Dr. Eyob Mamo
80.5K subscribers
3.3K photos
14 videos
5 files
3.1K links
Life skill development!
You can contact me
@DrEyobmamo
Download Telegram
“የመገፋት ስስነት”
“የመገፋት ስስነት”
(“የመገፋት ህመም” ከተሰኘው የዶ/ር ኢዮብ ማሞ መጽሐፍ የተወሰደ)

በስነ-ልቦናው ቋንቋ “የመገፋት ስስነት” (Rejection Sensitivity) የተሰኘው ሃሳብ ሰዎች በየእለት ኑሯቸው የሚያጋጥማቸውን ጥቃቅን የሰዎች ሁኔታ ከመገፋትና ከመገለል ጋር የማዛመድ ስስነትንና ዝንባሌን የሚያሳይ ጽንሰ-ሃሳባ ያመለክታል፡፡

አንዳንድ ሰዎች በመገፋት ዙሪያ እጅግ ስስ ከመሆናቸው የተነሳ እንደተገፉ የመሰላቸው ማንኛውም አይነት ሁኔታ ሲመለከቱ የመደናገጥና የመዋረድ ስሜት ይሰማቸዋል፡፡ ለምሳሌ፣ ሰዎች ሲያስጠብቋቸው፣ ስልካቸውን ካልመለሱላቸውና እንደዚህ የመሳሰሉ “አናሳ” የሆኑ ክስተቶች የዝቅተኝትን፣ የመናቅንና የመገለልን ስሜት ያመጣባቸዋል፡፡

“የመገፋት ስስነት” ዝንባሌን አስመልክቶ በርካታ ጥናቶች ተደርገዋል፡፡ ለምሳሌ፣ የዚህ ተጽእኖ ሰለባዎች፣ ሰዎች በፊት ገጽታቸው የሚያሳዩት ሁኔታ እነሱን ያለመቀበልና የመግፋት ምልክት እንዳለው ሲሰማቸው የአንጎል እንቅስቃሴያቸው (Brain Activity) በብዙ እጥፍ እንደሚጨምር ጥናቶቹ ይጠቁማሉ፡፡ በተጨማሪም፣ እነሱን የመግፋት ወይም የማግለል ገጽታ ሊኖረው የሚችልን ማንኛንም እንቀስቃሴም ሆነ ንግግር በንቃትና ሁኔታዎችን በማዛመድ የመመልከትና የመጠባበቅ ዝንባሌ ይታይባቸዋል፡፡

የዚህ ዝንባሌ አንዱ ጫና፣ አድልዎ-ተኮር ምላሽ (Attention Bias) ነው፡፡ ለምሳሌ፣ ለአስር ሰዎች የፍቅር ጥያቄ አቅርበው ዘጠኙ ተቀብለዋቸው አንዱ ብቻ ፍላጎት እንደሌለው ቢገልጽላቸው፣ እነሱ የሚያተኩሩትና ስሜታቸውን የሚነካው የዘጠኙ እሺታ ሳይሆን የአንዱ እምቢታ ነው፡፡ ይህ አይነቱ ትኩረትን ከመገፋት አንጻር ብቻ የመቃኘት አድሎአዊ አመለካከት የሚያስከትልባቸው የስነ-ልቦና ቀውስ በግል ሕይወታቸውም ሆነ በማሕበራዊ ግንኙነታቸው ላይ የሚስከትለው መዘዝ ቀላል አይደለም (ምንጭ፡- verywellmind.com)፡፡

ሁኔታውን ስንጨምቀው፣ በመገፋት ስቃይ ውስጥ ያለፈ ሰው የሰዎችን፣ በተለይም በእነሱ ሕይወት ስፍራ እንዳላቸው የሚሰማቸውን ሰዎች እያንዳንዱን ተግባር በመገመት በመላ-ምት የመኖር ዝንባሌ ያጠቃቸዋል፡፡ ይህ አሉታዊ-ገማችነት ገደብ የሌለው ሃሳብ-ወለድ አለም ውስጥ እንዲዋዥቁና የሌለንና ያልተፈጠረን ነገር በውስጣቸው እንዲያሰላስሉ ያደርጋቸዋል፡፡

“የመገፋት ስስነት” ያለባቸው ሰዎች አንድ ጊዜ እንደዚህ አይነት አለም ውስጥ ከገቡ በኋላ ሲያሰላስሉት ውለው ያደሩት ነገር በእነሱ ውስጥ “የሌለ እውነታ” ሆኖ ይኖራል፡፡ የዚህ ስሜት ውጤት ሰዎች የሚያደርጓቸውንም ሆነ የማያደርጓቸውን ነገሮች እየለቀሙና እየቆጠሩ ካለባቸው “የመገፋት ስስነት” ጋር የማዛመዝ ሁኔታ ነው፡፡

“የመገፋት ስስነት” ያለባቸው ሰዎች የሚሰማቸው ስሜት በእርግጥም ከእውነተኛ የመገፋት ልምምድ የመጣ ሊሆን ይችላል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ግን ለመገፋት ስሜት ስስ እንዲሆኑ ከዳረጋቸው ከእውነታ የራቀ እይታም ሊነሳ ይችላል፡፡ መነሻው ያም ሆነ ይህ፣ ሰዎች በዚህ የስሜት ተጽእኖ ውስጥ የሚገኙ ሰዎች ላለባቸው የስነ-ልቦና ቀውስ ትክክለኛውን መፍትሄ እንዲፈልጉ ይመከራሉ፡፡

(ከመገፋት ህመም የመላቀቂያውን እውቀት ለማግኘት መጽሐፉ ይነበብ)

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
የሚለቀቀውና የሚያዘው! (ክፍል አንድ)

ላላገባችሁ . . .

“የሰውን አእምሮ የሚያዞሩ ሁለት አስቸጋሪ ጉዳዮች አሉ፡፡ ከእኛ ጋር አብሮ መቆየት የማይፈልግን ሰው እንዴት እንዲቆይ ማድረግ ይቻላል? ከእኛ ተለይቶ ለመሄድ የማይፈልግን ሰውስ እንዴት እንዲሄድ ማድረግ ይቻላል? - Danny Devito

አሁን ባለንበት ዘመን ያላገቡ ወጣቶችን ስሜት ለቀውስ የሚዳርጉ ሁለት ልምምዶችን የሚገልጽ አባባል ነው፡፡
ያፈቀራችሁት ሰው “አልፈልግም፣ እሄዳለሁ” ሲል ወይም “አልፈልግም እሄዳለሁ” ያላችሁት ሰው “ሞቼ እገኛለሁ” ሲል ማድረግ የሚገባችሁን ካላወቃችሁ የሚደርስባችሁ የስሜት ቀውስ ረጅም ዘመን የሚከተል ሊሆን ይችላል፡፡

ያፈቀራችሁት ሰው “አልፈልግም፣ እሄዳለሁ” ሲል ያላችሁ ምርጫዎች

1. በልመና፣ በለቅሶና በተስፋ-ቢስነት እንዳይሄዱ ለማድረግ ሲታገሉ መክረም፡፡

2. በግዳጅ፣ በዛቻና መግቢያ መውጪያ በማሳጣት እንዳይሄዱ ለማድረግ መታገል፡፡

3. ስሜትን በትክክል ከገለጹ በኋላ እምቢታቸውን በመቀበል መልቀቅና ራስ ላይ በመስራት ጉዞን መቀጠል፡፡

የትኛው ውሳኔ ይሻላል? ለምን?

በነገው ፖስት ላይ “አልፈልግም፣ እሄዳለሁ” ያላችሁት ሰው “ሞቼ እገኛለሁ” ሲል ያላችሁን ምርጫ እንመለስበታለን፡፡

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
የሚለቀቀውና የሚያዘው! (ክፍል ሁለት)

ላላገባችሁ . . .

. . . ካለፈው የቀጠለ

“የሰውን አእምሮ የሚያዞሩ ሁለት አስቸጋሪ ጉዳዮች አሉ፡፡ ከእኛ ጋር አብሮ መቆየት የማይፈልግን ሰው እንዴት እንዲቆይ ማድረግ ይቻላል? ከእኛ ተለይቶ ለመሄድ የማይፈልግን ሰውስ እንዴት እንዲሄድ ማድረግ ይቻላል? - Danny Devito

አሁን ባለንበት ዘመን ያላገቡ ወጣቶችን ስሜት ለቀውስ የሚዳርጉ ሁለት ልምምዶችን የሚገልጽ አባባል ነው፡፡

በትናንትናው “ፖስቴ” የዚህን ሃሳብ ክፍል አንድ ያሰፈርኩኝ ስለሆነ እሱን መለስ በማለት ማንበባችሁን አትርሱ፡፡

ትናንትና እንደዚህ ብለን ነበር፡- ያፈቀራችሁት ሰው “አልፈልግም፣ እሄዳለሁ” ሲል ወይም “አልፈልግም እሄዳለሁ” ያላችሁት ሰው “ሞቼ እገኛለሁ” ሲል ማድረግ የሚገባችሁን ካላወቃችሁ የሚደርስባችሁ የስሜት ቀውስ ረጅም ዘመን የሚከተል ሊሆን ይችላል፡፡

“አልፈልግም፣ እሄዳለሁ” ያላችሁት ሰው ሞቼ እገኛለሁ ሲል ያላችሁ ምርጫዎች፡-

1. ስሜታቸው እንዳይጎዳ በማለት የማትፈልጉት አይነት ግንኙነት ውስጥ መግባት፡፡

2. ስለ እኔ ያላቸውን መረጃ በመጠቀም ወይም በሌሎች መንገዶች ይበቀሉኛል በሚል ፍርሃት መንቀሳቀስ አለመቻል፡፡

3. ስሜትን በትክክል ከገለጹ በኋላና በቂ ማብራሪያ ከሰጡ በኋላ ተገቢውንና ትክክለኛውን ውሳኔ በማድረግ ሰዎች የራሳቸው ስሜት ላይ እንዲሰሩ ጊዜ መስጠት፡፡

የትኛው ውሳኔ ይሻላል? ለምን?

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
የዓላማና የተስፋ ግንኙነት

በአንድ የማጎሪያ እስር ቤት ውስጥ በመቶዎች የሚቆጠሩ ታራሚዎች ነበሩ፡፡ እነዚህ ታራሚዎች በቂ የሆነና የተሟላ የምግብ አቅርቦት ነበራቸው፡፡ ከተወሰነ የማረሚያ ቤት ቆይታቸው በኋላ እርስ በርሳቸው ስለተላመዱ በተለያዩ ጨዋታዎች እየተደሰቱና አንዳንድ ሞያ ነክ ነገሮችንም እየሰሩ መረጋጋት ጀምረዋል፡፡

ብዙም ሳይቆዩ ግን ሁሉንም የተስፋ መቁረጥ ስሜት ተጫጫናቸው፡፡ በማረሚያ ቤቱ ውስጥ ተስፈኛ ሆነው የመቆየት አቅማቸውንም አጡ፡፡

የሆነው ነገር ይህ ነው፡፡ አንድ ቀን ጠዋት ሲነሱ በማረሚያ ቤቱ ግቢ አንድ ጥግ ላይ የተከመሩ አሸዋ የሞላባቸው ጆንያዎች ነበሩና እነዚህን ጆንያዎች ካሉበት በማንሳት ወደሌላው የማረሚያ ቤቱ ግቢ ጥግ እንዲወስዱና እንዲከምሯቸው ተነገራቸው፡፡ ሁሉም ታራሚዎች በመነሳሳት ያንን ሲያደርጉ ዋሉ፡፡ ከዚያም ወደማምሻው ላይ ጠዋት ወስደው የከመሩትን የጆንያ አሸዋ ክምር ወደ ነበረበት እንዲመልሱ ታዘዙና ይህ ስራ በየቀኑ እንደሚቀጥል ተነገራቸው፡፡

እነዚህ ታራሚች በተወካያቸው በኩል አሸዋ የሞላባቸው ጆንያዎች ወዲያና ወዲህ የሚመላለሱበት ዋና ዓላማ ምን እንደሆነ ሲጠይቁ የተሰጣቸው መልስ ምንም ዓላማ የሌለው ተግባር እንደሆነና አርፈው እንዲታዘዙ ተነገራቸው፡፡ በዚህ ጊዜ ነበር ስሜታቸው በጣም የወረደው፡፡

ምንም ዓላማ የሌለውን ተግባር ሲደጋግሙ መኖር ተስፋ ያስቆርጣል፡፡ ምናልባት ሁል ጊዜ ተስፋ መቁረጥ የሚጫጫነን የመኖራችንን ዓላማና ትርጉም እንዲሁም በየቀኑ የምናደርጋቸውን ነገሮች ለምን እንደምናደርጋቸው ዓላማቸውን በሚገባ ስላላወቅነው ይሆን?

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
የጠበቅነውና የሆነው ነገር ሊለያይ!

በአንድ ነገር ላይ ጊዜያችንን፣ ጉልበታችንን፣ ስሜታችንንና አንዳንዴም ገንዘባችንን አውጥተን፣ ሰርተንና ገንብተን የጠበቅነው ውጤት ሌላ ያገኘነው ውጤት ግን ሌላ ሲሆን ግር መሰኘታችን አይቀርም፡፡ ሆኖም፣ አንድን ነገር ጠብቀን የምንፈልገውና የምንጠባበቀው ውጤት ሳይሆን ሲቀር ለሁኔታው የምንሰጠው ምላሸ ወሳኝ ነው፡፡

ለማንኛውም ማየት የሚገቡን ሁኔታዎች . . .

1. ምናልባት የተሳሰተና መጀመር የሌለብንን ነገር ጀምረን ይሆናል

2. ምናልባት ትክክለኛውን ነገር ጀምረን የተጠቀምነው ስልት ግን የተሳሳተ ይሆናል

3. ምናልባት የተጀመረው ነገርም ሆነ የተጠቀምንበት ስልት ትክክለኛው ሆነው ሳለ የተጠባበቅነው ውጤት እውነታውን ያላገናዘበ ይሆናል

ሁኔታውን በእነዚህ ሶስት ሃሳቦች ከመዘናችሁ በኋላ መቆም ያለበትን ነገር ማቆም፣ መቀየር ያለበትን ስልት መቀየር ወይም ደግሞ ውጤትንና እውነታን በማገናዘብ የአመለካከት ማስተካከያ ማድረግ አስፈላጊ ነው፡፡

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
እውነተኞች እንሁን!

የአንድን ሰው እውነተኛ ማንነት ለማወቅ ከፈለክ እኩዮቹንና የበላዮቹን ሳይሆን የበታቾቹን በእንዴት አይነት ሁኔታ እንደሚያስተናግድ ተመልከተው፡፡ ከሰዎች ጋር ያለውን አቀራረብም ሆነ ለሰዎች የሚያሳየውን ሁኔታ በወቅቱ ከሚያገኘው ጥቅም አንጻር ሳይሆን በእውነትም ካለው ትክክለኛ አመለካከት በመነሳት የሚያደርግ እውነተኛ ሰው የሚታወቀው በዚህና በዚህ ብቻ ነው፡፡

እውነተኞች እንሁን! ትክክለኞች እንሁን! ጨዋነት ይገኝብን!

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
ተግባቦት ስንል ???!!!

አንድ ሰው እንዲህ አለ፣ “ስለ ተግባቦት ሳይገባኝ የኖርኩባቸውን አመታቶች ሳስባቸው ይቆጨኛል፡፡ ለሌሎች እድል ሳልሰጥ ብዙ ከማውራቴ የተነሳ ሰዎች ብዙ እንደማወራ ሊነግሩኝ ሲሞክሩ እንኳን ብዙ እንደማላወራ ለማሳመን ብዙ አወራ ነበር”፡፡
ሕይወት ማለት የሁለትዮሽ ንግግር (Dialogue) እና ተግባቦት ነች፡፡ ይህ ማለት ደግሞ እኛ ስናወራ እንደሚያደምጡን ሁሉ እኛም ሌሎችን ማድመጥ ማለት ነው፡፡

እንደመጥ! እናድምጥ!

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
በፍጹም አታቁም!

“አንድ ጊዜ ነገሮችን በቀላሉ የማቆም ልምምድ ከጀመርክ ሁኔታው ልማድ ይሆንብሃል” - Vince Lombardi

በፍጹም ተስፋ አትቁረጥ!

ጠቃሚና ዋጋ ያለው ግብን የምትከታተል ከሆነ፣ የሆነ ጊዜ ላይ ከዚህ በታች ያሉትን ሃሳቦች ማስተናገድህ አይቀርም፡

• “ይህ ነገር ካሰብኩት በላይ ከባድ ነው፡፡”

• “ለምንድን ነው ይህ ነገር ይህን ያህል ረጅም ጊዜ የወሰደብኝ?”

• “ይህ ነገር ወደፊት አልራመድ አለኝ፡፡”

• “ይህ ግብ ደጋግሞ እየተበላሸብኝ ነው፡፡”

• “ይህንን ነገር መቀጠል የምችል አይመስለኝም፡፡ ምን አስቤ ነው የጀመርኩት?”

“በፍጹም አላቆምም” የሚልን አመለካከት አዳብር፡፡ ተስፋ አለመቁረጥ የአመለካከት ጉዳይ ነው፡፡ ይህም አመለካከት ልታዳብረው የምትችለው አመለካከት ነው፡፡ ይህንን አመለካከት ለማዳበር ከሚረዱህ ልምምዶች መካከል የሚከተሉትን ሃሳቦች ደግመህና ደጋግመህ ለራስህ መናገር ነው፡-

• ነገሮች ሲከብዱብኝ በዓላማዬ ጸንቼ እቀጥላለሁ፡፡

• መንገድን እፈልጋለሁ ወይም እፈጥራለሁ፡፡

• ማንኛውም ችግር መፍትሄ አለው፣ እኔ ደግሞ መፍትሄውን ለማግኘት ብቃቱ አለኝ፡፡

• በየቀኑ የሚሰራውንና የማይሰራውን የመለየትን እውቀትና ግንዛቤ እያገኘሁ ነው፣ ይህም ማለት በጥንካሬና በጥበብ እየጨመርኩኝ ነው ማለት ነው፡፡

• መሰናክሎች ጊዜያዊ ናቸው፡፡

ከላይ ያሉትን ሃሳቦች ለራስህ ከተናገርክ በኋላ ቆም ብለህ አስብ! እንደገናም ወደፊት ቀጥል!

(“ጀምሮ መጨረስ” ከተሰኘው የዶ/ር ኢዮብ ማሞ መጽሐፍ የተወሰደ)

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
ለክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ
እንኳን ለትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
ሶስቱ ለስኬታማነት ግዴታ የሆኑ ነገሮች
ሶስቱ ለስኬታማነት ግዴታ የሆኑ ነገሮች

ክፍል አንድ፡- መግቢያና ገለጻ

ዛሬና በሚቀጥሉት ሶስት ቀናት በተሰማራችሁበት ወይም ወደፊት በምትሰማሩበት የስራው መስክ ስኬታማ ለመሆን የግድ የሚስፈልጓችሁን ሶስት ነገሮች እንመለከታለን፡፡ ለዛሬ የእነዚህን ሶስት ወሳኝ ነገሮች ገለጻና መግቢያ እንመለከትና ከነገ ጀምሮ አንድ በአንድ እንመለስባቸዋለን፡፡

የትም ሄዳችሁ የትም! ለስኬታማነታችሁ መሰረታዊ የሆኑ ሶስት ነገሮች አሉ፡፡ እነሱም፡-

1. ክህሎት (Competence)፡-

ክህሎት የሚወክለው የተሰማራንበት መስክ የሚፈልግብንን የሞያና የችሎታ ብቃት የማዳበራችንን ሁኔታና የሚሰራውን ስራ በብቃት የመስራታችንን ጉዳይ ነው፡፡ አንዳንድ ሰዎች ምንም ችሎታ ሳይኖራቸው እንዲሁ ጨዋ ስለሆኑና ደስ የሚል “ማንነት” ስላላቸው ብቻ በስራው ዓለም የሚሳካላቸው ይመስላቸዋል፡፡ ይህ ሁኔታ ለጊዜው የሚያስኬድ ቢመስልም ለብቻው ግን ብዙም ላያዛልቅ ይችላል፡፡

2. ባህሪይ (Character)፡-

ባህሪይ የሚወክለው በክህሎታችን ምክንያት ለገባንበት ስፍራ የሚመጥን የባህሪይ ጨዋነት የመያዛችንንና የሞራል ልእልናችን ላይ የመስራታችንን ሁኔታ ነው፡፡ አንዳንድ ሰዎች ጥሩ ችሎታና የሞያ ብቃት ይዘው ሳለ ባህሪያቸው ግን እጅግ አስቸጋሪ ስለሆነ ሞያቸው ጉዟቸው ይገታል፡፡

3. ውህደት (Chemistry)፡-

ውህደት የሚወክለው አብረውን ከሚገኙ ሰዎች ጋር በአንድ ዓላማ ለመሰለፍ፣ ልዩነትን አልፎ አንድነት ላይ ለማተኮርና አብሮ “ለመፍሰስ” ያለንን ፍላጎትና ጥበብ ነው፡፡ ምንም እንኳን በቂ የሞያ ብቃት፣ እንዲሁም መልካም ባህሪይና ሰው ጋር የማይደረስ ጨዋነት ቢኖረንም አጠገባችን ካሉ ሰዎች ጋር አብሮ ለመራመድ ፍላጎቱና ብልሃቱ ከሌለን ቀጣይነታችን አጠራጣሪ ነው፡፡

በነገ ማለዳ “ፖስቴ” ክህሎት (Competence) የተሰኘውን ወሳኝ ነጥብ አብራራለሁ፡፡

ፈጣሪ በስራው ዓለምም ሆነ በማህበራዊው ሕይወታችሁ ያሳድጋችሁ!

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
ክህሎት (Competence)

ሶስቱ ለስኬታማነት ግዴታ የሆኑ ነገሮች (ክፍል ሁለት)

በትናንትናው “ፖስቴ” ሶስቱ ለስኬታማ ግዴታ የሆኑትን ነገሮች መግቢያ ሰጥቻችኋለሁ፡፡ ዛሬ የምንመለከተው በተሰማራችሁበት ወይም ወደፊት በምትሰማሩበት የስራው መስክ ስኬታማ ለመሆን የግድ ከሚስፈልጓችሁ ሶስት ነገሮች መካከል የመጀመሪያውን ማለትም ክህሎት (Competence) የተሰኘውን ሃሳብ ነው፡፡

የትም ሄዳችሁ የትም! ክህሎት (Competence) ለስኬታማነታችሁ መሰረታዊ የሆነ ጉዳይ ነው፡፡ በመግቢያው ላይ እንደገለጽነው ክህሎት የሚወክለው የተሰማራንበት መስክ የሚፈልግብንን የሞያና የችሎታ ብቃት የማዳበራችንን ሁኔታና የሚሰራውን ስራ በብቃት የመስራታችንን ጉዳይ ነው፡፡

አንዳንድ ሰዎች ምንም ችሎታ ሳይኖራቸው እንዲሁ ጨዋ ስለሆኑና ደስ የሚል “ማንነት” ስላላቸው ብቻ በስራው ዓለም የሚሳካላቸው ይመስላቸዋል፡፡ ይህ ሁኔታ ለጊዜው የሚያስኬድ ቢመስልም ለብቻው ግን ብዙም ላያዛልቅ ይችላል፡፡

በክህሎት ልቆ ለመገኘት፡-

1. በእጃችን ላይ ሰዎች እኛን እስከመፈለግና ገንዘብንም እስከመክፈል ድረስ እንዲፈልጉን የሚያደርጋቸው ሞያ የመኖሩ ጉዳይ ላይ መስራት፡፡

2. ይህንን ሞያ ወቅቱ የሚፈልገው የእድገት ደረጃ ላይ መሆኑን ማረጋገጥና ተወዳዳሪ መሆን፡፡

3. ለወደፊቱ በሞያው አንጻር አዳዲስ እውቀቶች፣ ግኝቶችና አደራረጎች የመምጣታቸውን ጉዳይ መከታተልና ካለማቋረጥ መሻሻል፡፡

በነገ ማለዳ “ፖስቴ” ባህሪይ (Character) የተሰኘውን ወሳኝ ነጥብ አብራራለሁ፡፡
ፈጣሪ በስራው ዓለምም ሆነ በማህበራዊው ሕይወታችሁ ያሳድጋችሁ!

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
ባህሪይ (Character)

ሶስቱ ለስኬታማነት ግዴታ የሆኑ ነገሮች (ክፍል ሶስት)

በትናንትናው “ፖስቴ” ሶስቱ ለስኬታማ ግዴታ ከሆኑትን ነገሮች መካከል የመጀመሪያውን ማለትም ክህሎት (Competence) የተሰኘውን ሃሳብ ተመልክተናል፡፡ ዛሬ የምንመለከተው በተሰማራችሁበት ወይም ወደፊት በምትሰማሩበት የስራው መስክ ስኬታማ ለመሆን የግድ ከሚስፈልጓችሁ ሶስት ነገሮች መካከል ሁለተኛውን ማለትም ባህሪይ (Character) የተሰኘውን ሃሳብ ነው፡፡

የትም ሄዳችሁ የትም! ባህሪይ (Character) ለስኬታማነታችሁ መሰረታዊ የሆነ ጉዳይ ነው፡፡ በመግቢያው ላይ እንደገለጽነው ባህሪይ የሚወክለው በክህሎታችን ምክንያት ለገባንበት ስፍራ የሚመጥን የባህሪይ ጨዋነት የመያዛችንንና የሞራል ልእልናችን ላይ የመስራታችንን ሁኔታ ነው፡፡ አንዳንድ ሰዎች ጥሩ ችሎታና የሞያ ብቃት ይዘው ሳለ ባህሪያቸው ግን እጅግ አስቸጋሪ ስለሆነ የሞያ ጉዟቸው ይገታል፡፡

በባህሪይ ልቆ ለመገኘት፡-

1. ከሰዎች ጋር እንድንጋጭ የሚያደርግንን አጉል ባህሪያችንን ለማሰብና ለማግኘት ጊዜን መውሰድ፡፡

2. ብዙ ሰዎች የሚጠቁሙንን የአጉል ባህሪያችንን ጉዳይ በቁም ነገር በመውሰድ ማሰብ፡፡

3. አስቸጋሪ እንደሆነ ያሰብነውን ባህሪያችንን ለመለወጥ በማንበብ፣ ምክር በመቀበልና ሆን ብሎ የራስ-በራስ እርማት በመውሰድ ጉዞን መጀመር፡፡

በነገ ማለዳ “ፖስቴ” ውህደት (Chemistry) የተሰኘውን ወሳኝ ነጥብ አብራራለሁ፡፡

ፈጣሪ በስራው ዓለምም ሆነ በማህበራዊው ሕይወታችሁ ያሳድጋችሁ!

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
ውህደት (Chemistry)

ሶስቱ ለስኬታማነት ግዴታ የሆኑ ነገሮች (ክፍል አራት)
በትናንትናው “ፖስቴ” ሶስቱ ለስኬታማ ግዴታ ከሆኑትን ነገሮች መካከል ሁለተኛውን ባህሪይ (Character) የተሰኘውን ሃሳብ ተመልክተናል፡፡ ዛሬ የምንመለከተው በተሰማራችሁበት ወይም ወደፊት በምትሰማሩበት የስራው መስክ ስኬታማ ለመሆን የግድ ከሚስፈልጓችሁ ሶስት ነገሮች መካከል ሶስተኛውን ማለትም ውህደት (Chemistry) የተሰኘውን ሃሳብ ነው፡፡

የትም ሄዳችሁ የትም! ውህደት (Chemistry) ለስኬታማነታችሁ መሰረታዊ የሆነ ጉዳይ ነው፡፡ በመግቢያው ላይ እንደገለጽነው ውህደት የሚወክለው አብረውን ከሚገኙ ሰዎች ጋር በአንድ ዓላማ ለመሰለፍ፣ ልዩነትን አልፎ አንድነት ላይ ለማተኮርና አብሮ “ለመፍሰስ” ያለንን ፍላጎትና ጥበብ ነው፡፡ ምንም እንኳን በቂ የሞያ ብቃት፣ እንዲሁም መልካም ባህሪይና ሰው ጋር የማይደረስ ጨዋነት ቢኖረንም አጠገባችን ካሉ ሰዎች ጋር አብሮ ለመራመድ ፍላጎቱና ብልሃቱ ከሌለን ቀጣይነታችን አጠራጣሪ ነው፡፡

በውህደት ልቆ ለመገኘት፡-

1. ከሌሎች ሰዎች ጋር የተሰለፍኩበትን ዋና ዓላማ በሚገባ መለየት፣ መገንዘብና ማወቅ፡፡

2. ከሌሎች ሰዎች ጋር የተሰለፍኩበትን ዋና ዓላማ በሙሉ ልቤ መከታተሌን እርግጠኛ መሆን፡፡

3. በአጠገቤ ያሉ ሰዎች በአመለካከት፣ በልምምድም ሆነ በማንነት ከእኔ የሚለይ ነገር እንዳላቸው አምኖ በመቀበል አብሮ የመራመድን ባህል ማዳበር፡፡

ነገ በሌላ ሃሳብ እስከማገኛችሁ ሰላም ሁኑልኝ!

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
የስልጠና እድል!

ብዙዎቻችሁ በአካል በመገኘት በተለያዩ የሕይወት ክህሎቶች (Life Skills) ዙሪያ ስልጠናዬን መውሰድ እንደምትፈልጉ ስትገልጹልኝ ቆይታችኋል፡፡ በዚህ መሰረት፣ ለFacebook እና ለTelegram ተከታታዮቼ የስልጠና ፕሮግራሞችን በማዘጋጀት ላይ እገኛለሁ፡፡

በአዲስ አበባ በእቀድ ላይ ያለሁትን የስልጠና ጊዜ፣ ቦታና ሌሎች መረጃዎች በቅርቡ አሳውቃችኋለሁ፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በተለያዩ የሃገራችን ከተሞችና በውጪ ሃገሮች ላላችሁ ተከታታዮቼ ስልጠናዎችን ለመስጠት በእቅድ ላይ ነኝ፡፡

በቅርቡ ከማስባቸው ውጪ ሃገራት መካከል United Arab Emirates (ዱባይ እና አቡዳቢ) ይገኝበታል፡፡

በእነዚህ ከተሞች ለምትገኙ የሃገሬ ልጆች ስልጠናን ለመስጠት በማቀድ ላይ ስላለሁ፣ ለዝግጅት እንዲመቸኝ በዚያ የምገኙ ተከታታዮቼ የውስጥ መልእክት (Inbox) እንድታደርጉልኝና ስልጠናው ሲዘጋጅ በቀላሉ መረጃውን እንድናደርስላችሁ እንድታመቻቹ እጠይቃለሁ፡፡

የመለወጫ፣ የማደጊያና ወደ ስኬት ጎዳናችን የመዝለቂያ ዓመት ነው!!!

Dr. Eyob Mamo

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
አለቃ ወይስ መሪ?
አለቃ ወይስ መሪ?
(“አመራር A to Z” ከተሰኘው የዶ/ር ኢዮብ ማሞ መጽሐፍ የተወሰደ)

መሪ ሁሉ አለቃ ነው፣ አለቃ ሁሉ ግን መሪ አይደለም!

መሪ ባለው ቀደም ብሎ የመራመድ ሚና ፈርን የመቅደድ ሃላፊነቱ ስላለው አለቃም ነው ብንል አንሳሳትም፡፡ ሆኖም፣ በተለያዩ የስልጣን ምንጮች አለቃ የሆኑ ሁሉ መሪዎች ናቸው ለማለት አስቸጋሪ ነው፡፡ አለቃ፣ አለቃ ነው፤ በማስፈራት ይገዛል እንጂ አይመራም፡፡ መሪ አለቃ ነው ተብሎ ቢጠራም እንኳ በተለምዶ አለቆች የሚያሳዩትን ባህሪ አያንጸባርቅም፡፡ ስለዚህ መሪ የአለቅነቱ ዝንባሌ በጎላ ቁጥር የመሪነቱ መልክና ተጽእኖ እየደበዘዘና እየጠፋ ይሄዳል፡፡

ማንኛውም አለቃ መሪ ለመሆን በተከታዮቹ ወይም በሰራተኞቹ ላይ የአብሮ ሰራተኝነትን ስሜት ሊያሳድር ይገባዋል፡፡ “አለቃ ስለሆንኩኝ ብቻ ሊታዘዙኝና ሊያከብሩኝ ይገባል” ከሚል አመለካከት ወጥቶ በሚያስፈልጋቸው ሁኔታ ሁሉ ለመገኘት ራሱን በማቅረብ፣ ብቃቱን በማዳበርና በምሳሌነት በመምራት ተጽእኖን ማሳደር ይጠበቅበታል፡፡

ስለዚህም ሰዎች፣ መሪን በናፍቆትና በአክብሮት ሲታዘዙት፣ አለቃን ግን በፍርሃት ይታዘዙታል፡፡ የሚከተሉትን ንጽጽሮች እንመልከት፡፡

• አለቃ ሰዎችን በኃይል ይነዳል፤ መሪ ሰዎችን በመልካም ተጽእኖ ያነሳሳል፡፡

• አለቃ በስልጣኑ ላይ ይደገፋል፤ መሪ ባዳበረው ተቀባይነት ላይ ይደገፋል፡፡

• አለቃ ፍርሃትን ይለቅቃል፤ መሪ ፍቅርንና አክብሮትን ያስፋፋል፡፡

• አለቃ “እኔ” ማለት ያበዛል፤ መሪ “እኛ” ይላል፡፡

• አለቃ ስህተተኛው ማን እንደሆነ ያውጣጣል፤ መሪ ስህተቱን ፈልጎ ለማረም ይፈጥናል፡፡

• አለቃ ትኩረቱ ስራው መሰራቱ ላይ ብቻ ነው፤ መሪ ስራውን የሚሰሩት ሰዎች ላይም ትኩረቱን ይጥላል፡፡

• አለቃ ካላከበራችሁኝ ይላል፤ መሪ በሁኔታው መከበርን ያነሳሳል፡፡

በነገራችን ላይ የእውነተኛ መሪነት ጉዞ የሚጀምረው የአንድ ድርጅት የበላይ ከመሆን ሳይሆን አሁን ባለንበት ደረጃ ከሚኖረን ትክክለኛ መርህና ዝንባሌ መሆኑን አንዘንጋ፡፡

ዛሬ በመሪነት ሳይሆን በአለቅነት ዝንባሌ የሚሰሩ የድርጅት አመራሮች ትናንትና በመሪዎቻቸው የአለቅነት ዝንባሌ ሲበሳጩ የነበሩና ከዚያ ሁኔታ ትምህርትን ሳያገኙ ዛሬ ስልጣን ሲይዙ ያንንንው ስህተት የሚደግሙ ናቸው፡፡

አመራር ማለት መልካም ተጽእኖ በማምጣት ሰዎች ራእዩን በመከተላቸው የሚያገኙትን እድገትና ጥቅም በማሳየት ቀዳሚ መሆን ማለት ነው እንጂ ስልጣንን መቆናጠጥ ብቻ አይደለም፡፡

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
ትዳርና የስጋ ዘመዶች ጉዳይ (ክፍል አንድ)