Dilla University Official
18.3K subscribers
4.12K photos
23 videos
249 files
445 links
University of the Green Land
Download Telegram
‎የኩላሊት እጥበት ማዕከል ግንባታ የመሠረተ ድንጋይ ተቀመጠ
==============**********===========

‎ዲዩ: ነሐሴ 10/2018 አ.ም (ህ.ዓ.ግ)

‎በዲላ ከተማ በሜሪጆይ ኢትዮጵያ አማካኝነት ለሚገነባው የኩላሊት ዕጥበት ማዕከል ግንባታ፣ የዲላ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ እና የዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት እንዲሁም የድርጅቱ ኃላፊዎች በተገኙበት የመሠረተ ድንጋይ ተቀምጧል።

የዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ቶሎሳ ዳዲ (ዶ/ር) ዩኒቨርሲቲው በማህበረሰብ አገልግሎትና አጋርነት በኩል የተለያዩ ስራዎችን እያከናወነ መሆኑን አንስተው፣ የሜሪጆይ የኩላሊት ዕጥበት ማዕከል ተገንብቶ ለአገልግሎት እንዲበቃ ተቋሙ የበኩሉን እንደሚወጣ አስረድተዋል።

ዩኒቨርሲቲው በሆስፒታሉ አማካኝነት ከሚሰጠው አገልግሎት በተጨማሪ መሠል የማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎት ስራዎች ላይ ከወትሮው በተለየ መልኩ ድጋፍ እንደሚያደርግም አንስተዋል።

‎የዲላ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ መስፍን ደምሴ (ዶ/ር)ሜሪጆይ የኩላሊት እጥበት ማዕከል በከተማው መገንባቱ በጤናው ዘርፍ አዲስ ምዕራፍ እንደሚሆን ገልፀው፣ ተገንብቶ ለአገልግሎት እንዲበቃ ባለድርሻ አካላትን ለማስተባበር እና ፕሮጀክቱ እውን እንዲሆን በቁርጠኝነት እንደሚሰራ ገልፀዋል።

‎በከተማው የሜሪጆይ ኢትዮጵያ የኩላሊት እጥበት ማዕከል መገንባ፣ የማህበረሰቡን የጤና ዘርፍ ፍላጎት ለማሟላት ከፍተኛ ሚላ እንደሚኖረው የገለፁት ደግሞ የሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ የዲላ ቅርንጫፍ አስተባባሪ አቶ ግርማ ደብረ ናቸው።

ዲላ ዩኒቨርሲቲ፣ የዲላ ከተማ አስተዳደር እና ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ ማዕከሉ ተገንብቶ እስኪጠናቀቅ በትብብር ለመስራት እና ባለድርሻ አካላትን በማስተባበር ማዕከሉን እውን ለማድረግ እንደሚሰሩ በመድረኩ ተገልጿል።

#የአረንጓዴው_ምድር_ዩኒቨርሲቲው
#UniversityOfTheGreenland
👍1714
"ተቋሙ ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ እና ለአጀንዳ 2030 ግብ መሳካት ቁርጠኝነቱን እያሳየ ይገኛል" - ቶሎሳ ዳዲ (ዶ/ር)
===========*************============

ዲ.ዩ: ነሐሴ 11/12/2018ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ)

በዲላ ዩኒቨርሲቲ በመደራጀት ላይ የሚገኙ የስማርት መማሪያ ክፍሎች ያሉበትን ደረጃ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ቶሎሳ ዳዲ (ዶ/ር) ተዘዋውረው ተመልክተዋል።

በዩኒቨርሲቲው በአራቱም ጊቢዎች እጅግ ዘመናዊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች የተሟላላቸው የስማርት መማሪያ ክፍሎችን በማደራጀት ለመጪው የትምህርት ዘመን ዝግጁ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል።

ፕሬዝዳንቱ በሀሴዴላ ጊቢ እና በማስተማሪያ ሆስፒታሉ ፕሮጀክቱ የደረሰበትን ደረጃ የተመለከቱ ሲሆን፣ ዩኒቨርሲቲው አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶችን በማደራጀት ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ እና ለአጀንዳ 2030 ግብ መሳካት ቁርጠኝነቱን እያሳየ እንደሚገኝ አውስተዋል።

ፕሬዝዳንቱ አክለውም ፕሮጀክቱ እስኪጠናቀቅ ድረስ አስፈላጊው ሁሉ ድጋፍ እና ክትትል እንደሚደረግም ገልፀዋል።

ዲላ ዩኒቨርሲቲ በአዲሱ የትምህርት ዘመን፣ በርካታ አዳዲስ የትምህርት ግብዓቶችን በማሟላት ተማሪዎቹን ለመቀበል ዘርፈ ብዙ ተግባራትን እያከናወነ ስለመሆኑ ተገልጿል።

===###===

#የአረንጓዴው_ምድር_ዩኒቨርሲቲ
#UniversityOfTheGreenland
32👍1
Programs offered at Dilla University
16
ማስታወቂያ
👍3212
🔔አዲስ ማስታወቂያ📢
=====*****=====

በዲላ ዩኒቨርሲቲ የፈተና ማዕከል ለተመደባችሁ የድህረ ምረቃ መግብያ ፈተና ተፈታኞች በሙሉ

በዩኒቨርሲቲው የምትፈተኑ ተፈታኞች በቀን 20/12/2018ዓ.ም ከጧቱ 3:00 ጀምሮ እስከ 6:00 ባለው ጊዜ ብቻ መሆኑን አውቃችሁ ለፈተናው እንድትዘጋጁ ስንል እናሳስባለን።

#የአረንጓዴው_ምድር_ዩኒቨርሲቲ
#UniversityOfTheGreenland
#NGATEXAM
10👍3