኔ እንደሚያሳልፍ ይጠበቃል።

ኢሕአዴግን የመሰረተው የቀድሞው ብአዴን/አዴፓ በመፍረሱ ሒደት እጁን በማስገባቱ ደብረ ጺዮን ገብረሚካኤል ወቀሱ። የትግራይ ክልል ምክትል ርዕ-መስተዳድር ወቀሳ የተደመጠው ህወሓት በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ እያካሔደ በሚገኘው አስቸኳይ ጉባኤ ላይ ባደረጉት ንግግር ነው።https://p.dw.com/p/3ViVP?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
Deutsche Welle
የቀድሞው ብአዴን ኢሕአዴግ ሲፈርስ እጁን በማስገባቱ የህወሓት ሊቀ-መንበር ወቀሱ
ኢሕአዴግን የመሰረተው የቀድሞው ብአዴን/አዴፓ በመፍረሱ ሒደት እጁን በማስገባቱ ደብረ ጺዮን ገብረሚካኤል ወቀሱ። የትግራይ ክልል ምክትል ርዕ-መስተዳድር ወቀሳ የተደመጠው ህወሓት በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ እያካሔደ በሚገኘው አስቸኳይ ጉባኤ ላይ ባደረጉት ንግግር ነው።
የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ( ኦፌኮ ) በቀጣዩ ምርጫ ስልጣን ለመጋራትና ጥምር መንግስት መመስረት የሚያስችል ድምጽ ለማግኘት ፣ ከተሳካም መድረክ የሚመራው መንግስት እንዲዋቀር እየሰራ መሆኑን ሊቀመንበሩ ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ለዶይቼ ቬለ ተናገሩ።
ፓርቲው በቅርቡ ወደ ፓርቲው ለተቀላቀለው ጀዋር መሃመድ እና ሌሎች ግለሰቦች ዛሬ አቀባበል ያደረገ ሲሆን ፣መንግስት ከክራይ ቤቶች ሜክሲኮ አደባባይ አካባቢ የሰጠውን ቢሮውንም አስመርቋል።https://p.dw.com/p/3ViWo?maca=amh-RED-Telegram-dwcom

«በመድረክ የሚመራ መንግሥት እንዲቋቋም እንሰራለን» የኦፌኮ ሊቀ-መንበር መረራ ጉዲና
የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ( ኦፌኮ ) በቀጣዩ ምርጫ ስልጣን ለመጋራትና ጥምር መንግስት መመስረት የሚያስችል ድምጽ ለማግኘት ፣ ከተሳካም መድረክ የሚመራው መንግስት እንዲዋቀር እየሰራ መሆኑን ሊቀመንበሩ ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ለዶይቼ ቬለ ተናገሩ።
የሊቢያ ቀውስ እና የቱርክ ጣልቃ ገብነት
አውሮጳውያንም በሊቢያ ግጭት ላይ አንድ አቋም አለመያዛቸው ሌላው መፍትሄውን ያራቀ ችግር ነው።ለምሳሌ ኢጣልያ እንደ አብዛኛዎቹ የአውሮጳ ህብረት አባል ሀገራት የሲራጅ መንግሥት ደጋፊ ናት ።ፈረንሳይ ግን ሀፍጣርን ነው የምትደግፈው።በዚህ የተነሳም ሊቢያዊው የፖለቲካ ተንታኝ ሞሀመድ ፉአድ እንዳሉት የአውሮጳ ህብረት ሀፍጣር ላይ ጫና ሊያደርግ አይችልምhttps://p.dw.com/p/3ViTD?maca=amh-RED-Telegram-dwcom

አውሮጳውያንም በሊቢያ ግጭት ላይ አንድ አቋም አለመያዛቸው ሌላው መፍትሄውን ያራቀ ችግር ነው።ለምሳሌ ኢጣልያ እንደ አብዛኛዎቹ የአውሮጳ ህብረት አባል ሀገራት የሲራጅ መንግሥት ደጋፊ ናት ።ፈረንሳይ ግን ሀፍጣርን ነው የምትደግፈው።በዚህ የተነሳም ሊቢያዊው የፖለቲካ ተንታኝ ሞሀመድ ፉአድ እንዳሉት የአውሮጳ ህብረት ሀፍጣር ላይ ጫና ሊያደርግ አይችልም
ሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ ጠቅላላ ጉባዔ የኢሕአዴግን ውህደት ወይም የብልፅግና ፓርቲን መመሥረት እንደማይቀበለው አስታወቀ።የኢሕአዴግ መስራች የሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) የስራ-አስፈፃሚና የማዕከላዊ ኮሚቴዎች የኢትዮጵያ ገዢ ፓርቲ መዋሐዱን ከዚሕ ቀደም ተቃዉመዉት ነበር።ከትናንት ጀምሮ ለሁለት ቀን የመከረዉ የሕወሓት ጠቅላላ ጉባኤ ዛሬ ስብሰባዉን ሲያጠናቅቅ ባወጣው የአቋም መግለጫ ኢህአዴግን «ተዋሐደ» ሳይሆን «በክህደት ፈረሰ» ብሎታል።«ሕወሓት ብልፅግና ከተባለው፣ 'አዲስ፣ ሕገ- ወጥና ጥገኛ' ብሎ ከተገለፀዉ ፓርቲ ጋር አይዋሃድም» ብሏል፡፡ ከኢሕአዴግ ጋር የነበረው ሀብትና ንብረት ክፍፍል በሕጋዊ መንገድ እንደሚያስኬድ ማስታወቁን የመቀሌዉ ዘጋቢያችን ሚሊዮን ኃይለስላሴ ዘግቧል።
ላሙ በተባለዉ የኬንያ ከተማ በሚገኘዉ የአሜሪካ ጦር ሠፈር ላይ የሶማሊያዉ አሸባሪ ቡድን አልሸባብ ባደረሰዉ ጥቃት የጦር አዉሮፕላኖች እና ተሽከርካሪዎች መውደማቸውን የኬኒያ ባለስልጣናት አስታወቁ።የኬንያና የአሜሪካ ወታደሮች ጥቃቱን አደረሱ ከተባሉ ኃይላት ጋር በገጠሙት ዉጊያ በትንሹ አራት ታጣቂዎች መግደላቸዉን አስታዉቀዋል።በጦር ሠፈሩ በደረሰው ጥቃት በአሜሪካም ሆነ በኬኒያ ወታደሮች ላይ ስለደረሰ ጉዳት ግን የተባለ ነገር የለም። በጦር ሠፈሩ ቁጥራቸው ያልተገለጸ የኬኒያ ወታደሮችን ጨምሮ ከአንድ መቶ የማያንሱ ወታደራዊ ሠራተኞች እንደነበሩበት የአሶሽየትድ ፕረስ ዘገባ አመልክቷል።ለጥቃቱ አልሻባብ ሃላፊነቱን ወስዷል። አልሻባብ በኬኒያ ላይ «መጠነ ሰፊ » ያለውን ጥቃት እንደሚሰነዝርም ይፋ አድርጓል።ቡድኑ በዶናልድ ትራምፕ የአስተዳደር ዘመን በተደጋጋሚ የአሜሪካ የሰዉ አልባ አዉሮፕላን (ድሮን) ጥቃት ዒላማ ሆኖ ቆይቷል።በቅርቡ በሶማሊያ መዲና የአልሸባብ ታጣቂዎች ባፈነዱት ቦምብ የ79 ሰዎች ሕይወት ካጠፋ በኋላ የአሜሪካ የጦር አውሮፕላኖች በባደረሱት ጥቃት 7 የአልሸባብ አባላት መገደላቸዉ ተነግሮ ነበር።
ሰሜናዊ ኢጣልያ ዛሬ ሌሊት በደረሰ የተሽከርካሪ አደጋ ወጣቶች እንደሆኑ የተነገረላቸው ስድስት ጀርመናውያን ሲሞቱ አስራ አንዱ ጉዳት እንደደረሰባቸው የጣልያን ባለስልጣናት አስታወቁ።
አደጋው በሰሜናዊ ምስራቅ የጣልያን ግዛት ሌሊት ሰባት ሰዓት ላይ ነው የተከሰተው። የአደጋው መንስዔም አሽከርካሪው ከልክ ያለፈ መጠጥ ጠጥቶ በማሽከርከሩ የተፈጠረ ሳይሆን እንዳልቀረ ባለስልጣናቱ ተናግረዋል።አደጋው የደረሰበት የአልቶ አድጌ ግዛት ፕሬዚዳንት አርኖ ኮምፓትሸር « አዲሱን አመት በአሰቃቂ እና አሳዛኝ ገጠመኝ ለመቀበል ተገደድን » በማለት የአደጋውን አስከፊነት ገልጸዋል።
የመኪናው አሽከርካሪ ከፍተኛ መጠን ያለው አልኮል በመጠጣት ከመጠን ባለፈ ፍጥነት ሲያሽከረክር አደጋው መከሰቱን የካራቢኔሪ ፖሊስ ባለስልጣናት ለአሶሽየትድ ፕረስ ተናግረዋል።
ጀርመንኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች በስፋት እንደሚኖሩበት በተነገረለት በዚሁ በሰሜናዊ ጣልያን በሚገኘው ራስ ገዝ ክፍለ ሃገር የጀርመን ሃገር ጎብኚዎች የሚዘወተር ስፍራ ነው።