Dr. Eyob Mamo
79.4K subscribers
4.46K photos
16 videos
10 files
3.62K links
Life skill development!
You can contact me
@DrEyobmamo
Download Telegram
የመብሰላችን ምልክቶች

1. በለውጥ ውስጥ ቋሚ የሆነ ባህሪይና ተግባር ማሳየት፡፡

2. ምስጋናንና አድናቆትን ካለምንም መታበይ ማስተናገድ፡፡

3. እርማትንና ወቀሳን ካለምንም ስሜታዊነት መቀበል፡፡

4. ማህበራዊ ኑሮንና (ጓደኝነትን) እና የስራ ሃላፊነት ሳያጣርሱ በሚዛነዊነት መያዝ፡፡

5. ካለምንም ቁጥጥር ሃላፊነትን መወጣት፡፡

6. ሳያስቡ አለመጀመር፣ ከጀመሩ አለማቆም፡፡

7. ከመላ-ምት ከሚነሳ ፈራጅነትና ድምዳሜ መቆጠብ፡፡

8. በምንፈልገውና በሚያስፈልገን ነገሮች መካከል በመለየት የመሚያስፈልገንን ማስቀደም፡፡

9. በሕይወቱ በሚከናወነው ነገር ላይ ሃላፊነት መውሰድ፡፡

10. ይሆናልና ይሳካል ብለን ካወጅን በኋላ አቅዶ ወደመስራት ተግባራዊነት አልፎ መሄድ፡፡

እነዚህ አስር የበሳል ሰዎች ልምምዶች በማንኛውም የሕይወታችን መስኮች ተፈላጊና ስኬታማ ያደርጉናልና አንስራባቸው፡፡

የትኛውን አዳብራችኋል? በየትኛውስ ገና ማደግ ይቀራችኋል?

LIKE & SHARE !!!
👍11196🔥14😢1
ከፍርድ ነጻ የሆነ ሳምንት

ከሰው ጉዳይ ላይ መውጣት
!!!
👍118
ከፍርድ ነጻ የሆነ ሳምንት

ከሰው ጉዳይ ላይ መውጣት !!!


“ወሳኙና ትኩረታችንን ልንጥልበት የሚገባው ነገር የሌላው ሰው ጉዳይና ደካማ ጎን ላይ ሳይሆን የራሳችን ጉዳይ ላይ ሊሆን ይገባዋል”

አንድ በጣም የታወቀ የስኬት አሰልጣኝ በመካከለኛ እድሜ ላይ የሚገኙ ስኬት የጠማቸው ነጋዴዎችን ለተወሰኑ ሳምንታት ስልጠና በመስጠት ላይ ነው፡፡ የሳምንቱ የስልጠና ርእስ ከዋናው ዓላማችን የሚያስወጡንን ተጽእኖዎች ስለማስወገድ ነው፡፡ በእያንዳንዱ ሳምንት በአንድ አስፈላጊ ርእስ ላይ መመሪያ ከሰጣቸው በኋላ የሳምንቱን የቤት ስራ ይሰጣቸዋል፡፡

በእለቱ ከሰጣቸው ትኩረትን የመሰብሰብ ትምህርቶች መካከል አንድ አስፈላጊ ነጥብ ይገኝበታል፡፡ “አብዛኛውን ጊዜ” አለ ሃሳቡን ሲያብራራው፣ “ከዋናው ተግባራችን ሃሳባችንን በመስረቅና ትኩረታችንን በመውሰድ ጊዜአችንን የሚያባክኑብን ሁኔታዎች በማያገባን የሰዎች ጉዳይ ላይ መግባት ነው”፡፡ ይህንና ሌሎችን ሃሳቦች ከተናገረ በኋለ የሳምንቱን የቤት ስራ ሰጣቸው፡፡ “የዚህ ሳምንት የቤት ስራ ቀላል ነው፡፡ በዚህ ሳምንት ስለማንኛውም ሰው ማንነትና ተግባር ምንም አይነት የፍርድም ሆነ የሃሜት ሃሳብ ሳታስተናግዱ ለመቆየት ሞክሩ፡፡ ከሰዎች ጋርም ስትገናኙ ስለሌላ ሰው ምንም አይነት አሉታዊ ነገሮችን ላለመወያየት ጥረት አድርጉ፡፡ ይህንን ካደረጋችሁ በኋላ ይህንን ማድረግ ምን ያህል ቀላል ወይም ከባድ እንደነበረ ልምምዳችሁን ለሌሎች የስልጠና ተሳታፊዎች ለማካፈል ተዘጋጅታችሁ ኑ”፡፡

ሳምንቱ አልፎ ሁሉም የተሰጠውን የቤት ስራ ለማከናወን ሲታገል ቆይቶ ውጤቱን ይዞ መጥቷል፡፡ ማንም ሰው እጁን በማውጣት ስሜቱንና ገጠመኙን እንዲናገር ሲፈቀድ እጆች መውጣትና ሃሳቦች መሰንዘር ተጀመረ፡፡

አንዱ፣ “ስለሌላ ሰው ምንም አይነት የፍርድ ሃሳብ ላለማሰብ ሙከራ ባደረኩበት በዚህ ሳምንት የማስበው አጣሁ” አለ፡፡ ሲቀጥልም፣ “ለካስ አብዛኛዎቹ ሃሳቦቼ የተሞሉት ማን ምን እንዳደረገ፣ ማን ምን እንደመሰለ እና የመሳሰሉት በሰዎች ስህተት ላይ ያተኮረ ነበር፡፡ እነዚህን ሃሳቦች ሳቆም ሌሎች ነገሮችን ለማሰብ ብዙ ጊዜ ላገኝ እንደምችል ገባኝ” አለ፡፡

ሌላኛው ቀጠል አድርጎ፣ “እኔ የገባኝ አንድ ነገር ስለሰዎች ውድቀት ስህተትና ሌሎችም የወቀሳና የፍርድ ሃሳቦችን ማሰብ እንዴት በቀላሉ የሚለመድ እንደሆነና ስለሰዎችም ሆነ ስለሁኔታዎች ጤናማ ጤናማውን ማሰብ እንዴት ከባድ እንደሆነ ገባኝ፡፡ ይህንን የአስተሳሰብ ሂደት ለመለወጥ ከባድ እንደሆነና መደረግ ግን ያለበት እውነታ እንደሆነ ተገነዘብኩ” አለ፡፡ አብዛኛዎች ሰልጣኞች የሚናገሩት ነገር ነበራቸው፡፡

በመጨረሻም ለአንድ ሰው እድል ሲሰጥ በአጭሩ እንዲህ አለ፣ “ልክ ስለ ሰዎች የፍርድ፣ የሃሜትና የመሳሰሉትን አይነት ንግግሮች ማሰብና መናገር እንደማልፈልግ እንዳወቁ በየቀኑ ሊያገኙኝ የሚፈልጉ ጓደኞቼ እኔን የማግኘት ፍላጎት አጡ፡፡ እኔ የገባኝ፣ በየቀኑ እንድንገናኝ የሚያነሳሳን ነገር ስለ ሌሎች ሰዎች የምናመጣቸው ተራ ወሬዎች እንደሆኑ ነው፡፡”

የትኩረትን ኃይል በሚገባ የተገነዘበ ሰው ከማያገባውና እሱን ከማይመለከተው የሰው ጉዳይ ራሱን ያገለለ ሰው ነው፡፡ ስለ ሰዎች ስህተትና ጉድለት ማሰብ የሚገባው ጊዜ እንዳለ ያውቃል፡፡ ሆኖም ያንን የሚያደርገው ሰዎቹን በምን መልክ ሊደግፋቸው እንደሚችልና የመፍትሄ ምክንያት ከመሆን አንጻር እንጂ ስለነሱ በማሰላሰልና በማውራት ስውር የድል ስሜት ለማግኘት ወይም የእነሱን ተጽእኖ ለማውረድ አይደለም፡፡

“ትኩረት” ከተሰኘው የዶ/ር ኢዮብ መጽሐፍ ላይ የተቀነጨበ፡፡

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
143👍26🔥2
“በየትኛው መንገድ ልሂድ?”

“በመንገድ ላይ ስትሄድ ወደ መስቀለኛ መንገድ ላይ ደረሰች። ከዚያም፣ በየትኛው መንገድ ልሂድ? ብላ ጠየቀች። ወዴት መሄድ ትፈልጊያለሽ? የሚልን መልስ አገኘች፡፡ የእሷም ምላሽ፣ የምሄድበትን አላውቅም የሚል ነበር፡፡ ከዚያም ያገኘችው መልስ፣ እንግዲያው በየትኛው መንገድ መሄድ እንዳለብሽ ማወቅሽ ትርጉም የለውም የሚል ነበር” – Lewis Carroll

ምን አይነት መንገድ መከተል እንዳለበን፣ ጊዜያችንን ምን ላይ ማሳለፍ እንዳለበን፣ ምን አይነት ሰው ለእኛ እንደሚመጥን አውቀን መምረጥ እንዳለብን . . . ግራ ከገባን ቀድሞውኑ የምንሄድበትን አቅጣጫ አውቀን ስላልተነሳን ነው፡፡

ስለሕይወታችሁ አቅጣጫ ግራ የሚያዚያ ወር Book Reading Challenge ያስፈልጋችኋል!

ለሚያዚያ ወር reading challenge የተመረጠው መጽሐፍ፣ “ራእይን ማወቅ እና መኖር” የተሰኘው ነው፡፡

መጽሐፉን ለማንበብ ከአሁኑ በመመዝገብ ራሳችሁን አዘጋጁ፡፡

የንባብ ወር - ሚያዚያ / 2018

ለንባብ የተመረጠው መጽሐፍ - “ራእይን ማወቅ እና መኖር”

ንባቡ የሚጀመርበት ቀን - ሚያዚያ 1 / 2018

ንባቡ የሚጠናቀቅበት ቀን - ሚያዚያ 30 / 2018

ይህንን Book Club ለመቀላቀል፡- በዚህ 👉 @DrEyobmamo የቴሌግራም አድራሻ (user name) inbox በማድረግ ፍላጎታችሁን ስትገልጹ ሙሉ መረጃ ይላክላችኋል፡፡

Join now!!!
62👍28🔥6😁1😢1
ከተወሰኑ አመታት በኋላ!

🌟 ከተወሰኑ አመታት በኋላ በዙሪያችሁ የሚኖሯችሁን አልሚ ወይም አጥፊ ጓደኞች የሚወስነው ዛሬ ያዳበራችሁት አመለካከት ነው፡፡

🌟 ከተወሰኑ አመታት በኋላ የሚኖራችሁን የፍቅር ወይም የትዳር ግንኙነት አይነት የሚወስነው የዛሬ ወዳጅነት ምርጫችሁ ነው፡፡

🌟 ከተወሰኑ አመታት በኋላ የሚኖራችሁን እውቀት የሚወስነው ዛሬ የምታነቧቸው መጻሕፍትና የምትወስዷቸው ስልጠኛዎች ናቸው፡፡

🌟 ከተወሰኑ አመታት በኋላ የምትገቡበትን አዲስ የሕይወት ምእራፍ የሚወስነው ዛሬ ለማድረግ የቆረጣችሁት ለውጥ ነው፡፡

🌟 ከተወሰኑ አመታት በኋላ የምትኖሩትን የኑሮ ጥራት የሚወስነው ዛሬ ያዳበራችሁት ልማድ ነው፡፡

ጥራት ያለው ሕይወት በአንድ ጀንበር አይመጣም፡፡ በአንድ ጀንበር ብቅ ያለ ነገር ካለም ደግሞ በአንድ ጀንበር ጥልቅ ማለቱ ስለማይቀር ጥራትን ዛሬ ጀምረውና በምንም ነገር እንደማይቀለበስ ሆኖ እንዲበቅል ጊዜ ስጠው፡፡

1. የሕይወታችሁን ዋነኛ ራእይና ዓላማ ለይታችሁ እወቁ፡፡

2. የምትመጧቸውን ጓደኞችም ሆኑ የምትውሉበትን ቦታ ከዚያ ዓላማ አንጻር ቃኙት፡፡

3. አብዛኛው አእምሯችሁን የምትመግቡት አመለካከትም ሆነ የእውቀት ዘርፍ ከዋና ዓላማችሁ አንጻር አድርጉት፡፡

4. የየቀን ልምምዳችሁንና ልማዳችሁን ከዋናው ዓላማችሁ አንጻር ቃኙት፡፡


https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
99👍27🔥4😱1
ወይ ወደ ፊት ወይም ወደ ኋላ!

“ልክ ሕይወትን እንዴት መኖር እንዳለብኝ ያወቅሁ ሲመስለኝ ህይወት ትለወጣለች” - Hugh Prather

የሃርቫርድ ዩኒቨርስቲ ትንበያዎች

ሃርቫርድ የተሰኘው ታዋቂ ዩኒቨርስቲ ለውጥን አስመልክቶ ሶስት እውነታዎችን እንደተነበየ ብራያንና ፒተር ያስታውሱናል፡፡

1. አሁን በተሰማራህበት የስራ ወይም የንግድ ዘርፍ ውስጥ በመጪው ጥቂት አመታት ውስጥ ከመቸውም ጊዜ በበለጠ ሁኔታ በርካታ ለውጦች ይከሰታሉ፡፡

2. አሁን በተሰማራህበት የስራ ወይም የንግድ ዘርፍ ውስጥ በመጪው ጥቂት አመታት ውስጥ ከመቸውም ጊዜ በበለጠ ሁኔታ የጋለ ውድድርና ፉክክር ይከሰታል፡፡

3. አሁን በተሰማራህበት የስራ ወይም የንግድ ዘርፍ ውስጥ በመጪው ጥቂት አመታት ውስጥ ከመቸውም ጊዜ በበለጠ ሁኔታ በርካታ የእድል በሮች ይከፈታሉ፤ ሆኖም እነዚህ እድሎች አሁን ከምታደርጋቸው ነገሮች እጅግ የተለዩ ናቸው፡፡

ከዚህ ፈጣን ሂደት ጋር አብሮ ስለመራመድ ካሰባችሁ የሚያዚያ ወር Book Reading Challenge ይጠቅማችኋል!

ለሚያዚያ ወር reading challenge የተመረጠው መጽሐፍ፣ “ራእይን ማወቅ እና መኖር” የተሰኘው ነው፡፡

መጽሐፉን ለማንበብ ከአሁኑ በመመዝገብ ራሳችሁን አዘጋጁ፡፡

የንባብ ወር - ሚያዚያ / 2018

ለንባብ የተመረጠው መጽሐፍ - “ራእይን ማወቅ እና መኖር”

ንባቡ የሚጀመርበት ቀን - ሚያዚያ 1 / 2018

ንባቡ የሚጠናቀቅበት ቀን - ሚያዚያ 30 / 2018

ይህንን Book Club ለመቀላቀል፡- በዚህ 👉 @DrEyobmamo የቴሌግራም አድራሻ (user name) inbox በማድረግ ፍላጎታችሁን ስትገልጹ ሙሉ መረጃ ይላክላችኋል፡፡

Join now!!!
54👍9
የምርጫና የውሳኔዎቻችንን ጉዳይ!

የትናንትና ምርጫና ውሳኔያችንን ዛሬ እየኖርነው ነው፣ ወደድንም ጠላንም!
መልካም ውጤት ባላቸውና ውጤታቸው ደስ በማይሉን ምርጫና ውሳኔዎቻችን መካከል ያለውን ልዩነት ያመጣው ትክክለኛውን ሂደት ያለመከተላችን ሁኔታ ነው፡፡

ሂደቱ ብዙ ነገር ያካተተ ቢሆንም፣ ዋና ዋና የሆኑትን ሶስቱን ላስታውሳችሁ፡፡

1. ምርጫና ውሳኔ ከማድረጋችን በፊት ቆም ብለን እናስብ

አብዛኛው ውሳኔያችን የተዛባ የሚሆነው በጥድፊያና በሚገባ ሳናስብበት ስለምንወስን ነው፡፡ ከማንኛውም ምርጫና ውሳኔ በፊት ጊዜ ጊዜ መውሰድ አመለካከታችንን ያጠራልናል፣ የተለያዩ አማራጮችን እንድንመለከት ያስችለናል፣ እንዲሁም ጊዜ የሚፈታውን ሁኔታ ጊዜ እንዲፈታልን እድል ይሰጠናል፡፡

2. ሃሳባችንን በሚገባ እንጠይቅ

ማንኛውም ምርጫና ውሳኔያችን የሚነሳው ከሃሳባችን ነው፡፡ አንድን ነገር እናስባለን ከዚያም ድምዳሜ ላይ እንደርስና እንወስናለን፡፡ ይህንን ሂደት በቀላሉ ከመውሰድ በመቆጠብ በሃሳባችን የሚመጡትን ነገሮች በሚገባ በመጠየቅና እውነታው ጋር ለመድረስ ሂቱን በመከተል መስመር ልናስይዘው እንችላን፡፡
3. ከስሜታዊነት ይልቅ ምክንያታዊነትን እናስቀድም

የምርጫና የውሳኔ ወቅት ስሜታችን የተነሳሳበት ወቅት ነው፡፡ በአንድ ነገር ላይ ስሜት ሲጋጋል ምክንያታዊ መሆን ያስቸግረናል፡፡ ምክንያታዊ መሆን ማለት አንድ ውሳኔ ትክክለ መሆኑንና አለመሆኑን ከነምክንያቱ ማሰብና ድምዳሜ ላይ መድረስ ማለት ነው፡፡ ስለሆነም፣ ከስሜታዊነት ይልቅ ምክንያዊነትን እናስቀድም፡፡

መልካም ቀን!

LIKE & SHARE !!!

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
68👍12🔥1🤩1
7 ቀን ብቻ ቀረው !!!

የሚያዚያ
ወር Book Reading Challenge with Dr. Eyob

ለሚያዚያ ወር reading challenge የተመረጠው መጽሐፍ፣ “ራእይን ማወቅ እና መኖር” የተሰኘው ነው፡፡

መጽሐፉን ለማንበብ ከአሁኑ በመመዝገብ ራሳችሁን አዘጋጁ፡፡

የንባብ ወር - ሚያዚያ / 2018

ለንባብ የተመረጠው መጽሐፍ - “ራእይን ማወቅ እና መኖር”

ንባቡ የሚጀመርበት ቀን - ሚያዚያ 1 / 2018

ንባቡ የሚጠናቀቅበት ቀን - ሚያዚያ 30 / 2018

ይህንን Book Club ለመቀላቀል፡- በዚህ 👉 @DrEyobmamo የቴሌግራም አድራሻ (user name) inbox በማድረግ ፍላጎታችሁን ስትገልጹ ሙሉ መረጃ ይላክላችኋል፡፡

Join now!!!
29👍12😱1
አልፎ የመሄጃው መንገድ!

• ጥሩ ይሄድ የነበረ ስራ ሲበላሽ . . .

• ሰላምና የተረጋጋ የነበረው ውስጣችን ሲናጋ . . .

• ግሩም የነበረው የፍቅር ግንኙነት በድንገት ሲቋረጥ . . .

• ተስፋ አድርገነው የነበረው ነገር ውጤት ሳያመጣ ሲቀር . . .

• የጠበቅነው ሳይሆን፣ ያልጠበቅነው ሲሆን . . .

አልፈን የምንሄደው ፈጣሪ ወደዚህች ምድር ሲያመጣን ኖረን እንድናልፍ የሰጠንን ራእይ ስናገኘውና እሱን መከተል ስንጀምር ነው፡፡ ይህ ራእይ ከምንም ነገር ባሻገር አልፈን የመሄድን አቅም የሚሆነንን ታላቁ ስጦታችን ነው፡፡

ይህንን ራእይ የተሰኘ ድንቅ ነገር ለማወቅና ለመከተል የሚያግዛችሁን ልምምድ ከፈለጋችሁ የሚያዚያ ወር Book Reading Challenge ወሳኝ ነው!

ለሚያዚያ ወር reading challenge የተመረጠው መጽሐፍ፣ “ራእይን ማወቅ እና መኖር” የተሰኘው ነው፡፡

መጽሐፉን ለማንበብ ከአሁኑ በመመዝገብ ራሳችሁን አዘጋጁ፡፡

የንባብ ወር - ሚያዚያ / 2018

ለንባብ የተመረጠው መጽሐፍ - “ራእይን ማወቅ እና መኖር”

ንባቡ የሚጀመርበት ቀን - ሚያዚያ 1 / 2018

ንባቡ የሚጠናቀቅበት ቀን - ሚያዚያ 30 / 2018

ይህንን Book Club ለመቀላቀል፡- በዚህ 👉 @DrEyobmamo የቴሌግራም አድራሻ (user name) inbox በማድረግ ፍላጎታችሁን ስትገልጹ ሙሉ መረጃ ይላክላችኋል፡፡

Join now!!!
43👍21🔥1😱1
ጊዜ አባካኞች!

“እውነተኛው ችግራችን እድሜያችን አጭር የመሆኑና ፈጥኖ የማለፉ ጉዳይ ሳይሆን ጊያችንን ለማይሆን ነገር የማቃጠላችን ጉዳይ ነው” (Daily Wisdom)

ጊዜያችንን በሚገባ ከተጠቀምንበት ፈጣሪ በቂ እድሜ ሰጥቶናል፡፡ ይህንን የተሰጠንን እድሜ ከጊዜ አባካኝ ሁኔታዎች መጠበቅ የእኛ ድርሻ ነው፡፡

ጊዜ አባካኞች

1. ስላለፈውና መለወጥ ስለማንችለው ነገር በጸጸት መኖር

ትክክለኛው አማራጭ፡- ካለፈው በመማር ስህተትን አለመድገምና ለወደ ፊቱ ራስን ማዘጋጀት፡፡

2. ስለወደፊቱና ገና ለገና ሊሆን ይችላል ስለምንለው ነገር መጨነቅ
ትክክለኛው አማራጭ፡- ራስን ማሻሻል፣ ለነገው በሚገባ ማቀድ፣ ጸሎት ማድረግና ወደ ፊት መራመድ፡፡

3. የማንተገብረውን ነገር እያሰቡ በቀን ህልም መኖር

ትክክለኛው አማራጭ፡- የሕየወታችንን ዋና ዓላማ ለይቶ ማወቅ፣ በዚያ ዓላማ አንጻር ግብን ማውጣት፣ ራስን ማሻሻልና ወደ ግባችን መንቀሳቀስ

4. ሰዎች በእኛ ላይ ስላላቸው አመለካከት አብዝቶ ማሰብ
ትክክለኛው አማራጭ፡- ሰዎች ስለ እኛ የሚስቡት ነገር የእኛን ሁኔታ ሳይሆን የእነሱኑ አመለካት እንደሚያንጸባርቅ መገንዘብና የራስ ስራ ላይ ማተኮ፡፡

LIKE & SHARE !!!

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
47👍31🤩3🔥2
6 ቀን ብቻ ቀረው !!!

የሚያዚያ
ወር Book Reading Challenge with Dr. Eyob

ለሚያዚያ ወር reading challenge የተመረጠው መጽሐፍ፣ “ራእይን ማወቅ እና መኖር” የተሰኘው ነው፡፡

መጽሐፉን ለማንበብ ከአሁኑ በመመዝገብ ራሳችሁን አዘጋጁ፡፡

የንባብ ወር - ሚያዚያ / 2018

ለንባብ የተመረጠው መጽሐፍ - “ራእይን ማወቅ እና መኖር”

ንባቡ የሚጀመርበት ቀን - ሚያዚያ 1 / 2018

ንባቡ የሚጠናቀቅበት ቀን - ሚያዚያ 30 / 2018

ይህንን Book Club ለመቀላቀል፡- በዚህ 👉 @DrEyobmamo የቴሌግራም አድራሻ (user name) inbox በማድረግ ፍላጎታችሁን ስትገልጹ ሙሉ መረጃ ይላክላችኋል፡፡

Join now!!!
21👍4🔥1
የራእይ እና የራስ-በራስ ግምት ግንኙነት

“የራስ በራስ ግምት” (self esteem) ማለት እኛ ራሳችን በራሳችን ላይ የምናስቀምጠው የዋጋ ተመን ማለት ነው፡፡

በራሳችን ላይ ያለን ግምት እና ምልከታ እጅግ የወረደ ከሆነ ምናልባት የግል ራእይ በሚገባ ያለማወቅ ወይም እያወቁ አካሄዱን በሚገባ ያለመገንዘብ ምልክት ሊሆን ይችላል፡፡

ራእያቸውን በሚገባ አውቀው የሚከተሉ ሰዎች ከሁሉም በፊት በራሳቸው ላይ ያላቸው ግምት ልኩን ይይዛል፡፡ አጉል ከፍም፣ አጉል ዝቅም አይልም፡፡

ራእያቸውን ያላወቅ ሰዎች በራሳቸው ያላቸው ግምት ወረድ ስለሚል በአንድ በኩል የዝቅተኝነትን ስሜት በቀጥታ ሲያንጻባርቁ፣ በሌላ በኩል ደግሞ ያላቸውን መስመር ያልያዘ ሕይወት ለማስመሰል አሁል የበላይነትን ሁኔታ ሊያሳዩ ይችላሉ - ሳያስቡት!

የዚህ ሁኔታ መፍትሄው ራእይን ማወቅ ነው፡፡ ይህንን ራእይ የተሰኘ ድንቅ ነገር ለማወቅና ለመከተል የሚያግዛችሁን Book Reading Challenge ቀርቦላቸኋል!

ለሚያዚያ ወር reading challenge የተመረጠው መጽሐፍ፣ “ራእይን ማወቅ እና መኖር” የተሰኘው ነው፡፡

መጽሐፉን ለማንበብ ከአሁኑ በመመዝገብ ራሳችሁን አዘጋጁ፡፡

የንባብ ወር - ሚያዚያ / 2018

ለንባብ የተመረጠው መጽሐፍ - “ራእይን ማወቅ እና መኖር”

ንባቡ የሚጀመርበት ቀን - ሚያዚያ 1 / 2018

ንባቡ የሚጠናቀቅበት ቀን - ሚያዚያ 30 / 2018

ይህንን Book Club ለመቀላቀል፡- በዚህ 👉 @DrEyobmamo የቴሌግራም አድራሻ (user name) inbox በማድረግ ፍላጎታችሁን ስትገልጹ ሙሉ መረጃ ይላክላችኋል፡፡

Join now!!!
55👍22🔥1😱1
የዲሲፕሊን እና የራእይ ግንኙነት

“ዲሲፕሊንን ማዳበር” ማለት ከአንድ ዓላማ አንጻር አንድን ማድረግ ያለብኝን ነገር የወቅቱ ስሜቴ ቢፈቅድም ባይፈቅድም ማድረግ፣ አንድን ማድረግ የማይገባኝን ነገር ምንም ያህል የማድረግ ፍላጎቱ ቢኖረኝም አለማድረግ ማለት ነው፡፡

ከላይ ከተጠቀሰው የዲሲፕሊን ትርጉም አንጻር ራሳቸውን ሲያዩት ብዙ ሰዎች ዲሲፕሊን ያለው ሕይወት ለመኖር ሲታገሉ ራሳቸውን ያገኙታል፡፡

ይህ የሆነበት ምክንያት አንድን ዲሲፕሊን ለማዳበር ሲነሱ ከምንም ተጨባጭ ዓላማ ጋር ስለማያገናኙት ነው፡፡

በአጭሩ ሲገለጽ፣ ራእያችንን ከላወቅነውና ከዓላማ አንጻር የማንኖር ከሆነ ዲሲፕሊንን ለማዳበር ያስቸግረናል፡፡

በሕይወታችን አንድን ዲሲፕሊን ለማዳበር፣ በመጀመሪያ፣ ዲሲፕሊን ለማዳበር የፈለግንበትን ዓላማ ለይቶ ማወቅ፣ ሲቀጥል፣ የያዝነው ዓላማ የሚጠይቀውን ዲሲፕሊን ለይቶ ማወቅ፣ በመጨረሻም፣ ልምምዱን መጀመር፣ አለማቆም፣ ሲያቆሙ እንደገና ልማድ እስከሚሆን ድረስ መቀጠል፡፡

የዚህ ሁሉ ሂደት መነሻው ራእይን ማወቅ ነው፡፡ ይህንን ራእይ የተሰኘ ድንቅ ነገር ለማወቅና ለመከተል የሚያግዛችሁ Book Reading Challenge ቀርቦላችኋል!

ለሚያዚያ ወር reading challenge የተመረጠው መጽሐፍ፣ “ራእይን ማወቅ እና መኖር” የተሰኘው ነው፡፡

መጽሐፉን ለማንበብ ከአሁኑ በመመዝገብ ራሳችሁን አዘጋጁ፡፡

የንባብ ወር - ሚያዚያ / 2018

ለንባብ የተመረጠው መጽሐፍ - “ራእይን ማወቅ እና መኖር”

ንባቡ የሚጀመርበት ቀን - ሚያዚያ 1 / 2018

ንባቡ የሚጠናቀቅበት ቀን - ሚያዚያ 30 / 2018

ይህንን Book Club ለመቀላቀል፡- በዚህ 👉 @DrEyobmamo የቴሌግራም አድራሻ (user name) inbox በማድረግ ፍላጎታችሁን ስትገልጹ ሙሉ መረጃ ይላክላችኋል፡፡

Join now!!!
57👍6🔥2
5 ቀን ብቻ ቀረው !!!

የሚያዚያ ወር Book Reading Challenge with Dr. Eyob

ለሚያዚያ ወር reading challenge የተመረጠው መጽሐፍ፣ “ራእይን ማወቅ እና መኖር” የተሰኘው ነው፡፡

መጽሐፉን ለማንበብ ከአሁኑ በመመዝገብ ራሳችሁን አዘጋጁ፡፡

የንባብ ወር - ሚያዚያ / 2018

ለንባብ የተመረጠው መጽሐፍ - “ራእይን ማወቅ እና መኖር”

ንባቡ የሚጀመርበት ቀን - ሚያዚያ 1 / 2018

ንባቡ የሚጠናቀቅበት ቀን - ሚያዚያ 30 / 2018

ይህንን Book Club ለመቀላቀል፡- በዚህ 👉 @DrEyobmamo የቴሌግራም አድራሻ (user name) inbox በማድረግ ፍላጎታችሁን ስትገልጹ ሙሉ መረጃ ይላክላችኋል፡፡

Join now!!!
19👍7🔥2
ራእይ እያለ ልክ እንደሌለ!
👍51
ራእይ እያለ ልክ እንደሌለ!

አንዳንድ ሰዎች አስገራሚ የሆነ ራእይ እያላቸው ምንም ነገር ሳያከናውኑ ከአመት ወደ አመት ይሻጋገራሉ፡፡ ይህ ከሚሆንባቸው መንስኤዎች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፡፡

1. ፍርሃት

ራእይ እያለን ልክ እንደሌለን እንድንኖር የሚያደርጉን ምክንያቶች በርካታ ናቸው፡፡ ለምሳ፣ ባይሳካስ፣ ከጀመርኩኝ በኋላ ቢቋረጥስ፣ ደጋፊ ባጣስና የመሳሰሉት አይነት የፍርሃት ምንጮች ተጠቃሽ ናቸው፡፡
ይህንን እንቅፋት ለማለፍ፣ ፍርሃትን የማሸነፊያው ዋነኛ መንገድ ጥበብ በቶሞላበት ጥናት ላይ የተደገፈ እርምጃ መውሰድ እንደሆነ ማስታወስ ጠቃሚ ነው፡፡

2. የቁጥጥር ሰለባ መሆን

ራእይ እያለን ልክ እንደሌለን እንድንኖር የሚያደርጉን ምክንያቶች መካከል፣ ከፍቅር ወይም ከትዳር አጋር፣ እንዲሁም ከወላጆችና ከቤተሰብ ድጋፍን ማጣትና ክልከላን ማስተናገድ፡፡

ይህንን እንቅፋት ለማለፍ፣ ያሰብነውና የምናቅዳቸው ነገሮች ትክክለኛ መሆናቸው ካረጋገጥን በኋላ ለእነዚህ ሰዎች ያለንን አቋም በግልጽነትና በተረጋጋ ሁኔታ በመግለጽ ማድረግ የሚገባን ነገር ላይ ማተኮ አስፈላጊ ነው፡፡

ከላይ በተጠቀሰው ሁኔታ እና በመሰል ዘርፎች ዙሪያ መመሪያ እና ንቃተ-ህሊና ለማግኘት የሚያግዛችሁን Book Reading Challenge አዘጋጅቼላችኋለሁ!

ለሚያዚያ ወር reading challenge የተመረጠው መጽሐፍ፣ “ራእይን ማወቅ እና መኖር” የተሰኘው ነው፡፡

መጽሐፉን ለማንበብ ከአሁኑ በመመዝገብ ራሳችሁን አዘጋጁ፡፡

የንባብ ወር - ሚያዚያ / 2018

ለንባብ የተመረጠው መጽሐፍ - “ራእይን ማወቅ እና መኖር”

ንባቡ የሚጀመርበት ቀን - ሚያዚያ 1 / 2018

ንባቡ የሚጠናቀቅበት ቀን - ሚያዚያ 30 / 2018

ይህንን Book Club ለመቀላቀል፡- በዚህ 👉 @DrEyobmamo የቴሌግራም አድራሻ (user name) inbox በማድረግ ፍላጎታችሁን ስትገልጹ ሙሉ መረጃ ይላክላችኋል፡፡

Join now!!!
60👍20🔥3
እንደገና መጀመር ግድ ሲሆን!
👍6
እንደገና መጀመር ግድ ሲሆን!

አንዳንድ ጊዜ በአንድ አቅጣጫ ብዙ ከተጓዛችሁ በኋላ በነገሩ ትክክለኛነት፣ አትራፊነትም ሆነ አዛላቂነት ጥያቄ ይመጣባችኋል፡፡
ከሁሉም በፊት ማስታወስ ያለባችሁ፣ በአንድ አቅጣጫ ብዙ ስለተጓዛችሁ ወይም ብዙ ነገራችሁን “ኢንቨስት” ስላደረጋችሁ ብቻ በዚያው መቀጠል አለባችሁ ማለት አይደለም፡፡

ይህንን ስህተት እንድንሰራ የሚያደርጉን የሚከተሉት ስሜቶች ናቸው፡፡

1. የመክሰር ስሜት

2. የስኬተ-ቢስነት ስሜት

3. ተስፋ የማይቆርጡ እንደሆኑ የማስመስከር ስሜት

በእነዚህና በመሰል ስሜቶች ከመነዳት ይልቅ አንድን ጥያቄ ጠይቀን እንጀምር፡- “ዛሬ አዲስ የመጀመር እድል ቢኖረኝ ያንንው ነገር የማድረግና የመከተል ፍላጎቱ ይኖረኛል?

ይህንን ጥያቄ በሚገባ ከመለስን በኋላ የሚከተሉትን ሶስት አማራጮች በሚገባ ልናስብባቸውና ትክክለኛውን መንገድ ልንከተል ይገባናል፡፡

ምርጫ አንድ፡- የጀመርነውን ነገር መቀጠል

ይህንን ምርጫ ከወሰድን፣ ለሁኔታው ሙሉ ሃላፊነት መውሰድ ይኖርብናል፡፡ መነጫነጭ በማቆም፣ እንደገና በሚገባ በማሰብና አዲስ ኃይ በማሰባሰብ ወደ ፊት ለመቀጠል መዘጋጀት አስፈላጊ ነው፡፡

ምርጫ ሁለት፡- አቅጣጫን ማስተካከልና መቀየር

ይህንን ምርጫ ከወሰድን፣ እንደገና ከመጀመር ይልቅ አደራረጋችንን መቀየር፣ በራሳችንም ሆነ በሁኔታችን ላይ ያለንን አመለካከት መቀየርና በጥንቃቄ ለውጡን መምራት አስፈላጊ ነው፡፡

ምርጫ ሶስት፡- ሁሉን ነገር በማቆም እንደ አዲስ መጀመር

ይህንን ምርጫ ከወሰድን፣ ስር ነቀል ለውጥ በማድረግ፣ አድካሚ የሰው-ለሰው ግንኙነቶችን መለወጥ፣ ከዓላማችን ጋር የማይሄዱ የትምህርትም ሆነ የስራ ዘርፎቸን ቀየርና ከግል እሴቶቻችን ጋር የማይጣጣሙትን እንደገና መከለስ አስፈላጊ ነው፡፡

ለሶተኛው ምርጫ ተጨማሪ ምክሮች

• ማንኛውንም ነገር እንደገና መጀመር እንደሚቻል እናስታውስ!

• ከሁኔታዎች ጋር ትስስር ብንፈጥርም ታስረን ላለመቅረት መወሰን እንደምንችን አንዘንጋ!

• ከተጓዝነው ረጅም ርቀት ይልቅ የተጓዝንበት አቅጣጫ ወሳኝ እንደሆነ በመገንዘብ ቆራጥ እንሁን!

LIKE & SHARE !!!

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
84👍23🔥9