Dilla University Official
15.6K subscribers
3.19K photos
13 videos
237 files
433 links
University of the Green Land
Download Telegram
አምስተኛው ዙር የቡና ልማት ስልጠና ተጠናቀቀ

ዲ.ዩ፦ የካቲት 4/2017 ዓ/ም (ህ.ዓ.ግ)

የዲላ ዩኒቨርሲቲ የቡና ምርምርና ስልጠና ተቋም ለቡና ልማት ባለሙያዎች በቡና ልማት ዙሪያ ከማሳ እስከ ቅምሻ ያለውን ሂደት በተመለከተ ያተዘጋጀው የንድፈ ሀሳብና የተግባር ስልጠና ተጠናቋል።

አዲሱ ፍሪንጆ (ዶ/ር)፣ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ዩኒቨርሲቲ ኢንዱስትሪ ትስስርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር እና የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ፕሬዚዳንት ተወካይ በስልጠናው መዝጊያ መርሐግብር ላይ ባስተላለፉት የስራ መምሪያ ቡና በአካባቢያችንና ሀገራችን ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊና ማሕበራዊ ፋይዳ እንዳለው ጠቁመው ባለሙያዎች በስልጠናው ያገኙትን እውቀትና ክህሎት ወደ ተግባር በመቀየር የማሕበረሰቡን ኢኮኖሚያዊ አቅም በማሻሻል እንዲሁም የሀገራችን የምታገኘውን የውጭ ምንዛሬ ከፍ ለማድረግ ትኩረት ሰጥተው ስራቸውን እንዲያከናውኑ አሳስበዋል።

#ለዝርዝሩ👇
https://www.facebook.com/share/p/1EGGFVrUFa/
ማስታወቂያ
#ለSTEM_ማዕከል_ተማሪዎች

ማዕከሉ ባለው #የሳምንቱ_እረፍት_ቀናት መርሃ ግብር ለመሰልጠን ተወዳድራችሁ ያለፋችሁ ተማሪዎች ስልጠና የሚጀምረው በቀን የካቲት 08/2017 ዓ.ም መሆኑን እየገለጽን ለበለጠ መረጃ ከላይ የቀረበውን ማስታወቂያ እንድታነቡ እናሳስባለን።

ዲላ፤
የአረንጓዴው ምድር ዩኒቨርሲቲ
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት
FB: https://www.facebook.com/Du.edu.et
Telegram: https://t.me/dprd9
website: https://www.du.edu.et
Email: https://www.pirdir@du.edu.et
የአስተዳደር ልማት ምክትል ኘሬዝዳንት ቁልፍ የአፈፃፀም አመለካቾች ውል (KPI) ከዘርፉ ዳይሬክተሮች ጋር ተፈራረሙ

ዲዩ፣ የካቲት 04/2017 ዓም (ህ.ዓ.ግ)

የዲላ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደርና ልማት ምክትል ኘሬዝዳንት በዘርፉ ካሉ ዳይሬክተሮች ጋር ስራን በውጤት መለካት የሚያስችለውን ቁልፍ የአፈፃፀም አመላካቾች ውል (KPI) ተፈራርመዋል።

ማቲዎስ ሀብቴ (ዶ/ር)፣ የዲላ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደርና ልማት ምክትል ኘሬዝዳንት እንደገለፁት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከትምህርት ሚንስቴር ጋር በኘሬዝዳንቶቻቸች አማካኝነት ቁልፍ የአፈፃፀም አመላካቾች ውል (KPI) መፈራረማቸውን አስታውሰው ይህንኑ የአሰራር ስርዓት ወደታች ለማውረድ የዩኒቨርሲቲው ክቡር ፕሬዝዳንት ከምክትል ኘሬዝዳቶች ጋር የተፈራረሙ በመሆኑ የአስተዳደርና ልማት ምክትል ኘሬዝዳንት ዘርፍም በስሩ ላሉት ክፍሎች ስራን ለክቶ በመስጠት ለክቶ በመቀበል ሰራተኛው በውጤት የሚመዘንበት ስርዓት ለመዘርጋት እንዲያስችለው በዘርፉ ካሉ ዳይሬክተሮች ጋር የቁልፍ አፈጻጸም አመላካች ውል መፈራረማቸውን ገልጸዋል።

#ለዝርዝሩ👇
https://www.facebook.com/share/p/18EwD14RHy/
የፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ኃላፊ በዘርፉ ከሚገኙ ዳይሬክተሮች ጋር ቁልፍ የአፈፃፀም ውጤት አመላካቶች ውል ተፈራረሙ

ዲዩ የካቲት 7/2017 ዓ.ም. (ህ.ዓ.ግ)

የዲላ ዩኒቭርሲቲ ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ኃላፊ በዘርፉ ከሚገኙ ዳይሬክተሮች ጋር ቁልፍ የአፈጻጸም ውጤት አማላካቾች (KPI’s) ውል ተፈራርመዋል፡፡

አቶ መሳይ ፍቅሩ፣ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ኃላፊ ባደረጉት ንግግር በተቋም ደረጃ ክቡር ፕሬዝዳንቱ ከትምህርት ሚኒስቴር ኃላፊዎች ጋር ቁልፍ የአፈጻጸም ውጤት አማላካቾች (KPI’s) ውል መፈራረማቸውን አስገንዝበዋል።

#ለዝርዝሩ👇
https://www.facebook.com/share/p/12FWTtZhjpu/
#Coming_Soon
#Alumni_Forum @follower

Elias Alemu (PhD) is one of our distinguished alumni. He graduated from the Department of History at Dilla University in 1995 E.C. He served at different Universities at higher official levels. He has returned back to Dilla University in 2024 and nowadays, he become president of our university.


Dear Dr Elias, thank you for you came back and leading us. With a visionary approach, Dr Elias fosters a culture of innovation that enhances our institution's growth.

we are proud of being our former student and taking the lion's share for the alumni forum formation.

#በቅርብ_ቀን
#የቀድሞ_ተማሪዎች_መድረክ

ኤሊያስ አለሙ (ዶ/ር)፣ ከቀድሞ ተማሪዎቻችን አንዱ ናቸው። ዶ/ር ኤሊያስ በ 1995 ዓ.ም ከዲላ ዩኒቨርሲቲ ታሪክ ትምህርት ክፍል ተመርቀዋል። በተለያዩ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥም በኃላፊነት ቦታዎች አገልግለዋል። በአሁኑ ጊዜ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ሁነው በማገልገል ላይ ናቸው።


ዶ/ር ኤሊያስ ወደ ቀድሞ ቤቶ ተመልሰው የዩኒቨርሲቲያችንን እድገት ለማረጋገጥ እየሰሩ እና እየመሩን ስለሆነ እናመሰግናለን።


የቀድሞ ተማሪያችን በመሆኖ እና ለቀድሞ ተማሪዎች ፎረም ምስረታ እየሰጡት ባለው አመራር ኩራት ይሰማናል!

ዲላ፤
የአረንጓዴው ምድር ዩኒቨርሲቲ
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት
ዲላ፤
የአረንጓዴው ምድር ዩኒቨርሲቲ

የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት

FB: https://www.facebook.com/Du.edu.et
Telegram:https://t.me/dprd9
website: https://www.du.edu.et
Email: https://www.pirdir@du.edu.et
#ማስታወቂያ

ዲላ ዩኒቨርሲቲ ለሚያከብረው የቀድሞ ምሩቃን ቀን ምስረታ (Alumni Forum) በሚያዘጋጀው መጽሔት ላይ ሊወጡ የሚችሉ የተለያዩ : -
ወጐች ፣ መጣጥፎች ፤
ገጠመኞች ፣
ግጥሞች ፣ . . .
እንዲሁም ለየት ያሉ ትውስታ ቀስቃሽ ፎቶዎች ያላችሁ በሙሉ እስከ መጋቢት 17 ቀን 2017 ዓ.ም. ድረስ ከታች በተዘረዘሩት አድራሻዎች እንድትልኩልን በአክብሮት ተጋብዛችኋል።

የመላኪያ አድራሻዎች
pirdir@du.edu.et
https://t.me/DillauniversityPIR
engdiaw@gmail.com

ማሳሰቢያ፦ ጽሑፎቹ በአማርኛ አልያም በእንግሊዘኛ ቋንቋ ሊቀርቡ ይችላሉ።