Dilla University Official
18.3K subscribers
4.12K photos
23 videos
249 files
445 links
University of the Green Land
Download Telegram
"ተቋሙ ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ እና ለአጀንዳ 2030 ግብ መሳካት ቁርጠኝነቱን እያሳየ ይገኛል" - ቶሎሳ ዳዲ (ዶ/ር)
===========*************============

ዲ.ዩ: ነሐሴ 11/12/2018ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ)

በዲላ ዩኒቨርሲቲ በመደራጀት ላይ የሚገኙ የስማርት መማሪያ ክፍሎች ያሉበትን ደረጃ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ቶሎሳ ዳዲ (ዶ/ር) ተዘዋውረው ተመልክተዋል።

በዩኒቨርሲቲው በአራቱም ጊቢዎች እጅግ ዘመናዊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች የተሟላላቸው የስማርት መማሪያ ክፍሎችን በማደራጀት ለመጪው የትምህርት ዘመን ዝግጁ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል።

ፕሬዝዳንቱ በሀሴዴላ ጊቢ እና በማስተማሪያ ሆስፒታሉ ፕሮጀክቱ የደረሰበትን ደረጃ የተመለከቱ ሲሆን፣ ዩኒቨርሲቲው አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶችን በማደራጀት ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ እና ለአጀንዳ 2030 ግብ መሳካት ቁርጠኝነቱን እያሳየ እንደሚገኝ አውስተዋል።

ፕሬዝዳንቱ አክለውም ፕሮጀክቱ እስኪጠናቀቅ ድረስ አስፈላጊው ሁሉ ድጋፍ እና ክትትል እንደሚደረግም ገልፀዋል።

ዲላ ዩኒቨርሲቲ በአዲሱ የትምህርት ዘመን፣ በርካታ አዳዲስ የትምህርት ግብዓቶችን በማሟላት ተማሪዎቹን ለመቀበል ዘርፈ ብዙ ተግባራትን እያከናወነ ስለመሆኑ ተገልጿል።

===###===

#የአረንጓዴው_ምድር_ዩኒቨርሲቲ
#UniversityOfTheGreenland
32👍1
Programs offered at Dilla University
16
ማስታወቂያ
👍3212
🔔አዲስ ማስታወቂያ📢
=====*****=====

በዲላ ዩኒቨርሲቲ የፈተና ማዕከል ለተመደባችሁ የድህረ ምረቃ መግብያ ፈተና ተፈታኞች በሙሉ

በዩኒቨርሲቲው የምትፈተኑ ተፈታኞች በቀን 20/12/2018ዓ.ም ከጧቱ 3:00 ጀምሮ እስከ 6:00 ባለው ጊዜ ብቻ መሆኑን አውቃችሁ ለፈተናው እንድትዘጋጁ ስንል እናሳስባለን።

#የአረንጓዴው_ምድር_ዩኒቨርሲቲ
#UniversityOfTheGreenland
#NGATEXAM
10👍3
እንኳን አደረሳችሁ!
===*****===

መላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1ሺህ 501ኛው የነቢዩ መሀመድ የመውልድ በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

ዲላ ዩኒቨርሲቲ በዓሉ የሰላም የፍቅር እና የአንድነት እንዲሆንላችሁ ይመኛል።

ኢድ ሙባረክ!

#የአረንጓዴው_ምድር_ዩኒቨርሲቲ
21👍2
📢ክፍት የስራ መደብ ማስታወቂያ🔔
========*******========

ዲላ ዩኒቨርሲቲ ነሐሴ 24 ቀን 2018 ዓ/ም በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ባወጣው የአካዳሚክ ቅጥር ማስታወቂያ ላይ ለመመዝገብ የምትፈልጉ አመልካቾች ከዚህ በታች በተጠቀሰው የመመዝገቢያ ማስፈንጠሪያ https://srms.du.edu.et/duthvacancy እየገባችሁ ማመልከት የምትችሉ መሆኑን እናሳስባለን፡፡

መረጃውን ለጓደኞችዎ ያጋሩ!

===###===

#የአረንጓዴው_ምድር_ዩኒቨርሲቲ
#UniversityOfTheGreenland!
10
📢አዲስ ማስታወቂያ🔔
====********====

በዲላ ዩኒቨርሲቲ በ2019 የትምህርት ዘመን ላይ የድህረ ምረቃ ፕሮግራም (Postgraduate Program)በመደበኛ እንዲሁም በቅዳሜና እሁድ መርሀ ግብር ትምህርታችሁን መከታተል የምትፈልጉ ተማሪዎች ከነሐሴ 28/2018ዓ.ም ጀምሮ እስከ መስከረም 06/2019ዓ.ም ድረስ በዩኒቨርሲቲው ሬጅስትራር ጽህፈት ቤት በአካል በመቅረብ አለያም በዚህ ማስፈንጠሪያ https://portal.du.edu.et ገብታችሁ ማመልከት የምትችሉ መሆኑን እናሳስባለን።

የምንሰጣቸውን የትምህርት ዓይነቶችን ይመልከቱ፣ ዲላ ዩኒቨርሲቲን ይምረጡ።

መረጃውን ለጓደኞችዎ ያጋሩ!

===###===

#የአረንጓዴው_ምድር_ዩኒቨርሲቲ
#UniversityOfTheGreenland!
21👍7