ከ .... ለ....
83 subscribers
63 photos
8 videos
3 files
5 links
ከጓደኛህ መልካም የሆነውን ነገሩን አውጣለት ፣ አበረታታው ፣ እንደማይጠቅም አትንገረው፣ ለሀዘኑ ሳይሆን ለደስታው ምክንያት ሁን፣ለስኬቱ እንጅ ለውድቀቱ መንስኤ አትሁን ።
🍊🍸🍸🍸🍸🍸🍸
🍸🍊🍸🍸🍸🍸🍸
🍸🍸🍊🍸🍸🍸🍸
🍊🍊🍊🍊🍊🍊🍊
🍸🍊🍊🍊🍊🍊🍸
🍸🍸🍊🍊🍊🍸🍸
🍸🍸🍸🍊🍸🍸🍸

Just ፈታ ዘና
ለማንኛውም አስተያየት @forgive_them
Download Telegram
ደሞ እኮ ታምራለች
ፀሀይ የደቆሰው ስስ ቆዳ ታቅፋ
ደሞ እኮ ታምራለች
ያደፈ ታሪኳን በመልኳ ላይ ፅፋ
ልዕልት ናት እሷ ገጿ እንኳን ቢጠይም
ለተመልካች ፊቷ ውስጧ ባይታይም
ለኔ ብዙ ሆናለች ከቃላትም በላይ
ዕድሜዋን ያርዝመው ክፉዋን እንዳላይ
.
ለኔ ብዙ ሆናለች ልጅነቷን አጥታ
እናቴን ባርክልኝ የፍጥረታት ጌታ
🙏

      ለውድ እናቴ ❤️



@doshallom
@forgive_them
2👍1
Live stream started
Live stream finished (37 seconds)
ሙግት
((በውቀቱ ስዩም))
ጊዜ ለሰው ህይወት
ዘበት አይታክተው
እኔም ምላሽ ባጣም
መጠየቄን አልተው።
ኩታ ገጠም ናቸው
አልፋና ኦሜጋ
እንዴት ቀን ይመሻል
በቅጡ ሳይነጋ?
ማን ዘረፈው ጠጉሬን?
ማን አሰረው እግሬን?
ጉልበቴን ምን በላው?
አቅሜን ማን ወረሰው?
ተወልዶ ሳይጨርስ
እንዴት ያረጃል ሰው?

👉 @doshallom
👉 @forgive_them
በልብሽ  አስበሽ የኔን ልብ ለመስበር
እግርሽ ከኔ ርቆ ወደሌላ ሲበር
እመኚኝ ፍቅሬ ሆይ
ላለቅስ ይቅርና ሳቅ ሊገለኝ ነበር

ሚል ግጥም ሰጥቼሽ #ከቤቴ እንደገባሁ
ልክ እንደ ህፃን ልጅ አንገቴን ቀብሬ
ቁጭ ብዬ #አነባው

አየሽ! #መለየትሽ ቢያመኝ ሆዴን ቢያላውሰው
ምን ላርግ #ወንድ_ልጅ ነኝና
ባደባባይ #ስቄ ቤቴ ነው #የማለቅሰው!


#Like#ሼር_አድርጉ


@doshallom
@forgive_them

😉 𝐒𝐡𝐚𝐫𝐞
👍4
«ዝናብ እወዳለሁ ትላለህ፤ ሲዘንብብህ ግን ጃንጥላ ትዘረጋለህ።

ፀሐይ እወዳለሁ ትላለህ፤ ጸሐይ በወጣች ጊዜ ግን ጥላ ፍለጋ ትሮጣለህ።

ንፋስ እወዳለሁ ትላለህ፤ ዳሩ ንፋሱ ወደ ቤትህ እንዳይገባ መስኮትህን ትዘጋለህ።
…ለዚህም ነው "እወድሃለሁ" ስትለኝ የምፈራው።»
2👍1
አ.ን.ብ.ቡ.ት
#red-8

@forgive_them
@doshallom
👏3
ፀሎቷ የፃዲቅ
ህይወቷ የመናኝ
የሚዳስስ ጣቷ
ለእርኩሰት ሲያጸናኝ
እንዳልተዋት ፍቅር
እንዳላቅፋት እሳት
መልዓክ አሳድጎ
ሰይጣን የዳበሳት

አይ እሷ!
                 
#do
🙌 _ @forgive_them
🙌 _ @doshallom
👏2🔥1
እኔ ለሀገሬ"
እኔ ለሀገሬ
ይነጋል እያልኩኝ ፣ ጨለማው ገዘፈ
አንዱ ለፍቅረኛው
ብርሐኔ ነሽ የሚል ፣ ብዙ ግጥም ፃፈ፡፡

እኔ ለሐገሬ...
በተስፋ እያልኩኝ ፣ ሁሉም ነገር ያልፋል
አንዱ ለፍቅረኛው...
የኔ አለም አንቺ ነሽ ፣ የሚል ወግ ይፅፋል፡፡

እኔ ለሀገሬ
ለዘላለም ኑሪ
በማለት ስፀልይ ፣ ቆሜ ከመቅደሱ
የሴት ፀሎት ሰማሁ
"ለኔ ዘላለም ነው ፣ አንድ ቀን ያለሱ፡፡"

እኔ በሀገሬ...
ንፁ ደም መፍሰሱ ፣ ልቤ እያዘነ
አንዱ ለፍቅረኛው
በደሜ ውስጥ አለሽ ፣ በማለት ዘፈነ፡፡

እኔ ለሀገሬ
ተወርቶ የማያውቅ ፣ የሐዘን እንጉርጉሮ
ተፈቶ የማያልቅ ፣ የኑሮ ቋጠሮ
ርሐብ ቸነፈሩ
ዘሩ ዘር ማንዘሩ
ጦርነት ችግሩ
ጉድጓድ መቃብሩ
ስቃይ ስንክሳሩ፣
ሚያበቃበትን ቀን ፣ ስናፍቅ በልቤ
"ካንተ ናፍቆት በቀር
እጅጉን ደና ነኝ ፣ አንተው ነህ ሀሳቤ
ብላ ትፅፋለች
አንዲት ሴት ለፍቅሯ ፣ በሚላክ ደብዳቤ፡፡
፡፡፡
እኔ ለሀገሬ...
ስፀልይ ስማፀን
የጠፋ ሰላሟን ፣ እያልኩ እንዳይጠፋ
"ሰላሜ አንቺ ነሽ"
ይላታል ለፍቅሩ ፣ አፍቃሪ ፈላስፋ፡፡

እኔ ለሐገሬ
አንድቀን እያልኩኝ
ለአመታት ሲመረኝ ፣ የመኖር ትርጉሙ
ብዙ ገጣሚዎች
ስለ ከንፈር ጣዕም ፣ ግጥም አሳተሙ፡፡
፡፡
እኔ እኔ ማለት ያበዛሁኝ እኔ
ችግርና ስቃይ
ግፍና መከራ
ደም እና ደምባራ
መቼም የማይለቃት ፣ አንድ ሀገር ወድጄ
ስቃጠል ከምኖር ፣ ሲኦል ላይ ተጥጄ
ከዚ በላይ ስቃይ
ከዚህ በላይ ጤና ፣ ጤናዬን ሳይነሳኝ
አንቺን ባፈቅርሽስ...
ፍቅርሽ እውር አርጎኝ ፣ ሁሉን እንዲያስረሳኝ?
...
አፈቀርኩሽ በቃ!
እኔ አንቺን ሳፈቅርሽ
ሀገሬን ረሳሁ
ችግሬን ረሳሁ
ስቃዬን ረሳሁ
ሁሉንም ስረሳ...
"ኢትዮጵያ ሀሳቤ ነሽ!"
የሚል ግጥም ልፅፍ ፣ብእሬን አነሳሁ፡፡
ርእሱን ፅፌ ግጥሙንም ረሳሁ፡፡
ኢትዮጵያ ሀሳቤ  ነሽ።
ኢትዮጵያ ሀሳቤ  ነሽ።
ኢትዮጵያ ሀሳቤ  ነሽ፡፡
👍32
ሲሸሹኝ ስጎትት ሲርቁኝ ስጣራ፤
    ሲሄዱ ስከተል ሲዘጉኝ ሳወራ።

አሁንስ ዝም አልኩኝ ልቤን ደካከመው፤
    ሁለት እየሆነ አንድ ነው ያልኩት ሰው።

ብቻ በመንገዴ፥

ከነሳቸው ሠላም ከነሳቸው ጤና እኔ መከተሌ፤
ለበደለኝ ሁሉ ለበደልኩት ሁሉ ይቅርታ ነው ቃሌ።

ሄጃለሁ ከእንግዲህ በቃ ለልከተል🚶‍♀‍➡️🚶‍♀‍➡️🚶‍♀‍➡️🚶‍♀‍➡️🚶‍♀‍➡️

ዶዳ

@forgive_them
@doshallom
👍2
👍3🔥21
🥰2👏1👌1
<<ምኗን ስመሃት ነው?>>
<<ማንም ያልነካትን ቦታ>>
<<ከአንገቷ ነው ከደረቷ?>>
<<ከምትፅፍበት ከጣቷ>>
<<እንዴት አርጓት ነበር?>>
<<ጥላኝ እስከምትበር>>
<<በል ንስሃ ግባ>>
<<አንድኛዬን...ቤቴ ስትገባ>>


😮
@forgive_them
@doshallom
👍3👌3
ጣዕሙን የሚያውቀው
(ሳሙኤል አለሙ)

እንደ ሌላው
እንደ ሌላው፤
ሰርክ...
ጉንጭሽ ጋ አይደረስም
ረ------ጅም ነው ኬላው።

እያዩት...
            ያስውላል።
ዕሮብ ለት
እያዩት...
            ያፆማል።
አርብ ዕለት

እንደ እኛው
እንደ እኛው፤
አንቺ...
ከቶ አልተፈጠርሽም
በቀን ስድስተኛው።

ለምን...?
           አይባልም።
አይጠየቅም።
እንዴት...?
            አትለውም።
አትከራከርም።

ከአፈሩም ፣ ከውኃውም
ከእስትንፋሱም ፣ ሌላም
አለው... ሌላም...ሌላም
ሌላም አለው ያከለበት፤
ወተቱን እንዳ---
                ፈሰሰ---
                      ---በት
ጉንጭሽን የሳመው።
ጣዕሙን የሚያቀው።

     
   @ጮ

@forgive_them
@doshallom
2
Channel photo updated
እንደ ባለ ታንኳ
ውቅያኖስ መኃል
መቅዘፊያው ተሰብሮ ሐዘን እንደገባው፤

እንደ ብርቱ ንስር
ከዓለት ዓለት ሲጋጭ
እንደተበተነ አጥንትና ላባው፤

እንደ ሩህሩህ አባት
በኸር ልጁን ሲድር
እንደሚርበተበት ሆዱ እንደሚባባው፤

ፍቅርሽ እንደዚያ ነው
ሰውነቴን ቀድዶ ከውስጤ የገባው።

@ዶ

@doshallom
@forgive_them
1
I'm about to cash out $100! You are the next! https://os8.me/SxsFPW