በሀሮሬሳ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መማሪያ ክፍሎችን ለመገንባት የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ
============*============
ዲ.ዩ: ታህሳስ 04/2018ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ)
ዲላ ዩኒቨርሲቲ ከፍሊንትስቶን ኢንጂኔሪንግ ጋር በመሆን በሀሮሬሳ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለሚገነባው ተጨማሪ የመማሪያ ክፍሎች ግንባታ፣ ከከተማ አስተዳደሩ ጋር በመሆን የመሰረት ድንጋይ አኑሯል።
የዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ኤልያስ አለሙ (ዶ/ር) በመድረኩ ላይ ባደረጉት ንግግር፣ እንደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ዩኒቨርሲቲው ላለፉት ሁለት አስርት ዓመታት ሀገርን የሚያሻግሩ በርካታ ምሁራንን በማፍራት ሀገራዊ ተልዕኮውን ከመወጣት ጎን ለጎን የማህበረሰብ አገልግሎት ስራዎችንም እየሰራ መቆየቱን ጠቅሰዋል።
ፕሬዝዳንቱ አክለውም፣ ጊዜው አቅምን በመደመር የሚታይ ስራ የመስራት ጊዜ እንደመሆኑ፣ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን፣ ነገ ላይ እኛን ተክተው ሀገርን የሚያሻግሩ ህፃናት በእውቀት እንዲጎለብቱ ለማስቻል በማሰብ፣ ተጨማሪ ጥራታቸውን የጠበቁ መማሪያ ክፍሎችን ለመገንባት ዩኒቨርሲቲው እየሰራ መሆኑን አውስተው፣ ትምህርት ላይ መስራት ነገ ሀገርን በተሻለ መሰረት ላይ ለማጽናት እጅጉን እንደሚያግዝ ተናግረዋል።
"መሠል የማህበረሰብ አቀፍ ስራዎችን ለመስራት፣ የከተማ አስተዳደሩም ሆነ የዞኑ አመራሮች በሁሉም ረገድ ከጎናችን ስለምትቆሙ፣ ስለምትደግፉን እና የዚህ ተግባር ተጋሪ የሆነውን ፍሊንትስቶን ኢንጂነሪንግን ከልብ እናመሰግናለን" ብለዋል ፕሬዝዳንቱ በመልዕክታቸው።
የዲላ ከተማ ከንቲባ መስፍን ደምሴ (ዶ/ር) በበኩላቸው፣ የትምህርት ስብራትን ለመጠገን፣ በአንድ መማሪያ ክፍል የሚማሩ ተማሪዎች በደረጃው ልክ መሆን ወሳኝ መሆኑን አንስተው፣ የሚገነባው መማሪያ ክፍል ከዚህ አንፃር በት/ቤቱ የሚስተዋለውን ችግር ለመፍታት እንደሚረዳ አንስተዋል።
ትምህርት የእድገት ሁሉ መሰረት፤ የችግሮች ሁሉ መፍቻ ቁልፍ መሆኑን የተናገሩት ከንቲባው፣ የማህበረሰቡን ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና፣ ፖለቲካዊ ችግሮችን ለመፍታት እና ብልጽግናን ለማረጋገጥ ዕውቀት ወሳኝ መሆኑን ተናግረው፣ ትምህርት ላይ ከሁሉ በላቀ መልኩ በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት በከተማው ያሉ ለማህበረሰቡ ትርጉም ያላቸውን ስራዎች ለመስራት፤ ከተማውን እና ተቋሙን በጋራ በማስተሳሰር የማህበረሰቡን ችግር ለመፍታት ለሚያደርጉት ቀና ትብብርም ምስጋና አቅርበዋል ዶ/ር መስፍን።
የግንባታውን ስራ የሚያከናውነው ፍሊንትስቶን ኢንጂነሪንግ ተወካይ ኢንጂነር ዘገየ፣ ምስጉን ለሆነው ህዝብ ማስታወሻ የሚሆን፣ ትውልዱን በዕውቀት የሚገነባ፣ የትምህርት ቤት ግንባታ ስራ ላይ መሳተፍ እድል መሆኑን አንስተው፣ በተመሳሳይ በሌሎች ትምህርት ቤቶችም ተመሳሳይ ስራ ለመስራት፣ ከተያዘው ጊዜም ቀድሞ ለማስረከብ የሚቻላቸውን ሁሉ ርብርብ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል።
የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር ታሪኩ በቀለ ትምህርት ቤቱ በርካታ ምሁራንን ያፈራ እንደሆነ ጠቁመው ከቆይታ የተነሳ ዘመኑን የማይመጥን ከደረጃ በታች በሆኑ መማሪያ ክፍሎች እያስተማረ መሆኑን ተናግረው፣ አዳዲስ መማሪያ ክፍሎች ለመገንባት አጋሪነቱን ያሳያቸውን ዲላ ዩኒቨርሲቲን አመስግነዋል።
ግንባታው ከስልሳ ቀናት ባጠረ ጊዜ ይጠናቀቃል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፣ ሁለት የመማሪያ ብሎኮችን ለመገንባት የሚያስችል የመሰረት ድንጋይ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኤልያስ አለሙ፣ የዲላ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ዶ/ር መስፍን ደምሴ እና የፍሊንትስቶን ኢንጂነሪንግ ተወካይ ኢንጂነር ዘገየ፣ ሌሎችም የዩኒቨርሲቲው እና የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት በጋራ አኑረዋል።
ከሚሰራው የመማሪያ ክፍሎች ጎን ለጎንም ጥራታቸውን የጠበቁ መፀዳጃ ቤቶች እንደሚሰሩ ተገልጿል።
===###===
#የአረንጓዴው_ምድር_ዩኒቨርሲቲ

❤37👍12👎5
በቡና ጥራት ምርምር እና ቁሌት ዘዴዎች ላይ ለሴቶች ማህበር ስልጠና ተሰጠ
==========****=========
ዲላ፡ ታህሳስ 10/2018 ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ)
የዲላ ዩኒቨርሲቲ የቡና ምርምርና ስልጠና ተቋም ዳይሬክቶሬት በቡና ጥራት ግምገማ፣ በቡና ቁሌት እና በቡና ቅምሻ ርዕሶች ላይ ለ“ዉሊ አብንዶ” የሴቶች ማህበር ስልጠና ሰጥቷል። ስልጠናው 12 የማህበሩ ሴት አባላትን ያሳተፈ ነበር።
የዲላ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ አገልግሎትና አጋርነት ዳይሬክተር አቶ ተካልኝ ታደሰ፣ ስልጠናው ቡናን በጥራት ቆልቶ በማሸግ፣ ለሀገር ውስጥና ለውጭ ገበያ ማቅረብ እንዲቻል የሚያግዝ መሆኑን ገልፀው፣ ሙያዊ እገዛና የዕውቀት ሽግግር ማድረግ በጥራት ምርት ለማቅረብና ደንበኛን ለማፍራት እንደሚያግዝ አመልክተዋል።
አቶ ተካልኝ በተጨማሪም፣ ማህበራቱ ይህን ቴክኒካል ዕውቀት ቀድሞ ማግኘታቸው ሌሎችንም ሴቶች በተጠቃሚነት ለማሳተፍ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ጠቁመዋል።
የዲላ ዩኒቨርሲቲ የቡና ምርምርና ስልጠና ተቋም ዳይሬክተር አለሙ ደሳ (ዶ/ር) ስልጠናው ዩኒቨርሲቲው ለማህበረሰቡ ከሚያደርገው ድጋፍ አንዱ መሆኑን ገልጸው፣ ማህበሩ የቡናን ጥራት በጠበቀ መልኩ፣ ከዝግጅት ጀምሮ ለገበያ እስከማቅረብ ድረስ ያለውን ሂደት እንዲረዱ፣ በተግባር የተደገፈ የክህሎት ስልጠና መሆኑን እስረድተዋል።
ዳይሬክተሩ አክለውም፣ ስልጠናው ሴቶችን የኢኮኖሚ ተጠቃሚ ለማድረግ እንዲሁም የአካባቢው ቡና ጥራቱን ጠብቆ እና በሳይንሳዊ መንገድ ተዘጋጅቶ ለገበያ እንዲቀርብ አስፈላጊ ሚና እንደሚኖረው ጠቁመዋል።
በተያያዘ ዜና፣ በዲላ ዩኒቨርሲቲ የቡና ምርምርና ስልጠና ተቋም የሶስተኛ ዙር የቡና ሰልጣኞች በቡና ምርትና ልማት ዙሪያ የመስክ ጉብኝት አካሂደዋል። የመስክ ጉብኝቱ በክፍል ውስጥ በንድፈ ሃሳብ የተማሩትን ትምህርቶች በተግባር ለማጠናከር የተዘጋጀ ሲሆን፣ ከዘር ጀምሮ እስከ ችግኝ ዝግጅት፣ የችግኝ እድገትና እንክብካቤ ድረስ በተግባር እንዲማሩ ለማስቻል ነው።
ጉብኝቱ በዱመርሶ ችግኝ ጣቢያና በወናጎ ወረዳ በካራ ሶዲቲ ቀበሌ ያሉ የአርሶ አደር እና ሞዴል አርሶ አደር ማሳዎች ላይ የተደረገ ሲሆን፣ የዚህ ዙር ሰልጣኞችም በዩኒቨርሲቲው የሚሰጠው ስልጠና ከተግባራዊ ምልከታ ጋር በማጣጣም ያገኙት ዕውቀት በዘርፉ ላይ ለሚሰሩት ስራ እጅግ ጠቃሚ መሆኑን ተናግረዋል።
===###===
#የአረንጓዴው_ምድር_ዩኒቨርሲቲ!

❤12👎5👍3
CALL FOR INNOVATIVE PROJECT PROPOSALS
===========**==========
Dilla University, through the University–Industry Linkage and Technology Transfer (UIL-TT) Directorate, invites innovative and impactful project proposals for the 3rd Call for Innovative and Technology Projects – 2025.
We encourage faculty members, researchers, and innovators to submit proposals that address real-world challenges and promote technology transfer, innovation, and sustainable development.
📌 Deadline: 29 December 2025
Let’s transform ideas into solutions and strengthen innovation at Dilla University!
===###===
#University_of_the_Greenland!

❤17👍10👎1
ዲላ ዩኒቨርሲቲ አዲስ ገቢ ተማሪዎችን እየተቀበለ ነው
=========**==========
ዲላ ዩኒቨርሲቲ በ2018ዓ.ም በአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም ወደ ዩኒቨርሲቲው የተመደቡ አዲስ ገቢ ተማሪዎችን እየተቀበለ ነው።
በዘንድሮው የትምህርት ዘመን ወደ ዩኒቨርሲቲው የተመደቡ የአቅም ማሻሻያ ፕሮግራም ተማሪዎች ዛሬ እና ነገ ተጠቃለው የሚገቡ ይሆናል።
ዩኒቨርሲቲው እንኳን ወደ አረንጓዴው ምድር ዩኒቨርሲቲ በሰላም መጣችሁ እያለ መልካም ምኞቱን ይገልፃል።

❤42👍4👎3
ዲላ ዩኒቨርሲቲ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ
==========*=========
ታህሳስ 22/04/2018ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ)
ዲላ ዩኒቨርሲቲ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዲላ ዲስትሪክት ጋር 'ሲቢኢ በእጄ' የተሰኘ የዲታል ቁጠባና ብድር አገልግሎት ለማስጀመር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሟል።
በዚህ 'ሲቢኢ በእጄ' በተሰኘው አገልግሎት የዩኒቨርሲቲው ሰራተኞች ያለ ምንም ዋስትና በሞባይል ስልካቸው አማካኝነት ከአምስት መቶ እስከ አንድ መቶ ሃምሳ ሺህ ብር በፈለጉት ሰዓት የብድር አገልግሎት ማግኘት ይችላሉ ተብሏል።
የዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ኤልያስ አለሙ(ዶ/ር)፣ ስምምነቱ ዩኒቨርሲቲው የጀመረውን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ ከማጠናከር ባሻገር የዩኒቨርሲቲው ሰራተኞች ስራቸውን ተረጋግተው እንዲሰሩ ብሎም የብድር አገልግሎት እንዲያገኙ ያስችላል ብለዋል።
ዩኒቨርሲቲው የሰራተኞቹን ፍላጎት ያማከሉ በርካታ ፕሮጀክቶችን ወደ ተግባር ለማስገባት በርካታ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ ጠቁመው፣ በቀጣይ ለሚያከናውናቸው ስራዎች ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር በቅንጅት ለመስራት ዝግጁ ስለመሆኑ ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዲላ ዲስትሪክት ዳይሬክተር አቶ ሙሴ ከበደ በበኩላቸው፣ ባንኩ እየተገበረ ያለው ሲቢኢ በእጄ፣ የብድርና ቁጠባ ባህልን በማሳደግ የዩኒቨርሲቲው ሰራተኞችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ተናግረዋል። አክለውም የባንኩን መስፈርት ለሚያሟሉ የዩኒቨርሲቲው ሠራተኞች ባንኩ ለቤት መስሪያ፣ ለተሽከርካሪ መግዣና ለሌሎችም ፍላጎቶች የብድር አገልግሎት እንደሚሰጥ ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዲላ ዲስትሪክት ዲጂታል ባንኪንግ ስራ አስኪያጅ አቶ የሱፍቃድ ይርጋ፣ ፍላጎት ያላቸውን መምህራን እና ሰራተኞች ሲቢኢ በእጄ አካውንት በመክፍት በፈለጉበት ሰዓት ወደ ባንኩ በአካል መምጣት ሳያስፈልጋቸው ብድር መውሰድ እንደሚችሉ ጠቁመው በቀጣይም ለተቋሙ ሰራተኞች በብድር እና ቁጠባው አሰራር ስርዓት ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮች እንደሚዘጋጁ ገልፀዋል።
ስምምነቱን የዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ኤልያስ አለሙ(ዶ/ር)፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዲላ ዲስትሪክት ዳይሬክተር አቶ ሙሴ ከበደ የተፈራረሙ ሲሆን፣ ሁለቱ ተቋማት በቀጣይም በሌሎች የልማትና የቴክኖሎጂ ዘርፎች ላይ በትብብር ለመስራት ያላቸውን ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዲላ ዲስትሪክት ዲላ ዩኒቨርሲቲ ለባንኩ ላበረከተው የላቀ አስተዋፅኦ የምስጋና ምስክር ወረቀት አስረክቧል።

👍24❤23🙏3👎1
አዲስ ለገቡ የአቅም ማሻሻያ ኘሮግራም ተማሪዎች ገለፃ ተደረገ።
=======*=========
ዲ.ዩ: ታህሳስ 22/2018 ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ)
በ2018 ዓ.ሞ በአቅም ማሻሻያ ፕሮግራም ወደ ዩኒቨርስቲው ለተመደቡ አዲስ ገቢ ተማሪዎች ገለፃ ተሰጥቷል።
የዲላ ዩኒቨርሲቲ ዋና ሬጂስትራር አስናቀ ይማም (ዶ/ር)፣ በ2018 የትምህርት ዘመን የሪሚዲያል መግቢያ መስፈርቶችን አሟልተው ወደ ዩኒቨርሲቲው ለተመደቡ ተማሪዎች እንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈዉ፣ በአቅም ማሻሻያ ኘሮግራም ወደ ዩኒቨርሲቲው የተመደቡ በተፈጥሮ ሳይንስ ዘርፍ 2ሺ 674 እና በማህበራዊ ሳይንስ 1ሺ 484፣ በአጠቃላይ 4ሺህ 158 ተማሪዎች የተመደቡ መሆናቸውን ገልፀዋል።
የዲላ ዩኒቨርሲቲ ፍሬሽ ማን ፕሮግራም ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ዋና አስተባባሪ መምህር መንግሥቱ ተሾመ እንደተናገሩት ተማሪዎች እያንዳንዱን ተግባር ተከታትለው ተምረው ዉጤታማ መሆን እንዳለባቸው ግንዛቤ የማስጨበጥ ስራ መሠራቱን ተናግረዋል።
የዲላ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች አገልግሎት ም/ዲን እና የተማሪዎች አገልግሎት ዲን ተወካይ አቶ መልካሙ አለሙ በበኩላቸው ተማሪዎች በዶርሚተሪ አካባቢ፣ በምግብ አገልግሎት፣ በክሊኒክ አገልግሎት ዙሪያ እንዲሁም የመዝናኛ አገልግሎትን በተመለከተ፣ በሌላ በኩል የተማሪ መብቶች እና ግዴታዎች እንዲሁም የዲስፕሊን ቅጣት ሊያስከትሉ የሚችሉ ጉዳዮችን በተመለከተ ግንዛቤ መሠጠቱን ተናግረዋል።
ገለፃዉን ሲከታተሉ ካገኘናቸው ተማሪዎች መካከል እንደገለፁት በተቋሙ የተደረገላቸው አቀባበል እንዳስደሰታቸው እና በዩኒቨርሲቲው ቆይታቸው ሊጠብቋቸው ስለሚገባ የስነ-ምግባር መርሆዎች በቂ እዉቀት እንዳገኙ ገልፀዉልናል።

❤45🙏3👎2👍1