DW Amharic
52.3K subscribers
3.76K photos
869 videos
69 files
14.5K links
ይህ የዶይቼ ቬለ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው። ትኩስ ዜና፣ በአበይት ፖለቲካዊ፣ ኤኮኖሚያዊ፤ ማኅበራዊ እና ባሕላዊ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩር ትንታኔ ያቀርባል።
Download Telegram
https://p.dw.com/p/4EX30?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
👉🏾 @dwamharicbot
የአርብ ሐምሌ 15 ቀን 2014 ዓ.ም. ዐርዕስተ ዜና
ሦስት የሜቲክ ከፍተኛባለስልጣናት በሙስና ወንጀል ዛሬ እሥራት ተፈረደባቸው ባለሥልጣናቱ በመርከብ ጥገና ሰበብ ገንዘብ አባክነዋል የሚል ክስ ተመስርቶባቸው ሲሟገቱ ነበር።

የሶማሊያዉ አክራሪ ደፈጣ ተዋጊ ቡድን የአሸባብ ተዋጊዎች ኢትዮጵያ ድንበር አቅራቢያ በሚገኙ ሁለት መንደሮች ላይ ባለፈው ረቡዕ በከፈቱት ጥቃት በርካታ የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ልዩ ፖሊስ ባልደረቦችን ገደሉ። ሮይተር ዜና አገልግሎት የተገደሉትን ሰዎች ቁጥር 17 ሲል፣ ቢቢሲ ግን ቁጥሩን 87 ያደርሰዋል።
ሩስያና ዩክሬን እህል ወደ ውጭ ለመላክ የዩክሬንን የጥቁር ባህር ወደብ ለመክፈት ተስማሙ። ሁለቱ ወገኖች ወደቡን ለመክፈት የተስማሙት በተመድ እና በቱርክ ሸምጋይነት ነው።ዛሬ ኢስታንቡል ቱርክ ውስጥ የደረሱበት ስምምነት በሩስያና ዩክሬን ጦርነት ምክንያት የተባባሰውን ዓለም አቀፍ የምግብ ቀውስ ማስቆም ያስችላል የሚል ተስፋ ተጥሎበታል።
ሙሉውን ዜና ለማዳመጥ ከታች የሚገኘውን የድምጽ ማዕቀፍ ይጫኑ
የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዞች በምርታቸው ባለፉት አስር ወራት 330 ሚሊዮን ዶላር አድነዋል ተባለ

በኢትዮጵያ የሚገኙ ኢንተርፕራይዞች ባለፉት አስር ወራት ባመረቱት ምርት አገሪቱ ታወጣው የነበረውን 330 ሚሊዮን ዶላር ማዳናቸውን የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት አስታወቀ። በኢትዮጵያ የሚገኙ የኢንተርፕራይዝ ተቋማት ቁጥር 53 ሺሕ መድረሱን የድርጅቱ የኮምዩንኬንሽ ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ አሸናፊ መለሰ ተናግረዋል። https://p.dw.com/p/4EYI5?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
👉🏾 @dwamharicbot
ዶክተር ዮናስ ገዳ በመርሳት በሽታ ላይ ባደረጉት ጥናት ሽልማት አሸነፉ

በአሪዞና ባሮው የነርቭ በሽታ ኢንስቲትዩት ተመራማሪ ዶክተር ዮናስ ገዳ በመርሳት በሽታ ላይ ባደረጉት ጥናት የጎርጎሮሳዊው 2022 ዓመት አሸናፊ ሆነው ተመረጡ። ጥናቱ በአሜሪካና እና በጀርመን ሳይንቲስቶችበ ትብብር የተካሄደ ሲሆን ዶክተር ዮናስ ቡድኑን መርተዋል። https://p.dw.com/p/4EYFv?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
👉🏾 @dwamharicbot
በአፍሪቃ የግብርና ምርት እንዲጨምር አፍሪቃ ህብረት አሳሰበ

አጀንዳዎችን ለማሳካት፣ የፈጠራ ችሎታ ካላቸው መንግሥታት፣ የንግድ እና የሥነ ጥበብ ሰዎች ጋር ተባባሪ መሆን ያስፈልገናል። በስሪላንካ እንዳየነው፣ ዜጎች ምግብ ካጡ እና ከተራቡ፣ አስተማማኝ የሆነ ነገር ሲያጡ እና ተስፋ ሲቆርጡ ሰላም እና ደህንነት ሊኖር አይችልም።https://p.dw.com/p/4EX59?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
👉🏾 @dwamharicbot
በሱዳን ብሉ ናይል ግዛት የተቀሰቀሰዉ የጎሳ ግጭት

በሱዳን ብሉ ናይል ግዛት በሃዉሳ እና በርታ ጎሳዎች መካከል ግጭት ተቀስቅሶ ከ100 በላይ ሰዎች ተገደሉ ወደ 200 የሚጠጉ ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል። በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተፈናቅለው አስቸኳይ የሰብአዊ እርዳታ እየጠበቁ ነዉ። የሱዳን ወታደራዊ ባለስልጣናት ውጥረት ለማርገብ ተጨማሪ ወታደሮችን ወደ አካባቢው አስፍረዋል።https://p.dw.com/p/4EX5y?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
👉🏾 @dwamharicbot
የሐምሌ 16 ቀን 1014 ዓ/ም የዓለም ዜና በድምጽ
ርዕሶቹ
አዲስ አበባ ውስጥ የሽብር ጥቃት ሊፈጽሙ ነበር ያላቸውን ከ450 በላይ ሰዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የፌደራል የጸጥታ እና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል አስታወቀ። ግብረ ኃይሉ ዛሬ ባወጣው መግለጫ መሠረት ተጠርጣሪዎቹ አል ሸባብ እና አይ ኤስ እና በሀገር ውስጥ የሚንቀሳቀሱ የአራት ታጣቂ ቡድኖች አባላት ናቸው።

በምስራቅ አፍሪቃ በዚህ ዓመት ከ50 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ለከፍተኛ የምግብ ዋስትና እጦት ሊጋለጡ እንደሚችሉ የምስራቅ አፍሪቃ የልማት በይነ መንግስታት ወይም በእንግሊዘኛ ምህጻሩ ኢጋድ አስጠነቀቀ። ኢጋድ ትናንት አርብ ባወጣው መግለጫው በሶማሊያ እና ሱዳን ከ300 ሺ በላይ ሰዎች በከፋ የረሃብ ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኙ ገልጿል።

በማሊ በዋነኛው የመንግስት ወታደራዊ የጦር ሰፈር ላይ ለደረሰው ጥቃት ከአልቃኢዳ ጋር ግንኙነት እንዳለው የሚነገርለት እስላማዊ ቡድን ኃላፊነት ወሰደ። ቡድኑ ጥቃቱን የማሊ የመንግስት ኃይሎች ከሩሲያ ቅጥረኞች ጋር በማበራቸው የተሰጠ ምላሽ ነው ብሏል።

ሩሲያ በጥቁር ባህር ዳርቻ የምትገኘውን የዩክሬኗን የወደብ ከተማ ኦዴሳን በሚሳኤል መታች። የዛሬው የሩሲያ የሚሳኤል ጥቃት የተሰማው ሞስኮ ከኪዬቭ ጋር በወደብ ከተማዋ በኩል እህል ወደ ውጭ እንዲላክ ከስምምነት ከደረሱ ከሰዓታት በኋላ ነው።

የዓለም ጤና ድርጅት በርካታ ሀገራትን እያዳረሰ የሚገኘውን የጦጣ ፈንጣጣ በሽታ «ዓለም አቀፍ ስጋት» ሆኗል ሲል አወጀ።
https://p.dw.com/p/4EYZE?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
👉🏾 @dwamharicbot
ከሶማሊያ ወደ ኢትዮጵያ ድንበር ተሻግረው ጥቃት የፈጸሙ የአል ሸባብ ታጣቂዎች "ሙሉ በሙሉ መደምሰሳቸውን" የሶማሌ ክልል የጸጥታ ምክር ቤት አስታወቀ። የክልሉ ልዩ ኃይሎች ጥቃቱ ከተፈጸመበት ዕለት ጀምሮ ባካሔዱት ኦፕሬሽን ከ100 በላይ የአልሸባብ አባላት መገደላቸውን ምክር ቤቱ ትላንት ቅዳሜ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ ሙሁሙድ ኡመር የአል ሸባብ ታጣቂዎች ተደመሰሱ ከተባለበት ሁልሁል የተባለ አካባቢ የተመለሱ የክልሉ ልዩ ኃይል አባላትን ዛሬ እሁድ "ለሌላ ግዳጅ ወደ ሀገሪቱ ድንበር" መሸኘታቸውን የሶማሌ ክልል የኮምዩንኬሽን ቢሮ አስታውቋል።
የአል ሸባብ ታጣቂ ቡድን ከኢትዮጵያ ድንበር በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኙ ሁለት የሶማሊያ መንደሮች ላይ ጥቃት የፈጸመው ባለፈው ሐምሌ 13 ቀን 2014 ነበር። የአል ሸባብ አባላት በሶማሊያዋ ባኮል ግዛት ይድ እና አቶ በተባሉት መንደሮች በፈጸመው ጥቃት ሶስት ሰላማዊ ሰዎች ጨምሮ 17 ሰዎች መገደላቸውን አንድ የኢትዮጵያ የፖሊስ ኮማንደር ለሬውተርስ ተናግረዋል። አል ሸባብ ለጥቃቱ ኃላፊነት ወስዷል።
ከአራት ቀናት በፊት በተፈጸመው ጥቃት የአል ሸባብ ታጣቂዎች አቶ በተባለው ቦታ በኩል በሶማሌ ክልል አፍዴር ዞን ገብተው እንደነበር የሶማሌ ክልል የጸጥታ ምክር ቤት ትላንት ቅዳሜ ባወጣው መግለጫ አረጋግጧል። ታጣቂዎቹ "ሁልሁል በሚባል ንዑስ ቀበሌ" ተከበው ሙሉ በሙሉ መደምሰሳቸውን የገለጸው ምክር ቤቱ አስራ ሶስት ተሽከርካሪዎች መቃጠላቸውን፣ ስንቅ እና ትጥቃቸው መማረኩንም አትቷል። ታጣቂዎቹ በኤልከሬ ወረዳ በኩል ወደ ኦሮሚያ ክልል በመሻገር የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ሸኔ ከሚሉት ታጣቂ ቡድን ጋር የመገናኘት እቅድ እንደነበረው የሶማሌ ክልል የጸጥታ ምክር ቤት ትላንት ቅዳሜ ባወጣው መግለጫ አትቷል። 👉🏾 @dwamharicbot
ሩሲያ በጥቁር ባህር ዳርቻ በሚገኘው የኦዴሳ ወደብ ላይ ትላንት ቅዳሜ የፈጸመችው የሚሳይል ድብደባ አሜሪካ ለዩክሬን በሰጠቻቸው የጦር መሳሪያዎች ላይ ያነጣጠረ እንደነበር አስታወቀች። ሩሲያ የዩክሬን እህል በጥቁር ባህር ዳርቻ በሚገኙ ወደቦች አማካኝነት ለዓለም ገበያ እንዲቀርብ የሚፈቅድ ስምምነት ከፈረመች ከሰዓታት በኋላ የፈጸመችው ጥቃት ከፍተኛ ውግዘት አስከትሎባታል። ሩሲያ አራት ሚሳይሎች የተኮሰች ሲሆን ሁለቱ በዩክሬን ኃይሎች ሲከሽፉ የተቀሩት ሁለት ሚሳይሎች በኦዴሳ ወደብ ከፍተኛ ጉዳት አድርሰዋል።
የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር በዛሬው ዕለት ይፋ ባደረገው መግለጫ ሚሳይሎቹ በመርከብ ጥገና ማዕከል ላይ የተተኮሱ መሆናቸውን ገልጿል። በጥቃቱ የዩክሬን የጦር መርከብ እና አሜሪካ ለዩክሬን የሰጠቻቸው ሐርፐን ሚሳይሎች የተከማቹበት መጋዘን መውደሙን የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል።
ሩሲያ ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት፣ ከዩክሬን እና ከቱርክ ባለሙያዎች ጋር በተፈራረመችው ስምምነት እህል እና ሌሎች ሸቀጦች የጫኑ መርከቦች በሚያልፉበት የባህር ወሽመጥ ላይ ላለመተኮስ ተስማምታ እንደነበር የጀርመን ዜና አገልግሎት ዘግቧል። የዩክሬን ፕሬዝደንት ቮሎዶሚር ዜሌንስኪ ጥቃቱን አውግዘው የሩሲያ እርምጃ ውይይት መፍትሔ እንደማያመጣ ማሳያ ነው ብለዋል። 👉🏾 @dwamharicbot
ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ ከአንድ ሺሕ በላይ ስደተኞች ትላንት ቅዳሜ በጥቂት ሰዓታት ውስጥ ጣልያን መድረሳቸውን የአገሪቱ ባለሥልጣናት እና የግብረ ሰናይ ድርጅቶች አስታወቁ። ሌሎች በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የግብረ ሰናይ ድርጅቶች ያሰማሯቸው መርከቦች ከታደጓቸው በኋላ የሚቀበላቸው ወደቦች በመጠበቅ ላይ ናቸው።

ከታኅሳስ 23 እስከ ሐምሌ 15 ቀን 2014 ባሉት ጊዜያት 34,000 ሰዎች የሜድትራኒያን ባህርን በማቋረጥ ጣልያን መድረሳቸውን የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዘግቧል። ይኸ ቁጥር ባለፉት ሁለት ዓመታት በተመሳሳይ ወቅት ጣልያን ከገቡ ሰዎች ቁጥር እንደሚበልጥ የጣልያን አገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

በአሳ ማስገሪያ ጀልባዎች የሜድትራኒያን ባህርን ለማቋረጥ ጥረት በማድረግ ላይ የነበሩ 600 ሰዎችን ትላንት ቅዳሜ የንግድ መርከቦች እና የባህር ጠረፍ ጠባቂዎች በደቡብ ጣልያን ከምትገኘው ካላብሪያ ደሴት ታድገዋል። ሰዎቹ በሲሲሊ በሚገኙ የተለያዩ ወደቦች መውረዳቸውን የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዘግቧል። የጣልያን ባለሥልጣናት እስካሁን ባልታወቀ ምክንያት ሕይወታቸው ያለፈ የአምስት ስደተኞች አስከሬኖች አግኝተዋል።

ከቱኒዝያ እና ከሊቢያ ትላንት ቅዳሜ በተነሱ አስራ አምስት ጀልባዎች ኢትዮጵያን፣ ሱዳናውያን፣ ሶማሊያውያንን ጨምሮ የተለያዩ አገሮች ዜጎች ከጣልያኗ ላምፔዱሳ ደሴት ደርሰዋል። የጣልያን መገናኛ ብዙኃን እንደዘገቡት በላምፔዱሳ የሚገኙ የስደተኛ መቀበያዎች ተጨናንቀዋል። 👉🏾 @dwamharicbot
በመጪው የኬንያ ምርጫ ዋንኛ ተፎካካሪ የሆኑት ራይላ ኦዲንጋ በእጩ ፕሬዝዳንቶች መካከል በሚደረግ ክርክር እንደማይሳተፉ አስታወቁ። ኦዲንጋ ተፎካካሪያቸው በእጩዎች መካከል ሊደረግ በሚችል ክርክር የሙስና ጉዳይ እንዳይነሳ ለማድረግ እየሞከሩ ነው ሲሉ ከሰዋል።
የቀድሞው ጠቅላይ ምኒስትር ራይላ ኦዲንጋ እና ምክትል ፕሬዝደንት ዊሊያም ሩቶ ሐምሌ 25 ቀን 2014 በሚደረገው የኬንያ ምርጫ ዋንኛ ተፎካካሪ ናቸው።
የ77 ዓመቱ ኦዲንጋ ዛሬ እሁድ ባወጡት መግለጫ ግን በመጪው ማክሰኞ በእጩዎች መካከል ሊካሔድ ታቅዶ በነበረው ክርክር እንደማይሳተፉ አስታውቀዋል። የኦዲንጋን የምረጡኝ ዘመቻ የሚያከናውነው ቡድን ቃል አቀባይ ዊሊያም ሩቶ በቁልፍ ጉዳዮች ላይ የሚደረግን ክርክር ገሸሽ ለማድረግ እየሞከሩ ነው ሲሉ ከሰዋል። የኦዲንጋ ቃል አቀባይ በመግለጫቸው ሩቶ "ክርክሩ የኬንያ ቁልፍ የህልውና ጥያቄዎች በሆኑት ሙስና፣ ታማኝነት፣ ሥነ-ምግባር እና የአስተዳደር ጉዳዮች ላይ እንዳያተኩር ጠይቀዋል" ብለዋል።
"መሠረታዊ ጨዋነት ይጎድላቸዋል" ካሏቸው ዊሊያም ሩቶ ጋር የተጠቀሱት ጉዳዮች የማይካተቱበትን የክርክር መድረክ መጋራት ባለመፈለጋቸው ኦዲንጋ እንደማይሳተፉ መግለጫው ጠቁሟል። በምትኩ ኦዲንጋ በቴሌቭዥን በሚተላለፍ ውይይት የኬንያ መራጮች ለሚያነሷቸው ጥያቄዎች መልስ ይሰጣሉ ተብሏል። በሥልጣን ላይ የሚገኙት ኡኹሩ ኬንያታ የአገራቸው ዜጎች ድምጻቸውን ለምክትላቸው ዊሊያም ሩቶ እንዲሰጡ ጥሪ አቅርበዋል። ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ ለኬንያ ፕሬዝደንትነት ተወዳድረው ያልተሳካላቸው ራይላ ኦዲንጋ የወርሀ ሐምሌው ምርጫ የመጨረሻቸው ሊሆን ይችላል። 👉🏾 @dwamharicbot
ሩሲያ ለግብጽ ለመሸጥ ቃል የገባችውን እህል ማቅረብ እንደምትቀጥል የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላብሮቭ ማስተማመኛ ሰጡ። ውጭ ጉዳይ ምኒስትሩ ከሩሲያ እና ከዩክሬን ከፍ ያለ መጠን ያለው ስንዴ ለምትሸምተው አገር ማስተማመኛ የሰጡት የአፍሪካ ጉብኝታቸውን ዛሬ በግብጽ ሲጀምሩ ነው። ትላንት ቅዳሜ ወደ ካይሮ የተጓዙት ውጭ ጉዳይ ምኒስትሩ በዛሬው ዕለት ከግብጽ ፕሬዝደንት አብዱልፋታኅ አል ሲሲ ተገናኝተው ተነጋግረዋል።
ሰርጌይ ላቭሮቭ ከግብጽ ውጭ ጉዳይ ምኒስትር ሳሜህ ሽኩሪ ጋር በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ "የሩሲያ እህል ላኪዎች የገቡትን ውል እንደሚያከብሩ ማረጋገጫ ሰጥተናል" ሲሉ ተደምጠዋል። ግብጽ ባለፈው ዓመት ከዓለም ገበያ ከሸመተችው ስንዴ 80 በመቶው በሩሲያ እና በዩክሬን የተመረተ ነው። በጉዳዩ ላይ ከግብጽ አቻቸው መነጋገራቸውን የገለጹት ላቭሮቭ የሚመለከታቸው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ተጨማሪ ግንኙነት እንዲያደርጉ መስማማታቸውን ገልጸዋል።
የሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት ሁለቱ አገሮች ምርቶቻቸውን ለዓለም ገበያ የሚያቀርቡባቸውን የመርከብ እንቅስቃሴ በማስተጓጎል ብርቱ ጫና አሳድሯል። ጦርነቱ በዓለም ገበያ የሸቀጦች ዋጋ እንዲንር በማድረጉ የአፍሪካ አገራት የዳፋው ተቋዳሽ ናቸው። ዓለም አቀፍ ተቋማት ትኩረታቸውን በጦርነቱ ምክንያት ከዩክሬን የተፈናቀሉ ዜጎችን ወደ ማገዝ በማዞራቸው በአፍሪካ እና በመካከለኛው ምሥራቅ አገራት የሚገኙ የተቸገሩ ዜጎች የሚያገኙት እርዳታ ተመናምኗል።
ላብሮቭ ከግብጽ በተጨማሪ ኢትዮጵያ፣ ዩጋንዳ እና ኮንጎን ይጎበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል። የላብሮቭ የአፍሪካ ጉብኝት ሩሲያ ዩክሬንን በመውረሯ የገጠማትን ዲፕሊማሲያዊ መገለል ለመስበር የሚደረግ ጥረት አካል እንደሆነ አሶሼትድ ፕሬስ ዘግቧል።👉🏾 @dwamharicbot
በአሜሪካዋ ኦሬጎን በመካሔድ ላይ በሚገኘው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ጸጋይ በ5 ሺሕ ሜትር በተካሔደ ውድድር የወርቅ ሜዳልያ ባለቤት ሆነች። ጉዳፍ ውድድሩን በ14 ደቂቃ ከ46 ሰከንድ ከ29 ማይክሮ ሰከንድ ስታጠናቅቅ ኬንያዊቷ ቢያትሪስ ቼቤት ሁለተኛ ተከትላት ገብታለች። ሌላዋ ኢትዮጵያዊት ዳዊት ስዩም ሶስተኛ ሆና የነሐስ ሜዳልያ ስታገኝ ለተሰንበት ግደይ አምስተኛ ሆና አጠናቃለች።

የትላትናው ወርቅ ጉዳፍ በኦሬጎን በመካሔድ ላይ በሚገኘው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ያሸነፈችው ሁለተኛ ሜዳልያ ነው። የ25 ዓመቷ አትሌት በ1500 ሜትር ተወዳድራ የነሐስ ሜዳልያ ባለቤት መሆኗ አይዘነጋም።

ዛሬ በሚጠናቀቀው ሻምፒዮና በወንዶች የ5,000 ሜትር የሩጫ ውድድር ሙክታር ኢድሪስ፣ ሰለሞን ባረጋ እና ዮሚፍ ቀጀልቻ ኢትዮጵያን ወክለው ይወዳደራሉ። በሴቶች የ800 ሜትር የፍጻሜ ውድድር ድርቤ ወልተጂ ተሳታፊ ነች።

ኢትዮጵያ በሻምፒዮናው እስካሁን 4 የወርቅ፣ 4 የብር፣ 2 የነሐስ በአጠቃላይ 10 ሜዳልያዎች አግኝታለች። አሜሪካ፣ ኢትዮጵያ እና ኬንያ በሻምፒዮናው የሜዳልያ ሰንጠረዥ ከአንድ እስከ ሶስት ያለውን ደረጃ ይዘዋል።👉🏾 @dwamharicbot
የሐምሌ 17 ቀን 2014 የዓለም ዜና
• ከሶማሊያ ወደ ኢትዮጵያ ድንበር ተሻግረው ጥቃት የፈጸሙ የአል ሸባብ ታጣቂዎች "ሙሉ በሙሉ መደምሰሳቸውን" የሶማሌ ክልል የጸጥታ ምክር ቤት አስታወቀ። የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ ሙሁሙድ ኡመር የክልሉ ልዩ ኃይል አባላትን ዛሬ እሁድ "ለሌላ ግዳጅ ወደ ሀገሪቱ ድንበር" መሸኘታቸውን የሶማሌ ክልል የኮምዩንኬሽን ቢሮ አስታውቋል።
• በመጪው የኬንያ ምርጫ ዋንኛ ተፎካካሪ የሆኑት ራይላ ኦዲንጋ በእጩ ፕሬዝዳንቶች መካከል በሚደረግ ክርክር እንደማይሳተፉ አስታወቁ።
• ሩሲያ ለግብጽ ለመሸጥ ቃል የገባችውን እህል ማቅረብ እንደምትቀጥል የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላብሮቭ ማስተማመኛ ሰጡ። ውጭ ጉዳይ ምኒስትሩ ከሩሲያ እና ከዩክሬን ከፍ ያለ መጠን ያለው ስንዴ ለምትሸምተው አገር ማስተማመኛ የሰጡት የአፍሪካ ጉብኝታቸውን ዛሬ በግብጽ ሲጀምሩ ነው።
• ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ ከአንድ ሺሕ በላይ ስደተኞች ትላንት ቅዳሜ በጥቂት ሰዓታት ውስጥ ጣልያን መድረሳቸውን የአገሪቱ ባለሥልጣናት እና የግብረ ሰናይ ድርጅቶች አስታወቁ።
• በአሜሪካዋ ኦሬጎን በመካሔድ ላይ በሚገኘው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ጸጋይ በ5 ሺሕ ሜትር በተካሔደ ውድድር የወርቅ ሜዳልያ ባለቤት ሆነች። ዛሬ በሚጠናቀቀው ሻምፒዮና በወንዶች የ5,000 ሜትር እና በሴቶች 800 ሜትር ኢትዮጵያውያን የሚሳተፉባቸው ውድድሮች ለሊቱን ይካሔዳሉ
ዜናውን ለማድመጥ የድምጽ ማዕቀፉን ይጫኑ፦ https://p.dw.com/p/4EZov?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
👉🏾 @dwamharicbot
የሰዎች ለሰዎች የአግሮ እና ቴክኖሎጂ ኮሌጅ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 116 ተማሪዎች አስመረቀ። በኢትዮጵያ ጀርመን አምባሳደር ስቴፈን ኦውር የሰዎች ለሰዎች የግብረ ሰናይ ድርጅት ከጀርመን መንግስት በመተባበር በአነስተኛ የእርሻ መሬቶች ላይ ምርታማነትን ለማሳደግ በሚያስችሉ ማዕከላት ስራዎችን እያከናወነ መሆኑን ተናግረዋል https://p.dw.com/p/4EZbm?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
👉🏾 @dwamharicbot