DIRSANE TIBEB
195 subscribers
70 photos
2 videos
5 files
32 links
This channel is your visual arts Utopia. Dive deep into the world of film, TV, and art creation. From BTS secrets to practical how-to's, I'll share my insights and experiences 🎥 🎬

Join me @addispupi on this artistic journey & explore the magic of art.
Download Telegram
Checkout the official soundtrack for Civilization 6 :
Listed below are time stamps for game level and segment chapter tracks

0:00 - Ancient Era
2:59 - Medieval Era
7:54 - Industrial Era
12:11 - Atomic Era

It’s really amazing hearing our motherland distinct music genre in orchestrated full vibes such a way that lifting up those “Tizita and Bati” with the first Blues theme. 👏🏽👏🏽👏🏽

Composer : Geoff Knorr
Live Krar: Minale Bezu
Tenor Saxophone: Getachew Mekurya

Link Below 👇🏽
—————————
Join The Underground Art Movement!
ድርሳነ-ጥበብ / DIRSANE TIBEB @dirsanetibeb

https://youtu.be/mXTsJ5bjG-c
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Live Recording and Composing
———————
On the video Geoff Knorr(Composer)
Arranging and Recording soundtrack for official Civilization 6 Ethiopia Pack: New Fortress Pass

Enjoy !!
———————
Join The Underground Art Movement!
ድርሳነ-ጥበብ / DIRSANE TIBEB @dirsanetibeb
ጽሑፎች በፕሪሚየር ፕሮ
• Texts in Premiere Pro 2020 •


ጽሑፎች ለተለያዩ የቪዲዮ ስራዎቻችን እንደግብአት ልንጠቀማቸው እንችላለን። ለምሳሌ ያክል የሰራነውን ቪዲዮ ርዕስ ልንጽፍበት እንችላለን፤ ወይንም የቪዲዮችን መጨረሻ ወይም መጀመሪያ ላይ የሚታዩትን የባለሞያዎች ዝርዝር እና አንዳንዴም ለምንሰራው ታሪክ ገላጭ የሆኑ ምስለ ትንተናዎችን ለመጻፍ እንጠቀምበታለን።

በዚህ ክፍል ጽሑፎችን እንዴት እና በምን መሳሪያ/Tools ተጠቅመን ፕሪሚየር ፕሮ 2020 ላይ እንደምንጽፍ፣ መለከ ፊደላትን እንዴት እንደምንቀይር እና እንደምናስውብ እናያለን ጨምረንም በፊልሞች ላይ ያሉ የመጨረሻ የተዋናዮች እና ባለሞያዎች ዝርዝር እንዴት ወደላይ እንዲወጣ እንደምናረግ በተግባር እየሰራን በመጨረሻም ሌሎች ጠቃሚ የጽሑፍ አጠቃቀሞችን እናያለን።

በሚቀጥለው ቪዲዮ እስክንገናኝ
መለማመድ • መስራት • ድጋሚ-መስራት
————————
Join The Underground Art Movement!
ድርሳነ-ጥበብ / DIRSANE TIBEB @dirsanetibeb
👇🏽 ቪዲዮውን ከስር ያገኙታል

https://youtu.be/dfavWIYRbgY
ማስክ እና ትራክ በፕሪሚየር ፕሮ
• Mask and Tracking in Premiere Pro •

አንዳንድ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ላይ የአልኮል እና ያልተከፈለባቸው/አለአግባብ የሆኑ ማስታወቂያዎችን በደበዘዘ ምስል ሲሸፈኑ/ሲደበቁ አይታችሁ ታቃላችሁ? ይህ አሰራር ወይም ዘዴ ማስኪንግ(Masking) ተብሎ ይጠራል።

እነዚህ ምስሎች ወይም ቁሶች ተንቀሳቃሽ ሲሆኑ ለመሸፈን ሊያስቸግሩ ይችላሉ። ለምሳሌ ያክል የመኪና ታርጋ ሊሆን ይችላል ወይም የሰው ፊትም ሊሆን ይችላል፤ የፖሊስ ፕሮግራሞች ላይ ምስክርነት የሚሰጡ ሰዎችን ፊታቸው ብለርድ/ብዥታ/ ሆኖ አይታቹ ይሆናል እና በአጭሩ እነዚህን ቴክኒኮች አጭር እና ቀላል በሆነ ዘዴ ምንም ተጨማሪ ፕለጊን/Plugin ሳንጠቀም እናያለን።

በሚቀጥለው ቪዲዮ እስክንገናኝ
መለማመድ • መስራት • ድጋሚ-መስራት
————————
Join The Underground Art Movement!
ድርሳነ-ጥበብ / DIRSANE TIBEB @dirsanetibeb
👇🏽 ቪዲዮውን ከስር ያገኙታል

https://youtu.be/VbpB3CvZdr0
ካፒቴን ማርቬል ርዕስ አሰራር
• Captain Marvel Title Sequence •

ከሰሞኑ Marvel Studios የካፒቴን ማርቬል 2ትን ፊልም ዳይሬክት የሚያደርግ ሰው ቀጥረዋል እሱን ምክንያት በማድረግ ከዚህ በፊት የሰራነውን የካፒቴን ማርቬልን የመጀመሪያ ፊልም የማስታወቂያ ርዕስ አሰራርን የVideo Copilot ምርት የሆኑትን Element 3D እና Optical Flareን በመጠቀም ለመስራት እንሞክራለን።
በሚቀጥለው ቪዲዮ እስክንገናኝ

መለማመድ • መስራት • ድጋሚ-መስራት
————————
Join The Underground Art Movement!
ድርሳነ-ጥበብ / DIRSANE TIBEB @dirsanetibeb
👇🏽 ቪዲዮውን ከስር ያገኙታል


https://youtu.be/rfCd7Cp4pgc
ሦስት የገቢር አይነቶች
Story Clock - 3 Act Structure
_______________
ብዙ የተሳካላቸው የፊልም እና የቴያትር ፀሀፊያንና አጥኚዎች ፁሑፋቸውን በሦስት ክፍል ወይም ገቢር መጀመሪያ ፣ መሀል እና መጨረሻ በማለት የተዋቀረ አርገው ይከፍሉታል፡፡ ይህ ሲባል ግን ግድ በቅደም ተከተል መቀመጥ አለባቸው ማለት አይደለም የፈጠራ ችሎታችንን ተጠቅመን የራሳችንን አቀማመጥ ልናሲዘው እንችላለን፡፡

ገቢር 1/መጀመሪያ (ትውውቅ)
ይህ ክፍል መሪ ገፀ-ባህሪውን የምናስተዋውቅበት ሲሆን የሚኖርበት አለም ፤ ፍላጎቱን ፤ ከሌሎች ጏደኞቹ ጋር ያለውን ግንኙነት ወዘተ መደበኛውን/የተለመደውን ማሳየት ይጠበቅብናል፡፡ በመጨረሻም ገቢሩ ማለቁን ለማሳየት ወሳኝ የሆነ ክስተት/የመጀመሪያ ግጭት/ እንፈጥራለን ይህም ለገፀ-ባሕሪው ካአሁን በኅላ ኑሮው እንደቀድሞ እንደማይሆንና እንደተቀየረ የሚገነዘብበት ይሆናል፡፡

——————
Join The Underground Art Movement!
ድርሳነ-ጥበብ / DIRSANE TIBEB @dirsanetibeb
ሦስት የገቢር መዋቅሮች (የቀጠለ)
3 Act Structure
_______________

• ገቢር 2/መሀል (መጋፈጥ) •

በዚህ ክፍል ደግሞ በመጀመሪያው ገቢር የፈጠርነውን የመጀመሪያ ግጭት የምናግልበት/የምናጦፍበት ገቢር ሲሆን ዋና ገፀ-ባሕሪው ግጭቱን ለመፍታት ሲታገል የምናሳይበት ይሆናል አክሎም ወደመፍትሄው የተቃረበ እና ግጭቱን የፈታው እስኪመስለው ድረስ እንሄዳለን እውነቱ ሲገለጥ ግን ጭራሽ ግጭቱን እንዳባሰው እና እንደተሸነፈ የሚረዳበት ይሆናል፡፡ በመጨረሻም ይሄ ገቢር ማለቁን ለማሳየት ገፀ-ባሕሪው አንድ ትልቅ ነገር እንዲገነዘብ እናደርጋለን ይህም ግጭቱን ለመፍታት መጀመሪያ እራሱን መጋፈጥ እና የፍርሃቱን ጥግ ማሸነፍ እንዳለበት ይህ ሁለተኛውን ግጭት ይፈጥርልናል ወይም እንደ ለውጥ ቦታ(Turning Point) እንቆጥረውና ገፀ-ባሕሪው ለውጥ ይጀምራል፡፡

• ገቢር 3/መጨረሻ (መፍትሄ) •

አሁን በመጀመሪያው እና በሁለተኛው ግጭት የፈጠርናቸውን የመጨርሻው ጡዘት የምናደርስበት እና እስካሁን ለተነሱት ግጭቶች መፍትሄ የምንሰጥበት ወይም የምንፈታበት በተጨማሪም ለእስካሁኖቹ ጥያቄዎች መልስ የምንሰጥበት ይሆናል

አስተውሉ ይህ ለታሪክ አፃፃፍ እዲረዳ ተደርጎ እንደ ማነሳሻ/ማስተማሪያ የተሰራ ነው እንጂ ህግና ደንብ ወይም ግዴታ አይደለም፡፡

——————
Join The Underground Art Movement!
ድርሳነ-ጥበብ / DIRSANE TIBEB @dirsanetibeb
ኤዲቲንግ ምንድነው?
• What is Editing? •

ምስል እንና ድምጽ ማቀናበር /ኤዲቲንግ/ ከመጀመሮ በፊት ሊያዩት የሚገባ ስለ ኤዲትንግ ባለሞያዎች ስራ ወይም ኤዲቲንግ እራሱ ምን ያህል ጥቅም እንዳለው እና አስፈላጊነቱን በምሳሌ እና ቴክኒካዊ በሆነ መንገድ በጥልቅ እንድትገነዘቡ የሚያረጋቹ።

መነሳሳት • መፍጠር • መስራት
————————
ድርሳነ-ጥበብ / DIRSANE TIBEB @dirsanetibeb
👇🏽 ቪዲዮውን ከስር ያገኙታል

https://youtu.be/H9wWXes3QTw
እነዚህን እና ተመሳሳይ ይዘት ያላቸውን ቪዲዮዎችን ለማየት አዲሱ YouTube ቻናላችንን ይቀላቀሉ።
3ዲ ሞዴል ኮምፖዚቲንግ
• 3D Models Compositing •

በዚህ ክፍል ባጭሩ 3D Models ተጠቅመን እንዴት AfterEffects ላይ ላይት እና የተለያዩ Matterials እና Texutes እየሰጠን ቀጥታ ስራችንን እንደምናይ ቀጥለንም Animation እነዴት እንደምንሰራም እናያለን።

መለማመድ • መስራት • ድጋሚ-መስራት
————————
ድርሳነ-ጥበብ / DIRSANE TIBEB @dirsanetibeb

👇🏽 ቪዲዮውን ከስር ያገኙታል

https://youtu.be/AU8AmXLl_YY
ፕሪሚየር ፕሮ 101 - መሰረታዊ
• Premiere Pro 101 - Basics •

በዚህ ክፍል የኤዲቲንግ ፕሮጀክት እንዴት እንደሚከፈት፤ የስራቦታ እንዴት እንደሚስተካከል እና ሴቭ እንደሚደረግ እናያለን።

መለማመድ • መስራት • ድጋሚ-መስራት
————————
ድርሳነ-ጥበብ / DIRSANE TIBEB @dirsanetibeb

👇🏽 ቪዲዮውን ከስር ያገኙታል

https://youtu.be/4z9UZQSyAQo
Breakout Film Festival
(Short Film)

Awards & Prizes
Monthly winners will be awarded our official selection laurel.

Winners of Best Short Film 2020 and Best Short Film 2021 will be awarded $500 USD, official selection laurel and our coveted trophy.

Rules & Terms
Films must be between 1-40 minutes in length (including credits).

Only short narrative genres are accepted. Music videos and documentaries are not valid for this contest.

Filmmakers must have copyright over all footage and soundtrack.

Films must be of high-quality, at minimum FULL HD (1080p).

For more info. And submissions https://filmfreeway.com/breakoutfilmfestival
ብዙዎቻቹ ለጠየቃችሁን መልስ ይሆን ዘንድ

ብሬክአውት ፊልም ፌስቲቫል ከተመሰረተ 2 አመት ያስቆጠረ በየወሩ ኤዴንብራ፣ ስኮትላድ ውስጥ የሚደረግ የአጫጭር ፊልሞች ውድድር ነው።

የውድድሩ የየወሩ አሸናፊዎች ወይም የተመረጡ እጭር ፊልሞች በወሩ 20ኛው ቀን ላይ መመረጣቸውን የሚጠቁም መልዕክት በኢሜይላቸው አማካኝነት ይደርሳቸውና በስተመጨረሻም አሸናፊ የሆኑት $500 ሽልማትን ጨምሮ የላውሬል ይፋዊ ምርጥን እና አዲሱን ዋንጫ ያገኛሉ።

ስለዚህ በዚህ መሰረት አሁን የምታስገቡት የህዳር ወርን ሲሆን የሚቀጥለው ወር ማለትም ጥር ደግሞ የመጨረሻውን ወር ይሆናል ማለት ነው።

ለማመልከት የሚረዱ ህግና ደንቦች

• አይነት - ተራኪ ፊልም (ዘጋቢ ፊልም እና የሙዚቃ ቪዲዮ አይቻልም)

• ርዝመት - ከ1 እስክ 40 ደቂቃ (የመጨረሻው የባለሞያዎች ስም ዝርዝርን ጨምሮ)

• ጥራት - በትንሹ Full HD (1080p)

• ፊልሞቹ እ.ኤ.አ. ከጥር 1, 2016 በኋላ የተሰሩ መሆን አለባቸው።

• የፊልሙ ቋንቋ ከእንግሊዘኛ ውጪ ከሆነ የእንግሊዘኛ Subtitle.srt ማካተት አለባቹ።

• በሌላ ፌስቲቫል ላይ የተወዳደሩበት ፊልም በዚህም ላይ መወዳደሪያ ማድረግ ትችላላቹ።

• አጭር ፊልማችሁ ሌላ ድህረገጾች ላይ ለምሳሌ የYouTube ወይም Vimeo ላይ የተለቀቁ ቢሆንም ችግር የለውም።

• ይህ ውድድር ለፕሮፌሽናል ፊልም ሰሪዎች ለአንዴ ብቻ መወዳደር ሲቻል ለሌሎች ደሞ በተቃራኒው እስከፈለጉት ይቻላል።

• የቅጂ መብት - የፊልሙ ባለቤት ለሁሉም ላካተተው/ቸው footage እና soundtrack ሙሉ ባለቤት መሆን አለበት/ባት ወይም ባለቤትነት ማረጋገጫ ሊኖረው/ራት ይገባል።


እንግዲ ቤተሰቦች መልካም እድል እየተመኘን ላላቹ ጥያቄ በፌስቡክ ገፃችን መልዕክት መላክ እና ለጠለቀ ምልከታ እና ለመወዳደር ደሞ ዋናውን ድህረገፅ መጎብኘት ትችላላችሁ።
____
ድርሳነ-ጥበብ / DIRSANE TIBEB
@dirsanetibeb
ለመነሳሻ እንዲሆን ዘንድ ከጥር እስከ ሐምሌ ያሉትን አሸናፊ ፊልሞች እንሆ ሊንኩንም አብረን እድርገናል

- SEPTEMBER
- AUGUST
- JULY
- JUNE
- MAY
- APRIL
- MARCH
- FEBRUARY
- JANUARY
ብሬክአውት ፊልም ፌስቲቫል ከጥር እስከ ሐምሌ ያሉት አሸናፊዎች መረጃ