DW Amharic
56.3K subscribers
4.17K photos
991 videos
69 files
15.9K links
ይህ የዶይቼ ቬለ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው። ትኩስ ዜና፣ በአበይት ፖለቲካዊ፣ ኤኮኖሚያዊ፤ ማኅበራዊ እና ባሕላዊ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩር ትንታኔ ያቀርባል።
Download Telegram
«የተማሪዎቹ እገታ በብልጽግና የተቀነባበረ ነው»ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት የሚለው ቡድን
ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ብሎ የሚጠራው ፣መንግሥት ሸኔ የሚለው ቡድን በቅርቡ ከኦሮምያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የደባርቅ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን እግቷል መባሉን አስተባበለ። የኦሮምያ መንግሥት ኮምኒኬሽን ቢሮ በዚህ ሳምንት አጋማሽ ባወጣው መግለጫ አሸባሪ ያለውን ቡድኑን በአጋችነት ከሷል። እገታውን በገዥው የብልጽግና ፓርቲ አባላት የተቀነባበረ ያለው ቡድኑ ግን ለእገታው «የብልጽግና ካድሬዎች ፣ሰላዮች እና የፀጥታ ኅይሎች»ያላቸውን ተጠያቂ ማድረጉን አዲስ ስታንዳርድ የተባለው የሀገር ውስጥ የህትመት መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል።
ባለፈው ሳምንት ረቡዕ ሰኔ 26 ቀን 2016 ዓ.ም. ከአማራ ክልል ተነስተው ወደ አዲስ አበባ በመጓዝ ላይ የነበሩት ከ160 በላይ ተማሪዎች የታገቱት ገርባ ጉራቻ ከተማ አቅራቢያ ነበር። የኦሮምያ መንግሥት ከ167ቱ ታጋቾች መካከል 160ውን ማስለቀቅ መቻሉን እና ቀሪዎቹንም ለማስለቀቅ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ባለፈው ረቡዕ ነበር ያስታወቀው ።ይሁንና ዶቼቬለ ያነጋገራቸው የተማሪዎቹ ጓደኞችና ቤተሰቦች ግን እስከ ትናንት ድረስ ተማሪዎቹ አልተለቀቁም ብለዋል። ከእገታ ያመለጠ አንድ ተማሪም ትናንት እንደተናገረው ተማሪዎቹ አሁንም በአጋቾች እጅ ናቸው። ቤተሰቦች እንደሚሉት የሚገኙበት ሁኔታም አሰቃቂ ነው። አንድ የታጋች ተማሪ እህት ለዶቼቬለ እንደተናገሩት አጋቾቹ ደውለውላቸው ብዙ ገንዘብ እንዲያመጡ ጠይቀዋቸዋል።
ኢትዮጵያ ያለ እድሜ ጋብቻና የሴት ልጅ ግርዛትን በመከላከል ተሸለመች

ኢትዮጵያ ያለ እድሜ ጋብቻና የሴት ልጅ ግርዛትን ለመከላከል በሰራችው ውጤታማ በተባለ ሥራ በተባበሩት መንግስታት ሥነ ሕዝብ ድርጅት እውቅና ማግኘቷን የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሀን ዘገቡ ። የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ በትናንትናው እለት በኒውዮርክ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና መስሪያ ቤት ተገኝተው ሽልማቱን መቀበላቸውን መገናኛ ብዙሀኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃን ጠቅሰው ዘግበዋል። ሚኒስትሯ እውቅናና ሽልማቱ መንግስት ለሥርዓተ-ፆታ እኩልነትና ሴቶችን ለማብቃት ያለውን ቁርጠኝነት የበለጠ የሚያጠናክር ነው ማለታቸውም ተገልጿል።
የተባበሩት መንግስታት ሥነ ህዝብ ድርጅት (UNFPA) የኢትዮጵያ ቅርንጫፍ በኢትዮጵያ ያለ እድሜ ጋብቻና የሴት ልጅ ግርዛትን ለማስወገድ የተቋቋመውን ጥምረት እንኳን ደስ አላችሁ ብሏል ። ይሁንና ግጭት ባለበት የአማራ ክልል አካባቢዎች ያለ እድሜ ጋብቻ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መምጣቱን ዶቼቬለ ከዚህ ቀደም ዘግቧል።
ለመሆኑ በየአካባቢያችሁ ያለ እድሜ ጋብቻና የሴት ልጅ ግርዛት በምን ደረጃ ላይ ይገኛል? እስቲ የምታውቁትን አካፍሉን፦
«አዲስ ፓስፖርት በሁለት ወራት እድሳት ደግሞ በአንድ ወር መስጠት ተችሏል።»የኢትዮጵያ የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት

የኢትዮጵያ የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት በአሁኑ ጊዜ ፓስፖርት ማግኘት ችግር አይደለም ሲል አስታወቀ ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡት የአገልግሎቱ ባለሥልጣናት እንዳሉት ግን ችግሩ ሰንድ አሟልቶ አለመቅረብ ነው። ይህም ለአገልግሎት መጓተትና ለብልሹ አሰራር በር መክፈቱን ገልጸዋል። በአሁኑ ጊዜ ለአገልግሎቱ ጠያቂዎች ቀጠሮ ከተሰጠበት ጊዜ ጀምሮ አዲስ ፓስፖርት በሁለት ወራት፣ እድሳት ደግሞ ከቀጠሮ ጀምሮ በአንድ ወር ውስጥ መስጠት ተችሏል ብለዋል። በ2016 ዓመተ ምህረት 1.1 ሚሊዮን ፓስፖርት መታተሙን የተናገረው አገልግሎቱ አሁንም ቢሆን ችግሩ ሙሉ በሙሉ አለመቃለሉን ጋዜጣዊ መግለጫውን የተከታተለው ሰሎሞን ሙጬ ከአዲስ አበባ ዘግቧል። ከአዲስ ፓስፖርት አሰጣጥና ከፓስፖርት እድሳት ጋር በተያያዘ እናንተስ ምን ልምድ አላችሁ? አጋሩን
የኬንያ ፖሊስ አዛዥ ሥራቸውን ለቀቁ።
በሀገሪቱ በተቀጣጠለው ፀረ መንግሥት ተቃውሞ በርካቶች መሞታቸውን ተከትሎ ጠንካራ ትችት የተሰነዘረባቸው የፖሊስ አዛዥ ጃፌት ኮሜ በዛሬው ዕለት የስንብት ደብዳቤ አስገብተዋል። የኬንያ ፕሬዝደንት ጽሕፈት ቤት የኮሜን የስንብት ደብዳቤ ፕሬዝደንት ዊልያል ሩቶ መቀበላቸውን አረጋግጧል። ጽሕፈት ቤቱ አክሎም በቦታቸው ምክትል የኬንያ ፖሊስ አዛዥ የነበሩት ዳግላስ ካንጃ መተካታቸውን አስታውቋል። በሀገሪቱ የተካሄደውን ፀረ መንግሥት ተቃውሞ ያደራጀው ጀነሬሽን Z በአጭሩ ጄን Z የተሰኘው የኬንያ ወጣቶች ስብስብ በሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ የኃይል እርምጃ ወስዷል ያሉት የኬንያ ፖሊስ አዛዥ ሥልጣናቸውን እንዲቀቁ ግፊት ሲያደርግ ነበር።
ኻርቱም፤ የሱዳን ፖሊስ የውጪ ዜጎች ከኻርቱም እንዲወጡ ማዘዙ
የሱዳን የጸጥታ ኃይሎች የውጪ ዜጎች ከዋና ከተማዋ ኻርቱም እና በዙሪያ ካሉ አካባቢዎች እንዲወጡ ትዕዛዝ ሰጡ። ፖሊስ ባወጣው ማሳሰቢያ መሠረት የውጪ ዜጎች ከተባለው የሱዳን አካባቢ ለመውጣት የሁለት ሳምንት ጊዜ ብቻ ነው የተሰጣቸው። በመንግሥት ወታደሮችና በፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች መካከል የሚካሄደው ውጊያ ተጠናክሮ በመቀጠሉ የውጪ ዜጎች ለራሳቸው ደህንነት ሲሉ አካባቢውን ለቀው መውጣት እንዳለባቸው ፖሊስ አሳስቧል። ሮይተር መገናኛ ብዙሃንን ጠቅሶ እንደዘገበው፤ በፈጥኖ ደራሹ ኃይል ውስጥ የሌላ ሀገር ቅጥር ነፍሰገዳዮች የመኖራቸው ዘገባ ይፋ ከሆነ በኋላ፤ በተለይ ከሌሎች የአፍሪቃ ሃገራት በመጡ የውጪ ዜጎች ላይ ጥላቻ ይስተዋላል። ከቀናት በፊት ሕጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸው ከ150 በላይ የውጪ ዜጎች መታሰራቸውንም አመልክቷል።
የዶቼቬለ ስርጭት ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት በአሁኑ ጊዜ ፓስፖርት ማግኘት ችግር አይደለም ሲል ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቋል።
በሺህዎች የሚቆጠሩ የሶማሌላንድ ወታደሮች ለስልጠና ኢትዮጵያ ገብተዋል፤ የሶማሊያ ወታደሮች ደግሞ ኤርትራ ውስጥ እየሰለጠኑ ነው። እነዚህና ሌሎች ዘገባዎች በዜና መጽሔት ዝግጅታችን ይቀርባሉ።
ሳምንታዊው የወጣቶች መድረክ ተደራራቢ የአካል ጉዳት ሳይበግራት ሰሞኑን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተመረቀች አንዲት ታታሪ ወጣትን ያስተዋውቀናል። የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ቅኝት ደግሞ ሰሞኑን በማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች አነጋጋሪ በነበሩ ጉዳዮች ላይ የተሰጡ አስተያየቶችን ጨምቆ ያቀርብልናል። ለሁሉም ቀጠሮአችሁ ከምሽቱ አende ሰዓት ላይ ከሚጀምረው የዶቼቬለ የአማርኛው ስርጭት ጋር ይሁን
Finland
የሐምሌ 6 ቀን 2016 ዓ/ም የዓለም ዋና ዋና ዜና • ሞቃዲሾ ውስጥ እስር ቤት ሰብረው ለማምለጥ የሞከሩ አምስት የአልሸባብ አባላት መገደላቸውን የማረሚያ ቤቱ ባለስልጣናት አስታወቁ ። በሙከራው በነበረው የተኩስ ልውውጥ ሶስት የጥበቃ አባላትም ተገድለዋል።

• በናይሮቢ በቆሻሻ መጣያ ውስጥ ተቆራርጦ የተጣሉ የሰዎች አስክሬኖች ከተገኑ በኋላ የፖሊስ እጅ ይኖርበት እንደሁ እያመረመረ መሆኑን የኬንያ ፖሊስ ተከታታይ ቡድን አስታወቀ።

• በሳህል ሃገራት ከአልቃኢዳ እና ከአይ ኤስ ጋር ግንኙነት ባላቸው አክራሪ ኃይላት የተስፋፋው ሽብርተኝነት እና የተደራጁ ወንጀሎች በቀጣናው ብርቱ ስጋት መደቀናቸው የተመድ አስታወቀ።

• እስራኤል የሃማስ ወታደራዊ ክንፍ አዛዥን ዒላማ ያደረገ የአየር ጥቃት መፈጸሟን ካስታወቀች በኋላ ሐማስ ጥቃቱን ሐሰት ነው በማለት አስተባብሏል። ሐማስ ማስተባበያውን ያወጣው የእስራኤል ባለስልጣናት የሃማስ ወታደራዊ ክንፍ አዛዥ መሐመድ ደኢፍ የአየር ጥቃት ዒላማ መደረጉን ዛሬ ካስታወቁ በኋላ ነው ።

• አሜሪካ የረዥም ርቀት ተምዘግዛጊ ሚሳኤሎቿን ጀርመን የምትተክል ከሆነ በአጸፋው የአውሮጳ ዋና ዋና ከተሞችን ዒላማ ለማድረግ እገደዳለሁ ስትል ሩስያ አስጠነቀቀች።
https://p.dw.com/p/4iFvh?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
👉🏾 @dwamharicbot
የፕሪቶሪያው ግጭት የማቆም ስምምነት የአፈጻጸም ግምገማ
በአመዛኙ በጎ ነበር በተባለው የዚህ የስትራቴጂካዊ ግምገማ ውይይት፣ በሰሜን ኢትዮጵያ ሰላም ለማስፈን በሚደረገው ጥረት ዘላቂ ድጋፍ እንደሚያደርግ የአፍሪካ ሕብረት አቋሙን ያሳየበት እንደነበርም ተገልጿል። https://p.dw.com/p/4iFb3?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
👉🏾 @dwamharicbot