የምዝገባ ጥሪ ማስታወቂያ
======****======
በዲላ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛው ፕሮግራም በ2ኛ እና 3ኛ ድግሪ ለመማር አመልክታችሁ ተቀባይነት ያገኛችሁ አመልካቾች ምዝገባ የሚካሄደው፣ ከህዳር 9-10/2018ዓ.ም መሆኑን አውቃችሁ በተባሉት ቀናት ላይ በአካል በመቅረብ እንድትመዘገቡ እናሳውቃለን።
#የአረንጓዴው_ምድር_ዩኒቨርሲቲ

❤30👎19👍10
የዩኒቨርሲቲው የ10 ዓመት መሪ ዕቅድ ያለፉት የአምስት ዓመታት ትግበራ ተገምግሞ የቀጣይ አምስት አመት ስትራቴጂክ እቅድ እየተከለሰ ነው
==========*==========
ዲ.ዩ: ህዳር 06/03/2018ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ)
የዲላ ዩኒቨርሲቲ የ10 ዓመት መሪ ዕቅድ ያለፉት የአምስት ዓመታት ትግበራ ተገምግሞ የቀጣይ አምስት አመት ስትራቴጂክ እቅድ እየተከለሰ ይገኛል።
የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ኤልያስ አለሙ (ዶ/ር) ኮሚተው የደረሰበትን ደረጃ አስመልክቶ በሰጡት ማብራሪያ፣ ዩኒቨርሲቲው የተጀመረውን የትምህርት ሪፎርም ከግምት በማስገባት፣ የጀመራቸውን ስራዎች ይበልጥ ለማስቀጠል እና ቀሪ ተግባራትን ለመፈፀም በሚያስችል መልኩ፣ ያለፈው አምስት ዓመታት ትግበራ እንዲገመገም በማድረግ፣ የመጪውን አምስት አመታት ስትራቴጂክ እቅድን ደግሞ ለመከለስ ኮሚቴ አቋቁሞ እየሰራ እንደሚገኝ ጠቁመው፣ የአምስት ዓመቱ የግምገማ ስራ በጥሩ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ገልፀዋል።
የአስር ዓመት መሪ እቅዱ ተግባራዊ መሆን ከጀመረ አምስት አመታት የተቆጠሩ መሆናቸውን የተናገሩት ፕሬዝዳንቱ፣ ጊዜውን የዋጄ እና አሁናዊ የሀገር ፍላጎትን እና የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ደረጃ የሚመጥን እቅድ አድርጎ ለመከለስ ዩኒቨርሲቲው በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ አብራርተዋል።
የክለሳ ስራው የዩኒቨርሲቲውን የትኩረት መስኮች ያገናዘበ፣ ቁልፍ የውጤት አመልካች (KPI) ነጥቦችን ለማሳካት በሚያስችል መልኩ፣ ብሎም ሌሎች የትምህርት ሪፎርሙን ለማሳካት በሚያግዝ መንገድ እየተከለሰ እንደሚገኝ ፕሬዝዳንቱ አብራርተዋል።
ፕሬዝዳንቱ በስራው ላይ የበኩላቸውን ሚና እየተወጡ የሚገኙ የኮሚቴ አባላትንም አመስግነዋል።
===###===
#የአረንጓዴው_ምድር_ዩኒቨርሲቲ!

❤49👎41👍12🙏2
ለመላው የዩኒቨርሲቲያችን መምህራን እና ሰራተኞች በሙሉ ነገ ከ2:30 ጀምሮ በነባሩ ጊቢ ሁለገብ አዳራሽ በሚካሄደው መድረክ ላይ እንድትሳተፉ ተጋብዛችኋል።
እንዳያመልጥዎ!
#የአረንጓዴው_ምድር_ዩኒቨርሲቲ
እንዳያመልጥዎ!
#የአረንጓዴው_ምድር_ዩኒቨርሲቲ
👎55👍16❤10🙏2
"ከሙከራ ወደሚጨበጥ ለውጥ"
========*****========
ዲ.ዩ: ህዳር 16/2018 ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ)
የሌማት ትሩፋት ልማትን ማስፋት ኑሮን መደጎም ብቻ ሳይሆን ጤናማ አመጋገብን ለማረጋገጥ ያግዛል ሲሉ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ኤልያስ አለሙ (ዶ/ር) ተናገሩ።
በዲላ ዩኒቨርሲቲ በሰባት ሄክታር መሬት ላይ እየለማ የሚገኘው የጓሮ አትክልት ልማት፣ ሀገራዊ የሌማት ትሩፋት ኢንሼቲቭ አካል ሲሆን፣ የዩኒቨርሲቲው መምህራንም እየተጠቀሙበት ይገኛሉ።
ቀደም ሲል በሁለት ሄክታር መሬት ላይ በሙከራ ደረጃ መጀመሩን ያነሱት ፕሬዝዳንቱ፣ አሁን ላይ በሰባት ሄክታር መሬት ላይ እየለማ እንደሚገኝ አንስተው፣ ከዚህም በላይ የሚለሙ የአትክልት አይነቶችን እንዲሁም የሚለማበትን መሬት በማስፋት በዘርፉ የበለጠ ለውጥ ለማምጣት እንደሚሰራ ተናግረዋል።
እንደ ፕሬዝዳንቱ ገለፃ፣ ዩኒቨርሲቲው በተለያዩ አከባቢዎች በምርምር ዘርፍ ከሚሰራቸው የግብርና ስራዎቹ ጎን ለጎን፣ በሌማት ትሩፋት በኦዳያኣ ጊቢ የሚያከናውናቸው ተግባራት አንድም ለሰራተኞቹ በቅናሽ ዋጋ ምርቶቹን ለማቅረብ በሌላ በኩል ደግሞ የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ጤናማ አመጋገብን እንድያዘወትር ለማስቻል መሆኑን ገልፀዋል።
በዘርፉ የተመዘገበው ስኬት፣ ከሙከራ ወደሚጨበጥ ለውጥ ለመሸጋገራችን ትልቁ ማሳያ ነው ያሉት ፕሬዝዳንቱ፣ መሠል ስኬቶችን በሌሎች ስራዎቻችንም ላይ መድገም ይጠበቅብናል ብለዋል።
በኦዳያኣ ጊቢ የተጀመረውን በሌሎች ጊቢዎች ላይ በማስፋት በጥራት እና በብዛት በማልማት፣ ምርቶቹን ከዩኒቨርሲቲው ሰራተኞችም ባለፈ፣ ለውጪውም ማህበረሰብ ለማቅረብ በትኩረት እንደሚሰራ ፕሬዝዳንቱ አያይዘው ገልፀዋል።

👎47❤34👍13👌4
Congratulations!
At the 12th National Quality Award Ceremony held at the Grand Palace, Dilla University proudly received the Honorable Mention Certificate Award. This recognition was granted in acknowledgment of the University’s dedication to fulfilling its mission with quality, competence, and excellence.
In his message to the university community, President Dr. Elias Alemu remarked: “It is with great pride that we announce Dilla University has been awarded the Honorable Mention Certificate at the National Quality Award platform. He extended his congratulations to all involved.
He highlighted that this success reflects the outstanding contributions of the university’s leadership at every level, as well as the unwavering commitment of its faculty and staff. He extended his deepest gratitude and appreciation to everyone involved.
===###===
#University_of_the_Greenland

👎58👍40❤19👌7🙏2
Dilla University’s 7th Science Week is Here
===========**===========
Theme: Science for the Brightest Tomorrow
Get ready for two days of groundbreaking ideas, visionary dialogue, and academic inspiration!
👉 Date: 23–24 Hidar 2018 E.C
👉 Time: 2:30 LT
👉 Venue: Nebaru Campus, MPH
Keynote Speakers:
👉 Dr. Ir. Mesele Haile – Applied Research Commercialization for Societal Transformation
👉 Dr. Kula Kekeba – The Dilemmas of AI in Academic Research and Innovation
Organized by RTTVP, RPEDO, and UIL-TT, this event brings together researchers, students, and innovators to explore how science can shape a brighter future.
Don’t miss this chance to connect, learn, and lead the change!
Tag your friends, share the news, and let’s make #ScienceWeekDilla unforgettable!
DillaUniversity #ScienceWeek2025 #Innovation #AIinAcademia #ResearchForChange #BrightestTomorrow

👎31❤18👍11
የበጎ ፈቃደኞች ቀን
የአለም አቀፍ በጎ ፈቃደኞች ቀን በዲላ ዩኒቨርሲቲ በነገው ዕለት ይከበራል።
መላው የዩኒቨርሲቲው መምህራን፣ ሰራተኞች እንዲሁም ተማሪዎች ከጠዋቱ 2:30 ጀምሮ በነባሩ ጊቢ ሁለገብ አዳራሽ በመገኘት በፕሮግራሙ ላይ እንድትሳተፉ ስንል እናሳስባለን።
#የአረንጓዴው_ምድር_ዩኒቨርሲቲ!
የአለም አቀፍ በጎ ፈቃደኞች ቀን በዲላ ዩኒቨርሲቲ በነገው ዕለት ይከበራል።
መላው የዩኒቨርሲቲው መምህራን፣ ሰራተኞች እንዲሁም ተማሪዎች ከጠዋቱ 2:30 ጀምሮ በነባሩ ጊቢ ሁለገብ አዳራሽ በመገኘት በፕሮግራሙ ላይ እንድትሳተፉ ስንል እናሳስባለን።
#የአረንጓዴው_ምድር_ዩኒቨርሲቲ!
👎32❤13👍12🙏4
ዓለም አቀፍ የበጎ ፈቃደኞች ቀን ተከበረ
=======*========
ዲ.ዩ: ህዳር 26 /2018 ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ)
የዲላ ዩኒቨርሲቲ፣ ከኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ጌዴኦ ዞን ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት እና ከሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ ዲላ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ጋር በመተባበር ዓለም አቀፍ የበጎ ፍቃደኞች ቀንን "እያንዳንዱ አስተዋጽኦ አስፈላጊ ነው" በሚል መሪ ቃል በተለያዩ መርሃ ግብሮች አክብሯል።
የዲላ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደርና ልማት ምክትል ፕሬዝዳንት እና የፕሬዝዳንቱ ተወካይ ማቲዎስ ሀብቴ (ዶ/ር) ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር፤ በዩኒቨርሲቲው ለ2ኛ ጊዜ ለሚከበረው ዓለም አቀፍ የበጎ ፍቃደኞች ቀን እንኳን አደረሳችሁ በማለት፣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከመማር ማስተማር ባለፈ ማኅበራዊ ኃላፊነትንም እንዲወጡ ከትምህርት ሚኒስቴር በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ተማሪዎች ማኅበራዊ ኃላፊነታቸውን በመወጣት ፍሬያማ ዜጋ መሆን እንዲችሉ እንደ ተቋም ተማሪዎች በበጎ ፍቃድ አገልግሎት ማህበረሰቡን እንዲያገለግሉ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
የዲላ ዩኒቨርሲቲ ምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ፕሬዝዳንት ሀብታሙ ተመስገን (ዶ/ር)፤ ዩኒቨርሲቲው ባለፉት ጊዜያት የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ሊያረጋግጡ የሚችሉ ተግባራትን ሲሰራ መቆየቱን አውስተው፤ በተለይ ከቅርብ አመታት ወዲህ ደግሞ በማህበረሰብ አገልግሎትና አጋርነት ዳይሬክቶሬት ስር የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ክፍልን በማዋቀር በርካታ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል ብለዋል።
በመድረኩ ቁልፍ መልዕክት ያስተላለፉት፣ የሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ መስራችና ዋና ስራ አስኪያጅ ሲስተር ዘቢደር ዘውዴ፣ በመድረኩ ስለበጎነት ያላቸውን የረዥም ጊዜ ልምድና ተሞክሮ ለተሳታፊዎች አካፍለዋል።

👎17❤15👍1
"ትውልድን የማዳን፣ አሻራን የማኖር ተግባር"
========****=========
ዲ.ዩ: ህዳር 26/03/2018 ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ)
በዲላ ከተማ ሀሮረሳ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ላይ የመስክ ምልከታ ተደረገ። የዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ኤልያስ አለሙ (ዶ/ር) ከዲላ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ መስፍን ደምሴ (ዶ/ር)፣ እና ከሌሎች የዩኒቨርሲቲው አመራሮች ጋር በጋራ በመሆን ትምህርት ቤቱን ጎብኝተዋል።
የዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ኤልያስ አለሙ (ዶ/ር)፣ ትምህርት ቤቱ ረጅም ዕድሜ ያስቆጠረ፣ ብዙ የሀገር ባለውለታዎችን ያፈራ ሆኖ ሳለ፣ አሁን ባለው ሁኔታ ግን ከደረጃ በታች በሆኑ መማሪያ ክፍሎች ተማሪዎችን እያስተማረ እንደሚገኝ፣ የመምህር ለተማሪ ጥመርታውም ለማመን የሚከብድ ከደረጃ ዝቅ ያለ መሆኑን ተናግረዋል።
ዲላ ዩኒቨርሲቲ አጋር አካላትን በማስተባበር በተለያዩ የማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎት ስራዎች ላይ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል ያሉት ፕሬዝዳንቱ፣ በሀሮረሳ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ላይ ለመስራት የታቀደው ግን፣ ትውልድን የማዳን፣ አሻራን የማኖር ተግባር ነው ብለዋል።
ዩኒቨርሲቲው በሶስት (3) ወር ጊዜ ውስጥ ሁለት (2) የመማሪያ ብሎኮችን ሰርቶ ለትምህርት ቤቱ ለማስረከብ ፍሬያማ ምክክር ያደረገ ሲሆን፣ በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ የመሠረተ ድንጋይ እንደሚቀመጥ ተገልጿል።

👎42❤24👍10🙏9
የጥሪ ማስታወቂያ
====****====
በዲላ ዩኒቨርሲቲ በ2018 የትምህርት ዘመን ዲላ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም ተማሪዎች በሙሉ
👉 የመግብያ ቀን #ታህሳስ_20_እና_21/2018 ዓ.ም መሆኑን አውቃችሁ በተጠቀሱት ቀናት በሬጅስትራር ጽ/ቤት በአካል ተገኝታችሁ እንድትመዘገቡ እናሳውቃለን።
✍️ በተፈጥሮ ሳይንስ የተመደባችሁ #ኦዳያኣ_ጊቢ
✍️ በማህበራዊ ሳይንስ ዘርፍ የተመደባችሁ #ሀሴዴ_ጊቢ
👉ከተጠቀሰው ቀን ቀድሞም ሆነ ዘግይቶ የሚመጣን ተማሪ የማናስተናግድ መሆኑን እንገልፃለን።
ይህንን መረጃ ለጓደኞቻችሁ በማጋራት ሁሉም ጋር እንዲደርስ ያድርጉ።

❤74👎24👍15🙏14
በሀሮሬሳ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መማሪያ ክፍሎችን ለመገንባት የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ
============*============
ዲ.ዩ: ታህሳስ 04/2018ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ)
ዲላ ዩኒቨርሲቲ ከፍሊንትስቶን ኢንጂኔሪንግ ጋር በመሆን በሀሮሬሳ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለሚገነባው ተጨማሪ የመማሪያ ክፍሎች ግንባታ፣ ከከተማ አስተዳደሩ ጋር በመሆን የመሰረት ድንጋይ አኑሯል።
የዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ኤልያስ አለሙ (ዶ/ር) በመድረኩ ላይ ባደረጉት ንግግር፣ እንደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ዩኒቨርሲቲው ላለፉት ሁለት አስርት ዓመታት ሀገርን የሚያሻግሩ በርካታ ምሁራንን በማፍራት ሀገራዊ ተልዕኮውን ከመወጣት ጎን ለጎን የማህበረሰብ አገልግሎት ስራዎችንም እየሰራ መቆየቱን ጠቅሰዋል።
ፕሬዝዳንቱ አክለውም፣ ጊዜው አቅምን በመደመር የሚታይ ስራ የመስራት ጊዜ እንደመሆኑ፣ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን፣ ነገ ላይ እኛን ተክተው ሀገርን የሚያሻግሩ ህፃናት በእውቀት እንዲጎለብቱ ለማስቻል በማሰብ፣ ተጨማሪ ጥራታቸውን የጠበቁ መማሪያ ክፍሎችን ለመገንባት ዩኒቨርሲቲው እየሰራ መሆኑን አውስተው፣ ትምህርት ላይ መስራት ነገ ሀገርን በተሻለ መሰረት ላይ ለማጽናት እጅጉን እንደሚያግዝ ተናግረዋል።
"መሠል የማህበረሰብ አቀፍ ስራዎችን ለመስራት፣ የከተማ አስተዳደሩም ሆነ የዞኑ አመራሮች በሁሉም ረገድ ከጎናችን ስለምትቆሙ፣ ስለምትደግፉን እና የዚህ ተግባር ተጋሪ የሆነውን ፍሊንትስቶን ኢንጂነሪንግን ከልብ እናመሰግናለን" ብለዋል ፕሬዝዳንቱ በመልዕክታቸው።
የዲላ ከተማ ከንቲባ መስፍን ደምሴ (ዶ/ር) በበኩላቸው፣ የትምህርት ስብራትን ለመጠገን፣ በአንድ መማሪያ ክፍል የሚማሩ ተማሪዎች በደረጃው ልክ መሆን ወሳኝ መሆኑን አንስተው፣ የሚገነባው መማሪያ ክፍል ከዚህ አንፃር በት/ቤቱ የሚስተዋለውን ችግር ለመፍታት እንደሚረዳ አንስተዋል።
ትምህርት የእድገት ሁሉ መሰረት፤ የችግሮች ሁሉ መፍቻ ቁልፍ መሆኑን የተናገሩት ከንቲባው፣ የማህበረሰቡን ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና፣ ፖለቲካዊ ችግሮችን ለመፍታት እና ብልጽግናን ለማረጋገጥ ዕውቀት ወሳኝ መሆኑን ተናግረው፣ ትምህርት ላይ ከሁሉ በላቀ መልኩ በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት በከተማው ያሉ ለማህበረሰቡ ትርጉም ያላቸውን ስራዎች ለመስራት፤ ከተማውን እና ተቋሙን በጋራ በማስተሳሰር የማህበረሰቡን ችግር ለመፍታት ለሚያደርጉት ቀና ትብብርም ምስጋና አቅርበዋል ዶ/ር መስፍን።
የግንባታውን ስራ የሚያከናውነው ፍሊንትስቶን ኢንጂነሪንግ ተወካይ ኢንጂነር ዘገየ፣ ምስጉን ለሆነው ህዝብ ማስታወሻ የሚሆን፣ ትውልዱን በዕውቀት የሚገነባ፣ የትምህርት ቤት ግንባታ ስራ ላይ መሳተፍ እድል መሆኑን አንስተው፣ በተመሳሳይ በሌሎች ትምህርት ቤቶችም ተመሳሳይ ስራ ለመስራት፣ ከተያዘው ጊዜም ቀድሞ ለማስረከብ የሚቻላቸውን ሁሉ ርብርብ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል።
የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር ታሪኩ በቀለ ትምህርት ቤቱ በርካታ ምሁራንን ያፈራ እንደሆነ ጠቁመው ከቆይታ የተነሳ ዘመኑን የማይመጥን ከደረጃ በታች በሆኑ መማሪያ ክፍሎች እያስተማረ መሆኑን ተናግረው፣ አዳዲስ መማሪያ ክፍሎች ለመገንባት አጋሪነቱን ያሳያቸውን ዲላ ዩኒቨርሲቲን አመስግነዋል።
ግንባታው ከስልሳ ቀናት ባጠረ ጊዜ ይጠናቀቃል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፣ ሁለት የመማሪያ ብሎኮችን ለመገንባት የሚያስችል የመሰረት ድንጋይ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኤልያስ አለሙ፣ የዲላ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ዶ/ር መስፍን ደምሴ እና የፍሊንትስቶን ኢንጂነሪንግ ተወካይ ኢንጂነር ዘገየ፣ ሌሎችም የዩኒቨርሲቲው እና የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት በጋራ አኑረዋል።
ከሚሰራው የመማሪያ ክፍሎች ጎን ለጎንም ጥራታቸውን የጠበቁ መፀዳጃ ቤቶች እንደሚሰሩ ተገልጿል።

❤37👍12👎5
በቡና ጥራት ምርምር እና ቁሌት ዘዴዎች ላይ ለሴቶች ማህበር ስልጠና ተሰጠ
==========****=========
ዲላ፡ ታህሳስ 10/2018 ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ)
የዲላ ዩኒቨርሲቲ የቡና ምርምርና ስልጠና ተቋም ዳይሬክቶሬት በቡና ጥራት ግምገማ፣ በቡና ቁሌት እና በቡና ቅምሻ ርዕሶች ላይ ለ“ዉሊ አብንዶ” የሴቶች ማህበር ስልጠና ሰጥቷል። ስልጠናው 12 የማህበሩ ሴት አባላትን ያሳተፈ ነበር።
የዲላ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ አገልግሎትና አጋርነት ዳይሬክተር አቶ ተካልኝ ታደሰ፣ ስልጠናው ቡናን በጥራት ቆልቶ በማሸግ፣ ለሀገር ውስጥና ለውጭ ገበያ ማቅረብ እንዲቻል የሚያግዝ መሆኑን ገልፀው፣ ሙያዊ እገዛና የዕውቀት ሽግግር ማድረግ በጥራት ምርት ለማቅረብና ደንበኛን ለማፍራት እንደሚያግዝ አመልክተዋል።
አቶ ተካልኝ በተጨማሪም፣ ማህበራቱ ይህን ቴክኒካል ዕውቀት ቀድሞ ማግኘታቸው ሌሎችንም ሴቶች በተጠቃሚነት ለማሳተፍ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ጠቁመዋል።
የዲላ ዩኒቨርሲቲ የቡና ምርምርና ስልጠና ተቋም ዳይሬክተር አለሙ ደሳ (ዶ/ር) ስልጠናው ዩኒቨርሲቲው ለማህበረሰቡ ከሚያደርገው ድጋፍ አንዱ መሆኑን ገልጸው፣ ማህበሩ የቡናን ጥራት በጠበቀ መልኩ፣ ከዝግጅት ጀምሮ ለገበያ እስከማቅረብ ድረስ ያለውን ሂደት እንዲረዱ፣ በተግባር የተደገፈ የክህሎት ስልጠና መሆኑን እስረድተዋል።
ዳይሬክተሩ አክለውም፣ ስልጠናው ሴቶችን የኢኮኖሚ ተጠቃሚ ለማድረግ እንዲሁም የአካባቢው ቡና ጥራቱን ጠብቆ እና በሳይንሳዊ መንገድ ተዘጋጅቶ ለገበያ እንዲቀርብ አስፈላጊ ሚና እንደሚኖረው ጠቁመዋል።
በተያያዘ ዜና፣ በዲላ ዩኒቨርሲቲ የቡና ምርምርና ስልጠና ተቋም የሶስተኛ ዙር የቡና ሰልጣኞች በቡና ምርትና ልማት ዙሪያ የመስክ ጉብኝት አካሂደዋል። የመስክ ጉብኝቱ በክፍል ውስጥ በንድፈ ሃሳብ የተማሩትን ትምህርቶች በተግባር ለማጠናከር የተዘጋጀ ሲሆን፣ ከዘር ጀምሮ እስከ ችግኝ ዝግጅት፣ የችግኝ እድገትና እንክብካቤ ድረስ በተግባር እንዲማሩ ለማስቻል ነው።
ጉብኝቱ በዱመርሶ ችግኝ ጣቢያና በወናጎ ወረዳ በካራ ሶዲቲ ቀበሌ ያሉ የአርሶ አደር እና ሞዴል አርሶ አደር ማሳዎች ላይ የተደረገ ሲሆን፣ የዚህ ዙር ሰልጣኞችም በዩኒቨርሲቲው የሚሰጠው ስልጠና ከተግባራዊ ምልከታ ጋር በማጣጣም ያገኙት ዕውቀት በዘርፉ ላይ ለሚሰሩት ስራ እጅግ ጠቃሚ መሆኑን ተናግረዋል።

❤12👎5👍3