DW Amharic
43.4K subscribers
3.31K photos
764 videos
69 files
13.4K links
ይህ የዶይቼ ቬለ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው። ትኩስ ዜና፣ በአበይት ፖለቲካዊ፣ ኤኮኖሚያዊ፤ ማኅበራዊ እና ባሕላዊ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩር ትንታኔ ያቀርባል።
Download Telegram
ኢትዮጵያ እና የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት አቋም
የገንዘብ ሚንሰትር አቶ አህመድ ሺዴን ጨምሮ ሌሎች ባለስልጣናት ሰሞኑን ከዓለም ባንክ (WB) እና ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት(IMF) ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር በዩናይትድ ስቴትስ ተወያይተዋል። https://p.dw.com/p/4f3RI?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
አስተያየት ለመስጠት፣ ጥቆማ ለማድረስ ይኽን ቦት ይጠቀሙ 👉🏾
የደቡብ ሱዳን ታጣቂዎች በጋምቤላ ያደረሱት ጥቃት
በጋምቤላ ክልል አኙዋ ብሔረሰብ ዞን ጆር ወረዳ ውስጥ መጋቢት 26/2016 ዓ.ም ከደቡብ ሱዳን የመጡ ታጣቂዎችና በክልሉ ውስጥ የሚገኙ ጸረ ሰላም የተባሉ ሀይሎች በመተባበር ባደረሱት ጥቃት 738 ቤቶች መቃጠላቸው ተገለጸ፡፡ https://p.dw.com/p/4f3Gd?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
አስተያየት ለመስጠት፣ ጥቆማ ለማድረስ ይኽን ቦት ይጠቀሙ 👉🏾
በኢትዮጵያ ጉዳይ የሰባት ሀገራት የጋራ ጥሪ
ኢትዮጵያ ውስጥ የተወሳሰቡ የፖለቲካ እና የጸጥታ ቀውሶችን ለመፍታት ብሎም በሀገሪቱ ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ ብቸኛው መንገድ ሁሉንም ባለድርሻ አካላት ያሳተፈ ውይይት ማድረግ መሆኑን በኢትዮጵያ የሚገኙ የ 7 ሀገራት ኤምባሲዎች በጋራ ባወጡት መግለጫ ገለፁ። https://p.dw.com/p/4f2dQ?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
አስተያየት ለመስጠት፣ ጥቆማ ለማድረስ ይኽን ቦት ይጠቀሙ 👉🏾

DW
በሃሰተኛ ሰነድ ገንዘብ በማዘዋወር የተጠረጠሩት የሃይማኖት አባት ጉዳይ
ባለፈው ሳምንት በአፍሪካ ኅብረት ቅጥር ግቢ ውስጥ በሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ በአካል በመቅረብና ከአፍሪካ ኅብረት የክፍያ ሰነድ ጋር ተመሳስለው የተዘጋጁ የተለያዩ ሐሰተኛ ሰነዶችን በመጠቀም፣ ከአፍሪካ ኅብረት የባንክ ሒሳብ ወደ ሌላ የባንክ ሒሳብ ከስድስት ሚሊዮን ዶላር በላይ ለማዘዋወር ሲሞክሩ በቁጥጥር ስር ውለዋል። https://p.dw.com/p/4f3tt?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
አስተያየት ለመስጠት፣ ጥቆማ ለማድረስ ይኽን ቦት ይጠቀሙ 👉🏾
የሚያዝያ 14 ቀን 2016 ዓ.ም የስፖርት ዘገባ
22ኛ ሣምንቱን በያዘው በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግጨዋታ በሳምንቱ መጨረሻ የተገናኙት ኢትዮጵያ ቡናና መቻል 1 - 1 በመለያየት ነጥብ ተጋርተው ውጥተዋል። እንግሊዝ ፕሪምየርሊግ በሳምንቱ መጨረሻ ጨዋታዎች ሊቨርፑል ኤቨርተን ክርስታል ፓላስ እናአስቶን ቪላ ተጋጣሚዎቻቸውን አሽንፈዋል። ኤፍ ኤ ካፕ ማንችስተር ዪናትድና ማንችስተር ሲቲ ለዋንጫ ይፋለምሉ።
https://p.dw.com/p/4f3GK?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
አስተያየት ለመስጠት፣ ጥቆማ ለማድረስ ይኽን ቦት ይጠቀሙ 👉🏾

DW
የእስራኤል እና የኢራን ቁርቁስ ወዴት ያመራል?
የኢራን እና የእስራኤልን ቁርቁስ በአንክሮ የሚከታተሉ ጉምቱ ዲፕሎማቶች እና ተንታኞች መካከለኛው ምሥራቅን የሚያዳርስ ጦርነት እንዳይቀሰቀስ ሰግተዋል። በደማስቆ የተፈጸመ ጥቃት የሁለቱን ሀገራት የበርካታ አስርት ዓመታት የእጅ አዙር ፍልሚያ ገሀድ ቢያወጣውም በመካከላቸው በቂ ቂም እና አለመተማመን አለ። https://p.dw.com/p/4f0oi ?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
አስተያየት ለመስጠት፣ ጥቆማ ለማድረስ ይኽን ቦት ይጠቀሙ 👉🏾

DW
ከጅቡቲ የባሕር ወደብ አቅራቢያ ስደተኞችን የጫነች ጀልባ ሰጥማ በደረሰው አደጋ 16 ተሰዳጆች መሞታቸው ተገለጸ። የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ድርጅት IOM ዛሬ እንዳስታወቀው 28ቱ የጀልባዋ ተሳፋሪዎች እስካሁን አልተገኙም። ጀልባዋ 77 ተሰዳጆችን አሳፍራ እንደነበር ነው IOM በኤክስ ገጹ ይፋ ባደረገው አጭር መረጃ ያመለከተው። ከተሳፋሪዎቹ ውስጥም ልጆች እንደሚገኙበትም አስታውቋል። የጅቡቲ መንግሥት የአደጋ ጊዜ ሕይወት አድን ሠራተኞች ባሕር ላይ በደረሰው አደጋ የተጎዱትን ለማዳን ጥረት እያደረጉ እንደሆነም ገልጸዋል። እንዲህ ያለ አደጋ በተሰዳጆች ላይ በተጠቀሰው አካባቢ በሁለት ሳምንት ጊዜ ውስጥ ሲደርስ ይህ ለሁለተኛ ጊዜ ነው። የዛሬ ሁለት ሳምንት በጅቡቲ የባሕር ጠረፍ አቅራቢያ በደረሰው ተመሳሳይ የጀልባ አደጋ ልጆች ጨምሮ 38 ስተደኞች ሕይወታቸውን አጥተዋል። በተያያዘ ዜና ከፈረንሳይዋ ካሌ ደሴት ወደ ብሪታንያ ለመሻገር ሲሞክሩ አምስት ስደተኞች ባሕር ላይ በደረሰ አደጋ መሞታቸው ተሰምቷል። ሟቾቹን ጨምሮ ከመቶ በላይ ስደተኞችን ጭና የነበረች መርከብ የገጠማትን አደጋ ተከትሎ የፈረንሳይ የባሕር ኃይል መርከቦች በስፍራው ደርሰው ተሳፋሪዎቹን ለማውጣት መቻላቸው ነው የተገለጸው። ተሰዳጆቹ ወደ ብሪታንያ ለመሻገር በሞከሩበት ምሽቱን የብሪታኒያ መንግሥት በሀገሪቱ የሚገኙ ሕገወጥ ስደተኞችን ወደ ሩዋንዳ ለማሻገር የሚያስችለውን ሕግ አጽድቋል።
በአማራ ክልል ሰሜን ብሔራዊ ፓርክ የተከሰተው እሳት በቁጥጥር ስር መዋሉን የሰሜን ጎንደር አስተዳደር አስታወቀ። ሚያዝያ 10 ቀን 2016 ዓ ም ከምሽቱ ሦስት ሰዓት መንስኤው እስካሁን ባልታወቀ ምክንያት በፓርኩ የተለያዩ አካባቢዎች የእሳት ቃጠሎ መነሳቱ ነው የተገለጸው። እሳቱ በአካባቢው ሕዝብ ርብርብ በቁጥጥር ስር መዋሉን ዛሬ ለዶይቼ ቬሌ የተናገሩት የሰሜን ጎንደር ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ቢምረው ካሣ በድርጊቱ የተጠረጠሩ ሦስት ሰዎች መያዛቸውን አመልክተዋል። በተጠርጣሪዎቹ ላይ በሕግ አግባብ ምርመራ ተደርጎ ጉዳዩ የሚጣራ መሆኑን፤ ቃጠሎው ያደረሰው የጉዳት መጠንም ተጣርቶ ይፋ እንደሚደረግም አስታውቀዋል። የሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ የሚገኝበት አካባቢ ሦስት ዓይነት የአየር ጠባይ እንዳለና በየዓመቱም ተመሳሳይ የእሳት አደጋ በሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ እንደሚከሰት ነው ባለሥልጣኑ የገለጹት። ከቀናት በፊት የተነሳው እሳት በፓርኩ የተለያዩ ክፍሎች ላይ እንደነበር በማመልከትም ፓርኩ ጓሳ እንደመሆኑ የተዳፈነ እሳት ንፋስ አቀጣጥሎት እንዳይነሳ ክትትል የማድረግ ጥረት መኖሩንም ተናግረዋል። የሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ በጎርጎሪዮስ የዘመን ቀመር በ1978 በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና ባህል ድርጅት ዩኔስኮ በዓለም ቅርስነት ተመዝግቧል።
ህዝባዊ ወያነ ሃርነት ትግራይ (ህወሃት) ከገዢው ፓርቲ ብልጽግና ጋር ድርድር እያካሄዱ ነው መባሉን ህወሃት አስተባበለ። ፓርቲው በፌስቡክ ማኅበራዊ መገናኛ ገጹ ዛሩ ባሰራጨው አጠር ያለ መግለጫ ህወሃት ከብልጽግና ጋር የሚያደርገው ድርድር ከፕሪቶሪያ ስምምነት በኋላ የተፈጠረውን አንጻራዊ ሰላም ለማስፋትና ለማጠናከር ያለመ ነው ብሏል። ህወሃትና እና ብልጽግና መሠረታዊ የዓላማ እና የአስተሳሰብ ልዩነት እንዳላቸው ያመለከተው ፓርቲው ልዩነታቸው እንዳለ ሆኖ ሊወያዩባቸው የሚገቡ ብዙ አጀንዳዎች እንዳሉም አመልክቷል። እንዲያም ሆኖ «ህወሃት ከብልጽግና ጋር ለመቀላቀል ንግግሮች ተጀምረዋል የሚባለው አባባል ሙሉ በሙሉ ከእውነት የራቀ ነው» ሲል ይህን በተመለከተ የሚናፈሰውን መረጃ አስተባብሏል።
ፔን አሜሪካ የተሰኘው ሃሳብን በነጻነት ለመግለጽ መብት የሚሟገተው ተቋም የዘንድሮ ዓመታዊ የሽልማት መርሃግብሩን ሰረዘ። ተቋሙ መርሃግብሩን የሰረዘው ለሽልማት ከተመረጡት ግማሽ የሚሆኑት እጩ ጸሐፊዎች ጋዛ ላይ የሚካሄደው ጦርነት በመቃወም ራሳቸውን በማግለላቸው ነው። ፔን አሜሪካ በመጪው ሳምንት ሰኞ ዕለት ኒው ዮርክ ከተማ ላይ ሊያካሂድ አቅዶት የነበረውን የዘንድሮውን የሽልማት መርሃግብር መሰረዙን ትናንት ይፋ ማድረጉ ተሰምቷል። ለዚህ መርሃግብር በእጩነት ከተመረጡት ከ61 ጸሐፊዎችና ተርጓሚዎች፤ 28 የሚሆኑት ፔን አሜሪካ ለፍልስጤማውያን ጸሐፊዎች ድጋፍ አላደረገም ማለታቸው ነው የተገለጸው። ሥራዎቻቸውን ለግምገማ ካቀረቡት መካከልም ጽሑፎቻቸው እንዲመለሱላቸው የጠየቁም አሉ ነው የተባለው።
የድርጅቱ የፕሮግራም ኃላፊ ክላሪስ ሮዛስ ሻሪፍ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ድርጅታቸው እጩዎቹ በቀረቡበት ዘርፍ ላለመሳተፍ መወሰናቸውን እንደሚያከብር ተናግረዋል። ለውድድር የቀረቡት ሥራዎች በተከበሩና እና በጠንካራ ዳኞች ከተመረጡ በኋላ ይህ ያልተጠበቀ ነገር ሂደቱ እንዲቋረጥ በማድረጉ እንደሚያዝኑም አመልክተዋል። ይህ የፔን አሜሪካ ዓመታዊ መርሃግብር ከጎርጎሪዮሳዊው 1963 ዓም ጀምሮ በተለያዩ የስነጽሁፍ ዘርፎች በልብ ወለድ፤ በግጥም፤ የልጆች ስነጽሑፍና ቴያትር ጭምር ለተዘጋጁ ግሩም ሥራዎች እውቅና ሲሰጥ ቆይቷል። የዘንድሮው የሽልማት እጩዎች ራሳቸውን ያገለሉት ጋዛ ላይ የሚደርሰውን ወታደራዊ ጥቃት እንዲቃወም ለቀረበለት ጥሪ ምላሽ ባለመስጠቱ እንደሆነ ተገልጿል። በየካቲት ወር ከ1,300 የሚበልጡ ጸሐፊዎች እና ገጣሚዎች ተቋሙ መጽሐፍት ሲታገዱ እንደሚያደርጉት ለፍልስጤማውያን የሰብአዊ መብትም ድምጽ እንዲሆን ተጠይቆ ነበር። እጩዎቹ ራሳቸውን ካገለሉ በኋላ ፔን አሜሪካ ለአሸናፊነት የተመረጡትን ሥራዎች ይፋ አድርጓል።
የተከበራችሁ የዶቼ ቬለ አድማጭ ተከታታዮች፤ በየዕለቱ የዜና እና የዜና መጽሔት ጥንቅሮቻችንን ከዩቲዩብ ቻናላችን ማግኘት እንደምትችሉ እናስታውሳችሁ።
ትክክለኛው የዶይቼ ቬለ የዩቲዩብ ቻናል ከታች ያለው ሲሆን እስከዛሬ ሰብስክራብ ያላደረጋችሁ በማድረግ በዩቲዩብም ቤተሰብ እንሁን። ለሌሎችም ማጋራት አትርሱ። እናመሰግናለን።
https://www.youtube.com/@dwamharic/videos
የተወደዳችሁ የዶቹ ቬለ አድማጮች የሚያዝያ 15 ቀን 2016 ዓ.ም. ስርጭታችን ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ በፌስቡክ በቀጥታ ይደመጣል። ለዕለቱ ካጠናቀርናቸው ዘገባዎች መካከል፤
የኦሮሚያው ግጭት እና የሰላማዊ ሰዎች አበሳ፤
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የምሥራቅ ሀረርጌ ሀገረ ስብከት በሐረር ከተማ የሚገኝ የቤተክርስትያኒቱ ይዞታ ከሕግ ውጭ እንዲፈርስ ተደርጓል ማለቱ፤
በትግራይ ክልል ከተደረገዉ ጦርነት በኋላ የሥራ አጥነት ችግር፣ ስደት እና የወጣቶች ለሱስና ሌሎች ችግሮች ተጋላጭነት እያሻቀበ መሆኑን የሚያስቃኙት ይገኙበታል።
ኦቲዝም በነርቭ ከፍተኛ ህክምና ባለሙያ እንዴት ይገለጻል? ይህንን የሚመለከት መሰናዶም ይኖረናል።
በሰዓቱ ተገንታችሁ እንድትከታተሉን ከወዲሁ የአክብሮት ግብዣችን ይድረሳችሁ።
የኬንያ የተለያዩ ግዛቶች ውስጥ የጎርፍ መጥለቅለቅ እንቅስቃሴዎችን እንደገደበ እየተነገረ ነው። በዋና ከተማ ናይሮቢ ጎዳናዎች በጎርፍ በመዋጣቸው የኤኮኖሚ መናኸሪያ የሆነችውን ከተማ የአስቸኳይ ጊዜ የአደጋ ቀጣና እንዳስመሰላት የሚወጡ መረጃዎች ያመለክታሉ። የመሠረተ ልማቶች መቋረጥ፤ የነዋሪዎች መፈናቀልና የንብረት ውድመት ከባድ የኤኮኖሚ ኪሳራ እንዳስከተለ ነው ነዋሪዎች በማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ባጋሯቸው ቪዲዮና ፎቶዎች አማካኝነት የገለጹት። የኬንያ ቀይ መስቀል ይፋ ባደረገው መሠረት እስካሁን በሀገሪቱ በጎርፍ አደጋው ምክንያት የ38 ሰዎች ሕይወት ጠፍቷል። ከ11 ሺህ በላይ ሰዎችም ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል። የኬንያ ቀይ መስቀል በመላ ሀገሪቱ ከጎርፍ አደጋ 180 ሰዎችን ማትረፍ መቻሉንም አስታውቋል። የድርጅቱ ሀላፊ ቬናንት ናዲጊላ፤ ከመጋቢት አጋማሽ ጀምሮ የወረደው ዝናብ ኬንያ ውስጥ መጠለያን ጨምሮ የሰብአዊ እርዳታ ፈላጊዎችን እየፈጠረ መሆኑን ተናግረዋል። የኬንያ መንግሥት ከባዱን ዝናብ ተከትሎ የጎርፍ አደጋ ማስጠንቀቂያ አውጇል።