የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት
=====***======
የዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኤልያስ አለሙ መላው የክርስትና እምነት ተከታዮችን እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ በማለት መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል።
ፕሬዝዳንቱ በመልዕክታቸው፣ መላው የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ በዓሉን ሲያከብር፣ ያለው ለሌለው በማካፈል፣ በመረዳዳት ስሜት በፍፁም መተሳሰብ እና ወንድማዊ ፍቅር መሆን እንዳለበት አስገንዝበዋል።
ከቤተሰብ ብዙ ሺህ ኪሎሜትሮችን ርቀው በዓሉን በዩኒቨርሲቲው እያሳለፉ የሚገኙ ተማሪዎችም፣ ያላንዳች ሀሳብ በተለመደው መንገድ፣ ቤተሰብ ጋር ያሉ እስኪመስላቸው ድረስ በዓሉን በተለያዩ ስነ-ስርዓቶች እንዲያከብሩ ለማስቻል ዩኒቨርሲቲው የተለመደውን ሁሉ ነገር ለማድረግ ዝግጅቱን ማጠናቀቁንም ፕሬዝዳንቱ ገልፀዋል።
በዩኒቨርሲቲው ከኢትዮጵያውያን ተማሪዎች ጎን ለጎን የሌሎች ጎረበት ሀገራት ተማሪዎችም ስለመኖራቸው የተናገሩት ፕሬዝዳንቱ፣ በዓሉን የጋራ በማድረግ ኢትዮጵያዊ ባህላችንን እና መልካም እሴቶቻችንን ለሌሎች በማጋራት ልናሳልፍ ይገባል ብለዋል።
በመጨረሻም በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር፣ የአንድነት እና የደስታ በዓል እንዲሆን ተመኝተዋል።
================================
President of Dilla University Elias Alemu (PhD), has conveyed his heartfelt Christmas wishes to the entire Christian community on the joyous occasion commemorating the birth of Jesus Christ.
In his festive address, the President urged all members of the university to celebrate with a spirit of generosity—sharing with the less fortunate, offering comfort, and embracing humility and fraternal affection.
He further shared that the university has taken deliberate steps to ensure students far from home—some separated by thousands of kilometers—can still partake in Christmas traditions and feel a sense of familial warmth through organized events and gatherings.
Dr. Elias pointed out that alongside Ethiopian nationals, learners from various nations also study at Dilla. He encouraged everyone to celebrate collectively as an opportunity to showcase Ethiopia's rich cultural heritage and virtuous traditions.
The President expressed his hope that this Christmas be filled with peace, love, unity, and happiness.
===###===
#University_of_the_Greenland!

🙏36❤25👍8👎3
የስብሰባ ጥሪ
==****==
ለዲላ ዩኒቨርሲቲ መምህራን እና አስተዳደር ሠራተኞች የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማኅበር አባላት በሙሉ
የዲላ ዩኒቨርሲቲ መምህራን እና አስተዳደር ሠራተኞች የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማኅበር ጥር 02 ቀን 2018 ዓ.ም የማህበሩን 20ኛ አመት ምሥረታ በዓልን አስመልክቶ ጠቅላላ ጉባኤ ያካሄዳል፡፡
በዕለቱ ከጧቱ 2:30 ላይ በነባሩ ግቢ ሁለገብ አዳራሽ እንድትገኙ ማህበሩ ጥሪውን ያስተላልፋል።
#ማሳሰቢያ፡
1.ከአቅም በላይ ካልሆነ በስተቀር ማንኛውም የማህበሩ አባል በስብሰባው ላይ የመገኘት ግዴታ አለበት፡፡
2.በስብሰባው ላይ በተገኙ አባላት የሚወሰን ማንኛውም አይነት ውሳኔ ባልተገኙት አባላት ላይም ተፈፃሚ ይሆናል፡፡
3.የሰርቪስ አገልግሎት በየፈርማታው ስለሚዘጋጅ 2፡00 ሰዓት ቀደም ብላችሁ በየፈርማታው እንድትገኙ እናሳስባለን፡፡
ከተባበርን እንችላለን!
===###===
#የአረንጓዴው_ምድር_ዩኒቨርሲቲ

❤27👎6👍2
ለዲላ ዩኒቨርሲቲ ካምፓስ ፖሊስ አባላት የስራ ላይ ግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እየተሰጠ ነው
===========***============
ዲ.ዩ: ጥር 6/2018 ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ)
የዲላ ዩኒቨርሲቲ ከጌዴኦ ዞን ፖሊስ መምሪያ ጋር በመተባበር ለዩኒቨርሲቲው ካምፓስ ፖሊስ አባላት የስራ ላይ ግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እየሰጠ ይገኛል።
የዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ኤልያስ አለሙ (ዶ/ር)፣ በስልጠናው ላይ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር፣ ስልጠናው የዩኒቨርሲቲው ጥበቃ አካላት በቂ ግንዛቤ እንዲኖራቸው የዩኒቨርሲቲው ቦርድ ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ከዞኑ ፖሊስ መምሪያ ጋር በመተባበር እየተሰጠ እንደሚገኝ ገልፀው፣ ስልጠናው በዋናነት የዩኒቨርሲቲው ካምፓስ ፖሊስ አባላት በስራ ላይ የሚገጥሟቸውን ችግሮች እንዴት መፍታት እንደሚችሉ ከዞኑ ፖሊስ ትልቅ ልምድ እንዲወስዱ ለማስቻል መዘጋጀቱን ተናግረዋል።
ፕሬዝዳንቱ አያይዘውም፣ ሰልጣኞች ዲላ ዩኒቨርሲቲ በመማር ማስተማር በርካታ ስመ ጥር ዜጎችን በማፍራት የትልቅ ታሪክ ባለቤት የሆነ ተቋም መሆኑን በመገንዘብ፣ በቀጣይም ስራዎቹን በላቀ አፈፃፀም እንድያከናውን ብሎም ሰላማዊ የመማር ማስተማር ስራው እንዲሳለጥ፣ የካምፓስ ፖሊስ አባላት ስራቸውን በትልቅ የሀላፊነት ስሜት ማከናወን እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል።
የጌዴኦ ዞን ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር ብሩ ማርቆስ በበኩላቸው፤ ስልጠናው ከንደፈ ሃሳብ ባለፈ መሰረታዊ የውትድርናን የመስክ ስልጠናን ባካተተ መልኩ፣ በፖሊሳዊ ዲሲፒሊን ተመርቶ እንደሚሰጥ ገልጸው፣ ሰልጣኞች ከስልጠናው በኃላ ዩኒቨርሲቲውን የሚመጥን ስራ ለመስራት ስልጠናውን በኃላፊነት እንዲከታተሉ እንዲሁም ንቁ ተሳትፎ እንድያደርጉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
ስልጠናው የተግባር ስልጠናን ባካተተ መልኩ ለተከታታይ አስር ቀናት የሚሰጥ ስለመሆኑ በመድረኩ ተገልጿል።

❤27
ማስታወቂያ
==***==
በዚህ ወር ለሚሰጠው የድኅረ ምረቃ ፕሮግራም የመግቢያ ፈተና (NGAT) የአመልካቾች ምዝገባ ያድርጉ!
ምዝገባው የሚጠናቀቀው: ጥር 15/2018 ዓ.ም
የመመዝገቢያ ቅጽ ላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች በማሟላት https://ngat.ethernet.edu.et ላይ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑ እንገልፃለን። (ሊንኩ ክፍት እስከሚደረግ በትዕግስት ይሞክሩ)
🔔 ሁሉም አመልካቾች የፋይዳ መታወቂያ ሊኖራችሁ ይገባል። የምዝገባ እና የአገልግሎት ክፍያ 750 ብር በቴሌብር በኩል ብቻ መከፈል ይኖርባችኋል።
ፈተናው የሚሰጥበትን ቀን ወደፊት የሚያሳውቅ መሆኑን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ገልጿል።

❤17👍6
የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት
=====**=======
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ2018ዓ.ም የጥምቀት በዓል በሰላም አደረሳችሁ።
በዓሉ የሰላም፣ የአንድነት፣ የመተሳሰብ እና የፍቅር እንዲሆንላችሁ በራሴና በዩኒቨርሲቲው ማኔጅመንት ስም መልካም ምኞቴን እገልፃለሁ።
በዓሉን ስናከብር በፍፁም ኢትዮጵያዊ ባህላችን ለአቅመ ደካማ ወገኖቻችን ያለንን በማካፈል፣ በአንድነት ሆነን በደስታ ማክበር ይኖርብናል።
መልካም በዓል!
ኤልያስ አለሙ (ዶ/ር)
የዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት
===###===
#የአረንጓዴው_ምድር_ዩኒቨርሲቲ!

❤24👍20👎4
ዲላ ዩኒቨርሲቲ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ማዕደን ባለስልጣን ቢሮ ጋር የመግባቢያ ሰነድ ስምምነት ተፈራረመ
===========*===========
ዲ.ዩ: ጥር 13/05/2018 ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ)
ዲላ ዩኒቨርሲቲ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ማዕደን ባለስልጣን ቢሮ ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችለውን የመግባቢያ ሰነድ ስምምነት ተፈራርሟል።
የዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ኤልያስ አለሙ (ዶ/ር) በወቅቱ እንደተናገሩት፣ ዲላ ዩኒቨርሲቲ በክልሉ ያሉ የማዕድን ሀብቶችን እና ሌሎች የተፈጥሮ ፀጋዎችን በማጥናት፣ የክልሉን የማዕድን አቅም በመለየት ለክልሉ ቢሮ በማቅረብ ያለውን ሀብት በአግባቡ በመጠቀም ዘርፉ ለሀገር ዕድገት የሚጠበቅበትን እንዲያበረክት ለማድረግ፣ ከባለስልጣኑ ጋር በቅርበት ለመስራት እንደሆነ አንስተዋል።
እንደ ሀገር በርካታ የማዕድን ሀብቶች ቢኖሩም፣ ያለውን ሀብት ጥቅም ላይ በማዋል፣ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ ላይ የተሰራው ስራ አናሳ መሆኑን ያነሱት ፕሬዝዳንቱ፣ ይህንን ችግር ለመቅረፍ እንደ ሀገር የተያዘውንም እቅድ ለማሳካትና ዘርፉን በምርምር ለመደገፍ ዲላ ዩኒቨርሲቲ የዚህ ተግባር አካል እንዲሆን በመመረጡ የተሰማቸውን ደስታ ገልፀዋል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የማዕድን ባለስልጣን ምክትል ዳይሬክተር አቶ ማርክነህ ቦጋለ በበኩላቸው፣ ክልሉ በርካታ የማዕድን ሀብት እንዳለው በመግለጽ፣ ስምምነቱ ይህንን ሀብት እንደ ዲላ ዩኒቨርሲቲ ዓይነት አንጋፋ የትምህርት ተቋም እንዲያጠናውና ከዘርፉ ማግኘት ያለበትን እንዲያገኝ ለማስቻል ታስቦ መፈፀሙን አንስተዋል።
ስምምነቱ ለክልሉም ሆነ ለክልሉ ማህበረሰብ በርካታ እድሎችን ይዞ የሚመጣ፣ የክልሉን የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ መሠረት የሚጥል መሆኑም በመድረኩ ተገልጿል።

❤26👎6👌1
የዲላ ዩኒቨርሲቲ ስፖርት ልዑካን ቡድን በሀገር አቀፍ የስፖርት ፌስቲቫል ላይ እየተሳተፈ ነው
===========*****===========
ዲ.ዩ: ጥር 17/2018ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ)
በጅማ ዩኒቨርሲቲ አስተናጋጅነት በሚካሄደው የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የስፖርት ፌስቲቫል ላይ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ስፖርት ልዑካን ቡድን እየተሳተፈ ይገኛል።
የልዑካን ቡድኑ መሪ ማስረሻ ኤራጎ (ዶ/ር) እንደገለጹት፤ የስፖርት ፌስቲቫሉ በተማሪዎች መካከል ትስስርን ከመፍጠርና ባህልን ከማበልፀግ ባለፈ ተተኪ ስፖርተኞችን ለማፍራት ዓይነተኛ ሚና እንዳለው ተናግረዋል።
ቡድኑ ልምምድ ከሚሰራበት ጊዜ ጀምሮ የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራር ላደረገው እገዛ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
ለተከታታይ 15 ቀናት በሚካሄደው 10ኛው የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የስፖርት ፌስቲቫል ላይ 48 የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ተሳታፊ እንደሚሆኑ በመድረኩ ተገልጿል።
በዛሬው ዕለት በወጣው ፕሮግራም መሰረትም የዲላ ዩኒቨርሲቲ በነገው እለት የመጀመሪያ ጨዋታውን የሚያደርግ ይሆናል።

❤22👍22👎8
በቅርጫት ኳስ እና ቼዝ ውድድሮች ድላ ዩኒቨርሲቲ ተጋጣሚዎቹን አሸነፈ
===========****============
ዲ.ዩ: ጥር 18/2018ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ)
በጅማ ዩኒቨርሲቲ አስተናጋጅነት እየተካሄደ በሚገኘው የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የስፖርት ፌስቲቫል ላይ የዲላ ዩኒቨርሲቲ በሁለተኛው ቀን ጨዋታዎች በቅርጫት ኳስ እና ቼዝ ጨዋታዎች ድልን ተቀዳጅቷል።
ትላንት ጠዋት ላይ በነበሩ ጨዋታዎች የዲላ ዩኒቨርሲቲ ቅርጫት ኳስ ቡድን ከባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ጋር ጨዋታውን አድርጎ 52 ለ 41 በሆነ ውጤት አሸንፏል።
በሴቶች ቅርጫት ኳስ ውድድር ደግሞ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አቻው 45 ለ 18 ተሸንፏል።
ጠዋት ላይ በተደረገ የቼዝ ጨዋታ የዲላ ዩኒቨርሲቲ የቼዝ ስፖርት ቡድን የወራቤ ዩኒቨርሲቲን 3 ለ 0 በማሸነፍ ድልን ተቀዳጅቷል። በጠረጴዛ ቴኒስ ውድድርም የወራቤ ዩኒቨርሲቲን 2 ለ 1 በማሸነፍ በድል ተወጥቷል።
ከሰዓት ላይ በተደረገ የመረብ ኳስ የሴቶች ጨዋታ በሰላሌ ዩኒቨርሲቲ ሲሸነፍ፣ ምሽት 2 ሰዓት በተካሄደ የቅርጫት ኳስ (3×3) ጨዋታ ዲላ ዩኒቨርሲቲ የሰላሌ ዩኒቨርሲቲን 15 ለ 1 በሆነ ሰፊ ውጤት አሸንፏል።
ለአንጋፋው ዩኒቨርሲቲያችን መልካሙን ሁሉ እንመኛለን።

👍38❤26👎3