DW Amharic
44K subscribers
3.49K photos
800 videos
69 files
13.7K links
ይህ የዶይቼ ቬለ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው። ትኩስ ዜና፣ በአበይት ፖለቲካዊ፣ ኤኮኖሚያዊ፤ ማኅበራዊ እና ባሕላዊ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩር ትንታኔ ያቀርባል።
Download Telegram
በምርጫ 2013 ያልተሳተፉ የፖለቲካ ፓርቲዎች ስለ አዲሱ መንግሥት የሰጡት አስተያየት
በምርጫ 2013 ያልተሳተፉት የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግሬስ (ኦፌኮ)ና በአቶ ዳውድ ኢብሳ የሚመራው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ባለስልጣናት በአገሪቱ ዴሞክራሲና ሰላምን ከመሰረቱ ለማጠናከር ሁሉን አቀፍ ውይይት ያሻል ብለዋል፡፡የገዢው ፓርቲ ባለስልጣን ደግሞ መንግስት ሰላምን ከሚፈልግ የትኛውም አካል ጋር ለመደራደር ዝግጁ ነው ብለዋል፡፡https://p.dw.com/p/41PnZ?maca=amh-RED-Telegram-dwcom@dwamharicbot
የመጀመሪያው የወባ መከላከያ ክትባት ስራ ላይ እንዲውል መፈቀዱ
የድርጅቱ ዋና ፀሀፊ ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም ክትባቱ ስራ ላይ እንዲውል የተፈቀደበትን ወቅት ታሪካዊ ብለውታል። ድርጅቱ እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው ከጎርጎሮሳዊው 2019 አንስቶ በመካሄድ ላይ በነበረ ምርምር በጋና በኬንያ እና በማላዊ ከ800 ሺህ በላይ በሚሆኑ ህጻናት ላይ ከተካሄደ ክትትል በኋላ መሆኑን አስታውቋል።https://p.dw.com/p/41Pny?maca=amh-RED-Telegram-dwcom@dwamharicbot
የአውሮጳ ኅብረት ፓርላማ በመጪዎቹ ሶስት ሳምንታት ሁኔታዎች ካልተሻሻሉ በኢትዮጵያ መንግሥትና በህወሓት አመራሮች ላይ ማዕቀብ እንደሚጥል አስጠነቀቀ። ስለ ሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ትናንት የተነጋገረው የአውሮጳ ኅብረት ፓርላማ በኢትዮጵያ መንግሥት እና በህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ «ህወሓት » መካከል የሚካሄደዉ ጦርነት በአስቸኳይ እንዲቆምም ጠይቋል።ህወሓት ከአማራ እና ከአፋር ክልል በአስቸኳይ እንዲወጣና፤ የአማራ ክልላዊ መንግሥትም ምዕራብ ትግራይ ካሉት አካባቢ ጦሩን እንዲያስወጣም ጥሪ አቅርቧል።
የዘንድሮው የኖቤል የሰላም ሽልማት ለሁለት ጋዜጠኞች ተሰጠ። ፊሊፒናዊቷ ጋዜጠኛ ማርያ ርየሳና ሩስያዊው ጋዜጠኛ ዲሚትሪ ሙራቶቭ ሽልማቱ መመረጣቸውን የተናገረው የኖቤል ኮሚቴ ሽልማቱ የተሰጣቸው ሃሳብን በነፃ ለመግለጽ ላደረጉት ትግል መሆኑን አስታውቋል።

የተመድ የየሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን አጣሪ ቡድን በየመን ጦርነት በተፈጸሙ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች ላይ የሚያካሄደውን ምርመራ እንዲቀጥል የቀረበው የውሳኔ ሃሳብ ተቀባይነት ሳያገኝ ቀረ። ትናንት ጄኔቫ ውስጥ በተካሄደ ስብሰባ በውሳኔ ሀሳቡ ላይ በተሰጠ ድምጽ ምርመራው ለሁለት ዓመታት እንዲቀጥል የሚቃወመው ድምጽ ለጥቂት በልጦ ውሳኔ ሀሳቡ ሳያልፍ ቀርቷል።
https://p.dw.com/p/41STC?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
በድሬደዋ የደንጊ በሽታ ወረርሽኝ ተከሰተ
በድሬደዋ ከተማ የደንጊ በሽታ ወረርሽኝ መከሰቱን የአስተዳደሩ ጤና ቢሮ ኃላፊ ለዶይቼ ቬለ ተናገሩ። የድሬደዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ ኃላፊ ለምለም በዛብህ እንዳሉት ለ87 ናሙናዎች ምርመራ ተደርጎ አራት ሰዎች በደንጊ መያዛቸው ተረጋግጧል። ከመስከረም እስከ ኅዳር ባሉት ወራት በድሬደዋ ቺኩንጉንያ፣ ደንጊ እና ወባ በሽታዎች በወረርሽኝ መልክ ይከሰታሉ https://p.dw.com/p/41TPj?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
የፀጥታው ምክር ቤት ዳግም ስለ ኢትዮጵያ
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ኢትዮጵያ ባባረረቻቸው የመንግሥታቱ ድርጅት ሠራተኞች ጉዳይ ላይ ረቡዕ በአስቸኳይ ተሰብስቧል። ዓለም አቀፍ ድርጅቱ በኢትዮጵያ ጉዳይ ከአንድ ሳምንት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ለመምከር ሲሰሰበሰብ ሁለተኛው ነው። በስብሰባዎቹ የፀጥታው ምክር ቤት የተከፋፈለ ሐሳብ ተንጸባርቆበታል።https://p.dw.com/p/41S5I?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
የቅጥር ተግዳሮት በአፍሪቃ
የሥራ አጥነት ቁጥር አፍሪቃ ውስጥ ጨምሯል። በተለይ ወጣቶች ሥራ ማግኘት ይቸገራሉ። ሆኖም ግን ኢ-መደበኛ ዘርፎች እያበቡ ነው። አስተሳሰብን መቀየር ወሳኝ ነው ይላል አንድ የቅርብ ጊዜ ጥናት። https://p.dw.com/p/41S7q?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
የመስከረም 29/2014 ዓ/ም የዓለም ዜና በድምጽ
ርዕሶቹ
• የኢትዮጵያ መንግስት ወታደሮች እና አጋር ኃይሎች በአማራ ክልል የትግራይ ኃይሎች ላይ «መጠነ ሰፊ የአየር እና የምድር ጥቃት » መሰንዘር መጀመራቸውን የተራድዖ ድርጅቶች እና የትግራይ ኃይሎች አስታወቁ። የጥቃቱን መጀመር ከኢትዮጵያ መንግስትም ሆነ በጦርነቱ ከሚሳተፉ የክልል ባለስልጣናት በኩል እስካሁን ማረጋገጫ አልተገኘም።
• የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝብ ክልልን ለመመስረት አልያም በደቡብ ክልል ስር ለመተዳደር በተደረገው የሕዝበ ውሳኔ አዲሱን ክልል በደገፍ የተሰጠው ድምጽ በአብላጫ ማሸነፉን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ።
• በጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ የተሰየመው የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ ፅ/ቤት ሓላፊ የነበሩት ገብረመስቀል ካሳ ከሀገር ወጥተው ጥገኝነት ጠየቁ። ገብረመስቀል ካሳ በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ውስጥ በስራ ላይ በነበሩበት ወቅት የኤርትራ ወታደሮች ክልሉን ለቀው እንዲወጡ በግልጽ ይጠይቁ እንደነበር ተገልጿል።
• በሊቢያ መዲና ትሪፖሊ በስደተኞች በተጨናነቁ እስር ቤቶች ጣባቂዎች በከፈቱት ተኩስ ስድስት ስደተኞች ተገደሉ። በእስር ቤቱ ከነበረው የከፋ መጨናነቅ ለማምለጥ በተቀሰቀሰ ትርምስ ከተገደሉት በተጨማሪ በሌሎች ሃያ ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱን ዓለማቀፉ የስደተኞች ጉዳይ ድርጅት (አይ ኦ ኤም) አስታውቋል።
https://p.dw.com/p/41ToS?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝበ-ውሳኔ አስራ አንደኛው ክልል እንዲቋቋም ወሰነ
በደቡብ ክልል አምስት ዞኖች እና አንድ ልዩ ወረዳ የተካሔደው ሕዝበ-ውሳኔ አስራ አንደኛው የኢትዮጵያ ክልል እንዲቋቋም ወሰነ። ምዕራብ ኦሞ፣ ቤንች ሸኮ፣ ካፋ፣ ዳውሮ፣ ሸካ ዞኖችና ኮንታ ልዩ ወረዳ "ከደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ወጥተው የጋራ አንድ ክልል መመሥረታቸውን እደግፋለሁ" የሚለው አማራጭ 1 ሚሊዮን 221092 ድምጾች አግኝቷል https://p.dw.com/p/41TnI?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
የቻይና መንግሥት የታይዋኗ ፕሬዝደንት ሳይ ኢንግ ዌን የአገራቸው ብሔራዊ ቀን ሲከበር ያደረጉት ንግግር "ለጠብ የሚጋብዝ እና የተዛባ" ሲል አወገዘ። ታይዋን ነጻነቷን ለማግኘት የምታደርገው ግፊት የድርድርን በር ይዘጋል በማለት በቻይና መንግሥት የታይዋን ጉዳዮች ቢሮ አስጠንቅቋል።

ፕሬዝደንት ሳይ ኢንግ ዌን ዛሬ ጠዋት "ነፃነትም ሆነ ዴሞክራሲን አያመጣም" ያሉት እና "ቻይና የቀየሰችውን መንገድ፤ ማንም በኃይል በታይዋን ላይ እንዳይጭን ለማረጋገጥ አገራቸው የመከላከያ ኃይሏን ማጠናከር እንደምትቀጥል" ተናግረው ነበር። አገራቸው ከቻይና ያላት ወዳጅነት ቢሻሻል የሚል ተስፋ እንዳላቸው የጠቆሙት ፕሬዝደንቷ "በችኮላ እርምጃ አንወስድም። ነገር ግን የታይዋን ሕዝብ ለጫና እንደማይንበረከክ የተሳሳተ እምነት ሊኖር አይገባም" ብለዋል።

ሁለተኛው የዓለም ጦርነት ካበቃ በኋላ ላለፉት 72 ገደማ አመታት ቻይና እና ታይዋን በተለያዩ መንግሥታት ሲተዳደሩ ቆይተዋል። ይሁንና ከአምስት አመታት በፊት ሳይ ኢንግ ዌን በፕሬዝደንትነት ሲመረጡ የቻይናው ፕሬዝደንት ሺ ዢንፒንግ በሁለቱ አገሮች መካከል የነበረውን ይፋዊ ግንኙነት በማቋረጣቸው ውጥረት ነግሷል።

ቻይና 23 ሚሊዮን ገደማ ዜጎች ያላት ታይዋን የዋናው ቻይና አካል ነች የሚል አቋም ያላት ሲሆን ይኸን ለማረጋገጥ ኃይልን ጨምሮ ማናቸውንም አማራጮች ልትጠቀም እንደምትችል አስታውቃለች። ፕሬዝደንት ሺ ዢንፒንግ ትናንት ቅዳሜ ባደረጉት ንግግር "የአገራችን የተሟላ ውህደት እውን ሊሆን ይችላል" ብለው ነበር። የሺ መንግሥት በታይዋን ላይ ከሚያሳድረው ምጣኔ-ሐብታዊ፣ ፖለቲካዊ እና ዲፕሎማሲያዊ ጫና ባሻገር የታይዋንን የአየር ክልል በተደጋጋሚ የሚተላለፉት የቻይና ተዋጊ የጦር ጀቶች ጉዳይ ሁለቱን አገሮች ወደ ከፋ ግጭት ሊገፋቸው ይችላል የሚል ሥጋት ፈጥሯል። 👉🏾 @dwamharicbot
ባለፉት አራት ሣምንታት 946 ሰዎች በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ሳቢያ ሕይወታቸውን እንዳጡ የጤና ምኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ተናገሩ። ዶክተር ሊያ በትናንትናው ዕለት ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት ባለፈው አንድ ሣምንት ብቻ 308 ሰዎች በወረርሽኙ ሳቢያ ለሞት ተዳርገዋል። ይኸ ወረርሽኙ ከተቀሰቀሰ ወዲህ ከፍተኛው ቁጥር ነው። በዶክተር ሊያ ማብራሪያ መሠረት ባለፈው አንድ ሣምንት በአማካኝ 44 ሰዎች በየቀኑ ሞተዋል። ከሰኔ አጋማሽ እስከ ነሐሴ አጋማሽ ባለው ጊዜ ሕይወታቸውን ካጡ መካከል "አንድ የመጀመርያ [የኮቪድ-19 መከላከያ] ክትባት" የወሰዱ እንደሚገኙበት የገለጹት የጤና ምኒስትሯ የተቀሩት ያልተከተቡ መሆናቸውን ተናግረዋል።
የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ከተቀሰቀሰ ጀምሮ እስከ ትናንት መስከረም 29 ቀን 2014 ዓ.ም. ድረስ 5 ሺሕ 950 ሰዎች ሕይወታቸውን እንዳጡ የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስቴር እና የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዕለታዊ መረጃ ያሳያል።
ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ 6 ሺሕ 524 የላቦራቶሪ ናሙና ምርመራ 608 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። ይኸ ከተደረገው ምርመራ አኳያ አስር በመቶ ገደማ መሆኑ ነው። በኢትዮጵያ በአጠቃላይ እስካሁን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 354 ሺሕ 033 ደርሷል። እንደ አብዛኞቹ ደሐ አገሮች የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባት ፍትሐዊ ሥርጭት የሚፈትናት ኢትዮጵያ መከተብ የቻለችው 2 ሚሊዮን 956 ሺሕ 130 ሰዎችን ብቻ ነው።
ኢትዮጵያውያን የኮቪድ-19 መከላከያ እንዲከተቡ፤ የአፍ እና የአፍንጫ መሸንፈኛ በማድረግ እና ሌሎች የመከላከያ መንገዶችን ተግባራዊ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል። ምኒስትሯ በአገሪቱ ትምህርት ቤቶች ሲከፈቱ መምህራንን መከተብን ጨምሮ የወረርሽኙን ሥርጭት ለመከላከል የሚያግዙ እርምጃዎች ገቢራዊ ሊሆኑ እንደሚገባ ማሳሰቢያ ሰጥተዋል።
👉🏾 @dwamharicbot
የደቡብ ሱዳን ፕሬዝደንት ሳልቫ ኪር ሚያርዲት ዛሬ እሁድ ለሁለት ቀናት የሥራ ጉብኝት ወደ ግብጽ አቀኑ። የጸጥታ ጉዳዮች አማካሪያቸው ቱት ጋትሉዋክ ማኒሜ፣ የፕሬዝደንታዊ ጉዳዮች ምኒስትሩ ባርናባ ማርያል ቤንጃሚን እና የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ምኒስትሩ ማዪክ አዪ ዴንግ አብረዋቸው ወደ ካይሮ ተጉዘዋል። ሳልቫ ኪር በካይሮ ቆይታቸው ከግብጹ አቻቸው አብደል ፋታኅ አል-ሲሲ ጋር በሁለቱ አገሮች የጋራ ግንኙነት እና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ እንደሚወያዩ የደቡብ ሱዳን ፕሬዝደንት ጽህፈት ቤት አስታውቋል።
የምሥራቅ አፍሪቃ የልማት በይነ መንግሥታት ባለሥልጣን (ኢጋድ) የኢትዮጵያን ፌድራል መንግሥት ከትግራይ ኃይሎች ለማሸማገል ያጫቸው ሳልቫ ኪር ሚያርዲት የጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አሕመድን በዓለ ሲመት በአዲስ አበባ ከታደሙ መሪዎች አንዱ ናቸው።
በበዓለ ሲመቱ ወቅት ሳልቫ ኪር ከትግራይ መሪዎች ግንኙነት እንዲጀምሩ ጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ መስማማታቸውን ቃል አቀባያቸው አቴኒ ዌክ አቴኒ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሱዳን ተልዕኮ ለሚተዳደረው ራዲዮ ሚራያ ባለፈው ሣምንት ተናግረው ነበር። 👉🏾 @dwamharicbot
የኦስትሪያ መራሔ-መንግሥት ሰባስቲያን ኩርዝ ሥልጣን እንደሚለቁ አስታወቁ። ትናንት ቅዳሜ ሥልጣን እንደሚለቁ ይፋ ባደረጉት በኩርዝ ምትክ የኦስትሪያው ውጭ ጉዳይ ምኒስትር አሌክሳንደር ሻለንበርግ መራሔ-መንግሥትነቱን ይረከባሉ ተብሎ ይጠበቃል።
የ35 አመቱ ወግ አጥባቂ ሰባስቲያን ኩርዝ በሙስና ተሳትፎ ስማቸው ከተነሳ በኋላ ከሥልጣን እንዲለቁ ጫና በርትቶባቸው ቆይቷል።
የ52 አመቱ አሌክሳንደር ሻለንበርግ በዛሬው ዕለት ከፕሬዝደንት አሌክሳንደር ቫን ዴር ቤለን እና ምክትል መራሔ-መንግሥት ዌርነር ኮግለር ተገናኝተው የተወያዩ ሲሆን ሥልጣን ላይ የሚገኘው ጥምር መንግሥት እንዲቀጥል ፓርቲያቸው ድጋፍ እንደሚያደርግ ጥቆማ ሰጥተዋል።
ኩርዝ እና ዘጠኝ የፓርቲያቸው ሰዎች ከጎርጎሮሳዊው 2016 እስከ 2018 ባሉት አመታት የመንግሥትን ገንዘብ አዎንታዊ የብዙኃን መገናኛ ዘገባ ለማሰራት ጥቅም ላይ አውለዋል በሚል ተጠርጥረው ምርመራ እየተደረገባቸው እንደሚገኝ የኦስትሪያ ፖሊስ አስታውቋል። 👉🏾 @dwamharicbot
በደቡባዊ የመን የምትገኘው የኤደን ከተማ አስተዳዳሪ ላይ ባነጣጠረ የተሽከርካሪ ቦምብ ጥቃት በትንሹ አምስት ሰዎች ተገደሉ። ደቡባዊ የመንን ለመገንጠን የሚንቀሳቀሰው የደቡብ የመን የሽግግር ምክር ቤት አባላት የሆኑት የኤደን ከተማ አስተዳዳሪ አሕመድ ላምላስ እና የግብርና ምኒስትር ሳሌም አል-ሱጋትሪ "ከአሸባሪዎች የግድያ ሙከራ" ማምለጣቸውን መንግሥት የሚቆጣጠረው የዜና ወኪል ዘግቧል።
በጥቃቱ የአስተዳዳሪው ቃል አቀባይ፣ ፎቶ አንሺያቸው፣ የጠባቂዎቻቸው አዛዥ፣ አንድ አብረው ይጓዙ የነበሩ ግለሰብ እና አንድ መንገደኛ ሲገደሉ ሌሎች አስር ሰዎች ቆስለዋል። ከቆሰሉ ሰዎች መካከል አንድ ሕፃን እንደሚገኝበት የደቡብ የመን የሽግግር ምክር ቤት ወታደራዊ ቃል አቀባይ ተናግረዋል።
በኤደን ከተማ አል-ታዋሒ የተባለ አካባቢ ከደቡብ የመን የሽግግር ምክር ቤት ዋና መሥሪያ ቤት አጠገብ የተፈጸመው ጥቃት ዒላማ የነበሩት አሕመድ ላምላስ የሽግግር ምክር ቤቱ ዋና ጸሐፊ ናቸው። ለጥቃቱ እስካሁን ኃላፊነት የወሰደ ወገን ባይኖርም የደቡብ የመን የሽግግር ምክር ቤት ቃል አቀባይ አሊ አል-ቃጢሪ ኢስላማዊ ታጣቂዎች ያሏቸውን ተጠያቂ አድርገዋል።
👉🏾 @dwamharicbot
ፓኪስታናዊው የኑክሌር ሳይንቲስት አብዱልቃድር ክኻን በ85 አመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ። ሳይንቲስቱ በኮቪድ-19 ተይዘው ረዘም ላለ ጊዜ በሕመም ላይ እንደቆዩ ቤተሰቦቻቸው ይፋ አድርገዋል። የፓኪስታን የአገር ውስጥ ጉዳይ ምኒስትር ሼይክ ራሺም አሕመድ እንዳሉት ሳይንቲስቱ በኢስላማባድ በሚገኝ ሆስፒታል ዛሬ እሁድ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

አብዱል ቃድር ክኻን ከ50 ገደማ አመታት በፊት ፓኪስታን የኑክሌር ቦምብ የታጠቀችበትን መርሐ-ግብር ያስጀመሩ ሳይንቲስት ሲሆኑ በሥራቸው ውጤት ምክንያት አወዛጋቢ ነበሩ። በኢስላማባድ የቀብር ሥርዓታቸው ዛሬ ሲፈጸም በሺሕዎች የሚቆጠሩ የፓኪስታን ዜጎች የተገኙ ሲሆን የአገሪቱ ሰንደቅ ዓላማም ዝቅ ብሎ ተውለብልቧል። አብዱልቃድር ክኻን በደጋፊዎቻቸው ዘንድ "የፓኪስታን የኑክሌር ቦምብ አባት" እየተባሉ ይጠሩ ነበር።

ሳይንቲስቱ በኔዘርላንድስ ከተቀጠሩበት የምርምር ማዕከል ኋላ የፓኪስታንን የኑክሌር ቦምብ የሰሩበትን የዩራኒየም ማበልጸጊያ ቴክኖሎጂ ሰርቀዋል እየተባሉ በምዕራባውያኑ ይከሰሳሉ። አብዱልቃድር ክኻን ለፓኪስታን የኑክሌር ቦምብ ለመሥራት ምክረ ሐሳብ ያቀረቡት ሕንድ "ሰላማዊ የኑክሌር ፍንዳታ" ሙከራ ባደረገች በአመቱ ነው። ጊዜው ፓኪስታን የዛሬዋ ባንግላዴሽን አጥታ 90 ሺሕ ወታደሮቿም በሕንድ ተማርከው ቁጭት ላይ የምትገኝበት በመሆኑ በወቅቱ የአገሪቱ ጠቅላይ ምኒስትር ዙልፊካር አሊ ቡቶ ምክረ ሐሳባቸው ተቀባይነት አግኝቷል።

ፓኪስታን እና ሕንድ የኑክሌር ቦምብ ባለቤት ከሆኑ አገሮች ጎራ በይፋ የተመደቡት በጎርጎሮሳዊው 1998 ዓ.ም. ነበር። አብዱልቃድር ክኻን የኑክሌር ምሥጢሮችን ለኢራን እና ለሰሜን ኮሪያ አሳልፈው ሰጥተዋል የሚል ክስ ከአሜሪካ ቀርቦባቸዋል።
👉🏾 @dwamharicbot
ኢትዮጵያዊው ሰይፉ ቱራ በአሜሪካዋ ቺካጎ በተካሔደ የማራቶን የሩጫ ውድድር አሸነፈ። ሰይፉ ውድድሩን በ2 ሰዓት ከ06 ደቂቃ ከ12 ሰከንዶች አጠናቋል። ከዚህ ቀደም በ3000 እና 5000 ሜትሮች ይወዳደር የነበረው ሰይፉ ፊቱን ወደ ማራቶን ያዞረው ከአራት አመታት በፊት ነው። በማራቶን ባደረጋቸው ውድድሮች በደቡብ ኮሪያ ሴዑል ሁለተኛ ሲወጣ፤ በጣልያኗ ሚላን እና በቻይናዋ ሻንጋይ አሸናፊ ለመሆን በቅቷል። ከሁለት አመት በፊት በብራዚል ቦነስ አይረስ በተወዳደረበት የግማሽ ማራቶን የሩጫ ውድድር በ59 ደቂቃ ከ16 ሰከንዶች በማሸነፍ የግሉን ምርጥ ሰዓት አስመዝግቧል።
ሰይፉ ከ12 አመታት በኋላ በቺካጎ ማራቶን ሲያሸንፍ የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ነው። በዛሬው የቺካጎ ማራቶን ውድድር ሰይፉን በመከተል አሜሪካዊው ጋለን ሩፕ ሁለተኛ ወጥቷል። የኬንያው ኤሪክ ኪፕታኑይ ሶስተኛ ሆኖ ጨርሷል።
በሴቶች ኬንያዊቷ ሩትዝ ቼፕንጌቲች ውድድሩን በ2:22:31 በመጨረስ ቀዳሚ ሆናለች። አሜሪካውያኑ ኤማ ቤትስ እና ሳራ ሖል ሁለተኛ እና ሶስተኛ ሆነው ውድድሩን አጠናቀዋል። በውድድሩ የተሳተፈችው ኢትዮጵያዊቷ መሠረት በለጠ 10ኛ ሆና አጠናቃለች።
👉🏾 @dwamharicbot