የሚለቀቀውና የሚያዘው!
ላላገባችሁ . . .
“የሰውን አእምሮ የሚያዞሩ ሁለት አስቸጋሪ ጉዳዮች አሉ፡፡ ከእኛ ጋር አብሮ መቆየት የማይፈልግን ሰው እንዴት እንዲቆይ ማድረግ ይቻላል? ከእኛ ተለይቶ ለመሄድ የማይፈልግን ሰውስ እንዴት እንዲሄድ ማድረግ ይቻላል? - Danny Devito
አሁን ባለንበት ዘመን ያላገቡ ወጣቶችን ስሜት ለቀውስ የሚዳርጉ ሁለት ልምምዶችን የሚገልጽ አባባል ነው፡፡
1) ያፈቀራችሁት ሰው “አልፈልግም፣ እሄዳለሁ” ሲል ወይም 2) “አልፈልግም እሄዳለሁ” ያላችሁት ሰው “ሞቼ እገኛለሁ” ሲል ማድረግ የሚገባችሁን ካላወቃችሁ የሚደርስባችሁ የስሜት ቀውስ ረጅም ዘመን የሚከተል ሊሆን ይችላል፡፡
ያፈቀራችሁት ሰው “አልፈልግም፣ እሄዳለሁ” ሲል ያላችሁ ምርጫዎች:-
1. በልመና፣ በለቅሶና በተስፋ-ቢስነት እንዳይሄዱ ለማድረግ ሲታገሉ መክረም፡፡
2. በግዳጅ፣ በዛቻና መግቢያ መውጪያ በማሳጣት እንዳይሄዱ ለማድረግ መታገል፡፡
3. ስሜትን በትክክል ከገለጹ በኋላ እምቢታቸውን በመቀበል መልቀቅና ራስ ላይ በመስራት ጉዞን መቀጠል፡፡
የትኛው ውሳኔ ይሻላል? ለምን?
“አልፈልግም፣ እሄዳለሁ” ያላችሁት ሰው “ሞቼ እገኛለሁ” ሲል ያላችሁን ምርጫ እንመለስበታለን፡፡
https://t.me/Dreyob
https://m.youtube.com/user/naeleyob623
https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

❤90👍83🎉4😁2
የሚለቀቀውና የሚያዘው!
ላላገባችሁ . . .
. . . ካለፈው የቀጠለ
“የሰውን አእምሮ የሚያዞሩ ሁለት አስቸጋሪ ጉዳዮች አሉ፡፡ ከእኛ ጋር አብሮ መቆየት የማይፈልግን ሰው እንዴት እንዲቆይ ማድረግ ይቻላል? ከእኛ ተለይቶ ለመሄድ የማይፈልግን ሰውስ እንዴት እንዲሄድ ማድረግ ይቻላል? - Danny Devito
አሁን ባለንበት ዘመን ያላገቡ ወጣቶችን ስሜት ለቀውስ የሚዳርጉ ሁለት ልምምዶችን የሚገልጽ አባባል ነው፡፡
ቀደም ባለው “ፖስቴ” የዚህን ሃሳብ ክፍል አንድ ያሰፈርኩኝ ስለሆነ እሱን መለስ በማለት ማንበባችሁን አትርሱ፡፡
እንደዚህ ብለን ነበር፡- ያፈቀራችሁት ሰው “አልፈልግም፣ እሄዳለሁ” ሲል ወይም “አልፈልግም እሄዳለሁ” ያላችሁት ሰው “ሞቼ እገኛለሁ” ሲል ማድረግ የሚገባችሁን ካላወቃችሁ የሚደርስባችሁ የስሜት ቀውስ ረጅም ዘመን የሚከተል ሊሆን ይችላል፡፡
“አልፈልግም፣ እሄዳለሁ” ያላችሁት ሰው ሞቼ እገኛለሁ ሲል ያላችሁ ምርጫዎች፡-
1. ስሜታቸው እንዳይጎዳ በማለት የማትፈልጉት አይነት ግንኙነት ውስጥ መግባት፡፡
2. ስለ እኔ ያላቸውን መረጃ በመጠቀም ወይም በሌሎች መንገዶች ይበቀሉኛል በሚል ፍርሃት መንቀሳቀስ አለመቻል፡፡
3. ስሜትን በትክክል ከገለጹ በኋላና በቂ ማብራሪያ ከሰጡ በኋላ ተገቢውንና ትክክለኛውን ውሳኔ በማድረግ ሰዎች የራሳቸው ስሜት ላይ እንዲሰሩ ጊዜ መስጠት፡፡

👍119❤33🔥1
ከስህተት ወደ ስኬት!
“በፍጹም ልቀይራቸው የማልችላቸውን ስህተቶች ሰርቼ አውቃሁ፡፡ ነገር ግን፣ ያንንው ስህተት ደግሜ መስራት እስከማልችል ድረስ ለመልካም ተለውጬበታለሁ” (Steve Harvey)
ሕይወታችሁ “ከስህተት ወደ ስህተት” ሳይሆን “ከስህተት ወደ ስኬት” እንዲሆን ከፈለጋችሁ እኔ እንዳደረኩት የSteve Harveyን ምክር እንድትሰሙ ላደፋፍራቸሁ፡፡
የሚንቀሳቀስ ሰው ስህተትን የሚሰራ ሰው ነው፡፡ ስህተትን ላለመስራት ካለው ፍርሃት የተነሳ የማይንቀሰቀስ ሰው ደግሞ በፍርሃት ያለመንቀሳቀስንና የኋላ ቀርነትን ስህተት እየሰራ ነው፡፡
አንዳንዶቹ ስህተቶቻችን ምንም ብንታገል ውጤቱን መቀየር አንችልም፡፡ ስለሆነም፣ ከሁኔታው ትምህርትን አግኝተን ወደፊት ተመሳሳይ ስህተት እንዳይደገም በመጠንቀቅ ወደፊት እንድንቀጥ እንመከራለን፡፡
እባካችሁ በፍጹም ሊተካ የማይችለውን ውድ ጊዜያችሁን፣ መቀየር የማትችሉትን ስህተት ባመብሰልሰል አታባክኑት፡፡
እባካችሁ አንዴ ከተዛባ ሌላ ቀውስን ሊወልድ የሚችለውን የጤንነታችሁን ሁኔታ፣ መቀየር ስለማትችሉት ስህተት በመጨነቅ አታበላሹት፡፡
እባካችሁ ብትጠቀሙበት የወደፊት ሕይወታችሁን ስኬታማ ሊያደርግ የሚችለውን እምቅ አቅማችሁን፣ መቀየር የማትችሉትን ስህተት ስታወጡና ስታወርዱ አታዳፍኑት፡፡

👍241❤77🔥23😱3😁1🎉1
እኔ እና ፈጣሪዬ!!!
እኔ ከፈጣሪዬ ጋር ሆኜ ብቻዬን በመሆን ሙሉ ሰው ነኝ!
ከእኔ ቁጥጥር ውጪ የሆኑ ሁኔታዎች እያሉ እንኳን ሙሉ ሰው ነኝ!
ከእኔ ጋር መሆን የማይፈልጉ ሰዎች እያሉ እንኳን ሙሉ ሰው ነኝ!
ይሳካሉ ብዬ የጠበቀኳቸው ነገሮች ባይሳኩም እንኳን ሙሉ ሰው ነኝ!

👍370❤197🔥25🎉2
ራሳችሁን ምነው ችላ አላችሁት ??? !!!
• ሌሎች ሰዎችን የምትወዱትን ያህል ራሳችሁን ብትወዱ . . .
• የሌሎች ሰዎች ሰሜት እንዳየጎዳ የምትጠነቀቁትን ያህል የራሳችሁ ስሜት እንዳይጎዳ ብትጠነቀቁ . . .
• ለሰዎች ጥቅምና እድገት የመሯሯጣችሁን ያህል ራሳችሁን ለመጥቀምና ለማሳደግ ብትተጉ . . .
• ሰዎችን ለማስደሰት ስትሉ ጊዜን የመስጠታችሁን ያህል ለራሳችሁ ጊዜን ብትሰጡ . . .
• ሰዎቹን ላለማጣት ስትሉ ተገቢ ላልሆነው ነገር ሁሉ እሺ የማለታችሁን ያህል ራሳችሁን ላለማጣት ደግሞ እምቢ ማለትን ብትለማዱ . . .
ራሳችሁን አክብራችሁ፣ አሳድጋችሁና ጠብቃችሁ ለእነሱም በተረፋችሁ ነበር፡፡ አለዚያ ግን በቅድሚያ ራሳችሁን፣ ሲቀጥል ደግሞ ሌሎችን መጉዳታችሁ አይቀርም፡፡
እነዚህን ልምምዶች እስከምታዳብሩ ድረስ የትክክለኛ ነጻነትን ሕይወት ጣእም አታውቁትም፡፡
በአንዴ ላይሆን ቢችልም ቀስ በቀስ ልመዱት!

❤351👍154🔥11🎉7🤩7
የጠፋብን ውስጥ፣ የምንፈልገው ውጭ
አንድ ሰው አንድ ቀን ማታ እቤቱ እያለ ውድ የተባሉ እቃዎቹን ከሚያስቀምጠበት ሳጥን ውስጥ አንድ በጣም የሚወደውን ዳይመንድ መርጦ አወጣና በእጁ ይዞ እየተመለከተው ሳለ፣ በድንገት መብራጥ ጠፋበት፡፡
ልክ መብራቱ እንደጠፋበት በእጁ የያዘው ውድ ዳይመን ከእጁ አመለጠውና ወደቀ፡፡ ወዲያውኑ ሊፈልገው ቢሞክርም ጨለማ ነበረና የት እንደገባ እስከማይገኝ ድረስ ጠፋበት፡፡ ብዙ ሞክሮ ሲደክመው ከቤቱ ወጣ ሲል የመንገድ መብራቶች አካባቢውን ደመቅ አድርገው አብርተውት ተመለከተ፡፡ ከዚያም፣ “የጠፋብኝን ዳይመንድ እቤቴ ጨለማ ስለሆነ ስላላገኘሁት እዚህ ብርሃን ያለበት ቦታ ልፈልገው” ብሎ በማሰብ መፈለጉን ተያያዘው፡፡
ያንን በማድረግ ላይ እያለ አንድ በአካባቢው የሚዘዋወር ፖሊስ አገኘውና፣” ምን እየፈለክ ነው” አለው፡፡
ሰውዬውም መልሶ፣ “ዳይመን ከእጄ ወድቆ ጠፍቶብኝ ነው” አለው፡፡
ፖሊሱም ትንሽ ካፋለገው በኋላ ሲደክመው፣ “ለመሆኑ የቱ ጋር ነው የጠፋብህ” ብሎ ጠየቀው፣ ሰውየው፣ የጠፋብኝማ እቤቴ ነው፣ ነገር ግን እቤቴ መብራት ስለሌለና ጨለማ ስለሆነብኝ ነው እዚህ መብራት ያለበት ቦታ መፈለግ የጀመርኩት” አለው ይባላል፡፡
የብዙዎቻችን ችግር ይህ ይሆን! እኛው ውስጥ የጠፋብንን ነገር ሌላ ቦታ፣ ሌላ ሰው ጋር፣ ሌላ ሁኔታ ውስጥ ስንፈልግ መባዘናችን! እኛው ጋር ካለው የዝቅተኝነት ስሜት፣ ራስን ያለመቀበል ቀውስ፣ የመገፋት ህመምና የመሳሰሉት “ጨለማዎች” የሰወረብንን ውድ ነገር ሌላ ቦታ እንፈልገዋለን፡፡
“ሰዎች ቢቀበሉኝ እኮ . . .” እንላለን፣ ከተቀበሉን በኋላ ደግሞ ሰዎቹ ትተውን እንዳይዱ እንጨነቃለን፡፡ “ሃብት ብናገኝ እኮ . . .” እንላለን፣ ካገኘን በኋለ ደግሞ ሃብቱ እንዳይከስር ስንጨነቅ ቁጭ ብለን እናድራለን፡፡ “ዝነኛ ብሆንና Follower ባገኝ እኮ . . .” እንላለን፣ ካገኘን በኋላ ግን እያንድንዱ unfollow ያደረገን ሰው ሁኔታ ይጫጫነናል፡፡
ውስጣችሁ የጠፋባችሁን ነገር ሌላ ቦታ አትፈልጉት፤ ፈጽሞ አታገኙትም፡፡ በመጀመሪያ የጨለመባችሁንና ግራ የገባችሁን ነገር ፈጣሪ ይፍታላችሁ፡፡

Telegram
Dr. Eyob Mamo
Life skill development!
You can contact me
@DrEyobmamo
You can contact me
@DrEyobmamo
❤302👍202
የአንደበታችን ጉልበት!
አንድ ቀን የአምፖል ፈጣሪው ቶማስ ኤዲሰን ከትምህርት ቤት ወደ ቤቱ ሲመጣ ለእናቱ አንድን ወረቀት ሰጣትና “መምህሬ ይህንን ወረቀት ሰጠኝ እና ለእናትህ ብቻ በእጇ ስጥ ብሎ ነገረችኝ” አላት።
እናትዬው አይኖቿ እምባ እያቀረራቸው እንዲህ ስትል ለልጇ አነበበችለት፣ “ልጅሽ እጅግ አዋቂና ሊቅ ነው። ይህ ትምህርት ቤት ለእሱ በጣም የማይመጥንና ትንሽ ነው እና እሱን ለማሰልጠን ብቁ የሆኑ አስተማሪዎች ባለመኖራቸው ተመልሶ እንዳይመጣ፣ እዚያው እቤቱ አስተምሩት”፡፡
ከብዙ አመታት በኋላ፣ የቶማስ ኤዲሰን እናት ከሞተች በኋላ እና እሱም በአለም ላይ ካሉት ታላላቅ ፈጣሪዎች አንዱ ወደመሆን ከመጣ በኋላ፣ አንድ ቀን የቤተሰቡን የቆዩ ነገሮች ሲመለከት በድንገት በጠረጴዛው መሳቢያው ውስጥ በጥግ በኩል አንድ የታጠፈ ወረቀት አየ።
አንስቶም ከፈተው። በወረቀቱ ላይ እንዲህ የሚል ጽሑፍ አለ፡- “ልጅሽ ቶማስ ኤዲሰን የዘገምተኛነት ችግር ያለበት ልጅ ነው፡፡ ከአሁን በኋላ ወደ ትምህርት ቤት እንዲመጣ አንፈቅድለትም”፡፡
ትዝ ሲለው፣ ለካስ ያን ጊዜ ከትምህርት ቤት ይዞ የመጣው ትክክለኛ ጽሑፍ ይህ ነበር፡፡ እናት ግን ያን ጊዜ ይህንን ሃሳብ ባለመቀበልና በእሱ ላይ ላለመናገር በመወሰን ለውጣ እንዳነበበችለት ተገነዘበ፡፡
ቶማስ ኤዲሰን ለሰዓታት ካለቀሰ በኋላ በማስታወሻ ደብተሩ ላይ እንዲህ ሲል ጻፈበት፣ "ቶማስ ኤዲሰን የአዕምሮ ጉድለት ያለበት ልጅ ነበር፣ ጀግና እናቱ ግን የክፍለ ዘመኑ ሊቅ ወደመሆን ቀየረችው"፡፡
• ወላጆች ከልጆቻችሁ ጋር ስላላችሁ መስተጋብር (interaction) ከዚህ ታሪክ ምን ተማራችሁ?
• መምህራን በተማሪዎች ላይ ሊኖችሁ ስለሚገባ አመለካከትና አቀራረብ ከዚህ ታሪክ ምን ፍሬ ነገር አገኛችሁ?
• የሃገር መሪዎች የምትመሩትን ሕዝብ በምን አይን ልትመለከቱትና እንዴትስ ልታስተናግዱት እንደሚገባችሁ ከዚህ ታሪክ ምን ቁምነገር አገኛችሁ?
• አንባቢዎቼስ በዙሪያችሁ የሚገኙ የቅርብና የሩቅ ሰዎችን በምን መልኩ ማስተናገድ እንደሚገባችሁ ከዚህ ታሪክ ምን ቁም ነገር ቀረላችሁ?

👍307❤122🔥19🤩4
የስራና የትርፍ ሰዓቶቻችን ጉዳይ!
“በስራ ሰዓቶቻችን ወቅት የምናደርገው ነገር፣ የሚኖረንን ነገር ይወስናል፣ በትርፍ ሰዓታችን የምናደርገው ነገር ደግሞ ማንነታችንን ይወስናል” (Today's Wisdom)
የስራ ሰዓትን አስመልክቶ
በኑሮ ደረጃችሁና በገንዘብ አቅማችሁ ለማደግ ከፈለጋችሁ በስራ ሰዓታችሁ ወቅት የምትሰሩትን በሚገባ እወቁ፡፡ የሚያሳድጋችሁ ስራ ፍጠሩ፣ ያንንም በትጋት ስሩ፡፡
1. ብዙ ለፍታችሁ ጥቂት የሚከፍላችሁን ስራ ጉዳይ አስቡበት፡፡
2. ድግግሞሽና የበዛበትና በአመለካከት ወይም በእውቀት እንድታድጉ የማይሞግታችሁን ስራ ጉዳይ አስቡበት፡፡
የትርፍ ሰዓትን አስመልክቶ
በማንነትና በባህሪይ ልህቀት ለማደግ ከፈለጋችሁ በትርፍ ሰዓታችሁ የምታደርጓቸው ነገሮች ልክና ገደብ ያላቸው መሆናቸውን እርግጠኞች ሁኑ፡፡
1. የምትዝናኑባቸው ነገሮች ከአጉል ልማድና ሱስ የጸዱ የመሆናቸውን ጉዳይ አስቡበት፡፡
2. የትርፍ ጊዜ ማሳለፊያዎቻችሁ የአእምሮ እና የአካል እረፍትንም ጭምር የሚሰጧችሁ መሆናቸውን እርግጠኞች ሁኑ፡፡

❤206👍119🔥21😁3😢2
መርጣቸሁ ንገሩ
1. የወደፊት እቅዳችሁንና ዓላማችሁን
ጤናማዎቹ በማበረታታት ይደግፏችኋል፣ ቀናተኞቹ ግን ይቀኑባችሁና ያሰናክሉባችኋል፡፡
2. ስጋቶችና ፍርሃቶቻችሁን
ጤናማዎቹ በርቱ ብለው ያደፍፍሯችኋል፣ ጤናቢሶቹ ግን ይንቋችኋል፡፡
3. የሰራችኋቸውን ስህተቶችና ደካማ ጎናችሁን
ጤናማዎቹ በፍጹም ሳይለወጡባችሁ ከነስህተታችሁ ይቀበሏችኋል፣ ጤና ቢሶቹ ግን ከጀርባችሁ ሆነው ያወሩባችኋል፣ አንድ ቀን ጠብቀው ደግሞ ደካማ ጎናችሁን እናንተን ለመጉዳት ይጠቀሙበታል፡፡
የሚነገረውንና የማይነገረውን ለዩ፡፡ ለማን እንደሚነገርና ለማን እንደማይነገር ለዩ፡፡ ብልህ ሁኑ፡፡

👍201❤68🔥7😁1
ጥያቄ፡-
ዶ/ር አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ፡፡ አንዳንድ ጊዜ በሃገራችን የምንመለከተው ነገር ግራ ይገባኛል፡፡ በአንዳንድ መስሪያቤቶችና አብዛኛውን ጊዜ ደግሞ በሃገር ደረጃ አንድ ከሕዝብ ጋር የተገናኘ ሕግ ሲወጣ ሕዝቡ ሕጉን ተከትሎ ማስተካከል ላለበት ነገር የሚሰጠው ጊዜ በጣም አጭር ነው፡፡ ይህን ሁኔታ ከአመራር አንጻር ሲታይ መንስኤው ምን ይመስልሃል?
መልስ፡-
የጠቀስከውን ሃሳብ ሰዎች ከብዙ አቅጣጫ ተመልክተው ማብራሪያ ሊሰጡበት ይችላሉ፡፡ ከአመራር አንጻር ሲታይ ግን የሚከተሉትን መንስኤዎች መመልከት እንችላለን
1. ያልተደራጀ የአሰራር ስልት (system)
ማንኛውም ሕዝብ-ነክ አመራር በሚገባ የተደራጀና በየጊዜው የማይለዋወጥ የአሰራር ስልት ከሌለው፣ በታሰበበት መልኩ (proactive በመሆን) አቅዶ ከመስራት ይልቅ፣ ለመጣው ችግር ምልሽ በመስጠት (reactive በመሆን) ድንገተኛ ሕግን ያወጣል፡፡ ይህ ሕግ ደግሞ፣ “ከዛሬ ጀምሮ ይህ ነገር አይፈቀድም. . . ከነገ ጀምሮ ያኛው ነገር ተከልክሏል . . .” አይነት ባህሪይ ይኖረውን ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል፡፡
2. የመሪዎች መለዋወጥና የቅብብሎች ጉድለት
በማንኛውም ሕዝብ-ነክ ተቋማት ውስጥ በተለያዩ ምክንያቶች መሪዎች በቦታቸው የማይጸኑ ከሆነ፣ በሄደው የተተካው መሪ የተረከበውን ስራ በራሱ መንገድ ለመተግበር ይነሳል፡፡ የመሪዎች በቶሎ መለዋወጥ፣ ካለፈው እንዲቀጥል የሚያደርገው የቅብብሎሽ ሂደት እንዲከተል ስለማይፈቅድ ድንገተኛ ሕጎችንና መመሪያዎችን እያስፈጸመ ይኖራል፡፡
3. ሕጉ የሚወጣበት የመነሻ ሃሳብ
አንዳንድ ሕጎች ፈጥነው ብቅ ብለው፣ ፈጥነው የሚያልፉት ሕጉን የሚያወጡት ሰዎች በስሜታዊነት፣ ከአንድ ጥቅም አንጻር ወይም ከተለያዩ የተዛቡ የመነሻ ሃሳቦች ሲያደርጉት ነው፡፡ ከትክክለኛ ግምገማ፣ ጥናት እና ለአጠቃላይ ባለድርሻዎች ከመጥቀሙ አንጻር ከልተነሳ ሁሉም ነገር አሁን በአሁን ይሆናል፡፡
4. የግንዛቤ አቅም ማነስ
በሕዝብ-ነክ አመራር ውስጥ የሚገኙ ሰዎች ማሕበራዊ ሂደትን አስመልክቶ ከፍተኛ ግንዛቤን ሊያዳብሩ ይገባቸዋል፡፡ ሕጉ ሲወጣ ሕጉ የሚነካቸውን ሰዎችን ሁኔታ በሚገባ ያለመገንዘብ፣ የሕጉን ጥቅም ብቻ ሳይሆን የጎንዮሽ ጉዳት አለማሰብና አለመዘጋጀት፣ የሕጉ ተፈጻሚነት የሚነካቸው ሰዎች ለስነ-ልቦናም ሆነ ለሌሎች ዝግጅቶች ምን ያህል ጊዜ እንደሚፈልጉ በትክክል አለመገንዘብ የመሳሰሉት ተጠቃሽ ናቸው፡፡
5. በሕግ አውጪዎቹና በአስፈጻሚች መካከል ያለ ክፍተት
አንዳንድ ጊዜ ሕግ አውጪዎቹና መመሪያ የሚያስተላልፉት መሪዎች ትክክለኛ መመሪያና የታሰበበትን መንገድ ተከትለው ሳለ፣ አስፈጻሚዎቹ ያንን ተገንዝበው የተጠበቀውን መንገድ ካልተከተሉ መሪዎቹ ምንም ያህል የተስተካከለን ነገር ቢያወጡም አፈጻጸሙ ግን የተቻኮለና ጎጂ ይሆናል፡፡ አንዳንዶቹ በግድ-የለሽነት፣ ሌሎቹ ደግሞ የሕጉን ሂደት ለመገንዘብ ብቃት ካመኖር ይህ ሁኔታ ይከሰታል፡፡
በጥያቄው የተጠቀሰው ችግር መነሻ ያም ሆነ ይህ፣ ሕዝብ-ነክ አመራር እጅግ ማስተዋልን፣ መረጋጋትንና ነገሮችን ግራና ቀኝ በማየት ከማመዛዘን ሊነሳ ይገባዋል፡፡
ሆኖም፣ መሪዎች ምንም ያህል ጥንቃቄ ቢያደርጉም፣ ሁሉንም ቀዳዳ ደፍነው ላይጨርሱ እንደሚችሉና ስህተት ሊሰሩ እንደሚችሉ ማሰብም መልካም ነው፡፡

👍140❤28😱3
ውብ ቀን እንዲሆንልን!
ፈጣሪ አዲስን ቀን ውብ አድጎና ያስለመደንን የጸሃይ ብርሃን፣ እስትንፋስና የሚያስብ አእምሮ ሲሰጠን የቀረው ስራ የእኛ ነው፡፡ ይህ ስራ ግማሹ ውሳኔያችን፣ ግማሹ ደግሞ ጥንካሬያችን ነው!
የዛሬዋ ቀን ውብ እንድትሆን ውሳኔን ይጠይቃል፡፡ ይህ ውሳኔ፣ ለአናሳ ነገር አለመደላደልን፣ በጎ በጎውን ማሰብን፣ ያለፈውንና ፈጽሞ የማይመለሰውን መርሳትን፣ በእቅድ መኖርንና የመሳሰሉት ያካትታል፡፡
የዛሬዋ ቀን ውብ እንድትሆን ጥንካሬንም ይጠይቃል፡፡ ይህ ጥንካሬ፣ ምንም ነገር ብናደርግ መለወጥና ማስወገድ የማንችላቸውን ነገሮች ተቋቁሞ ማለፍን፣ መውጣትና መስራትን፣ በተከፈተልን መስክ ንቁ ተሳትፎ ማድረግንና የመሳሰሉትን ያካትታል፡፡
የቀናችሁን ውበት የሰዎች አመለካከትና ንግግር አይወስንላችሁ፡፡ በተሳካውና ባልተሳካው ምክንያትም ቢሆን የቀናችሁን ውበት አትወስኑት፡፡
“ቀኔ ውብ ነው!!!” ብላችሁ ጀምሩ፡፡
ውብ እና የተባረከ ቅዳሜ ይሁንላችሁ!

👍262❤119🔥10🎉4🤩4
መቅደም ያለበት ነገር!
• ማንንም ከማድመጣችሁ በፊት በቅድሚያ ትክክል እንደሆነ ህሊናችሁ የሚመሰክርላችሁን እውነት አድምጡ፡፡
• ማንንም ከመፍራታችሁ በፊት በቅድሚያ ፈጣሪን ፍሩ!
• ስለማንም ሰው ሁኔታ ከሌሎች ሰዎች ጋር ከማውራታችሁ በፊት በቅድሚያ ስለራሳችሁ ጉዳይ ከራሳችሁ ጋር አውሩ!
• ማንንም ሰው ከማገዛችሁ በፊት በቅድሚያ ራሳችሁን አግዙ!
• ያልሆነላችሁንና የሆነባችሁን ከማሰላሰላችሁ በፊት በቅድሚያ የሆነላችሁንና ያልሆነባችሁን አሰላስሉ!
መልካም እሁድ!

👍320❤133😱5🎉5😁3😢2
ዓላማችሁ ላይ እስከምትደርሱ ድረስ!
• ዛሬ ጥሩ ያልሆኑ ሁኔታዎችን ታግሳችሁ ለማለፍ ፈቃደኛ መሆን ይኖርባችኋል!
• ዛሬ ማግኘት የማትፈልጉትን ሰው ለጊዜው ለማግኘት ፈቃደኛ መሆን ይኖርባችኋል!
• ዛሬ መስራት የማትፈልጉትን የስራ ዓይነት ለጊዜው ለመስራት ፈቃደኛ መሆን ይኖርባችኋል!
• ዛሬ እጅግ አስቸጋሪ ከሆነ “አለቃ” ስር ለጊዜው ለመቆየት ፈቃደኛ መሆን ይኖርባችኋል!
• ዛሬ መኖር በማትፈልጉበት ቤት ለጊዜው ለመኖር ፈቃደኛ መሆን ይኖርባችኋል!
• ዛሬ መናገር የሚያምራችሁን ነገር ለጊዜው ዝም ብላችሁ ለማለፍ ፈቃደኛ መሆን ይኖርባችኋል!
ዓላማችሁን ከመከተል ግን በፍጹም ወደ ኋላ እንዳትሉ!

👍340❤161🎉7😱6🤩5🔥4
በቀላሉ አልናወጥም!
የሚከተለውን የአቋም መግለጫ ከእኔ እንድትጋሩ ልሞግታችሁ!
ማንም ሰው ስለእምነቴ ምንም አይነት ጤና-ቢስ ነገር ቢያስብና ቢናገር ስሜቴን አይነካውም፤ ምክንያቱም የማምነውን በሚገባ ስለማውቅ!
ማንም ሰው ስለ ዘሬና ስለቆዳ ቀለሜ ምንም አይነት ጤና-ቢስ ነገር ቢያስብና ቢናገር በራሴ ላይ ያለኝን አመለካከት አይነካውም፤ ምክንያቱም የራሴንም ሆነ የሌላውን ዘርና የቆዳ ቀለም በመቀበልና በማክበር ስለተደላደልኩኝ፡፡
ማንም ሰው ስለመልክና ቁመናዬ ምንም አይነት ጤና-ቢስ ነገር ቢያስብና ቢናገር ስነ-ልቦናዬን አያቃውሰውም፤ ምክንያቱም ራሴን የተቀበልኩና ፈጣሪ በሰጠኝ ማንነቴ የምተማመን ሰው ስለሆንኩኝ!
ማንም ሰው ስለችሎታዬ ምንም አይነት ጤና-ቢስ ነገር ቢያስብና ቢናገር እምቅ አቅሜን አይቀንሰውም፤ ምክንያቱም ብርቱና ደካማ ጎኔን በሚገባ ለይቼ በብርታቴ ላይ ካለማቋረጥ እሰራሁ በመሆኔ!
ማንም ሰው ስለ ዓላማዬና ስለራእዬ ምንም ጤና-ቢስ ነገር ቢያስብና ቢናገር ከመንገዴ አይመልሰኝም፤ ምክንያቱም ዓላማዬ በሚገባ የማውቅና በዚያም የጸናሁ ሰው በመሆኔ!
እኔ ሙሉ የሆንኩኝ፣ ነገሩ በሚገባ የገባኝና በሕብረተሰቡ መካከል ከሚገኝ አጉል ተጽእኖ ነጻ የሆነኩኝ ሰው ነኝ!

👍261❤98🎉4🔥1🤩1
“የግል ሕይወትን ማደራጀት”
(Organizing personal life)
የonline (telegram) ስልጠና ቅድመ-ማስታወቂያ!
የግል ሕይወታችንን ካላደራጀን የትኛውም ስራችንን ማደራጀት ያስቸግረናል፡፡
በሃገራችን የምናያቸውና ሌላው ሕብረተሰብ የሚመኛቸው መልካም ልምምዶቻችን እንደተጠበቁ ሆነው፣ እኛም ራሳችንን መለስ ብለን ስንመለከት እንዲስተካከሉ የምንፈልጋቸው በርካታ ጎድለቶች አሉብን፡፡
ከእነዚህ ሊቃኙ ከሚገባቸው የሕይወት ዘይቤዎቻችን አንዱና አንጋፋው የግል ሕይወት አደረጃጀት ጉዳይ ነው፡፡
የዚህ ክህሎት ጉድለት ከሚንጸባረቅባቸው ሁኔታዎች ዋነኛው፣ አንድን ነገር ለመጀመር መታገላችን፣ የጀመርነውን ነገር የማቋረጣችን ሁኔታ ነው፡፡
በተጨማሪም የቱ ጋር ተጀምሮ ወደየት አቅጣጫ እንደሚሄድ አለማወቅ፣ በሕይወት አለማደግና ያላደግንበትን ምክንያት አለማወቅ፣ የኋላ ቀርነት ስሜትና የመሳሰሉት ሁኔታዎች ያልተደራጀ ሕይወት ምልክቶች ናቸው፡፡
የምንኖረው ውድድር በሞላበት ዘመን ነው፡፡ ተሻሽሎና ተሽሎ ለመገኘት ሕይወትን ማደራጀት የግድ ነው፡፡
ሙሉ ማስታወቂያውን በሚቀጥለው ሳምንት ይጠብቁ፡፡

👍205❤55😱2
ከነማንነታችሁ የሚወዷችሁ!
በምንም አይነት አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ለብቻችሁ እየታገላችሁና እየለፋችሁ እንደሆነ ቢሰማችሁም፣ ስለእናንተ ሁኔታ ምንም ግድ የማይሰጣቸው ሰዎች ከመኖራቸው በበለጠ ሁኔታ ካለምንም ቅድመ ሁኔታ የሚወዷችሁ ሰዎች እንዳሉ በማሰብ ልባችሁን ደግፉ፡፡
አይዟችሁ!
https://t.me/Dreyob
https://m.youtube.com/user/naeleyob623
https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
በምንም አይነት አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ለብቻችሁ እየታገላችሁና እየለፋችሁ እንደሆነ ቢሰማችሁም፣ ስለእናንተ ሁኔታ ምንም ግድ የማይሰጣቸው ሰዎች ከመኖራቸው በበለጠ ሁኔታ ካለምንም ቅድመ ሁኔታ የሚወዷችሁ ሰዎች እንዳሉ በማሰብ ልባችሁን ደግፉ፡፡
አይዟችሁ!
https://t.me/Dreyob
https://m.youtube.com/user/naeleyob623
https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
❤271👍90🔥17😢2🎉1🤩1
ለራሳችሁ ያልሰጣችሁትን ነገር ከሰው አትጠብቁ!
ሰዎች እንዲሰጧችሁ የምትፈልጉትን ማንኛውም ነገር በመጀመሪያ ለራሳችሁ መስጠትን ተማሩ፡፡
• በሰዎች መወደድ ከፈለጋችሁ በመጀመሪያ ራሳችሁን ውደዱ፡፡
• በሰዎች ተቀባይነት ማግኘት ከፈለጋችሁ በመጀመሪያ ራሳችሁን ተቀበሉ፡፡
• በሰዎች መከበር ከፈለጋችሁ በመጀመሪያ ራሳችሁን አክብሩ፡፡
• ሰዎች ከእናንተ ጋር እንዲያሳልፉ ከፈለጋችሁ በመጀመሪያ ከራሳችሁ ጋር በቂ ጊዜን አሳልፉ፡፡
ይህንን ስታደርጉ ሰዎቹ ያንን ነገር ከሰጧችሁ፣ በሞላው ማንነታችሁ ላይ ስለጨመሩላችሁ አመስጋኝ ሆናችሁ መንገዳችሁን ትቀጥላላችሁ፡፡ የጠበቃችሁትን ከከለከሏችሁ ደግሞ ነገሩን ከራሳችሁ ስላገኛችሁት ሁኔታው ለጉዳት አይጥላችሁም፡፡
እንደ እውነቱ ከሆነ ለራሳችሁ ያልሰጣችሁትንና ከራሳችሁ የከለከላችሁትን ምንም ነገር ከሰዎች መጠበቅ በጣም ሞኝነትና የተዛባ አመለካከት ነው፡፡
ለራሳችሁ ያልሰጣችሁትን ነገር እንዴት ሌሎች ሰዎች ይስጧችሁ?
በነገራችን ላይ፣ ከላይ የተጠቀሱት፣ ራሳችሁን ያለመውደድ፣ ያለመቀበል፣ ያለማክበርና ለራሳችሁ ትኩረት ያለመስጠት ሁኔታ ካለባችሁ ይህ ችግራችሁ ለሰዎች በግልጽ እንደሚታይ ታውቃላችሁ?
ይህ ብቻ አይደለም፣ ይህ በራሳችሁ ላይ ያላችሁ አመለካከት ሌሎች ሰዎችም እንደዚያው እንዲመለከቷችሁ የማድረግ አጉል ተጽእኖ ለው፡፡

👍204❤83🔥12🎉3