DW Amharic
44K subscribers
3.49K photos
800 videos
69 files
13.7K links
ይህ የዶይቼ ቬለ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው። ትኩስ ዜና፣ በአበይት ፖለቲካዊ፣ ኤኮኖሚያዊ፤ ማኅበራዊ እና ባሕላዊ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩር ትንታኔ ያቀርባል።
Download Telegram
«በትግራይ የዜጎች ህይወት ለአደጋ እየተጋለጠ ነው»ነዋሪዎች
በትግራይ ከመስከረም ወር መጀመርያ ወዲህ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተሻሽሏል። ሆኖም ነዳጅና መድሐኒቶችን ጨምሮ ሌሎች ሸቀጦች ወደ ትግራይ ስለማይገቡ የዜጎች ሕይወት ለአደጋ እየተጋለጠ መሆኑን፤ የሸቀጦች ዋጋም እጅግ እየናረ መሄዱንም ነዋሪዎች ለዶቼ ቬለ ተናግረዋል።https://p.dw.com/p/41P7J?maca=amh-RED-Telegram-dwcom@dwamharicbot
ከካማሺ ዞን የተፈናቀሉ ሰዎች አቤቱታ
በቅርቡ በሴዳል እና ኦዳ ብልድግሉ ወረዳዎች በተስፋፋው የጸጥታ ችግር ምክንያት ከ13ሺ በላይ ዜጎች ተፈናቅለው ዳላቲ በተባለ የአሶሳ ዞን አንድ ቀበሌ እንደሚገኙ የቤኒሻንል ጉሙዝ ክልል የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ ባለፉት ሰባት ወራት ወደ ጫካ የሸሹ በርካታ የአካባቢው ነዋሪዎች ሰብአዊ ድጋፍ እንዳልደረሳቸው ነዋሪዎች ተናግረዋል።https://p.dw.com/p/41OZ8?maca=amh-RED-Telegram-dwcom@dwamharicbot
የተመድ ከኢትዮጵያ ስለተባረሩት ሠራተኞቹ ማስረጃ መጠየቁ
በተመድ የኢትዮጵያ ልዑክ አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ የፀጥታው ምክር ቤት ትናንት ስለጉዳዩ ባካሄደው ስብሰባ ልይ ለድርጅቱ የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ መግባቱን ሠራተኞቹም ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ እንደተነገራቸው ገልፀዋል።ስለሠራተኞቹ ጥፋት የተፃፈው ደብዳቤ እንዳልደረሳቸው የተናገሩት የድርጅቱ ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬሽ ማስረጃ እንዲቀርብላቸው ጠይቀዋል።https://p.dw.com/p/41PDL?maca=amh-RED-Telegram-dwcom@dwamharicbot
የመስከረም 27/2014 ዓ/ም የዓለም ዜና በድምጽ
ርዕሶቹ
• ኢትዮጵያ የመንግሥታቱን ድርጅት ሠራተኞች ላባረረችበት ክስ ማስረጃ እንድታቀርብ የድርጅቱ ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬሽ ጠየቁ። ጉተሬሽ ጥያቄውን ያቀረቡት የጸጥታው ጥበቃ ምክር ቤት ኢትዮጵያ ባባረረቻቸው የተመድ ሠራተኞች ጉዳይ ትናንት ባደረገው ስብሰባ ላይ ነው።
• ተቀናቃኝ የፖለቲካ ፓርቲዎችን በማካተት የተመሰረተውን አዲሱን የኢትዮጵያ መንግሥት ውጤታማነት በጥርጣሬ እንደሚመለከቱ ከምርጫው አስቀድመው ራሳቸውን ያገለሉት የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረንስ ኦፌኮ እና የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ኦነግ አስታወቁ።
• ታንዛንያዊው የ72 ዓመቱ ደራሲ አብዱልረዛቅ ጉርናህ የዘንድሮዉን የዓለም የስነጽሑፍ የኖቤል ሽልማት አሸነፉ ። አብዱልራዛቅ ለሽልማቱ የበቁት «ቅኝ ግዛት በስደተኛው ዕጣ ፈንታ ላይ ያሳደረውን ጉልህ ተጽዕኖ የሚጋፈጡ » የስነጽሑፍ ሥራዎችን በማበርከታቸው እንደሆነ የኖቤል ኮሚቴ አስታውቋል።
• የዓለም የጤና ድርጅት በታሪኩ ለመጀመርያ ጊዜ ውጤታማ ነው የተባለ የወባ በሽታ መከላከያ ክትባት አጸደቀ። «ሞስኪዩሪክስ » የተሰኘውን ይህንኑ አዲሱ ክትባት በሽታው በስፋት ጉዳት በሚያደርስባት አፍሪካ ለሕጻናት እንዲሰጥ መፍቀዱን ድርጅቱ አስታውቋል።
https://p.dw.com/p/41Pga?maca=amh-RED-Telegram-dwcom@dwamharicbot
ለሴቶች መብት የሚከራከሩ አዲሱ ጥምረት
አዲስ አበባ ጎዳና ላይ በጠራራ ፀሐይ በፖሊስ ክፉኛ ስትደበደብ የሚሳያወዉ ቪዲዮ የማኅበረሰቡን ልብ ሰብሮአል። ይህችን ሴትም ሆነ በአጠቃላይ ማኅበረሰቡን የሚጠብቀዉ ፖሊስ ነዉ። ፖሊስ ኅብረተሰቡን ከነዚህ መሰል ጥቃቶች መጠበቅ ያለበት ትልቁ አካል ነዉ። መንግሥትም ዞር ብሎ፤ ተቋማቱን መፈተሽ ይኖርበታል።https://p.dw.com/p/41OcA?maca=amh-RED-Telegram-dwcom@dwamharicbot
በምርጫ 2013 ያልተሳተፉ የፖለቲካ ፓርቲዎች ስለ አዲሱ መንግሥት የሰጡት አስተያየት
በምርጫ 2013 ያልተሳተፉት የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግሬስ (ኦፌኮ)ና በአቶ ዳውድ ኢብሳ የሚመራው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ባለስልጣናት በአገሪቱ ዴሞክራሲና ሰላምን ከመሰረቱ ለማጠናከር ሁሉን አቀፍ ውይይት ያሻል ብለዋል፡፡የገዢው ፓርቲ ባለስልጣን ደግሞ መንግስት ሰላምን ከሚፈልግ የትኛውም አካል ጋር ለመደራደር ዝግጁ ነው ብለዋል፡፡https://p.dw.com/p/41PnZ?maca=amh-RED-Telegram-dwcom@dwamharicbot
የመጀመሪያው የወባ መከላከያ ክትባት ስራ ላይ እንዲውል መፈቀዱ
የድርጅቱ ዋና ፀሀፊ ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም ክትባቱ ስራ ላይ እንዲውል የተፈቀደበትን ወቅት ታሪካዊ ብለውታል። ድርጅቱ እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው ከጎርጎሮሳዊው 2019 አንስቶ በመካሄድ ላይ በነበረ ምርምር በጋና በኬንያ እና በማላዊ ከ800 ሺህ በላይ በሚሆኑ ህጻናት ላይ ከተካሄደ ክትትል በኋላ መሆኑን አስታውቋል።https://p.dw.com/p/41Pny?maca=amh-RED-Telegram-dwcom@dwamharicbot
የአውሮጳ ኅብረት ፓርላማ በመጪዎቹ ሶስት ሳምንታት ሁኔታዎች ካልተሻሻሉ በኢትዮጵያ መንግሥትና በህወሓት አመራሮች ላይ ማዕቀብ እንደሚጥል አስጠነቀቀ። ስለ ሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ትናንት የተነጋገረው የአውሮጳ ኅብረት ፓርላማ በኢትዮጵያ መንግሥት እና በህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ «ህወሓት » መካከል የሚካሄደዉ ጦርነት በአስቸኳይ እንዲቆምም ጠይቋል።ህወሓት ከአማራ እና ከአፋር ክልል በአስቸኳይ እንዲወጣና፤ የአማራ ክልላዊ መንግሥትም ምዕራብ ትግራይ ካሉት አካባቢ ጦሩን እንዲያስወጣም ጥሪ አቅርቧል።
የዘንድሮው የኖቤል የሰላም ሽልማት ለሁለት ጋዜጠኞች ተሰጠ። ፊሊፒናዊቷ ጋዜጠኛ ማርያ ርየሳና ሩስያዊው ጋዜጠኛ ዲሚትሪ ሙራቶቭ ሽልማቱ መመረጣቸውን የተናገረው የኖቤል ኮሚቴ ሽልማቱ የተሰጣቸው ሃሳብን በነፃ ለመግለጽ ላደረጉት ትግል መሆኑን አስታውቋል።

የተመድ የየሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን አጣሪ ቡድን በየመን ጦርነት በተፈጸሙ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች ላይ የሚያካሄደውን ምርመራ እንዲቀጥል የቀረበው የውሳኔ ሃሳብ ተቀባይነት ሳያገኝ ቀረ። ትናንት ጄኔቫ ውስጥ በተካሄደ ስብሰባ በውሳኔ ሀሳቡ ላይ በተሰጠ ድምጽ ምርመራው ለሁለት ዓመታት እንዲቀጥል የሚቃወመው ድምጽ ለጥቂት በልጦ ውሳኔ ሀሳቡ ሳያልፍ ቀርቷል።
https://p.dw.com/p/41STC?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
በድሬደዋ የደንጊ በሽታ ወረርሽኝ ተከሰተ
በድሬደዋ ከተማ የደንጊ በሽታ ወረርሽኝ መከሰቱን የአስተዳደሩ ጤና ቢሮ ኃላፊ ለዶይቼ ቬለ ተናገሩ። የድሬደዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ ኃላፊ ለምለም በዛብህ እንዳሉት ለ87 ናሙናዎች ምርመራ ተደርጎ አራት ሰዎች በደንጊ መያዛቸው ተረጋግጧል። ከመስከረም እስከ ኅዳር ባሉት ወራት በድሬደዋ ቺኩንጉንያ፣ ደንጊ እና ወባ በሽታዎች በወረርሽኝ መልክ ይከሰታሉ https://p.dw.com/p/41TPj?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
የፀጥታው ምክር ቤት ዳግም ስለ ኢትዮጵያ
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ኢትዮጵያ ባባረረቻቸው የመንግሥታቱ ድርጅት ሠራተኞች ጉዳይ ላይ ረቡዕ በአስቸኳይ ተሰብስቧል። ዓለም አቀፍ ድርጅቱ በኢትዮጵያ ጉዳይ ከአንድ ሳምንት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ለመምከር ሲሰሰበሰብ ሁለተኛው ነው። በስብሰባዎቹ የፀጥታው ምክር ቤት የተከፋፈለ ሐሳብ ተንጸባርቆበታል።https://p.dw.com/p/41S5I?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
የቅጥር ተግዳሮት በአፍሪቃ
የሥራ አጥነት ቁጥር አፍሪቃ ውስጥ ጨምሯል። በተለይ ወጣቶች ሥራ ማግኘት ይቸገራሉ። ሆኖም ግን ኢ-መደበኛ ዘርፎች እያበቡ ነው። አስተሳሰብን መቀየር ወሳኝ ነው ይላል አንድ የቅርብ ጊዜ ጥናት። https://p.dw.com/p/41S7q?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
የመስከረም 29/2014 ዓ/ም የዓለም ዜና በድምጽ
ርዕሶቹ
• የኢትዮጵያ መንግስት ወታደሮች እና አጋር ኃይሎች በአማራ ክልል የትግራይ ኃይሎች ላይ «መጠነ ሰፊ የአየር እና የምድር ጥቃት » መሰንዘር መጀመራቸውን የተራድዖ ድርጅቶች እና የትግራይ ኃይሎች አስታወቁ። የጥቃቱን መጀመር ከኢትዮጵያ መንግስትም ሆነ በጦርነቱ ከሚሳተፉ የክልል ባለስልጣናት በኩል እስካሁን ማረጋገጫ አልተገኘም።
• የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝብ ክልልን ለመመስረት አልያም በደቡብ ክልል ስር ለመተዳደር በተደረገው የሕዝበ ውሳኔ አዲሱን ክልል በደገፍ የተሰጠው ድምጽ በአብላጫ ማሸነፉን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ።
• በጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ የተሰየመው የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ ፅ/ቤት ሓላፊ የነበሩት ገብረመስቀል ካሳ ከሀገር ወጥተው ጥገኝነት ጠየቁ። ገብረመስቀል ካሳ በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ውስጥ በስራ ላይ በነበሩበት ወቅት የኤርትራ ወታደሮች ክልሉን ለቀው እንዲወጡ በግልጽ ይጠይቁ እንደነበር ተገልጿል።
• በሊቢያ መዲና ትሪፖሊ በስደተኞች በተጨናነቁ እስር ቤቶች ጣባቂዎች በከፈቱት ተኩስ ስድስት ስደተኞች ተገደሉ። በእስር ቤቱ ከነበረው የከፋ መጨናነቅ ለማምለጥ በተቀሰቀሰ ትርምስ ከተገደሉት በተጨማሪ በሌሎች ሃያ ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱን ዓለማቀፉ የስደተኞች ጉዳይ ድርጅት (አይ ኦ ኤም) አስታውቋል።
https://p.dw.com/p/41ToS?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝበ-ውሳኔ አስራ አንደኛው ክልል እንዲቋቋም ወሰነ
በደቡብ ክልል አምስት ዞኖች እና አንድ ልዩ ወረዳ የተካሔደው ሕዝበ-ውሳኔ አስራ አንደኛው የኢትዮጵያ ክልል እንዲቋቋም ወሰነ። ምዕራብ ኦሞ፣ ቤንች ሸኮ፣ ካፋ፣ ዳውሮ፣ ሸካ ዞኖችና ኮንታ ልዩ ወረዳ "ከደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ወጥተው የጋራ አንድ ክልል መመሥረታቸውን እደግፋለሁ" የሚለው አማራጭ 1 ሚሊዮን 221092 ድምጾች አግኝቷል https://p.dw.com/p/41TnI?maca=amh-RED-Telegram-dwcom