በሀገራች በሴቶች ላይ ከሚከሰተው ካንሰር የ2ኛ ደረጃነትን ይይዛል። የብዙ እናቶችን ህይወት በአጪሩ ያስቀረ የካንሰር አይነት ነው። ምልክቱን የሚያሳየው መሰራጨት ሲጀምር እና ደረጃው ከፍ ሲል ነው። ይህ የካንሰር አይነት የማህፀን በር ካንሰር ይባላል።
መከላከል እና ቅድመ ጥንቃቄ ምርመራዎችን በማድረግ እንድሁም ቅድመ ካንሰር ምልክቶቹን በማወቅ ራስዎን እና ቤተሰብዎን ከዚህ አደገኛ የካንሰር በሽታ ይከላከሉ።
የዩቲዩቭ ቻናላችን subscribe ማድረገዎን አይርሱ።
👇👇👇👇👇
https://youtu.be/wZd3I8PP9I8

YouTube
የማህፀን በር ካንሰር መንስኤ እና ምልክቶች - Cervical cancer cause and symptoms.
በሀገራች በሴቶች ላይ ከሚከሰተው ካንሰር የ2ኛ ደረጃነትን ይይዛል። የብዙ እናቶችን ህይወት በአጪሩ ያስቀረ የካንሰር አይነት ነው። ምልክቱን የሚያሳየው መሰራጨት ሲጀምር እና ደረጃው ከፍ ሲል ነው። ይህ የካንሰር አይነት የማህፀን በር ካንሰር ይባላል።
መከላከል እና ቅድመ ጥንቃቄ ምርመራዎችን በማድረግ እንድሁም ቅድመ ካንሰር ምልክቶቹን በማወቅ ራስዎን እና ቤተሰብዎን ከዚህ አደገኛ የካንሰር በሽታ ይከላከሉ።…

❤1
ዶ/ር ዳዊት መኮንን (በማህፀንና ፅንስ ህክምና ረዳት ፕሮፌሰር) pinned «በሀገራች በሴቶች ላይ ከሚከሰተው ካንሰር የ2ኛ ደረጃነትን ይይዛል። የብዙ እናቶችን ህይወት በአጪሩ ያስቀረ የካንሰር አይነት ነው። ምልክቱን የሚያሳየው መሰራጨት ሲጀምር እና ደረጃው ከፍ ሲል ነው። ይህ የካንሰር አይነት የማህፀን በር ካንሰር ይባላል። መከላከል እና ቅድመ ጥንቃቄ ምርመራዎችን በማድረግ እንድሁም ቅድመ ካንሰር ምልክቶቹን በማወቅ ራስዎን እና ቤተሰብዎን ከዚህ አደገኛ የካንሰር በሽታ ይከላከሉ።…»
ወንዶች የመራባት እድላቸውን እንዴት መጨመር ይችላሉ?
🔎ጭንቀት ፣ ውጥረት እና ድካምን መቀነስና መቆጣጠር
🔎ሲጋራ እና የአልኮል መጠጦችን ያቁሙ
🔎ጤናማ እና የተስተካከለ የሰውነት ክብደት ይኑርዎ
🔎ከፍተኛ የዚንክ መጠን ያላቸው ምግቦች (ሥጋ ፣ እንቁላል ፣ ጥራጥሬዎችና የባህር ውስጥ ምግቦች) እንዲሁም ሰሊኒየም (የባህር ውስጥ ምግቦች ፣ እንጉዳይ ፣ ስጋና ለውዝ) እንዲሁም ቫይታሚን ኢ ይመገቡ
🔎በቻሉት መጠን የሃፍረተ ስጋ ፍሬዎ (Testicles) እንዲቀዘቅዙ ያድርጉ። ከዛሬ ጀምሮ ረዘም ላለ ጊዜ ሙቅ ሻወር እና ሳውና ባዝ አይውሰድ ምክንያቱም የስፐርም (Sperm) ሴሎችን ቁጥር ስለሚቀንስ ነው።
ዶ/ር ዳዊት

🔎ናሽ ኪን ይባላል ፤ በጣም ገና ያልደረሰ ህጻን በመባል አዲሱ የጊነስ ወርልድ ሪከርድ ባለቤት ነው።
🔎ናሽ ኪን በ21 ሳምንት የማህፀን ውስጥ እድሜው በሗላ በጁላይ 5, 2024 የአዮዋ ዩኒቨርሲቲ የጤና እንክብካቤ ስቴድ የቤተሰብ ህጻናት ሆስፒታል (University of Iowa Health Care Stead Family Children’s Hospital) ፣ በዩናይትድ እስቴትስ ኦፍ አሜሪካ ተወለደ።
🔎የአንድ ፅንስ አማካኝ የማህፀን ውስጥ ቆይታ 280 ቀናት (40 ሳምንታት) ሲሆን ናሽ ኪን ግን 133 ቀናትን ቀድሞ በ21 ሳምንት የማህፀን ውስጥ እድሜው ቆይታ በሗላ ተወለደ። ይህም በጣም ገና ያልደረሰ ግን ከሞት የተረፈ ህጻን በመባል አዲሱ የጊነስ ወርልድ ሪከርድ ባለቤት ሆኗል።
🔎ናሽ ኪን ከአባቱ ከራንዳል እና ከእናቱ ከሞሌ ኪን የተወለደ ሲሆን ፤ እሱ ከመወለዱ ከ6 ወር በፊት በ18 የእርግዝና ሳምንት ጊዜ ያለጊዜው በማህፀን በር (በማህፀን ጫፍ) እጥረት እና መከፈት ምክንያት ፅንስ ከተቋረጠ በሗላ ነበር ነሽ ኪን መረገዙ የታወቀው።
🔎በወቅቱ ሆስፒታል በሔደችበት ጊዜ የማህፀን በር 2 ሳንቲሜትር የከፈተ እና ምጥ ጀምሯት ነበር። በዚህ ምክንያት ናሽ ኪን በ21 የእርግዝና ሳምንት ጊዜው ተወለደ።
🔎ናሽ ኪን ሲወለድ የሳንባው ፣ የልቡ ፣ የአእምሮው እና የሌሎች የአካል ክፍሉ ሙሉ ለሙሉ እድገታቸውን ባለመጨረሳቸው የሆስፒታል ቆይታውን ከባድ ያደረገው ሲሆን ቤተሰቦቹ ከአንድ ወር የሆስፒታል ቆይታው በሗላ ተስፋቸው ለመለመ።
🔎አሁን ላይ ናሽ ኪን በባለፈው ሐምሌ አምስት 2025 የልደት በአሉን ያከበረ ሲሆን ከኖርማል ልጆ እድገት ትንሽ የዘገየ እና መዳህ የጀመረ መሆኑን ቤተሰቦቹ ገልፀዋል። የናሽ ኪን በህይወት መትረፍ የህክምናው አለም እድገት መርቀቁን ያሳየ ሆኗል።

የማህፀን ሉፕ (IUCD) የእርግዝና መከላከያ
🔎አስተማማኝ የእርግዝና መከላከያ ከሚባሉት ውስጥ የሚመደብ ሲሆን 99% እርግዝናን የመከላከል አቅም አለው። በመጀመሪያ አመት የመጠቀሚያ ጊዜ ከ0.1% -0.2% ባሉ ሴቶች ላይ እርግዝናን ላይከላከል ይችላል።
🔎ሁለት አይነት የማህፀን ሉፕ አሉ፥
1️⃣የመዳብ (copper) የማህፀን ሉፕ እና
2️⃣የሆርሞናል (levonorgestrel) የማህፀን ሉፕ ናቸው።
🔎የመዳብ (copper) የማህፀን ሉፕ ለ10 አመት ሲያገለግል ሆርሞናል (levonorgestrel) የማህፀን ሉፕ ግን ለ5 አመት ያገለግላል።
🔎እርግዝናን መከላከያ መንገዶቹ፥
1️⃣የማህፀን በር ፈሳሽ በማወፈር የወንድ የዘር ፍሬ ፈሳሽ ወደ ማህፀን እንዳይገባ ይከላከላል፣
2️⃣ለወንድ የዘር ፍሬ የማህፀን ግድግዳን ምቹ እንዳይሆን ያደርጋል፣
3️⃣የማህፀን ግድግዳን ፅንስ ለመቀበል ምቹ እንዳይሆን በማድረግ እርግዝናን ይከላከላል።
🔎ይህንን የእርግዝና መከላከያ ሁሉም ሴቶች መጠቀም ይችላሉ ፤ ነገር ግን ከዚህ በታች የተጠቀሱት ሴቶች መጠቀም የለባቸውም።
1️⃣የማህፀን የአፈጣጠር ችግር ያለባቸው
2️⃣የማህፀን እጢ ያለባቸውና የማህፀን ሉፑን ለማስገባት አስቸጋሪ ከሆነ
3️⃣ያልታከመ የማህፀን እና የማህፀን በር ኢንፌክሽን ያለባቸው
4️⃣የማህፀንና የማህፀን በር ካንሰር ያለባቸውና
5️⃣ምክንያቱ ያልታወቁ የማህፀን ደም መድማት ያለባቸው
Via ዶ/ር ዳዊት — የፅንስና የማህፀን ስፔሻሊስት ሀኪም

🔎ስለ ስንፈተ-ወሲብ ህክምና ነገ በዩቲዩቭ ቻናሌ ላይ ይለቀቃል።
🔎ለስንፈተ-ወሲብ ህክምና ተመራጩ የቱ ነው? ዘመናዊ ህክምና ወይስ ባህላዊ ህክምና።
🔎የዚህ ችግር ተጠቂ ከሆኑ ሀኪም መቼ ያማክራሉ?
🔎እነዚህን መሰል ለህይወት አስፈላጊ እውቀቶችን በዩቲዩቭ ቻናላችን ላይ ብቻ የምታገኙ መሆኑን ልንገልፅላችሁ እንፈልጋለን።
🔎ቀድመው ቻናላችንን ሰቭስክራይቭ ላደረጉ ነፃ የማማከር አገልግሎት ተጠቃሚ ይሆናሉ።
🔎የዩቲዩቭ ቻናሉን ለማግኘት በዚህ ሊንክ ይግቡ 👉 https://www.youtube.com/@drdawit

ለብዙዎች ትዳር መፍረስ ምክንያት ስለሆነው ስንፈተ-ወሲብ ህክምና እንድሁም ሀኪመዎን መቼ ማማከር እንዳለባችሁ በዩቲዩቭ ቻናላችን ማየት ትችላላችሁ።
የዩቲዩቭ ቻናል ከታች ባለው ሊንክ በመግባት ቪዲዮውን ተመልከቱ
👇👇👇👇👇👇👇
https://youtu.be/Z0_2y606ej8
የዩቲዩቭ ቻናል ከታች ባለው ሊንክ በመግባት ቪዲዮውን ተመልከቱ
👇👇👇👇👇👇👇
https://youtu.be/Z0_2y606ej8
YouTube
ለስንፈተ-ወሲብ ህክምና ተመራጩ የቱ ነው? ዘመናዊ ወይስ ባህላዊ ህክምና | @drdawit
#health #duet #fetaldevelopment #fetalgrowth #pregnancy
ወንድ ልክ እንደ ሴት ያርጣል?
#መልሱ፥ አዎ በደንብ ያርጣል!
☑️ሴት ስታርጥ #menopause ይባላል ፤ ነገር ግን ወንድ ሲያርጥ #andropause በመባል ይጠራል።
☑️የወንድ እና የሴት እርጣት ሂደቱ ይለያያል። ሴት አረጠች ስንል ለአንድ አመት ያህል ያለምንም ምክንያት የወር ማየት ካቆመች ነው። ይህ የሚያሳየው ያሏት የእንቁላል ክምችቶች ሙሉ ለሙሉ ሲያልቅ እና ኢስትሮጂን የሚባለውን ሆርሞን ማምረት ስታቆም ነው።
☑️ነገር ግን የወንድ እርጣት እንደ ሴት አይደለም ይለያል። በእድሜ ምክንያት የመጣ የቴስቴስትሮን መጠን ቀስ በቀስ መቀነስ ነው። ስለዚህ ወንድ የቴስቴስትሮን የማመንጨት አቅሙ ሙሉ ለሙሉ ሲቆም የወንድ እርጣት ይባላል። ከ30 አመት በሗላ የወንድ የቴስቴስትሮን መጠን በየአመቱ በ1% ይቀንሳል።
#የወንድ_እርጣት_ምልክቶች
🔎የወሲብ ፍላጎት መቀነስ
🔎የብልት የመቆም ችግር መከሰት
🔎የድካም ስሜት እና ጉልበት ማጣት
🔎የጡንቻዎች መቅጠን እና አቅም መቀነስ
🔎የሆድ ቦርጭ መጨመር
🔎የጡት መጠን መጨመር
🔎የአጥንት መሳሳት
🔎መነጫነጭ እና የሙድ መለዋወጥ
🔎ድባቴና የሀዘን መኖር
🔎ተነሳሽነት እና ኮንፊደስ ማጣት
🔎የአትኩሮት ማጣት ወይም መቀነስ
🔎የእንቅልፍ ማጣት እና የመሳሰሉት ናቸው።
Via ዶ/ር ዳዊት — የፅንስና የማህፀን ስፔሻሊስት ሀኪም
እነዚህን እና ሌሎች ጥሩ የጤና መረጃዎችን ለማግኘት የዩቲዩቭ ቻናሌን ከታች ባለው ሊንክ ይቀላቀሉ።
YouTube 👉 https://www.youtube.com/@drdawit

👍3❤1
የወለደች እናት ላይ ጥንቃቄ አድርጉ (ከወሊድ በሗላ የሚከሰት ድባቴ)
☑️አንድት እናት በእርግዝና አማካኝነት ብዙ አካላዊ እና አእምሯዊ ለውጦችን ታስተናግዳለች። በተመሳሳይ መልኩ ከወለደች በሗላም ብዙ ለውጦችን ታስተናግዳለች። ከነዚህ ለውጦች ውስጥ አንዱ postpartum psychosis (ከወሊድ በሗላ የሚከሰት ድባቴ) ነው።
☑️በዚች እናት ላይ ባሏ የሰራውን ፕራንክ አየሁት ፤ ለባሏ ቀልድ ሊመስል ይችላል ነገር ግን አደገኛ ነው። በዚህ ፅሁፌ መግለፅ የምፈልገው ስለ ፕራንኩ አይደለም። ነገር ግን ከወሊድ በሗላ በእናቶች ላይ ስለሚከሰተው አደገኛ አእምሯዊ ለውጥ ከፍተኛ የሆነ የባል እንክብካቤ እና ጥንቃቄ እንደሚፈልጉ ግንዛቤ ለመፍጠር እንጅ።
☑️ከወሊድ በሗላ የሚከሰት ድባቴ አነሳሽ ነገሮች የሚከተሉት ናቸው።
🔎ድህነት
🔎የእንቅልፍ መዛባት
🔎የቤተሰብና የማህበረሰብ ድጋፍ ማጣት
🔎የመጀመሪያ እርግዝና
🔎የቀደመ ተመሳሳይ ድባቴ ታሪክ መኖር
🔎በቤተሰብ ተመሳሳይ የድባቴ ታሪክ መኖር
🔎ሌሎች የአእምሮ ህሞች መኖር ለምሳሌ ባይፖላር ዲስኦርደር እና የመሳሰሉት ናቸው።
☑️ለዚህ በሽታ የተጋለጡ እናቶች ከመንፈሳዊ ጭንቀት እስከ ህፃን መጥላት ፣ መግደል እና ራስንም እስከ ማጥፋት ደረጃ ሊደርሱ ስለሚችሉ ከወሊድ በሗላ እና ነፍሰ-ጡር እናትን ጥንቃቄ የተሞላበት ቤተሰባዊ እና ፍቅር ሊሰጣቸው ይገባል።
Via ዶ/ር ዳዊት | የፅንስና የማህፀን ስፔሻሊስት ሀኪምና ረዳት ፕሮፌሰር

🙏6❤2
#Infertility በተለያየ ምክንያት መፀነስ (ማርገዝ) አለመቻል ቢሆንም የተለያዩ ህክምናዎችን በማግኝት ችግሩን መቅረፍ ይቻላል።
#Sterility ግን ፈፅሞ የመፀነስ እድል አለመኖርም ሲሆን ይህ አይነት ችግርም የመፈጠር እድሉ በጣም አነሳ ነው።
የመካንነት መንስኤ እና ህክምናው።
👇🏻👇🏻👇🏻👇🏻👇🏻👇🏻👇🏻👇🏻
https://youtu.be/YuHXrERQ3yI

ማርገዝ አለመቻል (መካንነት) ምንነት ፣ መንስኤ ፣ ህክምና እና መከላከያ መንገድ | Infertility cause and treatment | @drdawit
Infertility በተለያየ ምክናያት መፀነስ (ማርገዝ) አለመቻል ቢሆንም የተለያዩ ህክምናዎችን በማግኝት ችግሩን መቅረፍ ይቻላል።
Sterility ግን ፈፅሞ የመፀነስ እድል አለመኖርም ሲሆን ይህ አይነት ችግርም የመፈጠር እድሉ በጣም አነሳ ነው።
#infertility #food #duet #pregnancy #fetaldevelopment #habesha #series #infertilitytreatment #infe…

👍3
#የአፍ_ውስጥ_ካንሰር ዋና ዋና ምክንያቶች
🔎ሲጋራ መጨስ
🔎አልኮሆል መጠጣት
🔎ቶባኮ ማጨስና አልኮሆል መጠጣት (ሁለቱንም አብሮ መጠቀም በተናጠል ከሚያመጡት ችግር ድምር የበለጠ ነው)
🔎የሂዩማን ፓፒሎማ ቫይረስ ኢንፌክሽን (በተለይ #HPV16 ኢንፌክሽን)
ይህም ወሲብ በአፋቸው የሚፈፅሙ ሰዎች ከማይፈፅሙ ሰዎች ይልቅ 8.5 እጥፍ በላይ የአፍ ውስጥና የጉሮሮ ካንሰር እንደሚያዙ ጥናቶች አመላክተዋል።
የጉሮሮ ውስጥ ካንሰር ከማህፀን በር ካንሰር በላይ ነባራዊ እና የተለመደ እየሆነ መጥቷል።

በእርግዝና ጊዜ የሚከሰት የደም ግፊት (#Preeclampsia) ፅንስና እናት ላይ የሚያደርሰው ጉዳት
🔎በእርግዝና ጊዜ የሚከሰት የደም ግፊት ለማለት ከታች ያሉትን ሁለት ነግሮች ሲያሟላ ነው።
እነሱም፥
1️⃣ከአምስት የእርግዝና ወር በሗላ የሚከሰት የደም ግፊት ከሆነ
2️⃣የላይኛው (systolic) የደም ግፊት ከ140mmHg እና በላይ ሲሆን እና የታችኛው (diastolic) የደም ግፊት ከ90mmHg እና በላይ ሲሆን ነው።
🔎በእርግዝና ጊዜ የሚከሰት የደም ግፊት ከሌላው የደም ግፊት የሚለየው፥ በእርግዝና ጊዜ የሚከሰት የደም ግፊት መነሻ መንስኤው የፅንስ እንግደ ልጅ ሲሆን የሌላው የደም ግፊት አይነት ግን እንግደ ልጅ አይደለም።
🔎#እናት ላይ የሚያስከትለው ጉዳት፥
☑️የጉበት ጉዳት
☑️የኩላሊት ጉዳት
☑️የልብ ጉዳት
☑️የሳንባ ውሃ ማዘል
☑️የስኳር በሽታ
☑️የደም ግፊት
☑️ስትሮክ
☑️የጭንቅላት ውስጥ የደም ቱቦዎች መተርተርና የጭንቅላት ውስጥ ደም መፍሰስና ወዘተ…
🔎#ፅንስ ላይ የሚያስከትለው ጉዳት፥
🔘የፅንስ መቀንጨር
🔘 ውርጃ
🔘የፅንስ ያለጊዜው መወለድ
🔘የእንግደ ልጅ ቀድሞ መላቀቅ
🔘የሽርት ውሃ ማነስ
🔘የፅንስ መታፈን ፣ ሞት እና የመሳሰሉትን ጉዳት ያስከትላል።

❤2
በእናትና በልጅ መካከል ለሚፈጠረው ጠንካራ ፍቅር መነሻ ምክንያቶች ብዙ መላ-ምቶች አሉ። ከነዚህም መካከል፥
🔎የእርግዝና ሆርሞን የተባሉት ኦክሲቶሲን ፣ ፕሮላክቲንና ኢስትሮጂን በእርግዝና ጊዜ አእምሮን የመንከባከብና የመተሳሰር ስሜት እንዲኖረው በማድረግ ያዘጋጁታል።
🔎በወሊድ ጊዜ ወሊድን በማፋጠን እና ህፃን ጡት በሚጠባበት ጊዜ ወተት እንዲለቀቅ የሚያደርገው የፍቅር ሆርሞን በመባል የሚታወው ኦክሲቶሲን የተባለው ሆርሞን በብዛት መመንጨት ጠንካራ ፍቅር እንዲፈጠር ያደርጋል።
🔎የእናት ለልጇ የምትሰጠው ቋሚ እና ያልተቆራረጠ እንክብካቤ እና ምላሽ አማካኝነት የሚፈጠር ስነ-ልቦናዊ እና ስሜታዊ ትስስር ሌላው ጠንካራ ፍቅር እንዲፈጠር ያደርጋል።
🔎በሁለቱ ማለትም በእናት እና በልጅ መካከል ያለው ቆዳ ለቆዳ ንክኪ እናት የልጇን የሙቀት መጠን እና የልብ ምት እንድትቆጣጠር ያደርጋታል። በዚህ ምክንያት ስነ-ልቦናዊ እና ስሜታዊ ትስስር ይፈጠራል።
🔎ሌላው mirror neurons የሚባል theory ነው። ይህ መላ-ምት የሚገልፀው በእናት እና በልጅ መካከል የሚኖር ግንኙነት በእናት ዘንድ ስሜታዊ ነፀብራቅን ይፈጥራል። ማለትም ልጅ ሲጨነቅ ፣ ሲያለቅስ ፣ ሲራብ የሚፈጥራቸው ስሜቶች በእናት ህሊና ውስጥ የአዜኔታና ልጇን ለማረጋጋት የምታደርጋቸው ድርጊቶች ሁሉ በልጇ ላይ የሚፈጥረው ስነ-ልቦናዊ ምላሽ በመካከላቸው ጠንካራ የሆነ የመስጠት እና የመቀበል ስነ-ልቦናዊ ትስስርን ይፈጥራል። ይህም አንዱ መላ-ምት ነው።
🔎ልጅ ለረጅም ጊዜ አቅመ-ቢስ ፣ ደጋፊ ፈላጊ ፣ ለዚህ አለም አድስ ፍጥረት በመሆኑ ፤ እናት ለረጅም ጊዜ በልጇ ላይ የምታደርጋቸው ኢንቨስትመንቶች ለምሳሌ፥ መጋቢነቷ ፣ ጠባቂነቷ ፣ አስተማሪነቷ ፣ ተንከባካቢነቷ እነዚህ ሁሉ ተደማምረው የፍቅር ቁርኝታቸውን ጠንካራ ያደርጉታል።

❤5
በእርግዝና ጊዜ በቀን የሚፈቀደው ከፍተኛው የቫይታሚኖች መጠን (Upper Limit Dose)
🔘በእርግዝና ጊዜ ቪታሚኖች ለእናትም ሆነ ለፅንስ ጤና አስፈላጊ ናቸው። ነገር ግን ከመጠን በላይ ከተወሰዱ እናትንም ሆን ፅንሱን ይጎዳሉ።
🔘ከዚህ በታች የተመረጡ የቪታሚን አይነቶች በቀን የሚፈቀደው ከፍተኛው መጠናቸው ስለሆነ ከዚህ በላይ አይወሰዱም። ስለዚህ እነዚህን ቪታሚኖች ከመውሰዳችሁ በፊት መጠናቸውን በማየት እና ከዚህ በላይ ከሆነ እንዳትወስዱ ይረዳችሁ ዘንድ ከፍተኛ መጠናቸውን አስቀምጨላችሗለሁ።
🔎ቪታሚን ኤ — በቀን ከ3,000 ማይክሮ ግራም (micro gram) ወይም ከ10,000 ኢንተርናሽናል ዩኒት (IU - international unit) በላይ አይወሰድም
🔎ፎሊክ አሲድ (ቪታሚን ቢ9) — በቀን ከ1,000 ማይክሮ ግራም (micro gram) በላይ አይወሰድም
🔎ቪታሚን ኢ — በቀን ከ1,000 ሚሊ ግራም (milligram) በላይ አይወሰድም
🔎ቪታሚን ዲ — በቀን ከ4,000 ኢንተርናሽናል ዩኒት (IU - international unit) በላይ አይወሰድም
🔎ቪታሚን ሲ — በቀን ከ2,000 ሚሊ ግራም (milligram) በላይ አይወሰድም
ዶ/ር ዳዊት | የፅንስና የማህፀን ስፔሻሊስት ሀኪም

❤3
#ለወላጆች | ህፃናት በሚደፈሩበት ጊዜ ሊደረጉላቸው የሚገቡ ጥንቃቄዎች
🔴ዛሬ ዛሬ ላይ ብዙ ችግሮቻችን በዙና የህፃናት መደፈር አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን እረሳነው። ለዛሬ ፅሁፌ መግቢያ ይሆነኝ ዘንድ ዛሬ በስራዬ ላይ የገጠመኝን አንድ የመደፈር አደጋ ገጠመኝ ልንገራችሁ።
🔴የ6ኛ ክፍል ተማሪ ነች ፤ እድሜዋ ከ13 - 15 አመት አካባቢ ይሆናል። በጓደኛዋ ጋባዥነት የሆነ ቦታ ልውሰድሽ በማለት ትወስዳታለች። ከሔደችበት ቦታ የገጠማት ግን ያፈረጠመ ደፋሪ ወጣት ነበር። ማንም በሌለበት ይህች ታዳጊ ተደፈረች። ሁኔታው በፖሊስ ክትትል እና ምርመራ እየተካሔደበት ነው። መደፈሯንም በምርመራችን አረጋግጠናል። አሁን ይህን ለመግቢያ ያክል ልነግራችሁ ፈለኩ እንጂ ዋናው ሀሳቤ ከመደፈር በሗላ በፍጥነት ሊደረጉ የሚገባቸው የህክምና ምርመራዎች እና የሚሰጡ ህክምናዎች ላይ ነው።
🔴ስለዚህ ወላጆችም ሆነ ማንኛውም ቤተሰብ ከተቻለ ለልጆቻቸው ቀድመው አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ለልጆቻቸው የምክር አገልግሎት መስጠት አለባቸው።
🔴ነገር ግን አንድ ጊዜ የመደፈር አደጋ ከተከሰተ ግን ሳይዘገዩ ወደ ህክምና ተቋማት መውሰዳቸው የሚያገኙትን አገልግሎት እና ጥቅም በቀጣይ ልንገራችሁ።
1️⃣ኛ — የደረሰባቸው የመደፈር አደጋ ክብደት እና ጥልቀት ይመረመራል። አደጋው አካላዊ ጉዳቱ ከፍተኛ ከሆነ ለምሳሌ የመራቢያ አካል ጉዳት ፣ ፊስቱላ እና የመሳሰሉት ከደረሱ በፍጥነት ህክምና ይደረግላቸዋል።
Continue 👇

2️⃣ኛ — የአባላዘር በሽታዎች ለምሳሌ፥ የኤች አይቪ ፣ የሔፓታይተስ ቢ እና ሌሎች የአባላዘር በሽታዎች ምርመራ እና የመከላከያ መድሀኒት ያገኛሉ። እነዚህ የመከላከያ መድሀኒቶች ውጤታማነታቸው ተሎ ለመጡ ሲሆን እስከ 3 ቀን ድረስም ቢዘገዩ አገልግሎቱን ያገኛሉ።
🔎ምክንያቱም አብዛኞቹ ደፋሪዎች የአደንዛዥ እፅ መድሀኒት ተጠቃሚና ብዙ የአባላዘር በሽታ ተጠቂ ስለሆኑ ልጆቻችሁን ከነዚህ በሽታዎች መታደግ አለባችሁ።
🔎ስለዚህ ልጆቻችሁን ከኤች አይቪ ኤድስ ፣ ከሔፓታይተስ ቫይረስ እና ከሌሎች የአባላዘር በሽታዎች ትታደጋላችሁ።
3️⃣ኛ — ከአላስፈላጊ እርግዝና ለመጠበቅ የእርግዝና መከላከያ መድሀኒት ያገኛሉ።
4️⃣ኛ — የስነ-ልቦና የምክር አገልግሎትን ያገኛሉ። የተደፈሩ ልጆች ብዙ ጊዜ ለ Post traumatic stress disorder የተጋለጡ ስለሆነ በቤተስብም ሆነ በህክምና ቦታ ለደረሰባቸው ጉዳት እውቅና በመስጠት ጥንቃቄ የሞላበት እንክብካቤና ምክር ያስፈልጋቸዋል።
5️⃣ኛ — በመጨረሻም በቂ የህክምና መረጃዎችን ያገኛሉ። በፍጥነት ወደ ጤና ተቋም መሔድ አንዱ ጥቅሙ በቂ የህክምና መረጃን ማግኘት ሲሆን ለሀኪሙም ቅሪት መረጃዎች ሳይጠፉ ስለሚያገኝ መረጃችሁን ታገኛላችሁ።
🔎በአጠቃላይ ወላጆች ልጆቻቸውን ከመደፈር አደጋ ለመጠበቅ አስፈላጊውን አካላዊ እና ስነ-ልቦናዊ ዝግጅት እንዲኖራቸው ቀድመው መምከር እና ማዘጋጀት ያስፈልጋቸዋል።

❤6
በበዓላት ጊዜ በአመጋገብ ዙሪያ ሊደረጉ የሚገባቸው ጥንቃቄዎች፦
🚫በጣም ብዙ አለመመገብ (ቀስ በቀስ መጨመር) እና ጨጓራን ከማጨናነቅ መቆጠብ። በተጨማሪም በቀላሉ መፈጨት በሚችሉ ምግቦች እንደ አትክልት ፣ እርጎ ፣ ገንፎ በመሳሰሉ የምግብ አይነቶች መጀመር ለጨጓራ ጤና መልካም እና የሚመከር ነው።
🚫ቀስ በቀስ በጣም ያልበዛ ውሃ መጠጣት ያስፈልጋል። የምትጠጡት ውሃ ቀዝቃዛ ባይሆን ይመረጣል ፤ ነገር ግን በቀስታ መጠኑን መጨመር የተመረጠ ነው።
🚫የምትጠጡትን የቡና መጠን መቀነስ ማለትም ከ2-3 ሲኒ ባይበልጥ የተመረጠ ሲሆን በምትመገቡት ምግብ የስኳር መጠናቸው ከፍ ያሉ ምግቦችን መጠን መቀነስ በጣም አስፈላጊ ነው።
🚫በቂ እረፍ ውሰዱ ነገር ግን ሙሉ ለሙሉ በመተኛት እንቅስቃሴያችሁን አትገድቡ ፤ ከፍተኛ ከሆነ የአካል ብቃት እንቅስቃሴም ታቀቡ።
🚫አልኮል ከመጠጣት እና ሲጋራ ከማጨስ ተቆጠቡ። ምክንያቱም እነዚህ ነገሮች በፆም ለቆየ ጨጓራ ግድግዳ መቁሰል እና መላጥ አይነተኛ ምክንያቶች ስለሆኑ።
🚫የድካም ስሜት ፣ ማቅለሽለሽ ፣ ትውከት ፣ የደረት ውጋት ፣ ራስን የመሳት እና የመሳሰሉት ስሜቶች ከተሰሟችሁ በፍጥነት ሀኪማችሁን አማክሩ። እነዚህ እና መሰል ምልክቶች አደገኛ የጤና መታወክ ምልክቶች ናቸው።

#መልካም_ዜና
💊በዓመት ሁሌት ጊዜ ብቻ በሚወሰድ መድኃኒት ኤች.አይ.ቪ/ኤድስን መከላከል ተቻለ።
💊የዓለም ጤና ድርጅት እንዳስታወቀው፣ 2025ን ስንሰናበት በኤች.አይ.ቪ መከላከል ስራ ላይ ትልቅ ተስፋ ሰጪ ውጤት ተመዝግቧል። "ሌናካፓቪር" (Lenacapavir) የተባለው አዲሱ መድኃኒት ጨዋታ ቀያሪ (Game Changer) ሆኖ መጥቷል።
የመድኃኒቱ ልዩ ባህሪያት፡
✅ ለህክምናም ሆነ ለቅድመ-መከላከል (PrEP) ያገለግላል።
✅ የሚወሰደው በዓመት ሁለት ጊዜ ብቻ ነው።
✅ በየቀኑ መድኃኒት የመውሰድ ጫናን ያስቀራል።ይህ መድሐኒት በየ 6 ወሩ ብቻ የሚወሰድ ነው።
💊ይህ ሳይንሳዊ ግኝት ኤች.አይ.ቪን ከዓለም ለማጥፋት ለሚደረገው ጉዞ ትልቅ አቅም ነው ተብሏል።
💊አሁን ዋናው ትኩረት በ2026/27 የፈረንጆች ዓመት መድኃኒቱ ለሁሉም ፈላጊ ዜጎች በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲቀርብ ግፊት ማድረግ ነው ሲሉ ያሳወቁት የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ፀሐፊ ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሐኖም ናቸው።
ማሳሰቢያ
💊አሁንም ቢሆን ለኤች አይ ቪ/ኤድስ የመጨረሻ ፈዋሽ መድኃኒት ስላልተገኘለት መወሰድ ያለበት ጥንቃቀ ተጠናክሮ ልቀጥል ይገባል።